Telegram Web Link
መልካም ዕድል!
ከፍ የተደረጉ ኦዶችን አይተዋል ? እንግዲያውስ ተወራረዱባቸው!
Mjallby - Malmo FF
National Bank Egypt - Smouha
ለተሻለ ውርርድ ቤቲካን ይጠቀሙ! አሁኑኑ Betika.et ላይ /በቴሌግራም ቦታችን - @BetikaETBot ይወራረዱ!
TIKVAH-SPORT
Video
ፖርቹጋላዊው ሉዊስ ናኒ አዲስ አበባ ደርሷል !

ፖርቹጋላዊው የቀድሞ የማንችስተር ዩናይትድ የፊት መስመር ተጨዋች ሉዊስ ናኒ ዛሬ ጠዋት ወደ ኢትዮጵያ አዲስ አበባ መጥቷል።

ተጨዋቹ ወደ ኢትዮጵያ የመጣው የመቻል 80ኛ አመት የምስረታ በዓል ላይ ተካፋይ ለመሆን የቀረበለትን ግብዣ ተከትሎ መሆኑ ተገልጿል።

በተጨማሪም ናይጄሪያዊው የቀድሞ የአርሰናል ተጨዋች ንዋንኮ ካኑ በምስረታ በዓሉ ለመካፈል ወደ ኢትዮጵያ መምጣቱ ታውቋል።

ለተጫዋቾቹ የቱሪዝም ሚኒስቴር ሚኒስትር ዴኤታ አቶ ስለሺ ግርማ ፣ የመቻል ስፖርት ክለብ ቦርድ ሰብሳቢ ዶክተር ሰይፈ ጌታሁን እና የመከላከያ ሚዲያ ስራዎች ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር ብርጋዴር ጄኔራል ኩማ ሚደቅሳ አቀባበል አድርገዋል።

ምንጭ - የኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት ሚዲያ

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
የዌምበልደን ፍፃሜ ተፋላሚዎች ታወቁ !

ለአንድ መቶ ሰላሳ ሰባተኛ ጊዜ የሚካሄደው የዘንድሮው የ 2024 የታላቁ የዌምበልን የሜዳ ቴነስ ውድድር ፍፃሜ ተፋላሚዎች በሁለቱም ፆታዎች ተለይተው ታውቀዋል።

በወንዶች የዌምበልደን ፍፃሜ የባለፈው አመት የፍፃሜ ተፋላሚዎች ስፔናዊው ካርሎስ አልካራዝ እና ሰርቢያዊው ኖቫክ ጆኮቪች በድጋሜ ተገናኝተዋል።

ባለፈው አመት ስፔናዊው ካርሎስ አልካራዝ የሰባት ጊዜ የዌምበልደን አሸናፊውን ኖቫክ ጆኮቪች በመርታት የውድድሩ ወጣት አሸናፊ መሆን ችሎ ነበር።

በፍፃሜው ኖቫክ ጆኮቪች ከአራት ተከታታይ የዌምበልደን ድል በኋላ ባለፈው አመት የተቀማውን ክብር ለመመለስ ሲፋለም ወጣቱ ካርሎስ አልካራዝ በድጋሜ የድል ካባውን ለመድፋት ይፋለማል።

የአለም ቁጥር ሁለቱ የሜዳ ቴኔስ ተጨዋች ኖቫክ ጆኮቪች ከአለም ቁጥር ሶስቱ ካርሎስ አልካራዝ የሚያደርጉት የፍፃሜ ፍልሚያ የፊታችን እሁድ ይደረጋል።

በሴቶች የዌምበልን የሜዳ ቴነስ ውድድር ፍፃሜ ቼክ ሪፐብሊካዊቷ ባርቦራ ክሬቺኮቫ ከጣልያናዊቷ ጃሴሚን ፓኦሊኒ ጋር ተገናኝተዋል።

የአለም ቁጥር ሰባቷ ጃሴሚን ፓኦሊኒ እና የአለም ቁጥር ሰላሳ ሁለቷ ባርቦራ ክሬቺኮቫ የፍፃሜ ጨዋታቸውን በዛሬው ዕለት ያደርጋሉ።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
TIKVAH-SPORT
የዩራጓይ ተጨዋቾች ቅጣት ሊጣልባቸው ይችላል ! የደቡብ አሜሪካ እግርኳስ ማህበር ትላንት ሌሊት በዩራጓይ ተጨዋቾች እና ኮሎምቢያ ደጋፊዎች መካከል የተፈጠረውን ክስተት እየመረመረ እንደሚገኝ ባወጣው ይፋዊ መግለጫ አስታውቋል። በጨዋታው ዳርዊን ኑኔዝን ጨምሮ የዩራጓይ ብሔራዊ ቡድን ተጨዋቾች ወደ ተመልካች መቀመጫ ወንበር በመግባት ከኮሎምቢያ ደጋፊዎች ጋር ተደባድበው ነበር። ተጨዋቾቹ ከደጋፊዎች ጋር…
" እንዴት ለቤተሰብህ ላትከላከል ትችላለህ " ማርሴሎ ቤልሳ

የዩራጓይ ብሔራዊ ቡድን ዋና አሰልጣኝ ማርሴሎ ቤልሳ በኮሎምቢያ ጨዋታ በተፈጠረው ክስተት የደቡብ አሜሪካ እግርኳስ ፌዴሬሽን እና አዘጋጇ አሜሪካን ተጠያቂ አድርገዋል።

አሜሪካ ውድድሩን በብቃት ልታስተናግድ አለመቻሏን የገለፁት አሰልጣኝ ማርሴሎ ቤልሳ ቡድናቸው የተጫወተባቸውን ሜዳዎች " ተቀባይነት የሌላቸው " ሲሉ ተችተዋል።

የቀረቡት የልምምድ ስፍራዎች ጥራት የሌላቸው መሆኑንም አያይዘው የገለፁት አሰልጣኙ የነበረው የደህንነት ሁኔታም አስተማማኝ አለመሆኑ እንዳሳዘናቸው ተናግረዋል።

በስታዲየሙ የነበረው የፀጥታ አካል የዩራጓይ ተጨዋቾች ቤተሰቦችን ከሰከሩ ደጋፊዎች እንኳን ሊጠብቅ አልቻለም ነበር ሲሉ ማርሴሎ ቤልሳ ቅሬታቸውን አቅርበዋል።

የዩራጓይ ተጨዋቾች ሊጣልባቸው ስለሚችል ቅጣት ሀሳብ የተጠየቁት አሰልጣኝ ማርሴሎ ቤልሳ " ለእናትህ ፣ እህትህ እና ልጅህ እንዴት ላትከላከል ትችላለህ ?" ሲል መልሰዋል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
“ ጀርመን ውስጥ የኬንን የዋንጫ ጥማት አስቀጥያለሁ “ ዳኒ ኦልሞ

የስፔን ብሔራዊ ቡድን የመሐል ሜዳ ተጨዋች ዳኒ ኦልሞ ሀሪ ኬን ዋንጫ እንዳያሸንፍ የማድረግ ስራውን ገና አለማጠናቀቁን በሰጠው አስተያየት ተናግሯል።

" ጀርመን ውስጥ የዋንጫ እርግማኑን ሊያጠፋ የተቃረበውን ሀሪ ኬን አስቁሜው አስቀጥዬለታሁ " የሚለው ዳኒ ኦሎም " አሁንም ስራዬ ገና አልተጠናቀቀም " ሲል ተናግሯል።

ባለፈው አመት ባየር ሙኒክ ላይ ሀትሪክ በመስራት የጀርመን ሱፐር ካፕ ዋንጫን ሌፕዚግ እንዲያሳካ ያገዘው ዳኒ ኦልሞ " ነገም ሀትሪክ መስራት እና ማሸነፍ ህልሜ ነው " ብሏል።

የአውሮፓ ዋንጫ ፍፃሜ ጨዋታ ነገ ምሽት 4:00 በስፔን እና እንግሊዝ መካከል ይደረጋል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
" ከሜሲ ጋር መጫወት እፈልጋለሁ " ላሚን ያማል

ስፔናዊው የባርሴሎና ተስፈኛ ኮከብ ላሚን ያማል አርኣያው እንደሆነ ከሚናገርልት አርጀንቲናዊው ሊዮኔል ሜሲ ጋር መጫወት እንደሚፈልግ ተናግሯል።

" ከሜሲ ጋር መጫወት እፈልጋለሁ " የሚለው ያማል በቀጣይ አርጀንቲና ኮፓ አሜሪካን እንደምታሸንፍ ተስፋ አደርጋለሁ ስፔን የአውሮፓ ዋንጫን ካሸነፈች በ " Finalissima " ከእሱ ጋር መጫወት እችላለሁ " ሲል ተናግሯል ።

በኮፓ አሜሪካ እና አውሮፓ ዋንጫ አሸናፊዎች መካከል የሚደረገው የ " Finalissima " ዋንጫ ጨዋታ በሚቀጥለው ክረምት ሊደረግ እንደሚችል ተገልጿል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
የወርቅ ጫማውን ስድስት ተጨዋቾች ሊያሸንፉ ይችላሉ !

ዩኤፋ ያለውን ህግ ማሻሻሉን ተከትሎ የዘንድሮውን የ2024 አውሮፓ ዋንጫ ውድድር ስድስት ተጨዋቾች ሊጋሩት እንደሚችሉ ተገልጿል።

በነገው የፍፃሜ ጨዋታ ሀሪ ኬን እና ዳኒ ኦልሞ ወይም ሌላ ተጨዋች ግብ ማስቆጠር የማይችል ከሆነ የወርቅ ጫማው ለስድስት ተጨዋቾች እንደሚሰጥ ተነግሯል።

የወርቅ ጫማውን ለማሸነፍ ሀሪ ኬን ፣ ዳኒ ኦልሞ ፣ ሙሲያላ ፣ ኮዲ ጋክፖ ፣ ሽራንዝ እና ሚካውታድዝ በሶስት ግቦች በመምራት ላይ ይገኛሉ።

ዩኤፋ ከዚህ በፊት ተጨዋቾች በእኩል ግቦች ሲያጠናቅቁ ብዙ ለግብ የሆኑ ኳሶች አመቻችቶ ያቀበለውን ተጨዋች ይመርጥ ነበር።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
አስቶን ቪላ አማዱ ኦናናን ሊያስፈርም ነው !

በአሰልጣኝ ኡናይ ኤምሬ የሚመራው አስቶን ቪላ ቤልጂየማዊውን የመሐል ሜዳ ተጨዋች አማዱ እናና ከኤቨርተን ለማስፈረም መቃረባቸው ተነግሯል።

የ 22ዓመቱ የመሐል ሜዳ ተጫዋች አማዱ ኦናና በአስቶን ቪላ ቤት የረጅም ጊዜ ኮንትራት ለመፈረም ከስምምነት መድረሳቸው ተገልጿል።

የአውሮፓ ሻምፒየንስ ሊግ ተሳታፊው ክለብ አስቶን ቪላ አማዱ ኦናናን በ50 ሚልዮን ፓውንድ የዝውውር ሒሳብ ለማስፈረም መስማማታቸው ተዘግቧል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
ዩናይትድ ተጫዋቹን ሊሸጥ ነው !

ማንችስተር ዩናይትድ ፈረንሳዊውን የተከላካይ ስፍራ ተጨዋች ዊሊ ካምብዋላ ለስፔኑ ክለብ ቪያሪያል ለመሸጥ ከስምምነት መድረሳቸው ተገልጿል።

ቪያሪያል ተጨዋቹን በ10 ሚልዮን ዩሮ ለመግዛት ከማንችስተር ዩናይትድ ጋር ከስምምነት መድረሳቸው ተነግሯል።

ተጨዋቹ በቀጣይ የህክምና ምርመራውን በማድረግ ቪያሪያልን በይፋ ለመቀላቀል ቀጠሮ እንደተያዘለት ተዘግቧል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
TIKVAH-SPORT
አስቶን ቪላ አማዱ ኦናናን ሊያስፈርም ነው ! በአሰልጣኝ ኡናይ ኤምሬ የሚመራው አስቶን ቪላ ቤልጂየማዊውን የመሐል ሜዳ ተጨዋች አማዱ እናና ከኤቨርተን ለማስፈረም መቃረባቸው ተነግሯል። የ 22ዓመቱ የመሐል ሜዳ ተጫዋች አማዱ ኦናና በአስቶን ቪላ ቤት የረጅም ጊዜ ኮንትራት ለመፈረም ከስምምነት መድረሳቸው ተገልጿል። የአውሮፓ ሻምፒየንስ ሊግ ተሳታፊው ክለብ አስቶን ቪላ አማዱ ኦናናን በ50 ሚልዮን…
ጃሬድ ብራንዝዌት ኤቨርተንን ላይለቅ ይችላል !

የመርሲሳይዱ ክለብ ኤቨርተን አማካይ አማዱ ኦናና ወደ አስቶን ቪላ ማምራት በማንችስተር ዩናይትድ የሚፈለገውን ጃሬድ ብራንዝዌት ዝውውር ሊያስቀረው እንደሚችል ተገልጿል።

አማዱ ኦናን በ50 ሚልዮን ፓውንድ ለአስቶን ቪላ ለመሸጥ የተቃረበው ኤቨርተን ከፍተኛ የዝውውር ሒሳብ ካልቀረበላቸው ጃሬድ ብራንዝዌትን በዚህ ክረምት ላይሸጡት እንደሚችሉ ተነግሯል።

ቀያዮቹ ሴጣኖች ለ 21ዓመቱ ተከላካይ ጃሬድ ብራንዝዌት 50 ሚልዮን ፓውንድ የሚደርስ ሒሳብ አቅርበው በኤቨርተን ውድቅ እንደሆነባቸው ይታወሳል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
TIKVAH-SPORT
Photo
“ ለወጣቶች ልምዴን ለማካፈል ዝግጁ ነኝ “ ናኒ

በመቻል ስፖርት ክለብ ምስርታ ላይ ለመገኘት ግበዣ ቀርቦለት ለመጀመሪያ ጊዜ ወደ ኢትዮጵያ የመጣው ሉዊስ ናኒ በመምጣቱ በጣም ደስተኛ መሆኑን ገልጿል።

" ኢትዮጵያ በመምጣቴ በጣም ደስተኛ ነኝ " ያለው ሉዊስ ናኒ " ኢትዮጵያን ባህሏን ሕዝቧን ማወቅ እፈልጋለሁ ፣ በመቻል ስፖርት ክለብ የምስረታ በዓል እንድገኝ ግብዣ ሲቀርብልኝ በደስታ ነው የተቀበልኩት " ሲልም ተናግሯል።

ግብዣው ኢትዮጵያን ለማየት እና ለመጎብኘት ዕድል እንደሚፈጥርለት የገለፀው የቀድሞ የማንችስተር ዩናይትድ ተጨዋች ሉዊስ ናኒ " ኢትዮጵያን ጨምሮ በአፍሪካ እግር ኳስ ስፖርተኞችን ለማውጣት ወጣቶችን እና አካዳሚ ላይ መሥራት ይገባል።

በቀጣይ ለወጣቶች ልምዴን ለማካፈል ዝግጁ ነኝ ለዛም ነው ወደ ኢትዮጵያ የመጣሁት“። በማለት ተናግሯል።

ምንጭ - ኢዜአ

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
Forwarded from WANAW SPORT
🇪🇹 ዋናው ስፖርት 🤝

✍🏾 ታላቅ ስምምነት ከ #ዋናው! ✍🏾

#ቅርብ ቀን ይጠብቁን...

Instagram | Facebook | TikTok

🏅 ዋናው ወደፊት...

@wanawsportwear
ከተመረጡ ባንኮች ወደ M-PESA ገንዘብ በማስተላልፍ በቀላሉ ክፍያዎችን እንፈፅም ፤ እስከ 50 ብር ተመላሽ ስጦታ እናግኝ።

M-PESA ላይ እንመዝገብ፣ በM-PESA እንገበያይ!

🔗የM-PESAን ሳፋሪኮም መተግበሪያ በዚህ ሊንክ እናውርድ ፡ https://play.google.com/store/apps/details?id=et.safaricom.mpesa.lifestyle

የቴሌግራም ቻናላችንን እዚህ እንቀላቀል 👉https://www.tg-me.com/Safaricom_Ethiopia_PLC

ስለ አገልግሎታችን ማንኛውንም ጥያቄ ወይም መረጃ  በቴሌግራም   ቻናላችን https://www.tg-me.com/Safaricom_Ethiopia_PLC 24/7 ማግኘት ይቻላል!

#MPESASafaricom  #FurtherAheadTogether
“ ሳካ እንዴት እንደሚጫወት አውቃለሁ “ ኩኩሬላ

የስፔን ብሔራዊ ቡድን የመስመር ተጨዋች ማርክ ኩኩሬላ በነገ ምሽቱ የፍፃሜ ጨዋታ ቡካዩ ሳካን ሜዳ ላይ ምቾት ለማሳጣት እንደሚሞክር በሰጠው አስተያየት ተናግሯል።

" ቡካዩ ሳካ እንዴት እንደሚጫወት አውቃለሁ " የሚለው ኩኩሬላ ስለ እሱ ቪድዮች መመልከት አይጠበቅብኝም ምክንያቱም ሁሉንም የአርሰናል ጨዋታዎች ተመልክቻቸዋለሁ ብሏል።

ከሳካ ጋር መጫወት ከባድ መሆኑን የገለፀው ተጨዋቹ " ነገርግን ይህ ፈተና ያስደስተኛል የመጀመሪያ አላማዬ እሱን ሜዳ ላይ ምቾት ማሳጣት ነው " በማለት ተናግሯል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
" እንግሊዝ የብሔራዊ ቡድን ሪያል ማድሪድ ነች " ዋትኪንስ

የእንግሊዝ ብሔራዊ ቡድን የፊት መስመር ተጨዋች ኦሊ ዋትኪንስ በአሁን ሰዓት የሶስቱን አናብስት ማሸነፍ አስቸጋሪ መሆኑን በሰጠው አስተያየት ተናግሯል።

" እንግሊዝ ማለት የብሔራዊ ቡድን ሪያል ማድሪድ ነች " የሚለው ኦሊ ዋትኪንስ " ሁኔታው ተመሳሳይ እንደሆነ ያሳያል እኛን ማሸነፍ በጣም አስቸጋሪ ነው እኛ ለማሸነፍ አንድ የግብ እድል በቂያችን ነው በማለት ተናግሯል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
" ማይኖ ነገ ግብ እንደሚያገባ ይሰማኛል " ሩኒ

የቀድሞ የእንግሊዝ ብሔራዊ ቡድን ተጨዋች ዋይን ሩኒ ኮቢ ማይኖ በነገው የአውሮፓ ዋንጫ ፍፃሜ ጨዋታ ለቡድኑ ጉልህ ሚና እንደሚኖረው ተናግሯል።

“ ኮቢ ማይኖ በነገው ጨዋታ ግብ እንደሚያስቆጥር እና በእንግሊዝ ውስጥ ጉልህ ሚና እንደሚኖረው ይሰማኛል “ የሚለው ዋይን ሩኒ እሱ በጥቂት አመታት ከአለም ምርጥ ተጨዋቾች አንዱ ይሆናል ብሏል።

“ ቤሊንግሀም ፣ ላሚን ያማል ፣ ኒኮ ዊሊያምስ እና ፎደን በአጥቂ ስፍራ ነው የሚጫወቱት ኮቢ ማይኖ ትልቅ ዲሲፕሊን እና የጨዋታውን ጥልቅ ግንዛቤ የሚጠይቅ ቦታ ነው የሚጫወተው “ ሩኒ

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
" እንግሊዝ ሻምፒዮን የምትሆንበት ጊዜ አሁን ነው " ዴክላን ራይስ

የእንግሊዝ ብሔራዊ ቡድን የመሐል ሜዳ ተጨዋች ዴክላን ራይስ ቡድናቸው የአውሮፓ ዋንጫው ሻምፒዮን የሚሆንበት ጊዜ አሁን መሆኑን በሰጠው አስተያየት ተናግሯል።

" ከብሔራዊ ቡድን ጋር በተከታታይ ለሁለተኛ ጊዜ ለፍፃሜ የመድረስ አጋጣሚ አይገኝም " የሚለው ዴክላን ራይስ ከባለፈው ፍፃሜ ተምረናል ነገ ማሸነፍ ነው ፍላጎታችን ሲል ተደምጧል።

ስፔን ሮድሪ ብቻ ሳይሆን ጥሩ አማካዮች መያዟን የገለፀው ዴክላን ራይስ " እንግሊዝ የአውሮፓ ዋንጫውን የምታሸንፍበት ጊዜ አሁን ነው " በማለት ተናግሯል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
መልካም ዕድል!
ከፍ የተደረጉ ኦዶችን አይተዋል ? እንግዲያውስ ተወራረዱባቸው!
Spain - England
Argentina - Colombia
ለተሻለ ውርርድ ቤቲካን ይጠቀሙ! አሁኑኑ Betika.et ላይ /በቴሌግራም ቦታችን - @BetikaETBot ይወራረዱ!
Forwarded from HEY Online Market
•PlayStation 5, 73,000 Birr
•Playstaion 5 Slim, 78,000 Birr

•PlayStation 4 Slim, 35,000 Birr
•PlayStation 4 Pro, 43,000 Birr

•Playstaion portal, 35,000 Birr
•Meta Quest 2, 55,000 Birr
•Meta Quest 3, 83,000 Birr

Contact
0953964175 @heymobile

@heyonlinemarket
2024/10/03 11:26:07
Back to Top
HTML Embed Code: