Telegram Web Link
የፕርሚየር ሊግ መርሐግብሮች ይፋ ሆኑ !

የእንግሊዝ ፕርሚየር ሊግ የሚቀጥለው የ2024/25 የውድድር ዘመን የጨዋታ መርሐግብሮች ይፋ ተደርገዋል።

በዚህም መሰረት በውድድሩ የመጀመሪያ ሳምንት መርሐ ግብሮች :-

- ቼልሲ ከ ማንችስተር ሲቲ

- አርሰናል ከ ዎልቭስ

- ማንችስተር ዩናይትድ ከ ፉልሀም ( የሊጉ የመክፈቻ ጨዋታ )

- ኢፕስዊች ታውን ከ ሊቨርፑል

- ሌስተር ሲቲ ከ ቶተንሀም

- ዌስትሀም ዩናይትድ ከ አስቶን ቪላ

- ኤቨርተን ከ ብራይተን

የእንግሊዝ ፕርሚየር ሊግ የ2024/25 የውድድር አመት ነሐሴ 11/2016 ዓ.ም ጀምሮ ግንቦት 17/2017 ዓ.ም እንደተለመደው በተመሳሳይ ሰዓት በሚደረጉ ጨዋታዎች የሚጠናቀቅ ይሆናል።

* የመጀመሪያ ሳምንት ሙሉ መርሐግብር ከላይ በምስሉ ላይ ተያይዟል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
TIKVAH-SPORT
የፕርሚየር ሊግ መርሐግብሮች ይፋ ሆኑ ! የእንግሊዝ ፕርሚየር ሊግ የሚቀጥለው የ2024/25 የውድድር ዘመን የጨዋታ መርሐግብሮች ይፋ ተደርገዋል። በዚህም መሰረት በውድድሩ የመጀመሪያ ሳምንት መርሐ ግብሮች :- - ቼልሲ ከ ማንችስተር ሲቲ - አርሰናል ከ ዎልቭስ - ማንችስተር ዩናይትድ ከ ፉልሀም ( የሊጉ የመክፈቻ ጨዋታ ) - ኢፕስዊች ታውን ከ ሊቨርፑል - ሌስተር ሲቲ ከ ቶተንሀም…
#PremiereLeague

የእንግሊዝ ፕርሚየር ሊግ የ2024/25 የውድድር ዘመን መርሐግብሮች ይፋ ሲደረጉ በመጀመሪያ ሳምንት መርሐግብር ቼልሲን ከማንችስተር ሲቲ አገናኝቷል።

ተጠባቂው የማንችስተር ዩናይትድ እና ሊቨርፑል ጨዋታ በሊጉ ሶስተኛ ሳምንት መርሐግብር ኦልድትራፎርድ ስታዲየም ላይ ይደረጋል።

ተጠባቂው የሰሜን ለንደን ደርቢ በአርሰናል እና ቶተንሀም መካከል በአራተኛው ሳምንት መርሐግብር ሲደረግ መድፈኞቹ በአምስተኛ ሳምንት ማንችስተር ሲቲን ይገጥማሉ።

የመጀመርያው የማንችስተር ደርቢ ጨዋታ ታህሳስ ወር ውስጥ ኢትሀድ ስታዲየም ላይ ይደረጋል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
የጀርመን አዲስ ማልያ ከፍተኛ ፈላጊ አግኝቷል !

የጀርመን ብሔራዊ ቡድን ለ2024 አውሮፓ ዋንጫ ውድድር ያስተዋወቀው አዲስ የሜዳ ውጪ የሮዝ ቀለም ማልያ ከፍተኛ ፈላጊ ማግኘቱ ተገልጿል።

ማልያው ከወራት በፊት ለህዝብ ይፋ ሲደረግ የሀገሪቱን ሰንደቅ ዓላማ አላካተተም እንዲሁም ጀርመንን ለሚያክል ትልቅ ቡድን የማይመጥን ነው በሚል ከፍተኛ ተቃውሞ ቀርቦበት ነበር።

አሁን ላይ ማልያው ከተዋወቀበት ቀን እስከ አውሮፓ ዋንጫው መጀመሪያ ቀን ድረስ በብሔራዊ ቡድን የሜዳ ውጪ ማልያ ታሪክ ፈጣን ሽያጭ ማስመዝገብ መቻሉ ተገልጿል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
TIKVAH-SPORT
የኪሊያን ምባፔ ጉዳት መጠን ምን ይመስላል ? ፈረንሳይ ትላንት ምሽት ኦስትሪያን ገጥማ ባሸነፈችበት የአውሮፓ ዋንጫ የምድብ ጨዋታ ኪሊያን ምባፔ በነበረው ግጭት ምክንያት በአፍንጫው ላይ ጉዳት አጋጥሞታል። የሎስ ብላንኮዎቹ የፊት መስመር ተጨዋች ኪሊያን ምባፔ ከጉዳቱ በኋላ የ " X-rays " ምርመራ እንደተደረገለት እና በቀጣይ ህክምናውን እንደሚከታተል ተገልጿል። ኪሊያን ምባፔ በጉዳቱ ምክንያት…
ምባፔ ለኔዘርላንድ ጨዋታ ላይደርስ ይችላል !

ትላንት ምሽት በአፍንጫው ላይ ከባድ ጉዳት ያጋጠመው ፈረንሳዊው የፊት መስመር ተጨዋች ኪሊያን ምባፔ ለአርቡ የኔዘርላንድ ጨዋታ ላይደርስ እንደሚችል ተገልጿል።

ፈረንሳይ ከፖላንድ ጋር በምታደርገው የአውሮፓ ዋንጫ የምድብ የመጨረሻ ጨዋታ ኪሊያን ምባፔ የመድረስ እድል እንደሚኖረው ተዘግቧል።

ኪሊያን ምባፔ በጉዳቱ ምክንያት በቀሪ የአውሮፓ ዋንጫ ውድድር ጨዋታዎች ለመካፈል የፊት ጭምብል ( Masks ) እንደሚለብስ ተነግሯል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
🔥 የአውሮፓ ዋንጫ ጨዋታዎች በድምቀት ቀጥለዋል!

የዛሬ ጨዋታዎች መርሃ ግብር፡

⚽️ Turkey vs Georgia ከምሽቱ 1፡00 ሰዓት | 7፡00 PM በSS Football 225 ጎጆ ፓኬጅ በSS Euro2024 222 በሜዳ  ፓኬጅ

⚽️ Portugal vs Czech Republic ከምሽቱ 4፡00 ሰዓት | 10፡00 PM በSS Football 225 ጎጆ ፓኬጅ በSS Euro2024 222 በሜዳ  ፓኬጅ

🤔ዋንጫው የማን ነው? የእርሶን አስተያየት ያጋሩን                        

በጀርመን የሚደረጉትን ደማቅ ጨዋታዎች በቀጥታ በዲኤስቲቪ ሱፐርስፖርት ቻናሎች በወር ከ350 ብር ከጎጆ ፓኬጅ ጀምሮ ይከታተሉ!

የዲኤስቲቪ አገልግሎቶችን ለማግኘት ከታች ያለውን የMyDStv Telegram bot ሊንክ ይጫኑ!
👇
https://mydstv.onelink.me/vGln/eth2

#Euro2024onDStv #ሁሉምያለውእኛጋርነው #DStvEthiopia
Forwarded from WANAW SPORT
📢 በጥራት የተዘጋጁ #ቢብሶች ለእናንተ!

🔥 አሁኑኑ #ይዘዙን!

📌 ለበለጠ መረጃና ትዕዛዝ 📲 09011382830910851535 እና 0913586742 ላይ ይደውሉ።

👉🏾 እንዲሁም በቴሌግራም @Wanawsales ላይ የሽያጭ ሰራተኞቻችንን በቀጥታ በማናገር ይዘዙን።

🏅 ዋናው ወደፊት...

@wanawsportwear
የስፔን ላሊጋ መርሐ ግብር ይፋ ሆነ !

የ 2024/25 የውድድር ዘመን የስፔን ላሊጋ ውድድር መርሐ ግብር ይፋ ተደርጓል።

በመጀመሪያ ሳምንት መርሐ ግብር ሪያል ማድሪድ ከማዮርካ እንዲሁም ባርሴሎና ከቫሌንሽያ ጋር የሚገናኙ ይሆናል።

ተጠባቂው ኤል ክላሲኮ መቼ ይደረጋል ?

የቀጣይ ዓመት የሊጉ ተጠባቂው የኤል ክላሲኮ መርሐ ግብር የመጀመሪያ ጨዋታ በሪያል ማድሪድ ስታዲየም ሳንቲያጎ በርናቦ ጥቅምት 1/2017 ዓ.ም ይደረጋል።

በተጨማሪም ተጠባቂው የማድሪድ ደርቢ የመጀመሪያው ጨዋታ በአትሌቲኮ ማድሪድ ሜዳ መስከረም ወር ውስጥ ይደረጋል።

የስፔን ላሊጋ አዲሱ የውድድር ዘመን ከወራት በኋላ ነሐሴ 12/2016 ዓ.ም መደረጉን የሚጀምር ይሆናል።

*የመጀመሪያ ሳምንት ሙሉ መርሐ ግብር ከላይ በምስሉ ላይ ተያይዟል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
አርጀንቲናዊው ዳኛ የአውሮፓ ዋንጫ ጨዋታ ይመራል !

ዛሬ ምሽት በቱርክ እና ጆርጂያ መካከል የሚደረገውን የአውሮፓ ዋንጫ የምድብ የመጀመሪያ ጨዋታ አርጀንቲናዊው ዳኛ ፋኩንዶ ቴሎ በመሐል ዳኝነት የሚመራው ይሆናል።

አርጀንቲናዊው ዳኛ ፋኩንዶ ቴሎ ከአውሮፓ እግርኳስ ማህበር አባል ሀገራት ውጪ ሆኖ የአውሮፓ ዋንጫ ጨዋታን የመራ የመጀመሪያው አርጀንቲናዊ ዳኛ በመሆን አዲስ ታሪክ ይፅፋል።

ዋና ዳኛው በአውሮፓ ዋንጫው የዳኞች ቡድንን የተቀላቀለው ዩኤፋ እና የደቡብ አሜሪካ አቻው ያደረጉትን ዳኞች የመጋራት እና በጋራ የመስራት ስምምነት አካል መሆኑ ተገልጿል።

በጨዋታ መሐል የሚኖሩ አላስፈላጊ ባህሪዎችን በዝምታ እንደማያልፍ የተገለጸው የ 42ዓመቱ ዳኛ ከሁለት አመት በፊት በአንድ ጨዋታ ለአስር ተጨዋቾች ቀይ ካርዶችን መዞም ያውቃል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
TIKVAH-SPORT
ምባፔ ለኔዘርላንድ ጨዋታ ላይደርስ ይችላል ! ትላንት ምሽት በአፍንጫው ላይ ከባድ ጉዳት ያጋጠመው ፈረንሳዊው የፊት መስመር ተጨዋች ኪሊያን ምባፔ ለአርቡ የኔዘርላንድ ጨዋታ ላይደርስ እንደሚችል ተገልጿል። ፈረንሳይ ከፖላንድ ጋር በምታደርገው የአውሮፓ ዋንጫ የምድብ የመጨረሻ ጨዋታ ኪሊያን ምባፔ የመድረስ እድል እንደሚኖረው ተዘግቧል። ኪሊያን ምባፔ በጉዳቱ ምክንያት በቀሪ የአውሮፓ ዋንጫ ውድድር…
ኬቪን ዳንሶ ኪሊያን ምባፔን ይቅርታ ጠይቋል !

የኦስትሪያ ብሔራዊ ቡድን ተከላካይ ኬቪን ዳንሶ ትላንት ምሽት ከኪሊያን ምባፔ ጋር በነበራቸው ግጭት ምክንያት አፍንጫው ላይ ጉዳት በማስተናገዱ ይቅርታ ጠይቋል።

የሌንሱ ተጨዋች ኬቪን ዳንሶ በይቅርታ መልዕክቱም " የፈረንሳይ ህዝብ እና ኪሊያን ምባፔን ይቅርታ እጠይቃለሁ ፣ እሱን ለመጉዳት ፈልጌ አልነበረም በትሎ እንዲሻለው እና ወደ ሜዳ እንዲመለስ እመኛለሁ።"ሲል ተናግሯል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
" ቴንሀግ በመቆየቱ ደስተኛ ነኝ " ማይኖ

እንግሊዛዊው የመሐል ሜዳ ተጨዋች ኮቢ ማይኖ የማንችስተር ዩናይትድ አሰልጣኝ ኤሪክ ቴንሀግ በመቆየታቸው መደሰቱን ገልጿል።

" ኤሪክ ቴንሀግ ሁለት ዋንጫዎች አሸንፈዋል በቀጣይ ብዙ እንደሚሆን ተስፋ አለኝ " ሲል የተደመጠው ኮቢ ማይኖ ቀጣይ አሰልጣኛችንን ማወቃችን ተረጋግተን እንድንጫወት ያደርገናል እሱን አመስግኜ አልጨረስኩም ብሏል።

" የጋና የዘር ሀረግ ስላለኝ ሁልጊዜም እኮራለሁ ነገርግን ለእንግሊዝ ብሔራዊ ቡድን መጫወት የሁልጊዜ ህልሜ ነበር።" ማይኖ

ኮቢ ማይኖ ቀጥሎም እንግሊዛዊው የመሐል ሜዳ ተጨዋች ጁድ ቤሊንግሀም የባሎን ዶር ሽልማት እንደሚገባው ተናግሯል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
#EURO2024

የቱርክ ብሔራዊ ቡድን ከጆርጅያ ብሔራዊ ቡድን ጋር የአውሮፓ ዋንጫ ጨዋታቸውን የሚያደርጉበት ዶርትመንድ የአየር ሁኔታው ዝናባማ መሆኑ ተገልጿል።

አሁን ላይ ጨዋታው የሚደረግበት የዶርትመንድ ስታዲየም ጣራ በማፍሰስ ላይ እንደሚገኝ እና ስታዲየሙ ለደጋፊዎች መቀመጫ አስቸጋሪ እንደሆነ ተነግሯል።

የሁለቱ ብሔራዊ ቡድኖች ጨዋታ ምሽት 1:00 ሰዓት ይጀመራል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
የጨዋታ አሰላለፍ !

1:00 ቱርክ ከ ጆርጅያ

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
#EURO2024

የቱርክ ብሔራዊ ቡድን ደጋፊዎች እና የጆርጅያ ብሔራዊ ቡድን ደጋፊዎች ከጨዋታው አስቀድሞ በስታዲየሙ ውስጥ ግጭት ውስጥ መግባታቸው ተገልጿል።

የሁለቱ ብሔራዊ ቡድን ደጋፊዎች በስታዲየሙ ውስጥ ቁሳቁሶችን ሲወራወሩ መስተዋላቸው ተነግሯል።

አሁን ላይ በስታዲየሙ የተፈጠረውን ግጭት በአካባቢው የሚገኙ የፀጥታ አካላት ገብተው ማረጋጋታቸው ተዘግቧል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
#EURO2024

የጆርጅያ ብሔራዊ ቡድን በታሪኩ የመጀመሪያው የሆነውን በአውሮፓ ዋንጫ ውድድር ዛሬ ከቱርክ አቻው ጋር በሚያደርገው ጨዋታ ይጀምራል።

ጆርጅያ ባለፉት አስራ ሁለት ወራት በታሪክ ትልቁ የሆነውን የ 8ለ0 ድል እንዲሁም በታሪክ ትልቁ የሆነውን የ 7ለ1 ሽንፈት አስመዝግበው በአውሮፓ ዋንጫው ቀርበዋል።

በቀድሞ ፈረንሳዊ ተጨዋች ዊሊ ሳኞል የሚመራው የጆርጅያ ብሔራዊ ቡድን በ3-5-2 አሰላለፍ በመስመር በኩል ባሏቸው ተመላላሾች ጫና ፈጥሮ መጫወትን ይመርጣሉ።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
26 ' ቱርክ 1-0 ጆርጅያ

ሙልዱር

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
33 ' ቱርክ 1-1 ጆርጅያ

ሙልዱር ሚካውታድዜ

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
2024/09/30 02:14:57
Back to Top
HTML Embed Code: