Telegram Web Link
እረፍት | ቱርክ 1-1 ጆርጅያ

ሙልዱር       ሚካውታድዜ

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
66 ' ቱርክ 2-1 ጆርጅያ

ሙልዱር       ሚካውታድዜ
አርዳ ጉለር

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
90+6' ቱርክ 3-1 ጆርጅያ

ሙልዱር       ሚካውታድዜ
አርዳ ጉለር
አክቱርኮግሉ

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
ቱርክ ውድድሯን በድል ጀምራለች !

በአውሮፓ ዋንጫ የምድብ የመጀመሪያ ጨዋታ የቱርክ ብሔራዊ ቡድን ከጆርጅያ ብሔራዊ ቡድን ጋር ያደረገውን ጨዋታ 3ለ1 በሆነ ውጤት ማሸነፍ ችሏል።

ለቱርክ ብሔራዊ ቡድን የማሸነፊያ ግቦችን አርዳ ጉለር ፣ ሙልዱር እና አክቱርኮግሉ ከመረብ ሲያሳርፉ ለጆርጅያ ሚካውታድዜ አስቆጥሯል።

ቱርካዊው የሪያል ማድሪድ የመሐል ሜዳ ተጨዋች አርዳ ጉለር በትልቅ ውድድር ላይ ለቱርክ ብሔራዊ ቡድን ግብ ያስቆጠረ በእድሜ ትንሹ ተጨዋች መሆን ችሏል።

በምድቡ ሁለተኛ ጨዋታ ቅዳሜ ጆርጂያ ከቼክ እንዲሁም ቱርክ ከፖርቹጋል ጋር ይገናኛሉ።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
የጨዋታ አሰላለፍ !

4:00 ፖርቹጋል ከ ቼክ ሪፐብሊክ

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
" ሮናልዶ ግብ አስቆጣሪያችን ነው " ሮቤርቶ ማርቲኔዝ

የፖርቹጋል ብሔራዊ ቡድን አሰልጣኝ ሮቤርቶ ማርቲኔዝ የብሔራዊ ቡድኑ አምበል ክርስቲያኖ ሮናልዶ በቡድኑ ውስጥ ያለው ትልቅ ስም ስላለው ብቻ አለመሆኑን ገልጸዋል።

ሮናልዶ ከእድሜው መግፋት ጋር በተያያዘ መጠራት አልነበረበትም ለሚሉ ቅሬታዎች ምላሽ የሰጡት አሰልጣኝ ሮቤርቶ ማርቲኔዝ " ሮናልዶ ቡድኑ ውስጥ ያለው ለጥቅም ነው ማንም ሰው ስም ስላለው አልተጠራም።

ሮናልዶ ለአል ናስር በተጠናቀቀው አመት በሀምሳ አንድ ጨዋታዎች ሀምሳ ግቦች አስቆጥሯል ፣ እሱ ግብ አስቆጣሪያችን ነው።"በማለት ከተጨዋቻቸው ጎን መሆናቸውን ገልጸዋል።

የፖርቹጋል ብሔራዊ ቡድን ተከላካይ ሩበን ዲያስ በበኩሉ ሮናልዶ በቡድኑ መካተቱ እንዳስደሰተው የገለፀ ሲሆን " ሮናልዶ መነሳሳትን እና ሁሉም ነገር እንደሚቻል ማሳያ ነው።

ሮናልዶ አምበላችን ነው አሁንም ማሸነፍ ይፈልጋል እኛም እስከመጨረሻው እንከተለዋለን።"በማለት ተናግሯል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
" የማድሪድ ድጋፍ የበለጠ አነሳስቶኛል " አርዳ ጉለር

ቱርክ ጆርጂያን ባሸነፈችበት ጨዋታ ወሳኝ ግብ ያስቆጠረው እና የጨዋታው ኮከብ በመባል የተመረጠው አርዳ ጉለር ሪያል የማድሪድ ድጋፍ እንደጠቀመው ተናግሯል።

" አሰልጣኝ ካርሎ አንቾሎቲ ከጨዋታው በፊት መልዕክት ልከው መልካም ምኞታቸውን ገልፀውልኛል " ያለው አርዳ ጉለር ከሪያል ማድሪድ የተደረገልኝ ድጋፍ ትልቅ መነሳሳት ፈጥሮልኛል በማለት ተናግሯል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
" ፖርቹጋል ምድቡን ብቻ ሳይሆን ውድድሩን ልታሸንፍ ትችላለች " ቶማስ ሱሴክ

የቼክ ሪፐብሊክ ብሔራዊ ቡድን አምበል ቶማስ ሱሴክ ፖርቹጋል የዘንድሮውን የአውሮፓ ዋንጫ ውድድር ማሸነፍ ትችላለች የሚል እምነት እንዳለው ተናግሯል።

" ፖርቹጋል ምድቡን ብቻ ሳይሆን ውድድሩን ማሸነፍ ትችላለች " የሚለው ቶማስ ሱሴክ ባለፉት አመታት ጥራት እንዳላቸው አሳይተዋል ሮናልዶ ኮከባቸው ነው ባለፉት ሀያ አመታት የፖርቹጋል ትልቁ ኮከብ እሱ ነው ሲል ተደምጧል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
እረፍት | ፖርቹጋል 0 - 0 ቼክ ሪፐብሊክ

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
61 ' ፖርቹጋል 0 - 1 ቼክ ሪፐብሊክ

ፕሮቮድ

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
69 ' ፖርቹጋል 1 - 1 ቼክ ሪፐብሊክ

ህራናክ ( በራስ ላይ )                    ፕሮቮድ

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
88 ' ፖርቹጋል 1 - 1 ቼክ ሪፐብሊክ

ህራናክ ( በራስ ላይ )                    ፕሮቮድ

- ፖርቹጋል በጆታ አማካኝነት ያስቆጠረችው ግብ ከጨዋታ ውጪ በሚል ተሽሯል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
90 ' ፖርቹጋል 2 - 1 ቼክ ሪፐብሊክ

ህራናክ ( በራስ ላይ )                    ፕሮቮድ
ኮንሴካኦ

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
ፖርቹጋል ውድድሯን በድል ጀምራለች !

የፖርቹጋል ብሔራዊ ቡድን ከቼክ ሪፐብሊክ ብሔራዊ ቡድን ጋር ያደረገውን የአውሮፓ ዋንጫ የምድብ የመጀመሪያ ጨዋታ 2ለ1 በሆነ ውጤት ማሸነፍ ችሏል።

ለፖርቹጋል ብሔራዊ ቡድን የማሸነፊያ ግቦችን ፍራንሴስኮ ኮንሴካኦ እና ፕሮቮድ በራሱ ግብ ላይ ሲያስቆጥሩ ለቼክ ህራናክ ከመረብ አሳርፏል።

ፖርቹጋላዊው ተከላካይ ፔፔ በአውሮፓ ዋንጫ ውድድር የተሳተፈ በእድሜ ትልቁ ተጨዋች በመሆን አዲስ ታሪክ መፃፍ ችሏል።

ክርስቲያኖ ሮናልዶ በስድስት የአውሮፓ ዋንጫ ውድድሮች በመሳተፍ በውድድሩ ታሪክ ቀዳሚው ተጨዋች መሆን ችሏል።

በቀጣይ ቅዳሜ በምድብ ሁለተኛ ጨዋታ ፖርቹጋል ከቱርክ እንዲሁም ቼክ ከጆርጅያ ይጫወታሉ።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
Forwarded from HEY Online Market
Play More and Spend less!

•PS4 Slim, 34,999 Birr
•PS4 PRO, 41,999 Birr
•Original Controller 6,499 Birr

Contact Us
0953964175 @heymobile

@heyonlinemarket
ሽመልስ በቀለ 1⃣8⃣ ገስት ሀውስ

በውቢቷ ሀዋሳ ቆይታዎ የት ለማረፍ አስበዋል ? ንፁህ እና በደንበኞቻችን ተወዳጅ በሆነው የእንግዳ ማረፊያችን መጥተው የእረፍት ጊዜውን ያሳልፉ።

እንግዶቻችንን ተቀበልን ለእይታ ሳቢ በሆነው የእንግዳ ማረፊያችን ማስተናገድ ከጀመርን አመታትን አስቆጥረናል።

አድራሻችን :- ሀዋሳ አርቴፍሻል ስታዲየም መንገድ ላይ ያገኙናል።

ለተጨማሪ መረጃ እና ለትዕዛዝዎ ይደውሉልን :- 0928684848

#ShemelesBekele18
" ሮናልዶ የሚያደርገው ነገር የማይታመን ነው " ኢቫን ሀሴክ

የቼክ ሪፐብሊኩ ዋና አሰልጣኝ ኢቫን ሀሴክ ፖርቹጋላዊው ተጨዋች ክርስቲያኖ ሮናልዶ በዚህ እድሜው ለሚያደርገው ነገር ትልቅ አድናቆት እንዳላቸው ገልጸዋል።

" ሮናልዶ በዚህ እድሜው በእያንዳንዱ ጨዋታ የሚያደርገው ነገር የማይታመን ነው " ያሉት አሰልጣኝ ኢቫን ሀሴክ " እሱ በድጋሜ ታላቅነቱን አስመስክሯል እንዴት በአጋጣሚዎች ውስጥ መሳተፍ እንዳለበት ያውቃል።"ብለዋል።

" ለክርስቲያኖ ሮናልዶ ትልቅ አድናቆት አለኝ እሱ በአለም እግርኳስ ታሪክ ከታዩ ምርጥ ተጨዋቾች አንዱ ነው የሚደንቅ ሰው ነው።" አሰልጣኝ ኢቫን ሀሴክ

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
#EURO2024

የቼክ ሪፐብሊክ ብሔራዊ ቡድን በአውሮፓ ዋንጫ ከሚወዳደሩ ብሔራዊ ቡድኖች መካከል በአማካይ በእድሜ ትንሹ ብሔራዊ ቡድን ነው።

እንዲሁም የአዘጋጇ ሀገር ጀርመን ብሔራዊ ቡድን በውድድሩ ከሚሳተፉ ብሔራዊ ቡድኖች በአማካይ በእድሜ ትልቁ ብሔራዊ ቡድን ሆነዋል።

በአማካይ በእድሜ ትንሽ ቡድኖች የትኞቹ ናቸው ?

- ቼክ ሪፐብሊክ :- 25.5 አማካይ እድሜ

- ቱርክ :- 25.8 አማካይ እድሜ

- እንግሊዝ :- 26.1 አማካይ እድሜ

- ኔዘርላንድ :- 26.3 አማካይ እድሜ

- ዩክሬን :- 26.3 አማካይ እድሜ

በአማካይ በእድሜ ትልቅ ቡድኖች የትኞቹ ናቸው ?

- ጀርመን :- 28.6 አማካይ እድሜ

- ስኮትላንድ :- 28.3 አማካይ እድሜ

- ፖላንድ :- 27.8 አማካይ እድሜ

- ዴንማርክ :- 27.7 አማካይ እድሜ

- ስዊዘርላንድ :- 27.7 አማካይ እድሜ

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
2024/09/30 00:27:47
Back to Top
HTML Embed Code: