Telegram Web Link
54 ' ማንችስተር ዩናይትድ 0 - 2 ቶተንሀም

                             ጆንሰን
                             ኩሉሴቭስኪ

- የቶተንሀም ተጓዥ ደጋፊዎች አሰልጣኝ ኤሪክ ቴንሀግን “ ጠዋት ትሰናበታለህ " የሚል ዝማሬ እያሰሙ ይገኛሉ።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
64 ' ማንችስተር ዩናይትድ 0 - 2 ቶተንሀም

                             ጆንሰን
                             ኩሉሴቭስኪ

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
74 ' ማንችስተር ዩናይትድ 0 - 2 ቶተንሀም

                             ጆንሰን
                             ኩሉሴቭስኪ

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
77 ' ማንችስተር ዩናይትድ 0 - 3 ቶተንሀም

                             ጆንሰን
                             ኩሉሴቭስኪ
ሶላንኬ

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
85 ' ማንችስተር ዩናይትድ 0 - 3 ቶተንሀም

                             ጆንሰን
                             ኩሉሴቭስኪ
                             ሶላንኬ

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
90 ' ማንችስተር ዩናይትድ 0 - 3 ቶተንሀም

                             ጆንሰን
                             ኩሉሴቭስኪ
                             ሶላንኬ

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
ማንችስተር ዩናይትድ ሽንፈት አስተናግዷል !

ማንችስተር ዩናይትድ ከቶተንሀም ጋር ያደረጉትን የፕርሚየር ሊግ ስድስተኛ ሳምንት መርሐ ግብር 3ለ0 በሆነ ውጤት ተሸንፈዋል።

የቶተንሀምን የማሸነፊያ ግቦች ዶምኒክ ሶላንኬ ፣ ብሬናን ጆንሰን እና ኩሉሴቭስኪ ከመረብ ማሳረፍ ችለዋል።

በአሰልጣኝ ኤሪክ ቴንሀግ የሚመራው ማንችስተር ዩናይትድ በውድድር ዘመኑ ሶስተኛ የሊግ ሽንፈቱን አስተናግዷል።

ፖርቹጋላዊው አማካይ ብሩኖ ፈርናንዴዝ በማንችስተር ዩናይትድ ቆይታው የመጀመሪያ ቀይ ካርድ ተመልክቷል።

የሊግ ደረጃቸው ምን ይመስላል ?

8️⃣ኛ ቶተንሀም :- 10 ነጥብ
1️⃣2️⃣ኛ ማንችስተር ዩናይትድ :- 7 ነጥብ

ቀጣይ ጨዋታዎች ?

እሁድ አስቶን ቪላ ከ ማንችስተር ዩናይትድ

እሁድ ብራይተን ከ ቶተንሀም

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
በአሰልጣኝ ኤሪክ ቴን ሀግ ስር ክለቡ ወደ ኃላ እየተጓዘ ነው “

የቀድሞ የማንችስተር ዩናይትድ ተጫዋቾች በዛሬው ጨዋታ ቡድኑ ካስመዘገበው ውጤት በኃላ ሀሳበቸውን አካፍለዋል።

የቀድሞ ተጫዋች አሽሊ ያንግ “ ዩናይትዶች በሜዳ ላይ ያላቸውን አልሰጡም “ ሲል “ ምንም አይነት ፍላጎት አላሳዩም “ ብሏል።

አሽሊ ያንግ በተጨማሪም “ ቡድኑን በሜዳ ላይ የሚመራ ተጫዋች የለም ፣ ቶተንሀም በሜዳው የሚጫወት ይመስል ነበር “ በማለት ተናግሯል።

ጋሪ ኔቭል በበኩሉ “ የመጀመሪያ አጋማሽ የቡደ‍ኑ እንቅስቃሴ መጥፎ ነበር “ ሲል ተደምጧል።

የቀድሞ የመሐል ተከላካይ ሚኬል ሲልቬስተር የክለቡን ወቅታዊ ሁኔታ ሲተች “ ክለቡ በአሰልጣኝ ኤሪክ ቴን ሀግ ስር ወደ ኃላ እየተጓዘ ነው “ ሲል ሁኔታውን ገልፆል።

@tikvahethsport @kidusyoftahe
“ ድሉ የሚገባን ነው “

የቶተንሀሙ ተጫዋች ቫን ዴ ቫን ቡድናቸው በማንችስተር ዩናይትድ ላይ ያስመዘገበው ድል “ የሚገባን ነው “ ሲል ገልፆታል።

“ ድሉ የሚገባን ነው “ ያለው ቫን ዴ ቫን “ ጥሩ እግር ኳስ እንደምንጫወት አሳይተናል ፣ ዛሬ ማሸነፍ ይገባን ነበር “ በማለት ተናግሯል።

ቫን ዴ ቨን በምሽቱ መርሐ ግብር የጨዋታው ኮከብ በመባል መመረጥ ችሏል።

@tikvahethsport @kidusyoftahe
ይገምቱ ይሸለሙ

የሪያል ማድሪድ እና አትሌቲኮ ማድሪድን ጨዋታ ውጤት ገምተው በትክክል ላወቁ ሶስት ቤተሰቦቻችን የአንድ መቶ ብር ካርድ የምንሸልምዎ ይሆናል።

የውድድሩ ህጎች ምን ይመስላሉ ?

√ ተሳታፊዎች ግምቶቻቸውን ከዚህ ፖስት ስር ባለው የሀሳብ መስጫ ሳጥን #ብቻ ማስቀመጥ ይኖርባቸዋል።

√ ኤዲት የተደረጉ ምላሾች በፍፁም ተቀባይነት አይኖራቸውም።

√ ግምትዎን መላክ የሚቻለው እስከ 4:00 ሰዓት ብቻ ነው።

መልካም ዕድል !

@tikvahethsport    
በጎዶሎ ተጫዋች መጫወት ቀላል አይደለም “

በምሽቱ ጨዋታ በቀይ ካርድ የወጣው የማንችስተር ዩናይትድ አምበል ቡሩኖ ፈርናንዴዝ ቡድኑ “ የተቻለውን ሞክሯል “ ሲል ተደምጧል።

“ ቡድኑ ተስፋ አለመቁረጥ አሳይቷል ፣ በቡድን አጋሮቼ ኮርቻለሁ ፣ በጎዶሎ ተጫዋች መጫወት ቀላል አይደለም “ ብሩኖ ፈርናንዴዝ

የቡድኑ አምበል ጥፋት መሰራቱን አምኖ ነገር ግን “ የቀይ ካርዱ አያሰጥም “ በማለት የተመለከተው ቀይ ካርድ እንደማያሰጥ ገልፆል።

“ ማዲሰንን ጠይቄው ቀይ ካርድ እንደማሰጥ ነግሮኛል ቫር ለምን ሊመለከተው እንዳልፈለገ ሊገባኝ አልቻለም “ ሲል ብሩኖ ፈርናንዴዝ ተናግሯል።

@tikvahethsport @kidusyoftahe
ነገ አዲስ ቀን ነው “ ኤሪክ ቴን ሀግ

የቀያይ ሴጣኖቹ ዋና አሰልጣኝ ኤሪክ ቴን ሀግ ብሩኖ ፈርናንዴዝ የተመለከተው ቀይ ካርድ “ ጨዋታውን ቀይሮታል “ ብለዋል።

“ ነገ አዲስ ቀን ነው ፣ የተሻለ ነገር መስራት እና መማር ይኖርብናል “ አሰልጣኝ ኤሪክ ቴን ሀግ

አሰልጣኙ አያይዘውም “ ሙሉ ትኩረታችን በፖርቶ ጨዋታ ላይ ነው “ በማለት ስለቀጣይ መርሐ ግብሮች ማሰብ እንደሚገባ ተናግረዋል።

@tikvahethsport @kidusyoftahe
“ ቀይ ካርዱ ጨዋታውን አልቀየረውም “ ፖስቴኮግሉ

የቶተንሀሙ ዋና አሰልጣኝ አንሄ ፖስቴኮግሉ በምሽቱ ጨዋታ የብሩኖ ፈርናንዴዝ ቀይ ካርድ ጨዋታውን እንዳልቀየረው ገልጸዋል።

በጨዋታው የተመዘዘው ቀይ ካርድ “ ጨዋታውን ለውጦታል ብዬ አላስብም “ ያሉት አሰልጣኙ እንደውም ከዛ በፊት የጨዋታውን የበላይነት ወስደን ነበር ብለዋል።

“ ጥሩ እንቅስቃሴ አድርገናል ጨዋታውን በጥሩ ሁኔታ ጀምረን ግብም አስቆጥረናል ተጨማሪ ግብ ማስቆጠር እንችልም ነበር።“ አንሄ ፖስቴኮግሉ

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
ኤሪክ ቴንሀግ ስለ ወደፊት ቆይታቸው ምን አሉ ?

በውጤት ማጣት ውስጥ የሚገኙት ማንችስተር ዩናይትድ ዋና አሰልጣኝ ኤሪክ ቴንሀግ በቀጣይ የመሰናበት ስጋት እንደሌለባቸው ገልጸዋል።

“ ስንብት የሚያሳስበኝ ጉዳይ አይደለም “ ሲሉ አሰልጣኝ ኤሪክ ቴንሀግ በቀጣይ የመሰናበተት ስጋት እንደሌለባቸው ተናግረዋል።

“ ክረምት ላይ በዚህ ጉዳይ በደንብ ተነጋግረን ነው አብረን ለመቀጠል በጋራ የወሰንነው ፣ ግልጽ ግምገማም አድርገናል ትንሽ ጊዜ እንደሚወስድ እናውቃለን አንድ ላይ ነን “ ቴንሀግ

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
#TikvahGoal

እረፍት | አትሌቲኮ ማድሪድ 0-0 ሪያል ማድሪድ

ጨዋታውን እና አጫጭር ቪዲዮች በጎል ቻናላችን መከታተል ይችላሉ።

የጎል ቻናላችን 👉 https://www.tg-me.com/+rbdEU4UaEdQxYWFk

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
73 ' አትሌቲኮ ማድሪድ 0-1 ሪያል ማድሪድ

ሚሊታኦ

- የአትሌቲኮ ማድሪድ ደጋፊዎች ቁሳቁስ ወደ ሜዳ ውስጥ መወርወራቸውን ተከትሎ በአሁኑ ሰዓት ጨዋታው ተቋርጧል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
ናፖሊ የሴርያው መሪ ሆነዋል !

በጣሊያን ሴርያ ስድስተኛ ሳምንት መርሐ ግብር ናፖሊ ከሞንዛ ጋር ያደረጉትን ጨዋታ 2ለ0 በሆነ ውጤት ማሸነፍ ችለዋል።

የናፖሊን የማሸነፊያ ግቦች ፖሊታኖ እና ቅቫራትሼሊያ ከመረብ ማሳረፍ ችለዋል።

በሊጉ ደረጃ ሰንጠረዥ ስንተኛ ናቸው ?

1️⃣ኛ ናፖሊ :- 13 ነጥብ
1️⃣9️⃣ኛ ሞንዛ :- 3 ነጥብ

ቀጣይ ጨዋታቸው ምን ይመስላል ?

አርብ ናፖሊ ከ ኮሞ

እሁድ ሞንዛ ከ ሮማ

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
TIKVAH-SPORT
73 ' አትሌቲኮ ማድሪድ 0-1 ሪያል ማድሪድ ሚሊታኦ - የአትሌቲኮ ማድሪድ ደጋፊዎች ቁሳቁስ ወደ ሜዳ ውስጥ መወርወራቸውን ተከትሎ በአሁኑ ሰዓት ጨዋታው ተቋርጧል። @tikvahethsport     @kidusyoftahe
የማድሪድ ደርቢ በድጋሜ መካሄዱን ጀምሯል !

የአትሌቲኮ ማድሪድ ደጋፊዎች ቁሳቁስ ወደ ሜዳ መወርወራቸውን ተከትሎ ተቃርጦ የነበረው የማድሪድ ደርቢ ጨዋታ ከደቂቃዎች በኋላ በድጋሜ ጀምሯል።

ደጋፊዎቹ በድጋሜ ቁሳቁስ የሚወረውሩ ከሆነ ጨዋታው እንደሚራዘም ተገልጿል።

ሪያል ማድሪድ ጨዋታውን 1ለ0 በመምራት ላይ ይገኛል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
90 ' አትሌቲኮ ማድሪድ 1-1 ሪያል ማድሪድ

ኮሪያ                    ሚሊታኦ

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
ማድሪድ ደርቢ በአቻ ውጤት ተጠናቀቀ !

በስፔን ላሊጋ የስምንተኛ ሳምንት መርሐ ግብር ሪያል ማድሪድ ከአትሌቲኮ ማድሪድ ጋር ያደረጉትን ጨዋታ 1ለ1 በሆነ አቻ ውጤት አጠናቀዋል።

የሪያል ማድሪድን ግብ ኤደር ሚሊታኦ ከመረብ ማሳረፍ ሲችል አንሄል ኮሪያ በመጨረሻ ደቂቃ አትሌቲኮ ማድሪድን አቻ አድርጓል።

ብራዚላዊው የፊት መስመር ተጨዋች ቪንሰስ ጁኒየር በውድድር አመቱ አራት ለግብ የሆኑ ኳሶችን አመቻችቶ ማቀበል ችሏል።

በሊጉ ደረጃ ሰንጠረዥ ስንተኛ ናቸው ?

2️⃣ኛ. ሪያል ማድሪድ :- 18 ነጥብ
3️⃣ኛ. አትሌቲኮ ማድሪድ :- 16 ነጥብ

ቀጣይ ጨዋታቸው ምን ይመስላል ?

እሁድ ሪያል ሶሴዳድ ከ አትሌቲኮ ማድሪድ

ቅዳሜ ሪያል ማድሪድ ከ ቪያሪያል

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
2024/09/30 00:15:29
Back to Top
HTML Embed Code: