Telegram Web Link
" አላማችንን ለማሳካት ጥሩ እድል አግኝተናል " ሳውዝጌት

የእንግሊዝ ብሔራዊ ቡድን ዋና አሰልጣኝ ጋሪዝ ሳውዝጌት ቡድናቸው በምሽቱ ጨዋታ ተደራጅቶ እንደ ቡድን እንዲጫወት ከጨዋታው በፊት በሰጡት አስተያየት ገልጸዋል።

አሰልጣኝ ጋሪዝ ሳውዝጌት ምን አሉ ?

- " ለማሳካት ያሰብነውን አላማችንን ለማሳካት ጥሩ እድል አግኝተናል ስለፍፃሜው ለተጨዋቾቹ ብዙ መናገር አያስፈልግም ለፍፃሜ ተጨማሪ ማነሳሻ ነገር አያስፈልገውም።

- ዛሬ ጥሩ እንቅስቃሴ አድርገን ማሸነፍ እንፈልጋለን አስደሳች ታሪክ ይሆናል ዋንጫው በእጃችን ነው ያለው ህልማችንን ለማሳካት አንድ ጨዋታ ነው የሚቀረን።

- የስፔን ብሔራዊ ቡድን ኳስን ተቆጣጥሮ በጥሩ ሁኔታ የሚያጠቃ ቡድን ነው በደንብ ተደራጅተን መጫወት አለብን በመጨረሻው ጨዋታ ጥሩ ኳስ ተቆጣጥረናል።"ሲሉ ተደምጠዋል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
" ዋንጫውን ማሸነፍ እንፈልጋለን " ሉዊስ ዴ ላፉንቴ

የስፔን ብሔራዊ ቡድን ዋና አሰልጣኝ ሉዊስ ዴ ላፉንቴ ቡድናቸው በአውሮፓ ዋንጫ ፍፃሜ መድረሱ ትልቅ ስኬት መሆኑን ከምሽቱ ጨዋታ በፊት በሰጡት አስተያየት ተናግረዋል።

" እዚህ ባደረግነው ነገር ደስተኛ ነኝ በአውሮፓ ዋንጫ ፍፃሜ መድረስ በእግርኳስ ትልቅ ስኬት ነው " ያሉት አሰልጣኝ ሉዊስ ዴ ላፉንቴ ጨዋታውን አሸንፈን ዋንጫውን መውሰድ እንፈልጋለን ብለዋል።

" ከባድ ጨዋታ ይሆናል ብዬ እጠብቃለሁ ምክንያቱም ሁለቱም ጥሩ ቡድኖች ናቸው ፣ ጥሩ ጊዜ ላይ ነን የፍፃሜ እንደመሆኑ ተመጣጣኝ ጨዋታ እንመለከታለን።" ሉዊስ ዴ ላፉንቴ

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
TIKVAH-SPORT
“ ጀርመን ውስጥ የኬንን የዋንጫ ጥማት አስቀጥያለሁ “ ዳኒ ኦልሞ የስፔን ብሔራዊ ቡድን የመሐል ሜዳ ተጨዋች ዳኒ ኦልሞ ሀሪ ኬን ዋንጫ እንዳያሸንፍ የማድረግ ስራውን ገና አለማጠናቀቁን በሰጠው አስተያየት ተናግሯል። " ጀርመን ውስጥ የዋንጫ እርግማኑን ሊያጠፋ የተቃረበውን ሀሪ ኬን አስቁሜው አስቀጥዬለታሁ " የሚለው ዳኒ ኦሎም " አሁንም ስራዬ ገና አልተጠናቀቀም " ሲል ተናግሯል። ባለፈው አመት…
" የመጀመሪያ ዋንጫዬን ለማሸነፍ ሁሉንም መስዋዕትነት እከፍላለሁ " ኬን

የእንግሊዝ ብሔራዊ ቡድን የፊት መስመር ተጨዋች ሀሪ ኬን የመጀመሪያ የቡድን ዋንጫውን ለማሸነፍ ዛሬ ምሽት ሁሉም መስዋዕትነት ለመክፈል መዘጋጀቱን ገልጿል።

" የቡድን ዋንጫ አለማሸነፌ የሚደበቅ ሚስጥር " አይደለም የሚለው ሀሪ ኬን " አመታት በተቆጠሩ ቁጥር ይህንን የመቀየር ጉጉቴ እየጨመረ ነው ዛሬ የመጀመሪያ ዋንጫዬን አሸንፌ ምርጡን ምሽት ለማሳለፍ ሁሉንም ዋጋ እከፍላለሁ " ብሏል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
#CopaAmerica2024

በአሜሪካ አዘጋጅነት እየተካሄደ የሚገኘው የዘንድሮው የ2024 የኮፓ አሜሪካ ውድድር ፍፃሜ ጨዋታ ዛሬ ሌሊት 9:00 በአርጀንቲና እና ኮሎምቢያ መካከል ይደረጋል።

ትላንት በተደረገ የደረጃ ጨዋታ ዩራጓይ ካናዳን በመለያ ምት በማሸነፍ የውድድሩን ሶስተኛ ደረጃ በመያዝ ማጠናቀቅ ችለዋል።

የኮፓ አሜሪካ ፍፃሜ ጨዋታን ብራዚላዊው የ 44ዓመት ዳኛ ራፋኤል ክላውስ በመሐል ዳኝነት እንደሚመሩት ይፋ ተደርጓል።

በሀርድ ሮክ ስታዲየም ለሚደረገው የፍፃሜ ጨዋታ የቀረቡ የስታዲየም መግቢያ ትኬቶች ሙሉ ተሸጠው መጠናቀቃቸው ተገልጿል።

በኮፓ አሜሪካ ፍፃሜ ጨዋታ እረፍት ሰዓት ኮሎምቢያዊቷ አርቲስት ሻኪራ ስራዎቿን በማቅረብ ውድድሩን እንደምታደምቅ ይጠበቃል።

የውድድሩን ከፍተኛ ግብ አስቆጣሪዎች ደረጃ አርጀንቲናዊው የፊት መስመር አጥቂ ላውታሮ ማርቲኔዝ በአራት ግቦች እየመራው ይገኛል።

የኮፓ አሜሪካ አሸናፊዎች ስንት ያገኛሉ ?

- የዋንጫው አሸናፊ :- 16 ሚልዮን ዶላር

- የፍፃሜ ተፋላሚ :- 7 ሚልዮን ዶላር

- 3ኛ ደረጃ :- 5 ሚልዮን ዶላር

- 4ኛ ደረጃ :- 4 ሚልዮን ዶላር የሚሸለሙ ይሆናል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
TIKVAH-SPORT
አርሰናል ወጣት ግብ ጠባቂ ለማስፈረም ጠየቀ ! አማራጭ ግብ ጠባቂ ለማስፈረም በእንቅስቃሴ ላይ የሚገኘው አርሰናል የአያክሱን እንግሊዛዊ ወጣት ግብ ጠባቂ ቶሚ ሴትፎርድ ለማስፈረም የዝውውር ጥያቄ ማቅረባቸው ተገልጿል። ባለ ጥሩ ተሰጥኦ ባለቤት መሆኑ የተነገረው የ 18ዓመቱ ግብ ጠባቂ ቶሚ ሴትፎርድ በአያክስ ያለው ውል በ2025 የሚጠናቀቅ ሲሆን መድፈኞቹን መቀላቀል ይፈልጋል ተብሏል። መድፈኞቹ ከቀናት…
አርሰናል ግብ ጠባቂ ለማስፈረም ተስማማ !

ግብ ጠባቂ ለማስፈረም በእንቅስቃሴ ላይ የሚገኘው አርሰናል እንግሊዛዊውን ወጣት ግብ ጠባቂ ቶሚ ሴትፎርድ ለማስፈረም ከአያክስ ጋር ከስምምነት መድረሳቸው ተነግሯል።

ባለ ጥሩ ተሰጥኦ ባለቤት መሆኑ የተነገረው የ 18ዓመቱ ግብ ጠባቂ ቶሚ ሴትፎርድ በአርሰናል ቤት የአራት አመት ኮንትራት ለመፈረም ከስምምነት መድረሱ ተገልጿል።

መድፈኞቹ እንግሊዛዊውን ግብ ጠባቂ ቶሚ ሴትፎርድን በአንድ ሚልዮን ዩሮ ለማስፈረም መስማማታቸው ተገልጿል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
TIKVAH-SPORT
#CopaAmerica2024 በአሜሪካ አዘጋጅነት እየተካሄደ የሚገኘው የዘንድሮው የ2024 የኮፓ አሜሪካ ውድድር ፍፃሜ ጨዋታ ዛሬ ሌሊት 9:00 በአርጀንቲና እና ኮሎምቢያ መካከል ይደረጋል። ትላንት በተደረገ የደረጃ ጨዋታ ዩራጓይ ካናዳን በመለያ ምት በማሸነፍ የውድድሩን ሶስተኛ ደረጃ በመያዝ ማጠናቀቅ ችለዋል። የኮፓ አሜሪካ ፍፃሜ ጨዋታን ብራዚላዊው የ 44ዓመት ዳኛ ራፋኤል ክላውስ በመሐል ዳኝነት…
የኮፓ አሜሪካ ፍፃሜን የሚመሩት ዳኛ ማን ናቸው ?

የኮፓ አሜሪካ ፍፃሜ ጨዋታን ብራዚላዊው የ 44ዓመት ዳኛ ራፋኤል ክላውስ በመሐል ዳኝነት እንዲመሩት ተመርጠዋል።

ዋና ዳኛው የኮሎምቢያ ብሔራዊ ቡድን ከሁለት አመታት በፊት ለመጨረሻ ጊዜ በአርጀንቲና ብሔራዊ ቡድን ሲሸነፍ ጨዋታውን መርተው ነበር።

የኮሎምቢያ ብሔራዊ ቡድን ለመጨረሻ ጊዜ የተሸነፈው ከሁለት አመታት በፊት ከአርጀንቲና ብሔራዊ ቡድን ጋር ባደረጉት የአለም ዋንጫ ማጣሪያ ጨዋታ ነበር።

የኮሎምቢያ ብሔራዊ ቡድን ያለፉትን ሀያ ሰባት ጨዋታዎች ያልተሸነፉ ሲሆን ሀያ አንዱን ጨዋታዎች በአሸናፊነት መወጣት ችለዋል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
Forwarded from WANAW SPORT
🎁 #በፍፃሜው ይገምቱ፣ #ይሸለሙ!

🏆  በዛሬው ምሽት የ2024 አውሮፓ ዋንጫ የፍፃሜ ፍልሚያ ማን አሸንፎ ዋንጫውን ያነሳል?

🇪🇸 ስፔን ወይስ እንግሊዝ 🏴󠁧󠁢󠁥󠁮󠁧󠁿

💬 ግምትዎን
#በገፃችን ኮሜንት ላይ ብቻ ያስቀምጡልን!

⚠️ የውድድሩ ህጎች፦
👉🏾 የፍፃሜውን አሸናፊ ሀገር እስከ የግብ መጠኑ #በትክክል ቀድመው የሚገምቱ #3 ተከታታዮቻችን የዋናውን የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ማልያዎች ይሸለማሉ።
👉🏾 የዋናውን ማህበራዊ ገፆች መከተል፣ መወዳጀትና ማጋራት አይዘንጉ።
👉🏾 የተስተካከሉና ተደጋጋሚ መልሶች በፍፁም ተቀባይነት የላቸውም።
👉🏾 አንድ ተሳታፊ ከሁለት ጊዜ በላይ አይሸለምም፡፡

Instagram | Facebook | TikTok

🏅 ዋናው ወደፊት...

@wanawsportwear
TIKVAH-SPORT
ጆሽዋ ዚርክዜ ለዩናይትድ ፊርማውን አኖረ ! ኔዘርላንዳዊው የፊት መስመር ተጨዋች ጆሽዋ ዚርክዜ ወደ ማንችስተር ዩናይትድ የሚያደርገውን ዝውውር  ለማጠናቀቅ ያደረገውን የህክምና ምርመራ ማጠናቀቁ ተገልጿል። ተጨዋቹ አሁን ላይ በማንችስተር ዩናይትድ ቤት ለአንድ ተጨማሪ አመት የማራዘም አማራጭ ያካተተ የአምስት አመት ኮንትራቱን መፈረሙ ተገልጿል። ማንችስተር ዩናይትድ በቀጣይ የተጫዋቹን ዝውውር ይፋ…
ማንችስተር ዩናይትድ በይፋ ተጨዋች አስፈረመ !

ማንችስተር ዩናይትድ ኔዘርላንዳዊውን የፊት መስመር ተጨዋች ጆሽዋ ዚርክዜ ማስፈረማቸውን ይፋ አድርገዋል።

ኔዘርላንዳዊው የፊት መስመር ተጨዋች ጆሽዋ ዚርክዜ በማንችስተር ዩናይትድ ቤት እስከ 2029 የሚያቆየውን ኮንትራት መፈረም ችሏል።

በአሰልጣኝ ኤሪክ ቴንሀግ የሚመራው ማንችስተር ዩናይትድ ለተጨዋቹ ዝውውር 42.5 ሚልዮን ዩሮ መክፈላቸው ተገልጿል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
ዕለታዊ ከሳፋሪኮም ወደ ቴሌ የሚያስደውለን የድምፅ ጥቅል በመግዛት በእጥፍ የድምጽ ደቂቃዎች በሽ በሽ እያልን እንደዋወል!
0️⃣7️⃣👉🏼0️⃣9️⃣ ከሳፋሪኮም ጋር በአብሮነት አንድ ወደፊት⚡️

🔗የM-PESA ሳፋሪኮም መተግበሪያ በዚህ ሊንክ እናዉርድ:
https://play.google.com/store/apps/details?id=et.safaricom.
mpesa.lifestyle

ስለ አገልግሎታችን ማንኛውንም ጥያቄ ወይም መረጃ በቴሌግራም ቻናላችን
https://www.tg-me.com/Safaricom_Ethiopia_PLC 24/7 ማግኘት ይቻላል!

#MPESASafaricom
#SafaricomEthiopia
#1Wedefit
#Furtheraheadtogether
TIKVAH-SPORT
ማንችስተር ዩናይትድ በይፋ ተጨዋች አስፈረመ ! ማንችስተር ዩናይትድ ኔዘርላንዳዊውን የፊት መስመር ተጨዋች ጆሽዋ ዚርክዜ ማስፈረማቸውን ይፋ አድርገዋል። ኔዘርላንዳዊው የፊት መስመር ተጨዋች ጆሽዋ ዚርክዜ በማንችስተር ዩናይትድ ቤት እስከ 2029 የሚያቆየውን ኮንትራት መፈረም ችሏል። በአሰልጣኝ ኤሪክ ቴንሀግ የሚመራው ማንችስተር ዩናይትድ ለተጨዋቹ ዝውውር 42.5 ሚልዮን ዩሮ መክፈላቸው ተገልጿል።…
" ዩናይትድን መቀላቀል ለእኔ ክብር ነው " ዚርክዜ

ለቀያዮቹ ሴጣኖች በይፋ ፊርማውን ያኖረው ኔዘርላንዳዊውን የፊት መስመር ተጨዋች ጆሽዋ ዚርክዜ ማንችስተር ዩናይትድን መቀላቀል ለእሱ ክብር መሆኑን በሰጠው አስተያየት ተናግሯል።

" ለማሸነፍ ሁሉንም የሚሰጥ ተጨዋች ነኝ " የሚለው ጆሽዋ ዚርክዜ በቀጣይ አዲስ ፈተና ለመጋፈጥ እና ዋንጫዎች ለማሸነፍ ዝግጁ ነኝ ፣ ታላቅ ክለብ መቀላቀል ለእኔ ክብር ነው።"ብሏል።

" ከአሰልጣኝ ኤሪክ ቴንሀግ እና ከክለቡ ሀላፊዎች ጋር ከተነጋገርኩ በኋላ እዚህ የሚኖረው የወደፊት ሁኔታ አስደሳች እንደሚሆን አውቄያለሁ በክለቡ ስኬት የበኩሌን ለመወጣት ጓጉቻለሁ።" ዚርክዜ

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
TIKVAH-SPORT
የዌምበልደን ፍፃሜ ተፋላሚዎች ታወቁ ! ለአንድ መቶ ሰላሳ ሰባተኛ ጊዜ የሚካሄደው የዘንድሮው የ 2024 የታላቁ የዌምበልን የሜዳ ቴነስ ውድድር ፍፃሜ ተፋላሚዎች በሁለቱም ፆታዎች ተለይተው ታውቀዋል። በወንዶች የዌምበልደን ፍፃሜ የባለፈው አመት የፍፃሜ ተፋላሚዎች ስፔናዊው ካርሎስ አልካራዝ እና ሰርቢያዊው ኖቫክ ጆኮቪች በድጋሜ ተገናኝተዋል። ባለፈው አመት ስፔናዊው ካርሎስ አልካራዝ የሰባት ጊዜ…
ዌምበልደን በካርሎስ አልካራዝ አሸናፊነት ተጠናቀቀ !

ወጣቱ ስፔናዊ ካርሎስ አልካራዝ ለአንድ መቶ ሰላሳ ሰባተኛ ጊዜ የተካሄደውን የ 2024 ዌምበልደን የሜዳ ቴኒስ ውድድር ፍፃሜ ኖቫክ ጆኮቪችን በመርታት አሸናፊ ሆኗል።

የ 21ዓመቱ ካርሎስ አልካራዝ ሁለተኛ የዌምበልን የሜዳ ቴኒስ ውድድር ድሉን በተከታታይ አመታት ኖቫክ ጆኮቪችን በመርታት ማሳካት ችሏል።

በተጨማሪም ወጣቱ ካርሎስ አልካራዝ አራተኛ የግራንድ ስላም ዋንጫውን በማሳካት አስደናቂ ጊዜን በማሳለፍ ላይ ይገኛል።

ካርሎስ አልካራዝ በተመሳሳይ አመት የዌምበልደን እና ሮላንድ ጋሮስ ውድድርን ያሸነፈው በእድሜ ትንሹ ተጨዋች በመሆን አዲስ ታሪክ ፅፏል።

በተጨማሪም በተከታታይ አመት የዌምበልደን ውድድርን ያሸነፈ የመጀመሪያው ስፔናዊ እንዲሁም ሶስተኛው በእድሜ ትንሹ ተጨዋች መሆን ችሏል።

ስፔናዊው ካርሎስ አልካራዝ ከውድድሩ ፍፃሜ በፊት በሰጠው አስተያየት " እሁድ ለስፔናዊያን አስደሳች ቀን ይሆናል " ሲል አስተያየቱን ሰጥቶ ነበር።

ከድሉ በኋላ ስለ አውሮፓ ዋንጫ ፍፃሜ አስተያየቱን የሰጠው ካርሎስ አልካራዝ " የራሴን ስራ አጠናቅቄያለሁ በእግርኳስ ደግሞ የሚፈጠረውን እናያለን " ሲል ሀገሩ ስፔንን ለመደገፍ ጨዋታውን እንደሚመለከት ገልጿል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
የጨዋታ አሰላለፍ !

4:00 ስፔን ከ እንግሊዝ ( አውሮፓ ዋንጫ ፍፃሜ )

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
" ዊሊያምስን ለማስቆም የቻልኩትን አደርጋለሁ " ዎልከር

የእንግሊዝ ብሔራዊ ቡድን የመስመር ተጨዋች ካይል ዎከር በምሽቱ ጨዋታ ኒኮ ዊሊያምስን ለማስቆም የቻለውን ሁሉ እንደሚያደርግ ከጨዋታው በፊት ተናግሯል።

የኒኮ ዊሊያምስን በርካታ ቪድዮች መመልከቱን የገለፀው ካይል ዎከር " እሱ ፈጣን እና የተዋጣለት ባለተሰጥኦ ተጨዋች ነው ፣ ለማስቆም የቻልኩት ሁሉ አደርጋለሁ " ሲል ተናግሯል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
" ታሪክ የምንፅፍበት እድል አለን " ሳውዝጌት

የእንግሊዝ ብሔራዊ ቡድን ዋና አሰልጣኝ ጋሪዝ ሳውዝጌት ቡድናቸው ዛሬ ምሽት ትልቅ ታሪክ የሚፅፍበት እድል እንዳለው በሰጡት አስተያየት ተናግረዋል።

" ለታሪክ የሚቀመጥ ምሽት ማድረግ እንፈልጋለን " የሚሉት አሰልጣኝ ጋሪዝ ሳውዝጌት ቡድናችን ጥሩ መንፈስ ላይ ነው ዛሬ ታሪክ የምንፅፍበት ትልቅ እድል አለን ብለዋል።

አሰልጣኙ አያይዘውም በጨዋታው በቋሚ አሰላለፍ የገባው ሉክ ሾው ለጨዋታው ዝግጁ መሆኑን ሲገልፁ ልምድ ያለው እና ቡድኑ ሚዛኑን እንዲጠብቅ እንደሚያግዝ ገልጸዋል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
TIKVAH-SPORT
#CopaAmerica2024 በአሜሪካ አዘጋጅነት እየተካሄደ የሚገኘው የዘንድሮው የ2024 የኮፓ አሜሪካ ውድድር ፍፃሜ ጨዋታ ዛሬ ሌሊት 9:00 በአርጀንቲና እና ኮሎምቢያ መካከል ይደረጋል። ትላንት በተደረገ የደረጃ ጨዋታ ዩራጓይ ካናዳን በመለያ ምት በማሸነፍ የውድድሩን ሶስተኛ ደረጃ በመያዝ ማጠናቀቅ ችለዋል። የኮፓ አሜሪካ ፍፃሜ ጨዋታን ብራዚላዊው የ 44ዓመት ዳኛ ራፋኤል ክላውስ በመሐል ዳኝነት…
" ሜሲን ለማስቆም የሚያስችል መፍትሔ አላየሁም " ሀሜስ ሮድሪጌዝ

በኮፓ አሜሪካ ዋንጫ ጥሩ ግዜን በማሳለፍ ላይ የሚገኘው ኮሎምቢያዊው ተጨዋች ሀሜስ ሮድሪጌዝ ቡድናቸው በዛሬው ፍፃሜ አርጀንቲናን ለማሸነፍ መጓጓቱን ገልጿል።

አርጀንቲና ልምድ ያለው ጠንካራ ብሔራዊ ቡድን ነው የሚለው ሀሜስ ሩድሪጌዝ " ነገርግን እኛ ዋንጫውን ለማሸነፍ ጓጉተናል ዋናው ነገር ይህ ነው ፣ ከሜሲ ጋር ስፔን ውስጥ ተጫውቻለሁ ነገርግን እሱን ማስቆም የሚችል መፍትሔ ያገኘ አሰልጣኝ አላየሁም " ብሏል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
የእረፍት ሰዓት !

በአውሮፓ ዋንጫ ፍፃሜ እንግሊዝ ከ ስፔን ጋር እያደረጉ የሚገኙትን ጨዋታ 0ለ0 በሆነ አቻ ውጤት ወደ መልበሻ ቤት አምርተዋል።

🟨 የቢጫ ካርድ የተመለከቱ ተጫዋቾች እነማን ናቸው ?

- በመጀመሪያው አጋማሽ በእንግሊዝ በኩል ሀሪ ኬን እንዲሁም በስፔን በኩል ዳኒ ኦልሞ የማስጠንቀቂያ ካርድ ተመልክተዋል።

የጨዋታው የኳስ ቁጥጥር ምን ይመስላል ?

- በመጀመሪያው አጋማሽ ስፔን 69% - 31% የኳስ ቁጥጥር ብልጫ ነበራቸው።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
46 ’

ስፔን 1 - 0 እንግሊዝ ( አውሮፓ ዋንጫ ፍፃሜ )

ኒኮ ዊሊያምስ

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
54 ’

ስፔን 1 - 0 እንግሊዝ ( አውሮፓ ዋንጫ ፍፃሜ )

ኒኮ ዊሊያምስ

- ላሚን ያማል በአውሮፓ ዋንጫው አራት ለግብ የሚሆኑ ኳሶችን አመቻችቶ በማቀበል ቀዳሚው ተጨዋች መሆን ችሏል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
72 ’

ስፔን 1 - 1 እንግሊዝ ( አውሮፓ ዋንጫ ፍፃሜ )

ኒኮ ዊሊያምስ ፓልመር

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
2024/10/03 17:16:48
Back to Top
HTML Embed Code: