Telegram Web Link
ሽመልስ በቀለ 1⃣8⃣ ገስት ሀውስ

በውቢቷ ሀዋሳ ቆይታዎ የት ለማረፍ አስበዋል ? ንፁህ እና በደንበኞቻችን ተወዳጅ በሆነው የእንግዳ ማረፊያችን መጥተው የእረፍት ጊዜውን ያሳልፉ።

እንግዶቻችንን ተቀበልን ለእይታ ሳቢ በሆነው የእንግዳ ማረፊያችን ማስተናገድ ከጀመርን አመታትን አስቆጥረናል።

አድራሻችን :- ሀዋሳ አርቴፍሻል ስታዲየም መንገድ ላይ ያገኙናል።

ለተጨማሪ መረጃ እና ለትዕዛዝዎ ይደውሉልን :- 0928684848

#ShemelesBekele18
TIKVAH-SPORT
ኢትዮጵያን በኦሎምፒክ የሚወክሉ አትሌቶች ዛሬ ይለያሉ ! ዛሬ ምሽት በስፔን ኔርጃ ሀገራችን ኢትዮጵያን በቀጣዩ የፓሪስ ኦሎምፒክ ውድድር በ10,000 ሜትር የሚወክሉ አትሌቶችን ለመለየት የመምረጫ ውድድር እንደሚደረግ ተገልጿል። ከምሽቱ የመምረጫ ውድድር በኋላ ኢትዮጵያን በፓሪስ ኦሎምፒክ ውድድር 10,000 ሜትር የሚወክሉ አትሌቶች ተለይተው ይታወቃሉ ተብሎ ይጠበቃል። ከዚህ በተጨማሪም ዛሬ ምሽት…
ኢትዮጵያን በኦሎምፒክ የሚወክሉ አትሌቶች ተለይተዋል !

ኢትዮጵያን በቀጣዩ የፓሪስ ኦሎምፒክ ውድድር በ10,000 ሜትር የሚወክሉ አትሌቶችን ለመለየት እንዲሁም የኦሎምፒክ ሚኒማ ለማሟላት የሙከራ ውድድሮች በስፔን ኔርጃ ተካሂደዋል።

በ800ሜ ወንዶች በተደረገው የኦሎምፒክ ሚኒማ ማሟያ ውድድር ኢትዮጵያዊያን አትሌቶች 1:44:70 የሆነውን የኦሎምፒክ ሚኒማ ማሟላት ሳይችሉ ቀርተዋል።

በኦሎምፒክ 10000ሜ ሴቶች ኢትዮጵያን የሚወክሉ አትሌቶችን ለመለየ በተደረገው ውድድር ፎትዬን ተስፋይ ፣ ፅጌ ገብረሰላማ እና እጅጋየሁ ታዬ ተከታትለው በመግባት ማሸነፍ ችለዋል።

በወንዶች 10000ሜ ውድድር ዮሚፍ ቀጄልቻ ፣ በሪሁ አረጋዊ እና ሰለሞን ባረጋ ተከታትለው በመግባት ከአንደኛ እስከ ሶስተኛ ያለውን ደረጃ ይዘው ማጠናቀቅ ችለዋል።

በ1500ሜ ወንዶች ሚኒማ ማሟያ ውድድር አትሌት አበዲሳ ፈይሳ እና ሳሙኤል ተፈራ 3:33:50 የሆነውን የኦሎምፒክ ሚኒማ በሟሟላት አንደኛ እና ሁለተኛ ሆነው አጠናቀዋል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
" ጠንካራ ቡድን መሆናችንን እናውቃለን " ሉዊስ ዴ ላ ፉንቴ

የስፔን ብሔራዊ ቡድን ዋና አሰልጣኝ ሉዊስ ዴ ላ ፉንቴ ቡድናቸው ጠንካራ መሆኑን ዛሬ ከክሮሽያ ጋር ከሚያደርጉት ጨዋታ በፊት በሰጡት አስተያየት ተናግረዋል።

" በርካታ ባለ ጥሩ ተሰጥኦ ተጨዋቾችን ይዘናል "  ያሉት አሰልጣኝ ሉዊስ ዴ ላ ፉንቴ አንድ ላይ የምንጫወት ከሆነ ትልቅ ጥንካሬ ይሰጠናል በማለት ተናግረዋል።

አሰልጣኝ ሉዊስ ዴ ላ ፉንቴ ቀጥለውም ቡድናቸው ጥሩ መጫወት የሚችል ጠንካራ መሆኑን ገልፀው ሌሎች ሀገራትም በተመሳሳይ ደረጃ ስለሚሆኑ መጠንቀቅ አለብን ብለዋል።

የስፔን ብሔራዊ ቡድን ከክሮሽያ ብሔራዊ ቡድን ጋር ምሽት 1:00 ሰዓት በግዙፉ የበርሊን ኦሎምፒያስታድዮን ስታዲየም ይጫወታሉ።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
የሚል ዋል ቁጥር አንድ ግብ ጠባቂ ህይወቱ አለፈ !

የእንግሊዝ ሻምፒዮን ሺፑ ክለብ ሚል ዋል እና ምንቴኔግሮ ብሔራዊ ቡድን ግብ ጠባቂ ማቲሀ ሳርኪች በ 26ዓመቱ ህይወቱ ማለፉ ተገልጿል።

የሻምፒዮን ሺፑ ክለብ የሚል ዋል የግብ ጠባቂው ህይወት ማለፉን በይፋ ከማረጋገጥ ውጪ አሁን ላይ ተጨማሪ አስተያየት መስጠት እንደማይፈልጉ ገልፀዋል።

ግብ ጠባቂው ከአስር ቀናት በፊት የምንቴኔግሮ ብሔራዊ ቡድን በቤልጅየም በተሸነፈበት የወዳጅነት ጨዋታ ተሰልፎ መጫወት ችሎ ነበር።

ባለፈው አመት ከዎልቭስ ሚል ዋልን ተቀላቅሎ የክለቡ ቁጥር አንድ ግብ ጠባቂ መሆን ችሎ የነበረው ማቲሀ ሳርኪች በተጠናቀቀው አመት ካደረጋቸው ሳላሳ ሶስት ጨዋታዎች በአስራ ሁለቱ ግብ ሳይቆጠርበት መውጣት ችሏል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
የቀድሞ የአርሰናል ተጨዋች ህይወቱ አለፈ !

እንግሊዛዊው የቀድሞ የአርሰናል እና ኤቨርተን የፊት መስመር ተጨዋች ኬቪን ካምቤል በ54ዓመቱ ህይወቱ ማለፉ ተገልጿል።

በተንታኝነት እያገለገለ የነበረው የቀድሞ ተጨዋቹ ከሳምንት በፊት ከባድ ህመም አጋጥሞት ሆስፒታል ገብቶ እንደነበር ተዘግቧል።

የሰሜን ለንደኑ ክለብ አርሰናል እንዲሁም ኤቨርተን በቀድሞ ተጨዋቻቸው ህልፈተ ህይወት የተሰማቸውን ሀዘን በማህበራዊ ትስስር ገፃቸው ገልፀዋል።

ኬቪን ካምቤል በአርሰናል ቤት ባሳለፋቸው አመታት ሁለት መቶ አስር ጨዋታዎች ሲያደርግ ሀምሳ አምስት ግቦችንም ማስቆጠር ችሏል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
" ጥራት ያለው ቡድን አለን " አኬ

የኔዘርላንድ ብሔራዊ ቡድን የተከላካይ ስፍራ ተጨዋች ናታን አኬ ቡድናቸው ትልቅ ጥራት ያለው ጥሩ ስብስብ መያዙን በሰጠው አስተያየት ተናግሯል።

ለማንችስተር ሲቲ የሚጫወተው ናታን አኬ በንግግሩም " ትልቅ ጥራት ያለው በጣም ጠንካራ ስብስብ ስብስብ ይዘናል ጥሩ የተጨዋቾች አማራጭም አለን።"ሲል ተደምጧል።

ኔዘርላንድ ነገ ቀን 10:00 ሰዓት ከፖላንድ ጋር የአውሮፓ ዋንጫ የምድብ የመጀመሪያ ጨዋታዋን የምታደርግ ይሆናል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
Forwarded from WANAW SPORT
📢 ስለ #ዋናው አዲስ ምርት ያውቃሉ

👉🏾 ከነፃ ዴሊቨሪ ጋር በ1399 ብር ብቻ#ይዘዙን!

📌 ለበለጠ መረጃና ትዕዛዝ 📲 09011382830910851535 እና 0913586742 ላይ ይደውሉ።

👉🏾 እንዲሁም በቴሌግራም @Wanawsales ላይ የሽያጭ ሰራተኞቻችንን በቀጥታ በማናገር ይዘዙን።

🏅 ዋናው ወደፊት...

@wanawsportswear
#EURO2024

በአውሮፓ ዋንጫ የምድብ የመጀመሪያ ጨዋታ ዛሬ ምሽት 1:00 ሰዓት የስፔን ብሔራዊ ቡድን ከክሮሽያ አቻው ጋር ተጠባቂ ጨዋታውን ያደርጋል።

በጨዋታው 60,000 የክሮሽያ ብሔራዊ ቡድን ደጋፊዎች በግዙፉ ኦሎምፒያስታድዮን ስታዲየም እንደሚታደሙ ይጠበቃል።

በስፔን ብሔራዊ ቡድን በኩል 11,000 ደጋፊዎች ስታዲየም ተገኝተው ብሔራዊ ቡድናቸውን ያበረታታሉ ተብሎ እንደሚጠበቅ ተዘግቧል።

ጨዋታው 74,000 ተመልካች ማስተናገድ በሚችለው በሀገሪቱ ትልቁ የኦሎምፒያስታድዮን ስታዲየም ይደረጋል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
የጨዋታ አሰላለፍ !

10:00 ሀንጋሪ ከ ስዊዘርላንድ

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
ሉቺያኖ ስፓሌቲ ተጨዋቾች ላይ ገደብ ጥለዋል !

የጣልያን ብሔራዊ ቡድን አሰልጣኝ ሉቺያኖ ስፓሌቲ በአውሮፓ ዋንጫው ውድድር ወቅት የብሔራዊ ቡድኑ ተጨዋቾች ላይ የተለያዩ ገደቦችን መጣላቸው ተገልጿል።

በውድድሩ ወቅት ተጨዋቾቹ የ " PlayStation " ቪዲዮ ጌሞችን እንደከዚህ በፊቱ አዘውትረው መጫወት እንደማይችሉ አሰልጣኝ ሉቺያኖ ስፓሌቲ ማሳወቃቸው ተገልጿል።

በተጨማሪም የሞባይል ስልኮችን ከምሳ እና እራት በፊት ብቻ መጠቀም እንደሚችሉ እንዲሁም የጆሮ ማዳመጫ " Headphone " እንደተከለከሉ ተነግሯል።

እንዲሁም ተጨዋቾቹ ከእኩለ ሌሊት በኋላ መተኛት ግዴታቸው መሆኑ እና አላስፈላጊ ቀልድ እና የተጋነኑ ፈንጠዝያዎች መከልከላቸው ተዘግቧል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
TIKVAH-SPORT
Photo
#EURO2024

የሊቨርፑሉ የመሐል ሜዳ ተጨዋች ዶምኒክ ስቦዝላይ የሀንጋሪ ብሔራዊ ቡድንን በአምበልነት እየመራ የአውሮፓ ዋንጫ የምድብ የመጀመሪያ ጨዋታውን ያደርጋል።

የ 23ዓመቱ ተጨዋች ዶምኒክ ስቦዝላይ በአውሮፓ ውድድር ታሪክ ቡድኑን በአምበልነት መምራት የቻለ በእድሜ ትንሹ ተጨዋች በመሆን አዲስ ታሪክ ይፅፋል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
32 ' ሀንጋሪ 0-1 ስዊዘርላንድ

             ዱዋህ
 
@tikvahethsport     @kidusyoftahe
እረፍት | ሀንጋሪ 0-2 ስዊዘርላንድ

             ዱዋህ
             ኤቢሼር
 
@tikvahethsport     @kidusyoftahe
አዳማ ከተማ በሰፊ የግብ ልዩነት አሸነፈ !

በኢትዮጵያ ፕርሚየር ሊግ የሀያ ሰባተኛ ሳምንት መርሐ ግብር አዳማ ከተማ ከሀዋሳ ከተማ ጋር ያደረጉትን ጨዋታ 5ለ0 በሆነ ውጤት ማሸነፍ ችለዋል።

የአዳማ ከተማን የማሸነፊያ ግቦች ዮሴፍ ታረቀኝ 2x ፣ ነቢል ኑሪ ፣ አህመድ ረሺድ እና ቢኒያም አይተን ከመረብ ማሳረፍ ችለዋል።

የሊጉ ደረጃ ሰንጠረዥ ምን ይመስላል ? 

5️⃣ አዳማ ከተማ :- 44 ነጥብ

9️⃣ ሀዋሳ ከተማ  :- 36 ነጥብ

ቀጣይ መርሐ ግብር ምን ይመስላል ?

- አዳማ ከተማ ከ ባሕር ዳር ከተማ

- ሀዋሳ ከተማ ከ ወልቂጤ ከተማ

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
66 ' ሀንጋሪ 1 - 2 ስዊዘርላንድ

ቫርጋ          ዱዋህ
             ኤቢሼር
 
@tikvahethsport     @kidusyoftahe
90+2 ' ሀንጋሪ 1 - 3 ስዊዘርላንድ

ቫርጋ          ዱዋህ
                       ኤቢሼር
ኢምቦሎ
 
@tikvahethsport     @kidusyoftahe
የጨዋታ አሰላለፍ !

1:00 ስፔን ከ ክሮሽያ

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
ስዊዘርላንድ ውድድሯን በድል ጀምራለች !

የስዊዘርላንድ  ብሔራዊ ቡድን የአውሮፓ ዋንጫ የምድብ የመጀመሪያ ጨዋታውን ከሀንጋሪ አቻው ጋር አድርጎ 3ለ1 በሆነ ውጤት ማሸነፍ ችሏል።

ለስዊዘርላንድ ብሔራዊ ቡድን ግቦችን ክዋድዎ ዱዋህ ፣ ሚሼል ኤቢሼር እና ኢምቦሎ ከመረብ ሲያስቆጥሩ የሀንጋሪን ብቸኛ ግብ በርናባስ ቫርጋ ከመረብ አሳርፏል።

የስዊዘርላንድ ብሔራዊ ቡድን የፊት መስመር ተጨዋች ክዋድዎ ዱዋህ ለብሔራዊ ቡድኑ ባደረገው የመጀመሪያ ጨዋታው የመጀመሪያ ግቡን አስቆጥሯል።

የፊታችን እሮብ የስዊዘርላንድ ብሔራዊ ቡድን ሁለተኛ የምድብ ጨዋታውን ከስኮትላንድ ጋር ሲያደርግ ሀንጋሪ ከጀርመን ትጫወታለች።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
2024/06/24 13:32:01
Back to Top
HTML Embed Code: