Telegram Web Link
💥 ከአስገራሚ ትንቅንቅ በኋላ የአውሮፓ ዋንጫ ግማሽ ፍፃሜ ተፋላሚዎች ታውቀዋል!

ስፔን እና አዘጋጅ ሃገር ጀርመን ካሰናበታች በኋላ ዛሬ ምሽት 4፡00 ሰዓት ለአውሮፓ ዋንጫ ግማሽ ፍፃሜ ከፈረንሳይ ጋር ይገናኛሉ! ማን ወደ ቀጣዩ ዙር የሚያልፍ ይመስላችኋል?

⚽️ Spain vs France ሀምሌ 2 ከምሽቱ 4፡00 ሰዓት | 10፡00 PM

👉SS Football ቻናል 225 በጎጆ ፓኬጅ
👉SS Euro2024 ቻናል 222 በሜዳ  ፓኬጅ

ዛሬውኑ ደንበኝነትዎን ያራዝሙ ጨዋታዎችን ከትንታኔ ፣ ከተጫዋች ብቃት እስከ ቡድን ወኔ በሱፐርስፖርት ልዩ በቀጥታ ይከታተሉ!

የዲኤስቲቪ አገልግሎቶችን ለማግኘት ከታች ያለውን የMyDStv Telegram bot ሊንክ ይጫኑ!
👇
https://bit.ly/3RFtEvh

#Euro2024onDStv #ሁሉምያለውእኛጋርነው #DStvEthiopia
TIKVAH-SPORT
ቲያጎ አልካንትራ ጫማውን ሊሰቅል ነው ! በቅርቡ ከሊቨርፑል ጋር የተለያየው ስፔናዊው የመሐል ሜዳ ተጨዋች ቲያጎ አልካንትራ ራሱን ከእግርኳስ አለም ለማግለል ከውሳኔ መድረሱ ተገልጿል። ተደጋጋሚ ጉዳቶች ሲያጋጥሙት የነበረው የቀድሞ የባየር ሙኒክ ተጨዋች ቲያጎ አልካንትራ ጫማውን ለመስቀል መገደዱ ተዘግቧል። ቲያጎ አልካንትራ አብዛኛውን የእግርኳስ ህይወቱን ያሳለፈው በባየር ሙኒክ ቤት ሲሆን በቆየባቸው…
ቲያጎ አልካንታራ ወደ አሰልጣኝነት ?

የቀድሞ ስፔናዊ አማካይ ቲያጎ አልካንታራ የቀድሞ ክለቡ ባርሴሎና አሰልጣኞች ቡድንን እንዲቀላቀል ከአሰልጣኝ ሀንሲ ፍሊክ ጋር መነጋገሩ ተገልጿል።

ስኬታማ የእግርኳስ ህይወትን በባርሴሎና ፣ ባየር ሙኒክ እና ሊቨርፑል ያሳለፈው ቲያጎ አልካንታራ በ 33ዓመቱ ጫማውን መስቀሉ ይታወቃል።

የባርሴሎናው ዋና አሰልጣኝ ሀንሲ ፍሊክ የቀድሞ ተጨዋቻቸው ቲያጎ አልካንታራ የአሰልጣኝ ቡድኑን እንዲቀላቀል እንደሚፈልጉ ተገልጿል።

ቲያጎ አልካንታራ በቀጣይ በቀረበለት የአዲስ ሚና ሀላፊነት ጥያቄ አስቦበት ከውሳኔ እንደሚደርስ ተነግሯል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
TIKVAH-SPORT
ዩናይትድ ጆሽዋ ዚርክዜን ለማስፈረም ተቃርበዋል ! ማንችስተር ዩናይትድ ኔዘርላንዳዊውን የፊት መስመር ተጨዋች ጆሽዋ ዚርክዜ ከቦሎኛ ለማስፈረም የመጨረሻ ምዕራፍ ላይ መሆናቸው ተገልጿል። በኔዘርላንዳዊው አሰልጣኝ ኤሪክ ቴንሀግ የሚመራው ማንችስተር ዩናይትድ ከተጨዋቹ ጋር በግል ከስምምነት መድረሳቸው ተነግሯል። ቀያዮቹ ሴጣኖች የ 23ዓመቱን ተጨዋች ጆሽዋ ዚርክዜ ለማስፈረም የውል ማፍረሻ ለመክፈል…
ዩናይትድ ተጨማሪ አጥቂ ሊመለከት ይችላል !

የቦሎኛውን የፊት መስመር ተጨዋች ጆሽዋ ዚርክዜን ለማስፈረም ከጫፍ የደረሱት ማንችስተር ዩናይትዶች ተጨማሪ አጥቂ ሊያስፈርሙ እንደሚችሉ ተገልጿል።

ማንችስተር ዩናይትድ በቀጣይ ለመመልከት ከያዟቸው አጥቂዎች መካከል ኢቫን ቶኒ እና ዶምኒክ ካልቨርት ሌዊን ቀዳሚዎቹ መሆናቸው ተገልጿል።

ቀያዮቹ ሴጣኖች ተፈጥሯዊ ዘጠኝ ቁጥር አጥቂ ለመግዛት ጥሩ ሽያጮችን መፈፀም ሊጠበቅባቸው እንደሚችል ተዘግቧል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
ሞይስ ኪን ፊዮሬንቲናን ተቀላቀለ !

ጣልያናዊው የፊት መስመር ተጨዋች ሞይስ ኪን ከጁቬንቱስ በመልቀቅ ፊዮሬንቲናን መቀላቀሉ ይፋ ተደርጓል።

ፊዮሬንቲና ለተጨዋቹ ዝውውር 18 ሚልዮን ዩሮ የሚደረሰስ የዝውውር ሒሳብ ወጪ  እንደሚያደርጉ ተገልጿል።

የ 24ዓመቱ የፊት መስመር ተጨዋች ሞይስ ኪን ለፊዮረንቲና የአምስት አመት ኮንትራት መፈረሙ ተነግሯል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
TIKVAH-SPORT
ማድሪድ ተጨዋች ለማስፈረም ተቃርበዋል ! ሪያል ማድሪድ ፈረንሳዊውን የተከላካይ ስፍራ ተጨዋች ሌኒ ዮሮ ከሊል ለማስፈረም እያደረጉት የሚገኙት ንግግር ለስምምነት መቃረቡ ተገልጿል። ሎስ ብላንኮዎቹ ለተጨዋቹ ዝውውር እስከ 40 ሚልዮን ዩሮ የዝውውር ሒሳብ በማውጣት ለማስፈረም መቅረባቸው ተዘግቧል። የ 18ዓመቱ ተከላካይ ሌኒ ዮሮ ሪያል ማድሪድ ባቀረበለት ዝውውር ደስተኛ መሆኑ ሲገለፅ በሎስ ብላንኮዎቹ…
ዩናይትድ ለሌኒ ዮሮ የዝውውር ጥያቄ አቀረቡ !

ማንችስተር ዩናይትድ ፈረንሳዊውን የተከላካይ ስፍራ ተጨዋች ሌኒ ዮሮ ለማስፈረም ለሊል ሪያል ማድሪድ ካቀረበው የተሻለ 50 ሚልዮን ዩሮ የዝውውር ሒሳብ ማቅረባቸው ተገልጿል።

የስፔኑ ክለብ ሪያል ማድሪድ ተጨዋቹን በ40 ሚልዮን ዩሮ ለማስፈረም መቃረባቸው መዘገቡ ይታወቃል።

የ 18ዓመቱ ተከላካይ ሌኒ ዮሮ ሪያል ማድሪድን ለመቀላቀል እንደሚመርጥ ቢገለፅም ማንችስተር ዩናይትድ በዝውውሩ ገፍተው መቀጠላቸው ተነግሯል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
TIKVAH-SPORT
ዩናይትድ ለሌኒ ዮሮ የዝውውር ጥያቄ አቀረቡ ! ማንችስተር ዩናይትድ ፈረንሳዊውን የተከላካይ ስፍራ ተጨዋች ሌኒ ዮሮ ለማስፈረም ለሊል ሪያል ማድሪድ ካቀረበው የተሻለ 50 ሚልዮን ዩሮ የዝውውር ሒሳብ ማቅረባቸው ተገልጿል። የስፔኑ ክለብ ሪያል ማድሪድ ተጨዋቹን በ40 ሚልዮን ዩሮ ለማስፈረም መቃረባቸው መዘገቡ ይታወቃል። የ 18ዓመቱ ተከላካይ ሌኒ ዮሮ ሪያል ማድሪድን ለመቀላቀል እንደሚመርጥ ቢገለፅም…
ሊል የዩናይትድን ጥያቄ መቀበላቸው ተገለጸ !

የፈረንሳዩ ክለብ ሊል ማንችስተር ዩናይትድ ለተከላካይ ስፍራ ተጨዋቻቸው ሌኒ ዮሮ በይፋ ያቀረበውን 50 ሚልዮን ዩሮ የዝውውር ሒሳብ መቀበላቸው ተገልጿል።

ሊል ተጨዋቹ ማንችስተር ዩናይትድ ያቀረበለትን ጥያቄ እንዲቀበል መጠየቃቸው የተገለፀ ሲሆን ተጨዋቹ አሁንም ቅድሚያ የሚሰጠው ለሪያል ማድሪድ መሆኑ ተዘግቧል።

ሎስ ብላንኮዎ አዲስ ሒሳብ እስካሁን አለማቅረባቸው እና የሚጠበቀው ውሳኔ የተጨዋቹ መሆኑ ተነግሯል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
" የማስፈርማቸው ተጨዋቾች እንደ ልጆቼ ናቸው " ዲ ዘርቢ

የኦሎምፒክ ማርሴይ ዋና አሰልጣኝ ሮቤርቶ ዲ ዘርቢ ቡድናቸው ሊያስፈርመው እያነጋገረ የሚገኘው ሜሰን ግሪንውድ በትልቅ ደረጃ የሚጠራ ተጨዋች መሆኑን ገልጸዋል።

" ሜሰን ግሪንውድ ትልቅ ተጨዋች ነው " ያሉት አሰልጣኝ ሮቤርቶ ዲ ዘርቢ ስላለፈ ህይወቱ አላውቅም ነገርግን የትኛውንም ተጨዋች ካስፈረምኩ ልክ እንደ ልጄ ነው የማየው ሁልጊዜም እከላከልለታለሁ።"ብለዋል።

ማርሴይ ሜሰን ግሪንውድን ከማንችስተር ዩናይትድ ለማስፈረም የተቃረቡ ሲሆን የክለቡ ደጋፊዎች በበኩላቸው በዝውውር ደስተኛ እንዳልሆኑ በማህበራዊ ሚዲያዎች እየገለፁ ይገኛሉ።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
" አዚህ የቆየሁት ዋንጫዎችን ለማሸነፍ ነው " ቴንሀግ

የማንችስተር ዩናይትዱ ዋና አሰልጣኝ ኤሪክ ቴንሀግ በቀጣይ ክለቡ በቅርቡ ካሳካቸው የኤፌ ካፕ እና ካራባኦ ካፕ ዋንጫዎች ደረጃውን ከፍ እንደሚያደርግ ገልጸዋል።

" እዚህ ያለሁት ዋንጫዎችን ለማሸነፍ ነው " ያሉት ኤሪክ ቴንሀግ የኤፌ ካፕ እና ካራባኦ ካፕ ዋንጫዎች አሸንፈናል በቀጣይ ደረጃችንን ማሻሻል አለብን በማለት ተናግረዋል።

ከእረፍት በኋላ ቡድኑ በጥሩ ስሜት ወደ ካሪንግተን መመለሱን ያነሱት አሰልጣኝ ኤሪክ ቴንሀግ " በቀጣይ ሁሉንም ጨዋታዎች ማሸነፍ እንፈልጋለን የትኛውንም ቡድን እንደምናሸንፍ አሳይተናል ብለዋል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
Forwarded from WANAW SPORT
🎁 #ዛሬም ይገምቱ፣ #ይሸለሙ!

🏆  በዛሬው ምሽት የ2024 አውሮፓ ዋንጫ የግማሽ ፍፃሜ ፍልሚያ ማን ድል ይነሳል?

🇪🇸 ስፔን ወይስ ፈረንሳይ
🇫🇷

💬 ግምትዎን #በገፃችን ኮሜንት ላይ ብቻ ያስቀምጡልን!

⚠️ የውድድሩ ህጎች፦
👉🏾 የጨዋታን አሸናፊ ሀገር እስከ የግብ መጠኑ #በትክክል ቀድመው የሚገምቱ #2 ተከታታዮቻችን የዋናውን የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ማልያዎች ይሸለማሉ።
👉🏾 የዋናውን ማህበራዊ ገፆች መከተል፣ መወዳጀትና ማጋራት አይዘንጉ።
👉🏾 የተስተካከሉና ተደጋጋሚ መልሶች በፍፁም ተቀባይነት የላቸውም።
👉🏾 አንድ ተሳታፊ ከሁለት ጊዜ በላይ አይሸለምም፡፡

Instagram | Facebook | TikTok

🏅 ዋናው ወደፊት...

@wanawsportwear
" ምባፔ አምበል ለመሆን ብቁ አይደለም " ኢማኑኤል ፔቲት

የቀድሞ ፈረንሳዊ ተጨዋች ኢማኑኤል ፔቲት ኪሊያን ምባፔ የፈረንሳይ ብሔራዊ ቡድን አምበል ለመሆን ብቁ አለመሆኑን በሰጠው አስተያየት ተናግሯል።

" ኪሊያን ምባፔ አሁን ላይ አምበል መሆኑ ምንም ጥቅም የለውም የአምበልነት ሚናው አይገባውም ነበር ሜዳ ላይ በቂ ሀላፊነት አይወስድም በጥሩ አካላዊ ቁመና ላይም አይገኝም።"ሲል ኢማኑኤል ፔቲት ተናግሯል።

ኪሊያን ምባፔ ዛሬ ምሽት የሚጫወተው ተጋጣሚዋ ስፔን ሴለሆነች ብቻ ነው እንጂ ተጠባባቂ ይሆን ነበር ሲል የቀድሞ ተጨዋቹ ተናግሯል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
የጨዋታ አሰላለፍ !

4:00 ስፔን ከ ፈረንሳይ

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
#EURO2024

ስፔናዊው የፊት መስመር ተጨዋች ላሚን ያማል በአውሮፓ ዋንጫ ውድድር ግማሽ ፍፃሜ ጨዋታ የሚሳተፍ በእድሜ ትንሹ ተጨዋች በመሆን አዲስ ታሪክ ይፅፋል።

የ 16ዓመቱ የፊት መስመር ተጨዋች ላሚን ያማል በታላላቅ ኢንተርናሽናል ውድድሮች የተሳተፈ በእድሜ ትንሹ ተጨዋች በመሆንም የፔሌን ሪከርድ ይሰብራል።

ፔሌ እ.ኤ.አ 1958 በ17 አመቱ በአለም ዋንጫ ውድድር ግማሽ ፍፃሜ በመሳተፍ ባለታሪክ ተጨዋች ነበር።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
ሻኪራ የኮፓ አሜሪካ ፍፃሜን ታደምቃለች !

በታላላቅ ኢንተርናሽናል ውድድሮች ባቀረበቻቸው ታሪካዊ ዜማዎች የምትታወቀው ኮሎምቢያዊቷ አርቲስት ሻኪራ የኮፓ አሜሪካ ውድድር ፍፃሜን ታደምቃለች።

የ 47ዓመቷ አርቲስት ሻኪራ በእድሜ አንጋፋ ከሆኑ የስፖርት ውድድሮች አንዱ በሆነው የኮፓ አሜሪካ ውድድር የምታቀነቅን የመጀመሪያዋ አርቲስት እንደምትሆን ተገልጿል።

የኮፓ አሜሪካ ውድድር ፍፃሜ ጨዋታ የፊታችን እሁድ ሌሊት 9:00 ሰዓት 54,000 ደጋፊዎች በሚይዘው ሀርድ ሮክ ስታዲየም ይደረጋል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
TIKVAH-SPORT
ማርሴይ ሜሰን ግሪንውድን ማስፈረም ይፈልጋል ! ጣልያናዊውን አሰልጣኝ ሮቤርቶ ዲ ዘርቢን በአሰልጣኝነት የሾመው የፈረንሳዩ ክለብ ማርሴይ ሜሰን ግሪንውድን ከማንችስተር ዩናይትድ ለማስፈረም ንግግር መጀመሩ ተገልጿል። ማርሴይ በተጨዋቹ ዝውውር ዙሪያ ማንችስተር ዩናይትድን ማነጋገር መጀመራቸው የተገለፀ ሲሆን እስካሁን በዝውውር ሒሳብ ዙሪያ መደራደር እንዳልጀመሩ ተጠቁሟል። የ 22ዓመቱ የፊት መስመር…
ማርሴይ ግሪንውድን ለማስፈረም ተስማማ !

ማርሴይ እንግሊዛዊውን የፊት መስመር ተጨዋች ሜሰን ግሪንውድ ለማስፈረም ከማንችስተር ዩናይትድ ጋር ከስምምነት መድረሳቸው ተገልጿል።

ማንችስተር ዩናይትድ ለተጨዋቹ ዝውውር የቀረበለትን አጠቃላይ 31 ሚልዮን ዩሮ የሚደርስ የዝውውር ሒሳብ መቀበሉ ተነግሯል።

በተጨማሪም ማንችስተር ዩናይትድ ከወደፊቱ የተጨዋቹ ሽያጭ ከግማሽ በላይ የሚሆነውን ገንዘብ ለመውሰድ ከስምምነት እንደደረሱ ተዘግቧል።

በሁለቱ ክለቦች መካከል የተደረሰው ስምምነት እስካሁን የሜሰን ግሪንውድን ይሁንታ አለማግኘቱ ተጠቁሟል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
ተጀመረ

ስፔን 0 - 0 ፈረንሳይ

- አፍንጫው ላይ ባጋጠመው ጉዳት ምክንያት ግጭት መከላከያ ማክስ ሲያደርግ የነበረው ኪሊያን ምባፔ ዛሬ ያለ ማስክ በመጫወት ላይ ይገኛል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
8 ' ስፔን 0 - 1 ፈረንሳይ

ሙኣኒ

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
20 ' ስፔን 1 - 1 ፈረንሳይ

ያማል              ሙኣኒ


@tikvahethsport     @kidusyoftahe
25 ' ስፔን 2 - 1 ፈረንሳይ

ያማል              ሙኣኒ
ኦልሞ


@tikvahethsport     @kidusyoftahe
32 ' ስፔን 2 - 1 ፈረንሳይ

ያማል              ሙኣኒ
ኦልሞ

- የ 16ዓመቱ ያሚን ያማል በአውሮፓ ዋንጫ ውድድር ታሪክ በእድሜ ትንሹ ግብ አስቆጣሪ በመሆን አዲስ ታሪክ ፅፏል።

- ፈረንሳይ በአውሮፓ ዋንጫ ውድድሩ የመጀመሪያ ግባቸውን በጨዋታ ማስቆጠር ችለዋል።

- በውድድሩ ፈረንሳይ ባለፉት ጨዋታዎች ያስቆጠረቻቸው ሶስት ግቦች ሁለቱ በራስ ላይ የተቆጠሩ አንዱ ደግሞ በፍፁም ቅጣት ምት የተቆጠረ ነው።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
2024/10/03 04:31:44
Back to Top
HTML Embed Code: