Telegram Web Link
የአሰልጣኝ ጋሪዝ ሳውዝጌት የእንግሊዝ ቆይታ ?

የእንግሊዝ እግር ኳስ ማህበር አሰልጣኝ ጋሪዝ ሳውዝጌት በእንግሊዝ ብሔራዊ ቡድን አሰልጣኝነታቸው እንዲቀጥሉ እንደሚፈልጉ ተገልጿል።

እንግሊዝ እሁድ ከስፔን በምታደርገው የአውሮፓ ዋንጫ ፍፃሜ ጨዋታ ውጤት ምንም ቢሆን አሰልጣኝ ጋሪዝ ሳውዝጌት እንዲቀጥሉ ይፈልጋሉ።

አሰልጣኝ ጋሪዝ ሳውዝጌት የአውሮፓ ዋንጫው ከመጀመሩ አስቀድሞ ዋንጫውን የማያሸንፉ ከሆነ ብሔራዊ ቡድኑን ሊለቁ እንደሚችሉ ጠቁመው ነበር።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
TIKVAH-SPORT
Photo
የዩራጓይ ተጨዋቾች ቅጣት ሊጣልባቸው ይችላል !

የደቡብ አሜሪካ እግርኳስ ማህበር ትላንት ሌሊት በዩራጓይ ተጨዋቾች እና ኮሎምቢያ ደጋፊዎች መካከል የተፈጠረውን ክስተት እየመረመረ እንደሚገኝ ባወጣው ይፋዊ መግለጫ አስታውቋል።

በጨዋታው ዳርዊን ኑኔዝን ጨምሮ የዩራጓይ ብሔራዊ ቡድን ተጨዋቾች ወደ ተመልካች መቀመጫ ወንበር በመግባት ከኮሎምቢያ ደጋፊዎች ጋር ተደባድበው ነበር።

ተጨዋቾቹ ከደጋፊዎች ጋር ፀብ ውስጥ የገቡት የኮሎምቢያ ደጋፊዎች ቤተሰቦቻቸውን ለማጥቃት መሞከራቸውን ተከትሎ እንደሆነ መግለፃቸው ይታወሳል።

የሊቨርፑሉ ተጨዋች ዳርዊን ኑኔዝ እና በተፈጠረው አለመግባባት የተሳተፉ ሌሎች የዩራጓይ ተጨዋቾች ተፈፃሚነቱ እስከ ሊግ የሚደርስ የጨዋታ እገዳ ቅጣት ሊጠብቃቸው እንደሚችል ተገልጿል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
ለተሰንበት ግደይ ከኦሎምፒክ ለምን ቀረች ?

የዘንድሮው የአለም አትሌቲክስ የስፖርታዊ ጨዋነት ሽልማት አሸናፊዋ አትሌት ለተሰንበት ግደይ በዘንድሮው የ2024 ፓሪስ ኦሎምፒክ ውድድር ሀገሯን አትወክልም።

አትሌት ለተሰንበት በኦሎምፒክ ውድድር የማትሳተፈው በቅርቡ በፈፀመችው ጋብቻ ምክንያት በቂ የልምምድ ጊዜ ባለማግኘቷ መሆኑን የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ፕሬዝዳንት ረ/ኮሚሽነር ደራርቱ ቱሉ ከሸገር ኤፍኤም ጋር ባደረገችው ቆይታ ተናግራለች።

" ለተሰንበት ጋብቻ ፈፅማለች እኛም በጣም ደስ ብሎናል " ያለችው ደራርቱ ቱሉ "  በአጋጣሚ ለጋብቻ ስነ ስርዓቱ መሄድ አልቻልንም ለሌሎች አትሌቶች እንደምናደርገው ወይ ከኦሎምፒክ ስንመለስ ያለችበት ሄደን እንኳን ደስ አለሽ እንላታለን " ብላለች።

" ለተሰንበት ግደይ ጨዋ እና በሐይማኖቷ ጠንካራ የሆነች አትሌት ነች እንደ እናት በጣም ደስ ብሎኛል ፣ ለሁሉም አትሌቶች የምመኘው ነው ብትመጣ እና በኦሎምፒክ አብራን ብትሆን ደስ ይለን ነበር።" ደራርቱ ቱሉ

አትሌት ለተሰንበት ግደይ ከወራት በፊት በትግራይ ክልል መቐለ ከተማ በሐይማኖታዊ ስነ-ስርዓት ጋብቻዋን ፈፅማለች።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
TIKVAH-SPORT
አርሰናል ወጣት ግብ ጠባቂ ለማስፈረም ጠየቀ ! አማራጭ ግብ ጠባቂ ለማስፈረም በእንቅስቃሴ ላይ የሚገኘው አርሰናል የአያክሱን እንግሊዛዊ ወጣት ግብ ጠባቂ ቶሚ ሴትፎርድ ለማስፈረም የዝውውር ጥያቄ ማቅረባቸው ተገልጿል። ባለ ጥሩ ተሰጥኦ ባለቤት መሆኑ የተነገረው የ 18ዓመቱ ግብ ጠባቂ ቶሚ ሴትፎርድ በአያክስ ያለው ውል በ2025 የሚጠናቀቅ ሲሆን መድፈኞቹን መቀላቀል ይፈልጋል ተብሏል። መድፈኞቹ ከቀናት…
አርሰናል ሶስት ግብ ጠባቂ ማስፈረም ይፈልጋል !

የሰሜን ለንደኑ ክለብ አርሰናል በዝውውር መስኮቱ መጀመሪያ ሶስት ግብ ጠባቂዎችን ለማስፈረም አቅደው እየተንቀሳቀሱ መሆኑ ተገልጿል።

መድፈኞቹ የቁጥር አንድ ግብ ጠባቂ ቦታውን ስፔናዊውን ዴቪድ ራያ በቋሚነት በማስፈረም መጀመራቸው ተነግሯል።

መድፈኞቹ በቀጣይ ቁጥር ሁለት እና ቁጥር ሶስት ግብ ጠባቂ ለማስፈረም በጥረት ላይ እንደሚገኙ ተዘግቧል።

አሮን ራምስዴል በቀጣይ ክለቡን ከለቀቀ በቁጥር ሁለት ግብ ጠባቂነት ስፔናዊውን የእስፓኞል ግብ ጠባቂ ሁዋን ጋርሽያ የመጀመሪያ ምርጫቸው እንደሚያደርጉ ተገልጿል።

በተጨማሪም ቁጥር ሶስት ግብ ጠባቂ አድርገው የመጀመሪያ ተመራጭ ያደረጉት የዝውውር ጥያቄ ያቀረቡለትን የ 18ዓመቱን የአያክስ ግብ ጠባቂ ቶሚ ሴትፎርድ መሆኑ ተገልጿል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
TIKVAH-SPORT
ዩናይትድ ዝውውሮቹን በፍጥነት ማጠናቀቅ ይፈልጋሉ ! በዝውውር መስኮቱ ንቁ ተሳትፎ እያደረጉ የሚገኙት ማንችስተር ዩናይትዶች የማትያስ ዴሊትን እና ጆሽዋ ዚርክዜን ዝውውር በፍጥነት ለማጠናቀቅ እየሰሩ መሆኑ ተገልጿል። ማንችስተር ዩናይትድ አሁን ላይ ከባየር ሙኒክ ጋር በማትያስ ዴሊት የዝውውር ሒሳብ ዙሪያ ለስምምነት መቃረባቸው ተነግሯል። ቀያዮቹ ሴጣኖች በተጨማሪም ጆሽዋ ዚርክዜን ዝውውር ለማጠናቀቅ…
የሙኒክ ደጋፊዎች ዴሊት እንዳይለቅ ድምጽ አሰባሰቡ !

የጀርመኑ ክለብ ባየር ሙኒክ ደጋፊዎች የተከላካይ ስፍራ ተጨዋቹ ማትያስ ዴሊት ወደ ማንችስተር ዩናይትድ የሚያደርገውን ዝውውር ለማስቆም ድምጽ ማሰባሰባቸው ተገልጿል።

ማትያስ ዴሊት ባየር ሙኒክን እንዳይለቅ በተጀመረው የድምፅ ማሰባሰብ ሂደት ላይ 68,000 የክለቡ ደጋፊዎች መፈረማቸው ተነግሯል።

ማንችስተር ዩናይትድ ተጫዋቹን በ50 ሚልዮን ዩሮ የዝውውር ሒሳብ ለማስፈረም ከባየር ሙኒክ ጋር ለመስማማት መቃረባቸው ይታወቃል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
TIKVAH-SPORT
ማድሪድ ለኪሊያን ምባፔ አቀባበል ያደርጋል ! ሪያል ማድሪድ በቅርቡ ወደ ቡድናቸው የቀላቀሉትን ፈረንሳዊው የፊት መስመር ተጨዋች ኪሊያን ምባፔ ቀጣይ ሳምንት ደማቅ አቀባበል እንደሚያደርጉለት ይፋ አድርገዋል። ሎስ ብላንኮዎቹ ለኪሊያን ምባፔ ቀጣይ ሳምንት ማክሰኞ ሐምሌ 9/2016 ዓ.ም ይፋዊ አቀባበል በሳንቲያጎ በርናቦ ስታዲየም ማዘጋጀታቸውን አስታውቀዋል። ኪሊያን ምባፔ ከይፋዊ ትውውቁ በኋላ በሳንቲያጎ…
በምባፔ አቀባበል ላይ 80,000 ደጋፊዎች ይጠበቃሉ !

ሪያል ማድሪድ በሳንቲያጎ በርናቦ ፈረንሳዊውን የፊት መስመር ተጨዋች ኪሊያን ምባፔ ለማስተዋወቅ ያዘጋጀው የመግቢያ ትኬቶች ተሸጠው መጠናቀቃቸው ተገልጿል።

ይህንንም ተከትሎ በአቀባበል ስነስርዓቱ 80,000 የሪያል ማድሪድ ደጋፊዎች በሳንቲያጎ በርናቦ ስታዲየም ይገኛሉ ተብሎ ይጠበቃል።

በአቀባበሉ ዚነዲን ዚዳንን ጨምሮ በርካታ የሪያል ማድሪድ የቀድሞ ታሪካዊ ተጨዋቾች እንዲገኙ ግብዣ እንደቀረበላቸው ተነግሯል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
Forwarded from WANAW SPORT
🇪🇹 WANAW 🤝 ESCFUK 🇬🇧

የኢትዮጵያ ስፖርትና ባህል ፌደሬሽን በዩናይትድ ኪንግደም ከሐምሌ 12-14፣ 2024 የሚያዘጋጀው 12ኛው አመታዊ የስፖርትና የባህል ፌስቲቫል ዛሬ ይጀምራል!

ዋናው ስፖርት የዚህ ደማቅ ፌስቲቫል ይፋዊ ስፖንሰር እና ትጥቅ አቅራቢ በመሆኑ በድጋሚ የተሰማውን ኩራት ይገልፃል።

Instagram | Facebook | TikTok

🏅 ዋናው ወደፊት...

@wanawsportwear
🎉ፏ ፈሽ በአርባምንጭ ከሳፋሪኮም ጋር!🎊

ሳፋሪኮም ኢትዮጵያ የ2016 ሳፋሪኮም ታላቁ የአርባምንጭ ሩጫ የክብር ስፖንሰር በመሆኑ ታላቅ ኩራት ይሰማዋል! ለመጀመሪያ ግዜ እየተደረገ ባለው በዚህ የታላቁ ኢትዮጵያ የሩጫ ውድድር በአረንጓዴዋና ውቢቷ አርባምንጭ ተገናኝተን በጋራ ፏ ፈሽ እንበል!

🎽የታላቁን የአርባምንጭ ሩጫን ቲሸርት በM-PESA እየገዛን ከሴቻ (ፌሬንድሽ ካፌ) ወይም ከሲቀላ(ቱሪስት ሆቴል) እንውሰድ!

🌴 ሐምሌ 7 እንገናኝ!

🔗የM-PESA ሳፋሪኮም መተግበሪያ በዚህ ሊንክ እናዉርድ:
https://play.google.com/store/apps/details?id=et.safaricom.mpesa.lifestyle
ስለ አገልግሎታችን ማንኛውንም ጥያቄ ወይም መረጃ በቴሌግራም ቻናላችን https://www.tg-me.com/Safaricom_Ethiopia_PLC 24/7 ማግኘት ይቻላል!

#MPESASafaricom
#SafaricomEthiopia
#1Wedefit
#Furtheraheadtogether
#EURO2024

እንግሊዝ ውስጥ በርካታ ትምህርት ቤቶች ተማሪዎቻቸው በመጪው ሰኞ ጠዋት ከተለመደው የመግቢያ ሰዓት ዘግይተው እንዲገቡ ፍቃድ እንደሚሰጡ ተገልጿል።

ትምህርት ቤቶቹ ይህንን የሚያደርጉት ተማሪዎቹ እሁድ ምሽት እንግሊዝ ከስፔን ጋር የምታደርገውን የአውሮፓ ዋንጫ ፍፃሜ ጨዋታ አምሽተው እንዲመለከቱ መሆኑ ተነግሯል።

አንዳንድ ትምህርት ቤቶች ዛሬ ተማሪዎቻቸው የእንግሊዝ ብሔራዊ ቡድን ማልያን ለብሰው እንዲገቡ መፍቀዳቸው ተገልጿል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
ምባፔ የራሱን ክለብ ሊገዛ መሆኑ ተገለጸ !

ፈረንሳዊው የሪያል ማድሪድ የፊት መስመር ተጨዋች ኪሊያን ምባፔ በቀጣይ የራሱን እግርኳስ ክለብ ለመግዛት ማቀዱ ተገልጿል።

ኪሊያን ምባፔ እና ቤተሰቡ በቀጣይ በፈረንሳይ ሁለተኛ ሊግ የሚወዳደረውን ኮን እግርኳስ ክለብ ለመግዛት ማሰባቸው ተነግሯል።

ምባፔ በልጅነቱ ተጫውቶበት እንደነበር የተገለፀው ክለቡ በአሁን ሰዓት በፈረንሳይ ሊግ ሁለት ሲወዳደር ባለፈው አመት ዘጠነኛ ደረጃን በመያዝ አጠናቋል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
ማንችስተር ሲቲ ከተጫዋቹ ጋር ተለያየ !

ስፔናዊው የግራ መስመር ተጫዋች ሰርጂዮ ጎሜዝ ማንችስተር ሲቲን በመልቀቅ የስፔኑን ክለብ ሪያል ሶሴዳድ መቀላቀሉ ይፋ ተደርጓል።

ከሁለት አመታት በፊት ከአንደርሌክት ማንችስተር ሲቲን የተቀላቀለው ተጨዋቹ በ 10 ሚልዮን ዩሮ ሪያል ሶሴዳድን መቀላቀሉ ተገልጿል።

ተጨዋቹ በሪያል ሶሴዳድ ቤት አስከ 2030 የሚያቆየውን የስድስት አመት ኮንትራት መፈረሙ ተዘግቧል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
TIKVAH-SPORT
ጆኒ ኢቫንስ በዩናይትድ ሊቆይ ነው ! ማንችስተር ዩናይትድ የተከላካይ ስፍራ ተጨዋቹን ጆኒ ኢቫንስ ኮንትራት ለተጨማሪ አመት ለማራዘም ንግግር ላይ መሆናቸውን አስታውቀዋል። እንግሊዛዊው ግብ ጠባቂ ቶም ሂተን በተመሳሳይ ውሉን ለማራዘም ከክለቡ ጋር በንግግር ላይ መሆናቸው ተዘግቧል። የክለቡ አካዳሚ ውጤት የሆነው ብራንደን ዊሊያምስ በበኩሉ ከክለቡ ጋር ከአመታት በኋላ መለያየቱ ይፋ ተደርጓል። ማንችስተር…
ዩናይትድ የተጫዋቹን ውል አራዘመ !

ማንችስተር ዩናይትድ የተከላካይ ስፍራ ተጨዋቹን ጆኒ ኢቫንስ ኮንትራት ለተጨማሪ አመት ማራዘማቸውን ይፋ አድርገዋል።

ጆኒ ኢቫንስ በማንችስተር ዩናይትድ ቤት ለተጨማሪ አንድ የውድድር አመት ለመቆየት ፊርማውን ማኖሩ ተገልጿል።

“ ውሌን በማንችስተር ዩናይትድ በማራዘሜ ተደስቻለሁ ፣ ባለፈው በጋራ ያሳካነው ኤፌ ካፕ የማይረሳ ነበር አሁንም በቀጣይ ተጨማሪ ዋንጫዎችን ማሸነፍ እንደምንችል አውቃለሁ።"ሲል ኢቫንስ ከፊርማው በኋላ ተናግሯል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
ኬፓ አሪዛባላጋ ወደ ሳውዲ ሊያመራ ነው !

ስፔናዊው የምዕራብ ለንደኑ ክለብ ቼልሲ ግብ ጠባቂ ኬፓ አሪዛባላጋ በቀጣይ ወደ ሳውዲ አረቢያ ሊግ ለማምራት በንግግር ላይ መሆኑ ተገልጿል።

የ 29ዓመቱ ግብ ጠባቂ ኬፓ አሪዛባላጋ አሁን ላይ የሳውዲ አረቢያውን ክለብ አል ኢትሀድ ለመቀላቀል በንግግር ላይ እንደሚገኝ ተዘግቧል።

ኬፓ አሪዛባላጋ ያለፈውን የውድድር አመት በሪያል ማድሪድ ቤት በውሰት ማሳለፉ ይታወሳል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
የአውሮፓ ዋንጫ ፍፃሜ ደረሰ!

ከከባድ ትንቅንቅ በኋላ ስፔን እና እንግሊዝ ለፍፃሜ ሐምሌ 7 ከምሽቱ 4፡00 ሰዓት በጀርመን ኦሎምፒያስታዲዮን ይገናኛሉ!

እንግሊዝ ለመጀመሪያ ጊዜ ዋንጫውን ታነሳ ይሆን? ስፔንስ የአሸናፊነት መንገዷን ትቀጥል ይሆን? 

⚽️ Spain vs England ሐምሌ 7 ከምሽቱ 4፡00 ሰዓት | 10፡00 PM

👉SS Football ቻናል 225 በጎጆ ፓኬጅ
👉SS Euro2024 ቻናል 222 በሜዳ  ፓኬጅ

ዛሬውኑ ደንበኝነትዎን ያራዝሙ ጨዋታዎችን ከትንታኔ ፣ ከተጫዋች ብቃት እስከ ቡድን ወኔ በሱፐርስፖርት ልዩ በቀጥታ ይከታተሉ!

የዲኤስቲቪ አገልግሎቶችን ለማግኘት ከታች ያለውን የMyDStv Telegram bot ሊንክ ይጫኑ!
👇
https://bit.ly/3RFtEvh

#Euro2024onDStv #ሁሉምያለውእኛጋርነው #DStvEthiopia
ኢንተር ሚላን የአሰልጣኙን ውል አራዘመ !

የጣልያን ሴርያው ክለብ ኢንተር ሚላን የአሰልጣኝ ሲሞን ኢንዛጊን ኮንትራት ለተጨማሪ አመታት ማራዘማቸውን ይፋ አድርገዋል።

ከኢንተር ሚላን ጋር የመጀመሪያ የስኩዴቶ ዋንጫቸውን ያሳኩት ጣልያናዊው አሰልጣኝ ሲሞን ኢንዛጊ በክለቡ ለተጨማሪ ሁለት አመታት ለመቆየት ፊርማቸውን አኑረዋል።

ሲሞን ኢንዛጊ ከኢንተር ሚላን ጋር ባለፉት አመታት ምን አሳኩ ?

1️⃣ የሴርያ ዋንጫ

2️⃣ ኮፓ ኢጣልያ

3️⃣ ሱፐር ኮፓ እንዲሁም አንድ ጊዜ ለአውሮፓ ሻምፒየንስ ሊግ ፍፃሜ መድረስ ችለዋል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
TIKVAH-SPORT
ጆሽዋ ዚርክዜ ዛሬ ምሽት ወደ እንግሊዝ ያመራል ! ኔዘርላንዳዊው የፊት መስመር ተጨዋች ጆሽዋ ዚርክዜ ከቦሎኛ ወደ ማንችስተር ዩናይትድ የሚያደርገውን ዝውውር ለማጠናቀቅ ዛሬ ምሽት ወደ እንግሊዝ እንደሚያመራ ተገልጿል። የ 23ዓመቱ የፊት መስመር ተጨዋች ጆሽዋ ዚርክዜ በነገው ዕለት የህክምና ምርመራውን በማድረግ በይፋ ማንችስተር ዩናይትድን ይቀላቀላል። ማንችስተር ዩናይትድ ተጫዋቹን በ 42.5 ሚልዮን…
ጆሽዋ ዚርክዜ ለዩናይትድ ፊርማውን አኖረ !

ኔዘርላንዳዊው የፊት መስመር ተጨዋች ጆሽዋ ዚርክዜ ወደ ማንችስተር ዩናይትድ የሚያደርገውን ዝውውር  ለማጠናቀቅ ያደረገውን የህክምና ምርመራ ማጠናቀቁ ተገልጿል።

ተጨዋቹ አሁን ላይ በማንችስተር ዩናይትድ ቤት ለአንድ ተጨማሪ አመት የማራዘም አማራጭ ያካተተ የአምስት አመት ኮንትራቱን መፈረሙ ተገልጿል።

ማንችስተር ዩናይትድ በቀጣይ የተጫዋቹን ዝውውር ይፋ ያደርጋሉ ተብሎ ይጠበቃል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
TIKVAH-SPORT
ጄደን ሳንቾ ወደ ዩናይትድ ልምምድ ሊመለስ ነው ! የማንችስተር ዩናይትድ ተጨዋቾች በነገው እለት ሰኞ የቅድመ ውድድር ዝግጅታቸውን ለማድረግ ካሪንግተን ልምምድ ማዕከል ሪፖርት እንደሚገኙ ተገልጿል። በውሰት ለዶርትመንድ ሲጫወት የነበረው እና ከአሰልጣኝ ኤሪክ ቴንሀግ ጋር ያለውን ችግር ያልፈታው ጄደን ሳንቾ ነገ ወደ ክለቡ መመለስ እንደሚጠበቅበት ተነግሯል። ማንችስተር ዩናይትድን በቋሚ ዝውውር ለመልቀቅ…
ጄደን ሳንቾ ወደ ልምምድ ተመለሰ !

እንግሊዛዊው የማንችስተር ዩናይትድ የፊት መስመር ተጨዋች ጄደን ሳንቾ ከቡድኑ ጋር መደበኛ ልምምድ መጀመሩን ክለቡ ይፋ አድርጓል።

ጄደን ሳንቾ በዚህ ሳምንት ከአሰልጣኝ ኤሪክ ቴንሀግ ጋር ለንግግር ተቀምጦ እንደነበር ሲገለፅ አዎንታዊ ውይይት ማድረጋቸው ተነግሯል።

ባለፈው የውድድር አመት ተጨዋቹ ከአሰልጣኝ ኤሪክ ጋር የገባውን አለመግባባት ተከትሎ ከቡድኑ ተገሎ እንደቆየ እና በኋላም በውሰት ወደ ዶርትመንድ እንዳመራ ይታወሳል።

አሁን ላይ አሰልጣኝ ኤሪክ ቴንሀግ እና ሳንቾ አለመግባባታቸውን ወደ ጎን በመተው ወደፊት ለመቀጠል መስማማታቸው ሲገለፅ ለቀጣይ የቅድመ ውድድር ጨዋታዎች ዝግጁ እንደሚሆንም ተነግሯል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
" በክለቡ ውስጥ መጠነ ሰፊ ለውጥ መጥቷል " አርቴታ

የሰሜን ለንደኑ ክለብ አርሰናል ዋና አሰልጣኝ ሚኬል አርቴታ ባለፉት ጥቂት አመታት በክለቡ በሁሉም ቦታዎች ከአመት አመት መጠነ ሰፊ ለውጦች እየመጡ መሆኑን ገልጸዋል።

" አርሰናል አሁን የአስተሳሰብ ለውጥ አድርጎ ስለ ማሸነፍ እያሰበ ነው " ያሉት ሚኬል አርቴታ በክለቡ በሁሉም ቦታዎች የሚታዩ መጠነ ሰፊ ለውጦች እየመጡ ነው ብለዋል።

ለውጥ የመጣው በዋናው ቡድን ብቻ አለመሆኑን ያነሱት ሚኬል አርቴታ " የአካዳሚ እና ሴት ቡድናችን አቋምም ተቀይሯል ፣ በዋናው ቡድን የፈጠርነው ከባቢ የተለየ ነው " ሲሉ ገልጸዋል።

አሰልጣኝ ሚኬል አርቴታ ቀጥለውም ቡድናቸው በቀጣይ ቡድኑን በሚፈልግበት ቦታ ማስቀመጥ እና ለማሸነፍ ከበቂ በላይ መሆኑን ማመን እንዳለበት አሳስበዋል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
TIKVAH-SPORT
ኬፓ አሪዛባላጋ ወደ ሳውዲ ሊያመራ ነው ! ስፔናዊው የምዕራብ ለንደኑ ክለብ ቼልሲ ግብ ጠባቂ ኬፓ አሪዛባላጋ በቀጣይ ወደ ሳውዲ አረቢያ ሊግ ለማምራት በንግግር ላይ መሆኑ ተገልጿል። የ 29ዓመቱ ግብ ጠባቂ ኬፓ አሪዛባላጋ አሁን ላይ የሳውዲ አረቢያውን ክለብ አል ኢትሀድ ለመቀላቀል በንግግር ላይ እንደሚገኝ ተዘግቧል። ኬፓ አሪዛባላጋ ያለፈውን የውድድር አመት በሪያል ማድሪድ ቤት በውሰት ማሳለፉ…
ቼልሲ ለኬፓ የቀረበለትን ጥያቄ ውድቅ አደረገ !

የምዕራብ ለንደኑ ክለብ ቼልሲ የሳውዲ አረቢያው ክለብ አል ኢትሀድ ስፔናዊውን ግብ ጠባቂ ኬፓ አሪዛባላጋ ለማስፈረም ያቀረበውን ይፋዊ ጥያቄ ውድቅ ማድረጋቸው ተገልጿል።

ሰማያዊዎቹ ግብ ጠባቂውን በቋሚ ዝውውር ለመሸጥ ከአል ኢትሀድ እና ሌሎች ክለቦች ጋር ንግግራቸውን መቀጠላቸው ተነግሯል።

የ 29ዓመቱ ግብ ጠባቂ ኬፓ አሪዛባላጋ ያለፈውን የውድድር አመት በሪያል ማድሪድ ቤት በውሰት ማሳለፉ ይታወሳል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
Forwarded from HEY Online Market
•PlayStation 5, 73,000 Birr
•Playstaion 5 Slim, 78,000 Birr

•PlayStation 4 Slim, 35,000 Birr
•PlayStation 4 Pro, 43,000 Birr

•Playstaion portal, 35,000 Birr
•Meta Quest 2, 55,000 Birr
•Meta Quest 3, 83,000 Birr

Contact
0953964175 @heymobile

@heyonlinemarket
2024/10/03 13:30:48
Back to Top
HTML Embed Code: