Telegram Web Link
11' ጣልያን 1-1 አልባንያ

ባስቶኒ                ባህራሚ

*አልባንያ ጣልያን ላይ በሀያ ሁለት ሰከንዶች ያስቆጠሩት የመሪነት ግብ በአውሮፓ ውድድር ታሪክ ፈጣኑ ግብ በመሆን ተመዝግቧል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
18' ጣልያን 2-1 አልባንያ

ባስቶኒ                ባህራሚ
ባሬላ

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
እረፍት | ጣልያን 2-1 አልባንያ

ባስቶኒ                ባህራሚ
ባሬላ

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
ጣልያን ውድድሯን በድል ጀምራለች !

በአውሮፓ ዋንጫ የምድብ የመጀመሪያ ጨዋታ የጣልያን ብሔራዊ ቡድን ከአልባንያ ብሔራዊ ቡድን ጋር ያደረገውን ጨዋታ 2ለ1 በሆነ ውጤት ማሸነፍ ችሏል።

የጣልያን ብሔራዊ ቡድንን የማሸነፊያ ግቦች አሌሳንድሮ ባስቶኒ እና ኒኮሎ ባሬላ ከመረብ ሲያሳርፉ ለአልባንያ ነዲም ባህራሚ አስቆጥሯል።

ምድቡን ስፔን እና ጣልያን በግብ ክፍያ ተበላልጠው በሶስት ነጥብ አንደኛ እና ሁለተኛ በመሆን መምራት ጀምረዋል።

በምድቡ ሁለተኛ ጨዋታ ቀጣይ ሳምንት ሐሙስ
ጣልያን ከስፔን እንዲሁም እሮብ አልባንያ ከክሮሽያ ጋር ይገናኛሉ።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
ሽመልስ በቀለ 1⃣8⃣ ገስት ሀውስ

በውቢቷ ሀዋሳ ቆይታዎ የት ለማረፍ አስበዋል ? ንፁህ እና በደንበኞቻችን ተወዳጅ በሆነው የእንግዳ ማረፊያችን መጥተው የእረፍት ጊዜውን ያሳልፉ።

እንግዶቻችንን ተቀበልን ለእይታ ሳቢ በሆነው የእንግዳ ማረፊያችን ማስተናገድ ከጀመርን አመታትን አስቆጥረናል።

አድራሻችን :- ሀዋሳ አርቴፍሻል ስታዲየም መንገድ ላይ ያገኙናል።

ለተጨማሪ መረጃ እና ለትዕዛዝዎ ይደውሉልን :- 0928684848

#ShemelesBekele18
🌙 እንኳን ለዒድ አል አድሃ (አረፋ) በዓል በሰላም አደረሳችሁ!

ዒድ ሙባረክ!!
" ስፔን ማሸነፍ ይገባታል " ሞድሪች

የክሮሽያ ብሔራዊ ቡድን አምበል ሉካ ሞድሪች በትላንት ምሽቱ የአውሮፓ ዋንጫ የምድብ የመጀመሪያ ጨዋታ ስፔን በክሮሽያ ላይ የተቀዳጀችው ድል እንደሚገባት ተናግሯል።

" አንዳንድ ቀን እንደሚፈጠረው ሁሉ ዛሬ ነገሮች በፈለግነው መንገድ አልሄዱልንም " ሲል ከጨዋታው በኋላ አስተያየቱን የሰጠው ሞድሪች ስፔን ማሸነፍ ይገባት ነበር ብሏል።

ሉካ ሞድሪች ቀጥሎም " ዛሬ ብንሸነፍም በቀጣዩ ጨዋታ የተሻልን እንደምንሆን እና እንደሚሳካልን እርግጠኛ ነኝ አልባንያን ግዴታ ማሸነፍ አለብን " ሲል ተደምጧል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
TIKVAH-SPORT
ሮናልዲንሆ የብራዚልን ጨዋታ እንደማይመለከት ገለጸ ! ብራዚላዊው የቀድሞ ኮከብ ሮናልዲንሆ በቀጣዩ የኮፓ አሜሪካ ውድድር የሀገሩ ብራዚልን ጨዋታዎች መመልከት እንደማይፈልግ በኢንስታግራም የማህበራዊ ትስስር ገፁ አሳውቋል። የብራዚል ብሔራዊ ቡድኑ በመጥፎ ሁኔታ ውስጥ መሆኑን የተናገረው ሮናልዲንሆ " በቀጣዩ ኮፓ አሜሪካ የብራዚልን ጨዋታዎች አልመለከትም በድሎችም አልደሰተም " ሲል ተናግሯል። " ብሔራዊ…
" ሮናልዲንሆ ትኬት ሲጠይቅ ነበር " ራፊንሀ

የብራዚል ብሔራዊ ቡድን የፊት መስመር ተጨዋች ራፊንሀ ብራዚላዊው የቀድሞ ተጨዋች ሮናልዲንሆ የጨዋታ መመልከቻ ትኬቶች ሲጠይቅ እንደነበር ገልጿል።

ሮናልዲንሆ በቀጣይ የብራዚል ጨዋታዎችን መመልከት እንደማይፈልግ መግለፁን እንደተመለከተ የተናገረው ራፊንሀ " ነገርግን ሮናልዲንሆ ከቀናት በፊት ቪንሰስ ጁኒየርን የጨዋታ መመልከቻ ትኬት ጠይቆት ነበር " ብሏል።

ሮናልዶንሆ ትላንት በማህበራዊ ትስስር ገፁ በብራዚል ብሔራዊ ቡድን ደካማ አቋም ምክንያት ከዚህ በኋላ ጨዋታዎቹን መመልከት ማቆሙን ገልፆ ነበር።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
" በስፔን ጨዋታ የታክቲክ ለውጥ እናደርጋለን " ሉቺያኖ ስፓሌቲ

የጣልያን ብሔራዊ ቡድን አሰልጣኝ ሉቺያኖ ስፓሌቲ ቡድናቸው ትላንት ምሽት ባስመዘገበው ድል ቢደሰቱም ያደረገው እንቅስቃሴ የሚደነቅ አለመሆኑን ከጨዋታው በኋላ ገልጸዋል።

አሰልጣኙ ከጨዋታው በኋላ በሰጡት አስተያየትም " ጨዋታውን በትክክል ተጫውተናል እውነት ነው ነገርግን ውጤቱ የሁለቱን ቡድኖች ልዩነት አያሳይም ፣ በመጨረሻ ሰዓት የአቻነት ግብ ለማስተናገድ ተቃርበን ነበር።"ብለዋል።

በቀጣይ ከስፔን ጋር ለሚያደርጉት ጨዋታ የታክቲክ ለውጥ ሊያደርጉ እንደሚችሉ የጠቆሙት አሰልጣኝ ሉቺያኖ ስፓሌቲ " ስፔን ከአልባንያ በተለየ መልኩ ታዘጋጀናለች።

ከአልባንያ ጋር ካደረግነው በተሻለ ኳሱን ማፍጠን አለብን ከስፔን ጋር በብዛት ኳስ ወደፊት በመውሰድ እና ከተከላካይ ጀርባ መጫወት እንፈልጋለን።"ብለዋል።

ጣልያን በድጋሜ የአውሮፓ ዋንጫውን ታሳካ እንደሆነ የተጠየቁት ሉቺያኖ ስፓሌቲ " ወሳኙ የምናሳየው ብቃት ነው ፣ የእግርኳሳችን ብራንድ እና ቡድናችን ይጠቅመናል።"ሲሉ መልሰዋል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
ባየር ሙኒክ የተጫዋቹን ውል አራዝሟል !

የጀርመን ቡንደስሊጋው ክለብ ባየር ሙኒክ የመሐል ሜዳ ተጨዋቻቸው አሌክሳንደር ፓቭሎቪችን ኮንትራት ለተጨማሪ አመታት ማራዘማቸውን ይፋ አድርገዋል።

ጀርመናዊው የመሐል ሜዳ ተጨዋች አሌክሳንደር ፓቭሎቪች በባየር ሙኒክ ቤት እስከ 2029 የሚያቆየውን የአምስት አመት ውል መፈረሙ ይፋ ሆኗል።

አሌክሳንደር ፓቭሎቪች ውሉን ካራዘመ በኋላ በሰጠው አስተያየት " ባየር ሙኒክ ልቤ ውስጥ ያለ ክለብ ነው እዚህ በመሆኔ ኩራት እና ደስታ ይሰማኛል ፣ ከቡድኑ ጋር ዋንጫዎችን ማሸነፍ እፈልጋለሁ።"ብሏል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
ጋሪዝ ሳውዝጌት የቡድን መሪዎችን አቋቁመዋል !

የእንግሊዝ ብሔራዊ ቡድን ዋና አሰልጣኝ ጋሪዝ ሳውዝጌት በብሔራዊ ቡድኑ ስብስብ ውስጥ " የቡድን መሪዎች " ማቋቋማቸው ተገልጿል።

አሰልጣኙ በስብስቡ ውስጥ ባቋቋሙት የቡድን መሪዎች ውስጥ ሀሪ ኬን ፣ ካይል ዎከር ፣ ጁድ ቤሊንግሀም እና ዴክላን ራይስ መካተታቸው ተነግሯል።

አሰልጣኝ ጋሪዝ ሳውዝጌት የቡድን መሪዎችን ያቋቋሙት በቡድኑ ውስጥ ያለውን ሁኔታ በደንብ ለመረዳት እና ከወጣት ተጨዋቾች ጋር በደንብ ለመግባባት መሆኑ ተገልጿል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
" የአውሮፓ ዋንጫውን እንደምናሸንፍ እናምናለን " ፓልመር

የእንግሊዝ ብሔራዊ ቡድን የፊት መስመር ተጨዋች ኮል ፓልመር እንግሊዝ የዘንድሮውን የአውሮፓ ዋንጫ ውድድር ማሸነፍ እንደምትችል ተናግሯል።

" የቡድን ስብስባችን ድንቅ ነው " ሲል የገለጸው ኮል ፓልመር " እኛ የአለም ምርጥ ተጨዋቾች አሉን የአውሮፓ ዋንጫውን እንደምናሸንፍ አምናለሁ እኛ የተሻለ የማሸነፍ እድል ያለን ይመስለኛል።"ብሏል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
ቫን ዳይክ የሜዳው ጥራት እንዳሰጋው ገለጸ !

የኔዘርላንድ ብሔራዊ ቡድን አምበል ቨርጅል ቫን ዳይክ ቡድናቸው ዛሬ ከፖላንድ ጋር ጨዋታውን የሚያደርግበት ስታዲየም ጥራት እንዳሰጋው አስተያየቱን ሰጥቷል።

" ጨዋታችንን የምናደርግበት ስታዲየም ጥሩ አይመስለኝም ፣ ነገርግን በፍጥነት ልንላመደው ይገባል ተጋጣሚያችንንም እንደዛው።" ሲል ቫን ዳይክ ተናግሯል።

ስለ ዋንጫው አሸናፊነት ያነሳው ቨርጅል ቫን ዳይክ " እንግሊዝ በጣም ጥሩ ቡድን ናቸው ፣ ፈረንሳይ እና ጀርመንም እንደዛው እኛ ከዋንጫ ተፎካካሪዎች ውስጥ እንደምንሆን ተስፋ አደርጋለሁ።"ብሏል።

ኔዘርላንድ ዛሬ ቀን 10:00 ከፖላንድ ጋር ሃምቡርግ ከተማ በሚገኘው የጀርመን ሁለተኛ ሊጉ ክለብ ሀምቡርገር ስታዲየም ቮልክስፓርክስታዲዮን የሚጫወቱ ይሆናል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
#EURO2024

ኔዘርላንድ ከፖላንድ ጋር ዛሬ ቀን 10:00 ለሁለቱም ሀገራት በቅርብ ርቀት ላይ በሚገኘው የጀርመኑ ሃምቡርግ ከተማ የአውሮፓ ዋንጫ ጨዋታቸውን ያደርጋሉ።

ጨዋታው የሚደረግበት ከተማ ለሁለቱም ሀገራት አማካይ ቦታ ላይ መሆኑ በርካታ ደጋፊዎች በከተማዋ እንዲገኙ እና የምድብ ጨዋታውን ከሌሎች በተለየ መልኩ ደማቅ እንዲሆን አድርጎታል።

የምድብ ጨዋታው የሚደረግበት የጀርመኑ ሃምቡርግ ከተማ ከኔዘርላንድ ድንበር 200 ኪ.ሜ እንዲሁም ከፖላንድ ድንበር 300 ኪ.ሜ ርቀት ላይ ይገኛል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
Forwarded from WANAW SPORT
#ዋናው ስፖርት ለመላው የእስልምና እምነት ተከታዮች እንኳን ለዒድ አል አድሃ (አረፋ) በዓል በሰላም አደረሳችሁ ይላል፡፡

ዒድ ሙባረክ!


Instagram | Facebook | TikTok

🏅 ዋናው ወደፊት...

@wanawsportwear
መልካም ዕድል!
ከፍ የተደረጉ ኦዶችን አይተዋል ? እንግዲያውስ ተወራረዱባቸው!
Poland - Netherlands
Serbia - England
ለተሻለ ውርርድ ቤቲካን ይጠቀሙ! አሁኑኑ Betika.et ላይ /በቴሌግራም ቦታችን - @BetikaETBot ይወራረዱ!
የቡናማዎቹ ታዳጊዎች ሻምፒዮን ሆነዋል !

የኢትዮጵያ ቡና ከ 20ዓመት በታች ቡድን ከመቻል አቻው ጋር ያደረገውን U-20 የኢትዮጵያ ፕርሚየር ሊግ ፍፃሜ ጨዋታ በማሸነፍ ሻምፒዮን ሆነዋል።

የኢትዮጵያ ቡና ታዳጊዎች ከመቻል ታዳጊዎች ጋር ያደረጉት የፍፃሜ ጨዋታ መደበኛው የጨዋታ ክፍለ ጊዜ 0ለ0 መጠናቀቁን ተከትሎ በተሰጠ መለያ ምት ቡናማዎቹ ባለድል ሆነዋል።

የዘንድሮውን የኢትዮጵያ ከ 20ዓመት በታች ፕርሚየር ሊግ ውድድር መቻል ሁለተኛ እንዲሁም ኢትዮ ኤሌክትሪክ ሶስተኛ ደረጃን ይዘው አጠናቀዋል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
የጨዋታ አሰላለፍ !

10:00 ፖላንድ ከ ኔዘርላንድ

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
#EURO2024

ኔዘርላንድ ከፖላንድ ጋር ከሚያደርጉት ጨዋታ በፊት በስታዲየሙ አካባቢ በተፈጠረ ክስተት አንድ ግለሰብ ስለታማ እና ተቀጣጣይ ነገሮችን ይዞ ፖሊሶችን ሲያስፈራራ እንደነበር ተገልጿል።

ግለሰቡ በአካባቢው በነበረ የፖሊስ የፀጥታ አካል በጥይት የመመታት የሀይል እርምጃ እንደተወሰደበት የአካባቢው ፖሊስ አስታውቋል።

ግለሰቡ አሁን ላይ በተወሰደበት የሀይል እርምጃ መቁሰሉ እና የህክምና እርዳታ እየተደረገለት መሆኑን የአካባቢው ፖሊስ ጨምሮ ገልጿል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
2024/10/02 12:37:21
Back to Top
HTML Embed Code: