Telegram Web Link
የጨዋታ አሰላለፍ !

1:00 ቤልጅየም ከ ስሎቫኪያ

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
Forwarded from WANAW SPORT
🎁 #ይገምቱ#ይሸለሙ እንደቀጠለ ነው!

🏆  በምሽቱ የ2024 አውሮፓ ዋንጫ 4ኛ ቀን ጨዋታ ማን ያሸንፍ ይሆን?

🇦🇹 ኦስትሪያ ወይስ ፈረንሳይ 🇫🇷

💬 ግምትዎን #በፌስቡክ ገፃችን (https://www.facebook.com/wanawsportwear) ኮሜንት ላይ ብቻ ያስቀምጡልን!

⚠️ የውድድሩ ህጎች፦
👉🏾 የጨዋታውን አሸናፊ ሀገር እስከ የግብ መጠኑ #በትክክል ቀድመው የሚገምቱ #2 ተከታታዮቻችን የዋናውን የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ማልያዎች ይሸለማሉ።
👉🏾 የዋናውን ማህበራዊ ገፆች መከተል፣ መወዳጀትና ማጋራት አይዘንጉ።
👉🏾 የተስተካከሉና ተደጋጋሚ መልሶች በፍፁም ተቀባይነት የላቸውም።

Instagram | Facebook | TikTok

🏅 ዋናው ወደፊት...

@wanawsportwear
TIKVAH-SPORT
ፕርሚየር ሊግ አዲስ ቴክኖሎጂ ሊሞክር ነው ! የእንግሊዝ ፕርሚየር ሊግ ክለቦች ከሚቀጥለው የውድድር ዘመን ጀምሮ አዲስ የጨዋታ ውጪ ቴክኖሎጂ ( SAOT ) ለመሞከር በሙሉ ድምፅ መስማማታቸው ተገልጿል። በሊጉ ለመጀመሪያ ጊዜ ተግባራዊ የሚሆነው የጨዋታ ውጪ ቴክኖሎጂ ዩኤፋ ለአውሮፓ ሻምፒየንስ ሊግ ጨዋታዎች ላይ የሚጠቀመውን ካሜራ እና ሶፍትዌር እንደሚጠቀም ተነግሯል። አዲሱ ቴክኖሎጂ የጨዋታ ውጪ…
በፕርሚየር ሊግ በቀጣይ ምን አዲስ ነገር እንመለከታለን ?

- የእንግሊዝ ፕርሚየር ሊግ ከሚቀጥለው የውድድር አመት ጀምሮ የጨዋታው አሰላለፍ ጨዋታው ከመጀመሩ ሰባ አምስት ደቂቃዎች አቀድሞ ይፋ የሚደረግ ይሆናል።

- ፕርሚየር ሊግ ከሚቀጥለው የውድድር ዘመን የመጀመሪያ የብሔራዊ ቡድኖች እረፍት በኋላ አዲሱን የጨዋታ ውጪ ቴክኖሎጂ ( SAOT ) ተግባራዊ ያደርጋል።

- አዲሱ ቴክኖሎጂ የጨዋታ ውጪ እንቅስቃሴን መስመር በፍጥነት በማስመር እንደሚያሳውቅ እና በአንድ ውሳኔ እስከ ሰላሳ ሰከንድ መቆጠብ እንደሚችል መዘገቡ አይዘነጋም።

- በሚቀጥለው የውድድር አመት የቫር ውሳኔ ስታዲየም በሚገኝ ስክሪን ለተመልካች ይቀርባል እንዲሁም ዳኞች ውሳኔውን ለደጋፊዎቹ ያብራራሉ።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
8 '

ቤልጅየም 0-1 ስሎቫኪያ

ሽራንዝ

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
#እረፍት

ቤልጅየም 0-1 ስሎቫኪያ

        ሽራንዝ

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
57 '

ቤልጅየም 0-1 ስሎቫኪያ

        ሽራንዝ

- ሮሜሉ ሉካኩ ለቤልጂየም ያስቆጠረው የአቻነት ግብ ከጨዋታ ውጪ በሚል በቫር ተሽሯል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
88 '

ቤልጅየም 0-1 ስሎቫኪያ

        ሽራንዝ

- ሮሜሉ ሉካኩ ለቤልጂየም ያስቆጠረው የአቻነት ግብ በእጅ ተነክቷል በሚል በቫር ተሽሯል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
ቤልጂየም ሽንፈት አስተናግዳለች !

በአውሮፓ ዋንጫ የምድብ የመጀመሪያ ጨዋታ የቤልጅየም ብሔራዊ ቡድን ከስሎቫኪያ ብሔራዊ ቡድን ጋር ያደረገውን ጨዋታ 1ለ0 በሆነ ውጤት ተሸንፈዋል።

ለስሎቫኪያ ብሔራዊ ቡድን የማሸነፊያ ግቧን ኢቫን ሽራንዝ ከመረብ ማሳረፍ ችሏል።

ስሎቫኪያ በታሪካቸው ለሶስተኛ ጊዜ የአውሮፓ ዋንጫ ውድድር ጨዋታ ድላቸውን ማሳካት ችለዋል።

ሁለቱ ብሔራዊ ቡድኖች ያደረጉት በታሪክ የመጀመሪያው የነጥብ ጨዋታ በስሎቫኪያ አሸናፊነት ተጠናቋል።

በምድቡ ሁለተኛ ጨዋታ የፊታችን ቅዳሜ ቤልጂየም ከሮማንያ እንዲሁም ዩክሬን ከስሎቫክያ ጋር ይገናኛሉ።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
የጨዋታ አሰላለፍ !

4:00 ኦስትሪያ ከ ፈረንሳይ

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
#EURO2024

- የኦስትሪያ ብሔራዊ ቡድን ያለ ወሳኙ ተጨዋቻቸው ዴቪድ አላባ እንዲሁም ሌላኛውን የቡድኑ ቁልፍ ተጨዋች ዣቬር ሽላገር በጉዳት አጥተው በአውሮፓ ዋንጫው ይሳተፋሉ።

- ኦስትሪያ በተጨማሪም ቁጥር አንድ ግብ ጠባቂዋን አሌክሳንደር ሽላገር እንዲሁ በጉዳት አጥታ በአውሮፓ ዋንጫው ለመቅረብ ተገዳለች።

- ምሽት ከፈረንሳይ ጋር የምትፋለመው ኦስትሪያ ካለፉት አስራ ሁለት ጨዋታዎች ሰባት ግቦችን ለቡድኑ ያስቆጠረውን የፍሬቡርግ አጥቂ ሚሼል ግሪጎሪትሽን እንደ ወሳኝ ተጨዋቿ ትመለከታለች።

- የፈረንሳይ ብሔራዊ ቡድን የምንግዜም ከፍተኛ ግብ አስቆጣሪው ኦሊቬ ጅሩ በብሔራዊ ቡድኑ የመጨረሻ ውድድሩን የሚያደርግ ሲሆን በምሽቱ ጨዋታ በተጠባባቂነት ይጀመራል።

- የፈረንሳይ ብሔራዊ ቡድን አሰልጣኝ ዲዲዬ ዴሻምፕ ከዚህ በፊት በተጠባባቂነት የሚያስጀምሩትን የአርሰናል ተከላካይ ዊሊያም ሳሊባ በቋሚ አሰላለፍ አካተዋል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
38 ' ኦስትሪያ 0 - 1 ፈረንሳይ

ዎበር ( በራስ ላይ )

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
እረፍት | ኦስትሪያ 0 - 1 ፈረንሳይ

                   ዎበር ( በራስ ላይ )

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
ፈረንሳይ ውድድሯን በድል ጀምራለች !

በአውሮፓ ዋንጫ የምድብ የመጀመሪያ ጨዋታ የፈረንሳይ ብሔራዊ ቡድን ከኦስትሪያ ብሔራዊ ቡድን ጋር ያደረገውን ጨዋታ 1ለ0 በሆነ ውጤት ማሸነፍ ችሏል።

ለፈረንሳይ ብሔራዊ ቡድን የማሸነፊያ ግቧን ማክሲሚላን ዎበር በራሱ ግብ ላይ ከመረብ ማሳረፍ ችሏል።

በጨዋታው የአል ኢትሀዱ የመሐል ሜዳ ተጨዋች ንጎሎ ካንቴ የጨዋታው ኮከብ ተጨዋች ተብሎ መመረጥ ችሏል።

በምድቡ ሁለተኛ ጨዋታ የፊታችን አርብ ፈረንሳይ ከኔዘርላንድ እንዲሁም ኦስትሪያ ከፖላንድ ጋር ይገናኛሉ።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
መልካም ዕድል!
ከፍ የተደረጉ ኦዶችን አይተዋል ? እንግዲያውስ ተወራረዱባቸው!
Turkey - Georgia
Portugal - Czech Republic
ለተሻለ ውርርድ ቤቲካን ይጠቀሙ! አሁኑኑ Betika.et ላይ /በቴሌግራም ቦታችን - @BetikaETBot ይወራረዱ!
Play More and Spend less!

•PS4 Slim, 34,999 Birr
•PS4 PRO, 41,999 Birr
•Original Controller 6,499 Birr

Contact Us
0953964175 @heymobile

@heyonlinemarket
የኪሊያን ምባፔ ጉዳት መጠን ምን ይመስላል ?

ፈረንሳይ ትላንት ምሽት ኦስትሪያን ገጥማ ባሸነፈችበት የአውሮፓ ዋንጫ የምድብ ጨዋታ ኪሊያን ምባፔ በነበረው ግጭት ምክንያት በአፍንጫው ላይ ጉዳት አጋጥሞታል።

የሎስ ብላንኮዎቹ የፊት መስመር ተጨዋች ኪሊያን ምባፔ ከጉዳቱ በኋላ የ " X-rays " ምርመራ እንደተደረገለት እና በቀጣይ ህክምናውን እንደሚከታተል ተገልጿል።

ኪሊያን ምባፔ በጉዳቱ ምክንያት የቀዶ ጥገና ህክምና #እንደማይደረግለት ሲገለፅ ከህክምናው በኋላ ወደ ውድድር መመለስ እንዲችል የሚረዳው ጭምብል ( Masks ) እንደሚለብስ ተነግሯል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
" ፈረንሳይ ያስመዘገበችው ድል ይገባታል " ራኚክ

የኦስትርያ ብሔራዊ ቡድን ዋና አሰልጣኝ ራልፍ ራኚክ በምሽቱ የአውሮፓ ዋንጫ ጨዋታ የፈረንሳይ ብሔራዊ ቡድን ድሉ እንደሚገባው ገልጸዋል።

" ጥሩ የግብ እድሎችን ፈጥረናል ፈረንሳይም እንደዛው ግብ ጠባቂያችን ጥሩ ስራ ሰርቷል በቡድኑ ላይ አስተያየት የለኝም ተጋጣሚያችን ማን እንደሆነ መርሳት የለብንም " ሲሉ ራልፍ ራንግኒክ ተናግረዋል።

" ጨዋታውን ተሸንፈናል እውነት ለመናገር ፈረንሳይ ከእኛ የተሻለ የግብ እድል ፈጥራለች የሚገባቸው ድል ነው ፣ ነገርግን እስከመጨረሻው ተፋልመናል አሁን ስለቀጣዩ ጨዋታ ማሰብ አለብን።" ራልፍ ራኚክ

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
" ሮናልዶን እንዴት ማቆም እንደሚቻል አላውቅም "

የቼክ ሪፐብሊክ ተከላካይ ቶማስ ቪልቼክ ፖርቹጋላዊውን ተጨዋች ክርስቲያኖ ሮናልዶ እንዴት ማቆም እንዳቀደ ሲጠየቅ " ይህንን ሚስጥር ባውቅ እሸጠው ነበር " ሲል ምላሽ ሰጥቷል።

" ሮናልዶን እንዴት ማቆም እንደሚችል ባውቅ በውድ ዋጋ እስካሁን እሸጠው ነበር " ሲል የተደመጠው ተጨዋቹ " እንደሱ አይነት ተጨዋቾች ውሳኔያቸውን በሰከንድ ውስጥ ይቀይራሉ መጠንቀቅ እና ትንሽ እድለኛ መሆን አለብን " ብሏል።

የፖርቹጋል ብሔራዊ ቡድን ዛሬ ምሽት 4:00 ሰዓት ከቼክ ሪፐብሊክ ብሔራዊ ቡድን ጋር የአውሮፓ ዋንጫ የምድብ የመጀመሪያ ጨዋታውን ያደርጋል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
2024/09/30 04:25:16
Back to Top
HTML Embed Code: