Telegram Web Link
መቻል ወሳኝ ድል አሳክቷል !

በኢትዮጵያ ፕርሚየር ሊግ የሀያ ሰባተኛ ሳምንት መርሐ ግብር መቻል ከፋሲል ከነማ ጋር ያደረጉትን ጨዋታ 1ለ0 በሆነ ውጤት ማሸነፍ ችለዋል።

የመቻልን የማሸነፊያ ግብ አብዱ ሙተለቡ ከመረብ ማሳረፍ ችሏል።

በዋንጫ ፉክክር ውስጥ የሚገኘው መቻል ማሸነፉን መውጣቱን ተከትሎ ከሊጉ መሪ ያለውን የነጥብ ልዩነት ወደ ሶስት ማጥበብ ችሏል።

የሊጉ ደረጃ ሰንጠረዥ ምን ይመስላል ? 

2️⃣ መቻል :- 54 ነጥብ

7️⃣ ፋሲል ከነማ  :- 40 ነጥብ

ቀጣይ መርሐ ግብር ምን ይመስላል ?

- ሲዳማ ቡና ከ መቻል

- ሻሸመኔ ከተማ ከ ፋሲል ከነማ

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
የኢትዮጵያ ፕርሚየር ሊግን ማን ሊያሸንፍ ይችላል ?

ፍፃሜውን ሊያገኝ የተቃረበው የ2016 ኢትዮጵያ ፕርሚየር ሊግ ውድድር ለዋንጫው አሸናፊነት ኢትዮጵያ ንግድ ባንክን እና መቻልን አፋጦ ይገኛል።

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ሊጉን በሀምሳ ሰባት ነጥቦች በበላይነት ሲመራ መቻል በሶስት ነጥቦች ዝቅ ብሎ ሁለተኛ ደረጃ ላይ ይገኛል።

ቀጣይ ጨዋታቸው ምን ይመስላል ?

- ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ :- ቅዱስ ጊዮርጊስ ፣ ሻሸመኔ ከተማ እና ኢትዮጵያ መድን

- መቻል :- ሲዳማ ቡና ፣ አዳማ ከተማ እና ድሬዳዋ ከተማ

የሊጉ ሻምፒዮን ማን ይሆናል

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
ሬስ ኔልሰን አርሰናልን መልቀቅ ይፈልጋል !

እንግሊዛዊው የፊት መስመር ተጨዋች ሬስ ኔልሰን በዚህ ክረምት ሌላ የሚፈልገው ክለብ ካገኘ መመልከት እንደሚፈልግ ለአርሰናል ማሳወቁ ተገልጿል።

በጥር ወር የተጨዋቾች የዝውውር መስኮት ለሬስ ኔልሰን የቀረበውን ጥያቄ ውድቅ ያደረጉት መድፈኞቹ በበኩላቸው ተጫዋቹን ለመሸጥ የሚገደዱ ከሆነ 20 ሚልዮን ፓውንድ እንደሚፈልጉ ተነግሯል።

በአርሰናል ቤት ብዙም የመጫወት እድል ያላገኘው የ 24ዓመቱ ተጨዋች ሬስ ኔልሰን ባለፈው ክረምት የአራት አመት ኮንትራት መፈረሙ ይታወሳል።

ተጫዋቹን ለማስፈረም ዌስትሀም ዩናይትድ ፣ ኖቲንግሃም ፣ ፉልሀም እና ክሪስታል ፓላስ ፍላጎት እንዳላቸው ተዘግቧል።

@tikvahethsport           @kidusyoftahe
TIKVAH-SPORT
አሰልጣኝ ኤዲን ቴርዚች ከሀላፊነታቸው ለቀቁ ! ጀርመናዊው የቡንደስሊጋው ክለብ ቦርስያ ዶርትመንድ ዋና አሰልጣኝ ኤዲን ቴርዚች ከክለቡ አሰልጣኝነታቸው መልቀቃቸው ይፋ ተደርጓል። አሰልጣኝ ኤዲን ቴርዚች ከቦርስያ ዶርትመንድ ጋር በጋራ ስምምነት መለያየታቸውን በይፋ አስታውቀዋል። የ 41ዓመቱ አሰልጣኝ ኤዲን ቴርዚች ቦርስያ ዶርትመንድን እየመሩ የዘንድሮው የአውሮፓ ሻምፒየንስ ሊግ ፍፃሜ ተፋላሚ እንደነበሩ…
ዶርትመንድ ኑሪ ሳሂን በአሰልጣኝነት ሾመ !

ከጀርመናዊው አሰልጣኝ ኤዲን ቴርዚች ጋር የተለያየው የቡንደስሊጋው ክለብ ቦርስያ ዶርትመንድ አዲስ አሰልጣኝ መሾማቸውን ይፋ አድርገዋል።

ዶርትመንድ ቱርካዊውን የቀድሞ ተጨዋቻቸው ኑሪ ሳሂንን የክለቡ ዋና አሰልጣኝ አድርገው በሀላፊነት መሾማቸውን አስታውቀዋል።

ለቦርስያ ዶርትመንድ በሁለት መቶ ሰባ አራት ጨዋታዎች ተሰልፎ መጫወት የቻለው ኑሪ ሳሂን ባለፈው አመት በኤዲን ቴርዚች የአሰልጣኝ ቡድን ውስጥ ተካቶ ሰርቷል።

የ 35ዓመቱ የቀድሞ የመሐል ሜዳ ተጨዋች ኑሪ ሳሂን ቦርስያ ዶርትመንድን ለሶስት አመታት ለማሰልጠን ፊርማውን ማኖሩ ተገልጿል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
ማንችስተር ዩናይትድ የዝውውር ጥያቄ አቀረበ !

ማንችስተር ዩናይትድ እንግሊዛዊውን የመሐል ተከላካይ ጃሬድ ብራንዝዌት ለማስፈረም ለኤቨርተን ይፋዊ የዝውውር ጥያቄ ማቅረባቸው ተገልጿል።

ቀያዮቹ ሴጣኖች ለ 21ዓመቱ ተጨዋች ጃሬድ ብራንዝዌት ዝውውር የመጀመሪያ 35 ሚልዮን ፓውንድ ማቅረባቸው ተነግሯል።

የመርሲሳይዱ ክለብ ኤቨርተን በበኩሉ የቀረበው የዝውውር ሒሳብ ከሚጠበቀው በታች ነው ብለው እንደሚያምኑ ሲገለፅ ውድቅ ለማድረግ ማሰባቸው ተዘግቧል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
Forwarded from WANAW SPORT
🎁 #ይገምቱ#ይሸለሙ!

🏆  በዛሬው ምሽት የ2024 አውሮፓ ዋንጫ መክፈቻ ጨዋታ ማን ያሸንፍ ይሆን?

🇩🇪 ጀርመን ወይስ ስኮትላንድ 🇸🇪

💬 ግምትዎን #በቴሌግራም ገፃችን (https://www.tg-me.com/wanawsportwear) ኮሜንት ላይ ብቻ ያስቀምጡልን!

⚠️ የውድድሩ ህጎች፦
👉🏾 የጨዋታውን አሸናፊ ሀገር እስከ የግብ መጠኑ #በትክክል ቀድመው የሚገምቱ #2 ተከታታዮቻችን የዋናውን የጂም ማልያዎች ይሸለማሉ።
👉🏾 የዋናውን ማህበራዊ ገፆች መከተል፣ መወዳጀትና ማጋራት አይዘንጉ።
👉🏾 የተስተካከሉ መልሶች በፍፁም ተቀባይነት የላቸውም።

Instagram | Facebook | TikTok

🏅 ዋናው ወደፊት...

@wanawsportwear
ድሬዳዋ ከተማ ድል አድርጓል !

በ2016 የኢትዮጵያ ፕርሚየር ሊግ ሀያ ሰባተኛ ሳምንት መርሐ ግብር ድሬዳዋ ከተማ ከቅዱስ ጊዮርጊስ ጋር ያደረጉትን ጨዋታ 1ለ0 በሆነ ውጤት ማሸነፍ ችለዋል።

የድሬዳዋ ከተማን የማሸነፊያ ግብ ተመስገን ደረሰ ከመረብ ማሳረፍ ችሏል።

የአምናው የሊጉ አሸናፊ ቅዱስ ጊዮርጊስ በውድድር አመቱ #ስምንተኛ ሽንፈቱን አስተናግዷል።

ፈረሰኞቹ ካለፉት ዘጠኝ የሊግ ጨዋታዎች ማሸነፍ የቻሉት በአንዱ ነው በአምስቱ ሲሸነፍ በሶስቱ አቻ ተለያይተዋል።

የሊጉ ደረጃ ሰንጠረዥ ምን ይመስላል ? 

5️⃣ ቅዱስ ጊዮርጊስ :- 43 ነጥብ

8️⃣ ድሬዳዋ ከተማ  :- 40 ነጥብ

ቀጣይ መርሐ ግብር ምን ይመስላል ?

- ቅዱስ ጊዮርጊስ ከ ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ

- ድሬዳዋ ከተማ ከ ሀድያ ሆሳዕና

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
" እዚህ የመጣነው ጥሩ ውጤት ለማስመዝገብ ነው " ሞድሪች

የክሮሽያ ብሔራዊ ቡድን የመሐል ሜዳ ተጨዋች ሉካ ሞድሪች ቡድናቸው በአውሮፓ ዋንጫ ውድድር ትልቅ ውጤት ለማስመዝገብ መዘጋጀቱን ተናግሯል።

ነገ ከስፔን ጋር ከሚያደርጉት ጨዋታ በፊት አስተያየቱን የሰጠው ሉካ ሞድሪች " በአለም ዋንጫ እንዳደረግነው ጥሩ ውጤት ማስመዝገብ እንፈልጋለን ወደዚህ የመጣነው ትልቅ ውጤት አልመን ነው " ብሏል።

በአውሮፓ እና አለም ዋንጫ ውድድሮች ዙሪያ እየተሰጡ ስለሚገኙ አስተያየቶች የተጠየቀው ሞድሪች " ሁለቱን ላወዳድር አልፈልግም ነገርግን አለም ዋንጫ ከባድ ይመስለኛል አለም ዋንጫ የአለም ምርጥ ቡድኖችን የሚያገናኝ ብቸኛው ውድድር ነው።"ብሏል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
TIKVAH-SPORT
አዳም ላላና ወደ ሳውዝሀምፕተን ሊያመራ ነው ! እንግሊዛዊው የብራይተን የመሐል ሜዳ ተጨዋች አዳም ላላና በቀጣይ ወደ ቀድሞ ክለቡ ሳውዝሀምፕተን ሊያመራ መሆኑ ተገልጿል። በብራይተን ቤት ስድስት አመታትን ያሳለፈው አዳም ላላና በዚህ ክረምት ውሉ ሲጠናቀቅ ክለቡን እንደሚለቅ ማሳወቁ ይታወቃል። የቀድሞ የሊቨርፑል የመሐል ሜዳ ተጨዋች አዳም ላላና አሁን ላይ ዝውውሩ ባይጠናቀቅም የቀድሞ ክለቡን ሳውዝሀምፕተን…
አዳም ላላና ሳውዝሀምፕተንን ተቀላቀለ !

እንግሊዛዊው የመሐል ሜዳ ተጨዋች አዳም ላላና የቀድሞ ክለቡ ሳውዝሀምፕተንን ለአንድ የውድድር አመት መቀላቀሉ ይፋ ተደርጓል።

አዳማ ላላና በቅርቡ አራት አመታትን ካሳለፈበት ብራይተን ኮንትራቱ መጠናቀቁን ተከትሎ መለያየቱ ይታወሳል።

የቀድሞ የሊቨርፑል የመሐል ሜዳ ተጨዋች አዳም ላላና የቀድሞ ክለቡን ሳውዝሀምፕተን ከአስር አመታት በኋላ በድጋሜ ተቀላቅሏል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
የጨዋታ አሰላለፍ !

4:00 ጀርመን ከ ስኮትላንድ

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
#EURO2024

11 '  ጀርመን 1 - 0 ስኮትላንድ

ቨርትዝ

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
19 '  ጀርመን 2 - 0 ስኮትላንድ

ቨርትዝ
ሙሲያላ

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
45+1 '  ጀርመን 3 - 0 ስኮትላንድ

ቨርትዝ
ሙሲያላ
ሀቨርትዝ

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
እረፍት |  ጀርመን 3 - 0 ስኮትላንድ

ቨርትዝ
ሙሲያላ
ሀቨርትዝ

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
67 '  ጀርመን 4 - 0 ስኮትላንድ

    ቨርትዝ
    ሙሲያላ
    ሀቨርትዝ
ፉልክሩግ

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
86 '  ጀርመን 4 - 1 ስኮትላንድ

    ቨርትዝ ሩዲገር ( በራስ ላይ )
    ሙሲያላ
    ሀቨርትዝ
    ፉልክሩግ

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
90 '  ጀርመን 5 - 1 ስኮትላንድ

    ቨርትዝ         ሩዲገር ( በራስ ላይ )
    ሙሲያላ
    ሀቨርትዝ
    ፉልክሩግ
ኤምሪ ቻን

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
ጀርመን ውድድሯን በድል ጀምራለች !

የጀርመን ብሔራዊ ቡድን የአውሮፓ ዋንጫ የመክፈቻ ጨዋታውን ከስኮትላንድ አቻው ጋር አድርጎ 5ለ1 በሆነ ውጤት ማሸነፍ ችሏል።

ለጀርመን ብሔራዊ ቡድን ግቦችን ፍሎሪያን ቨርትዝ ፣ ጀማል ሙሲያላ ፣ ካይ ሀቨርትዝ ፣ ኒክላስ ፉልክሩግ እና ኤምሪ ቻን ሲያስቆጥሩ የስኮትላንድን ብቸኛ ግብ ሩዲገር በራሱ ግብ ላይ ከመረብ አሳርፏል።

የ 21ዓመቱ የፊት መስመር ተጨዋች ፍሎርያን ቨርትዝ በአውሮፓ ዋንጫው ለጀርመን ብሔራዊ ቡድን ግብ ያስቆጠረ በእድሜ ትንሹ ተጨዋች በመሆን አዲስ ታሪክ ፅፏል።

የ 36ዓመቱ የጀርመን ብሔራዊ ቡድን አሰልጣኝ ጁሊያን ኔግልስማን በውድድሩ ታሪክ ብሔራዊ ቡድን የመራ በእድሜ ትንሹ አሰልጣኝ መሆን ችሏል።

ኒክላስ ፉልክሩግ ለጀርመን ብሔራዊ ቡድን ባደረጋቸው አስራ ሰባት ጨዋታዎች አስራ ሁለት ግቦችን ማስቆጠር ችሏል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
Play More and Spend less!

•PS4 Slim, 34,999 Birr
•PS4 PRO, 41,999 Birr
•Original Controller 6,499 Birr

Contact Us
0953964175 @heymobile

@heyonlinemarket
2024/06/28 11:33:35
Back to Top
HTML Embed Code: