Telegram Web Link
#EURO2024

አሰልጣኝ ሮናልድ ኮማን ከደቂቃዎች በኋላ በሚጀመረው ጨዋታ በቀኝ መስመር ላይ የማጥቃት ባህሪ ካለው የባየር ሌቨርኩሰኑ ፍሪምፖንግ ይልቅ የመከላከል ባህሪ ያለውን ዴንዜል ዱምፍሪሴን ምርጫቸው አድርገዋል።

ኔዘርላንድ በጨዋታው በፊት መስመሩ ዌግሆርስት ፣ ማለን እና ጆሽዋ ዝርኪዜ እንዲሁም በአማካይ ስፍራ ዊናልደም እና ግራቨንበርች የመሳሰሉ ተጨዋቾችን በተጠባባቂነት አሳልፋለች።

በጉዳት ምክንያት ከጨዋታው ውጪ በሆነው ሮበርት ሌዋንዶውስኪ ምትክ አዳም ቡክሳ የፖላንድን የፊት መስመር ይመራል።

የ 27ዓመቱ ተጨዋች አዳም ቡክሳ በቱርኩ ክለብ አንታላይስፑር ያሳለፈው ጥሩ የውድድር እንዲሁም በብሔራዊ ቡድኑ ያለው ጥሩ ሪከርድ የሌዋንዶውስኪ ትክክለኛ ምትክ ሆኖ አቅርቦታል።

ሮበርት ሌዋንዶውስኪ ከጨዋታው ውጪ መሆኑን ተከትሎ ፒዮትር ዜሊንስክ ፖላንድን በአምበልነት እየመራ ወደ ሜዳ ይገባል።

" ሌዋንዶውስኪ ሊያግዘን ባለመግባቱ በጣም ያሳዝናል እሱ ታላቅ ተጨዋች ቢሆንም እኔም ሆንኩ ጓደኞቼ ጨዋታውን ለማሸነፍ ያለንን እንሰጣለን።"ሲል የናፖሊው ተጨዋች ፒዮትር ዜሊንስክ ተናግሯል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
" ሁሉም እንድንሸነፍ ፈርዶብናል "

የፖላንድ ብሔራዊ ቡድን አሰልጣኝ ሚቻል ፕሮቤርዝ አሁን ላይ ሁሉም ሰው ፖላንድ በኔዘርላንድ ትሸነፋለች ብሎ እያወራ እንደሚገኝ ገልጸዋል።

" ሁሉም ሰው እንድንሸነፍ ፈርዶብናል " ያሉት አሰልጣኙ ሰዎች እንደሚያስቡት ከሆነ እኛ ምንም የማሸነፍ እድል የለንም ነገርግን እኔ ዋና ነገር ቡድን መገንባት ነው ብዬ አስባለሁ እርስበርስ የሚሰራ ቡድን።"ሲሉ ተደምጠዋል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
15 ' ፖላንድ 1 - 0 ኔዘርላንድ

ቡክሳ

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
29 ' ፖላንድ 1 - 1 ኔዘርላንድ

ቡክሳ ጋክፖ

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
እረፍት | ፖላንድ 1 - 1 ኔዘርላንድ

    ቡክሳ      ጋክፖ

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
ወላይታ ድቻ ድል አድርጓል !

በኢትዮጵያ ፕርሚየር ሊግ የሀያ ሰባተኛ ሳምንት መርሐ ግብር ወላይታ ድቻ ከሀድያ ሆሳዕና ጋር ያደረጉትን ጨዋታ 2ለ1 በሆነ ውጤት ማሸነፍ ችለዋል።

የወላይታ ድቻን የማሸነፊያ ግቦች አብነት ደምሴ እና ብሩክ ማርቆስ በራሱ ግብ ላይ ከመረብ ሲያሳርፉ ለሀድያ ሆሳዕና ተመስገን ብርሀኑ አስቆጥሯል።

ወላይታ ድቻ ካለፉት አስራ አራት የሊግ ጨዋታዎች ሁለተኛ ድላቸውን አሳክተዋል።

የሊጉ ደረጃ ሰንጠረዥ ምን ይመስላል ? 

1️⃣0️⃣ ሀድያ ሆሳዕና :- 35 ነጥብ

1️⃣3️⃣ ወላይታ ድቻ  :- 32 ነጥብ

ቀጣይ ጨዋታ ምን ይመስላል ?

- ድሬዳዋ ከተማ ከ ሀድያ ሆሳዕና

- ሀምበሪቾ ዱራሜ ከ ወላይታ ድቻ

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
83 " ፖላንድ 1 - 2 ኔዘርላንድ

    ቡክሳ      ጋክፖ
ዌግሆርስት

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
ኔዘርላንድ ውድድሯን በድል ጀምራለች !

በአውሮፓ ዋንጫ የምድብ የመጀመሪያ ጨዋታ የኔዘርላንድ ብሔራዊ ቡድን ከፖላንድ ብሔራዊ ቡድን ጋር ያደረገውን ጨዋታ 2ለ1 በሆነ ውጤት ማሸነፍ ችሏል።

ለኔዘርላንድ ብሔራዊ ቡድን የማሸነፊያ ግቦችን ኮዲ ጋክፖ እና ዎት ዌግሆርስት ከመረብ ማሳረፍ ችሏል።

ለፖላንድ ብሔራዊ ቡድን የመሪነት ግብ አዳም ቡክሳ ከመረብ አሳርፏል።

የሊቨርፑሉ የፊት መስመር ተጨዋች ኮዲ ጋክፖ ለኔዘርላንድ ብሔራዊ ቡድን አስረኛ ግቡን ከመረብ ማሳረፍ ችሏል።

ዎት ዌግሆርስት ለኔዘርላንድ ብሔራዊ ቡድን ተቀይሮ በገባባቸው አስራ አንድ ጨዋታዎች ሰባት ግቦች አስቆጥሯል።

በምድቡ ሁለተኛ ጨዋታ ቀጣይ ሳምንት አርብ ኔዘርላንድ ከፈረንሳይ እንዲሁም ፖላንድ ከኦስትሪያ ጋር ይገናኛሉ።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
የጨዋታ አሰላለፍ !

1:00 ስሎቬኒያ ከ ዴንማርክ

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
TIKVAH-SPORT
በእንግሊዝ ጨዋታ አነስተኛ አልኮል ያለው መጠጥ ይቀርባል ! የእንግሊዝ ብሔራዊ ቡድን በአውሮፓ ዋንጫው መጀመሪያ እሁድ ከሰርቢያ ጋር በሚያደርገው ጨዋታ በስታዲየሙ አነስተኛ የአልኮል መጠን ያለው መጠጥ እንደሚቀርብላቸው ተገልጿል። በውድድሩ ከሚደረጉት ጨዋታዎች ሁሉ አነስተኛ የአልኮል መጠን ያለው መጠጥ የሚቀርብበት ብቸኛው ጨዋታ እንደሚሆንም ተነግሯል። ይህ የሆነው 40,000 ገደማ የእንግሊዝ ብሔራዊ…
#EURO2024

የእንግሊዝ ብሔራዊ ቡድን ዛሬ ምሽት ከሰርቢያ ብሔራዊ ቡድን ጋር ከሚያደርጉት ጨዋታ አስቀድሞ በደጋፊዎቹ መካከል ግጭት መፈጠሩ ተገልጿል።

ግጭቱ የተፈጠረው በርካታ የሰርቢያ ብሔራዊ ቡድን ደጋፊዎች ሲጠቀሙበት በነበረው ባር ውስጥ መሆኑ ሲገለፅ በገጭቱ ወቅት ወንበሮች እና ጠረጴዛዎችን ሲወራወሩ እንደነበር ተዘግቧል።

በግጭቱ የተወሰኑ ደጋፊዎች ጉዳት እንደደረሰባቸው በማህበራዊ ሚዲያዎች እየተዘዋወሩ የሚገኙ ተንቀሳቃሽ ምስሎች ያስረዳሉ።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
" ያስመዘገብነው ድል በደንብ ይገባናል " ኮማን

የኔዘርላንድ ብሔራዊ ቡድን አሰልጣኝ ሮናልድ ኮማን ቡድናቸው ከደቂቃዎች በፊት ያስመዘገበው ድል እንደሚገባው ከጨዋታው በኋላ በሰጡት አስተያየት ተናግረዋል።

"በጥሩ ሁኔታ ተጫውተናል ብዙ የግብ እድሎችን መፍጠርም ችለናል ፣ አራት ማግባት እንችልም ነበር ድሉ በደንብ ይገባናል።"ሲሉ አሰልጣኝ ሮናልድ ኮማን ተናግረዋል።

የቡድኑን የማሸነፊያ ግብ ያስቆጠረው ዎት ዌግሆርስት በበኩሉ " የተሰማኝን ደስታ ለመግለጽ እቸገራለሁ ፣ ለቡድኑ አቻ ሆነን ተቀይሬ ከገባሁ እንደማስቆጠር ተናግሬ ነበር።"ሲል ተደምጧል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
17 ' ስሎቬኒያ 0 - 1 ዴንማርክ

ኤሪክሰን

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
እረፍት | ስሎቬኒያ 0 - 1 ዴንማርክ

                    ኤሪክሰን

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
ኢትዮጵያ መድን በአሸናፊነቱ ቀጥሏል !

በኢትዮጵያ ፕርሚየር ሊግ የሀያ ሰባተኛ ሳምንት መርሐ ግብር ኢትዮጵያ መድን ከሻሸመኔ ከተማ ጋር ያደረጉትን ጨዋታ 2ለ0 በሆነ ውጤት በማሸነፍ ደረጃቸውን ማሻሻል ችለዋል።

የኢትዮጵያ መድንን የማሸነፊያ ግቦች አብዲሳ ጀማል እና ምንተስኖት ከበደ በራሱ ግብ ላይ ከመረብ ማሳረፍ ችለዋል።

ያለፉትን አስር ጨዋታዎች ያልተሸነፈው ኢትዮጵያ መድን #ሰባተኛ ተከታታይ ድሉን ማስመዝገብ ችሏል።

ኢትዮጵያ መድን ባለፉት ስባት ጨዋታዎች አስራ ዘጠኝ ግቦችን በተጋጣሚ መረብ ላይ ሲያስቆጥር የተቆጠረበት ሁለት ግብ ብቻ ነው

የሊግ ደረጃቸው ምን ይመስላል ?

9️⃣ ኢትዮጵያ መድን :- 37 ነጥብ

1️⃣5️⃣ ሻሸመኔ ከተማ :- 14 ነጥብ

ቀጣይ ጨዋታ ምን ይመስላል ?

- ኢትዮጵያ መድን ከ ኢትዮጵያ ቡና

- ሻሸመኔ ከተማ ከ ፋሲል ከነማ

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
የሶስቱ አናብስት ቁልፍ ተጨዋች ሀሪ ኬን !

የእንግሊዝ ብሔራዊ ቡድን ዛሬ ምሽት ከሰርቢያ ጋር በሚያደርገው የአውሮፓ ዋንጫ ጨዋታ ቁልፍ ተጨዋቻቸው ሀሪ ኬን ቡድኑን በአምበልነት እየመራ ወደ ሜዳ ይገባል።

ሀሪ ኬን ዛሬ ምሽት በአራት ታላላቅ ውድድሮች የእንግሊዝ ብሔራዊ ቡድንን በአምበልነት የመራ የመጀመሪያው እንግሊዛዊ ተጨዋች በመሆን ታሪክ ይፅፋል።

በተጨማሪም ሀሪ ኬን በታላላቅ ውድድሮች ለብሔራዊ ቡድኑ ተሰልፎ በመጫወት የአሽሊ ኮልን የሀያ ሁለት ጨዋታዎች ሪከርድ ያሻሽላል።

ሀሪ ኬን ባለፉት ሶስት ታላላቅ ውድድሮች ለሶስቱ አናብስት አስራ ሁለት ግቦች አስቆጥሮ ሶስት አመቻችቶ ማቀበል ችሏል።

ባለፉት ሶስት ታላላቅ ውድድሮች ሀሪ ኬን የእንግሊዝ ብሔራዊ ቡድንን አርባ በመቶ ግቦች በማስቆጠር የቡድኑ ወሳኝ ተጨዋችነቱን አስመስክሯል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
75 " ስሎቬኒያ 1 - 1 ዴንማርክ

ጃንዛ                    ኤሪክሰን

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
#EURO2024

በአውሮፓ ዋንጫ የምድብ የመጀመሪያ ጨዋታ የዴንማርክ ብሔራዊ ቡድን ከስሎቬኒያ ብሔራዊ ቡድን ጋር ያደረገውን ጨዋታ 1ለ1 በሆነ አቻ ውጤት አጠናቀዋል።

የዴንማርክ ብሔራዊ ቡድንን ቀዳሚ ያደረገች ግብ ክርስቲያን ኤሪክሰን ከመረብ ሲያሳርፍ ኤሪክ ጃንዛ ስሎቬኒያን አቻ አድርጓል።

የ 32ዓመቱ ተጨዋች ክርስቲያን ኤሪክሰን በአውሮፓ ዋንጫው ግብ ያስቆጠረ በእድሜ ትልቁ ዴንማርካዊ ተጨዋች መሆን ችሏል።

በምድቡ ሁለተኛ ጨዋታ ቀጣይ ሳምንት ሐሙስ ዴንማርክ ከእንግሊዝ እንዲሁም ስሎቬኒያ ከሰርቢያ ጋር ይገናኛሉ።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
የጨዋታ አሰላለፍ !

4:00 እንግሊዝ ከ ሰርቢያ

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
2024/10/02 10:31:46
Back to Top
HTML Embed Code: