Telegram Web Link
አሰልጣኝ ኤዲን ቴርዚች ከሀላፊነታቸው ለቀቁ !

ጀርመናዊው የቡንደስሊጋው ክለብ ቦርስያ ዶርትመንድ ዋና አሰልጣኝ ኤዲን ቴርዚች ከክለቡ አሰልጣኝነታቸው መልቀቃቸው ይፋ ተደርጓል።

አሰልጣኝ ኤዲን ቴርዚች ከቦርስያ ዶርትመንድ ጋር በጋራ ስምምነት መለያየታቸውን በይፋ አስታውቀዋል።

የ 41ዓመቱ አሰልጣኝ ኤዲን ቴርዚች ቦርስያ ዶርትመንድን እየመሩ የዘንድሮው የአውሮፓ ሻምፒየንስ ሊግ ፍፃሜ ተፋላሚ እንደነበሩ ይታወሳል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
ሮቤርቶ ዲ ዘርቢ ወደ ማርሴይ ሊያመሩ ነው !

ጣልያናዊው የቀድሞ የብራይተን አሰልጣኝ ሮቤርቶ ዲ ዘርቢ የፈረንሳዩን ክለብ ኦሎምፒክ ማርሴይ ለመረከብ ንግግር ላይ መሆናቸው ተገልጿል።

አሰልጣኝ ሮቤርቶ ዲ ዘርቢ ከማርሴይ የሶስት አመት ኮንትራት እንደቀረበላቸው ተነግሯል።

አሰልጣኙ ማርሴይን ለመረከብ አሁን ላይ ሙሉ ስምምነት ላይ ባይደርሱም ንግግሮች በጥሩ መልኩ መቀጠላቸው ተዘግቧል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
ዌስትሀም ዩናይትድ ተጨዋች አስፈርመዋል !

ዌስትሀም ዩናይትድ ብራዚላዊውን የመሐል ሜዳ ተጨዋች ሉዊስ ጉልሄርሜ ከፓልሜይራስ ማስፈረማቸውን ይፋ አድርገዋል።

የ 18ዓመቱ ተጨዋች ሉዊስ ጉልሄርሜ ለዌስትሀም ዩናይትድ ለአንድ ተጨማሪ አመት የመቆየት አማራጭ ያካተተ የአምስት አመት ኮንትራት መፈረሙ ተገልጿል።

ዌስትሀም ዩናይትድ ለተጨዋቹ ዝውውር 30 ሚልዮን ዩሮ የዝውውር ሒሳብ ማውጣታቸው ተገልጿል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
Forwarded from WANAW SPORT
🔥 #እንዳያመልጥዎ፣ ይዘዙን!

📌 ለበለጠ መረጃና ትዕዛዝ 📲 09011382830910851535 እና 0913586742 ላይ ይደውሉ።

👉🏾 እንዲሁም በቴሌግራም @Wanawsales ላይ የሽያጭ ሰራተኞቻችንን በቀጥታ በማናገር ይዘዙን።

Instagram | Facebook | TikTok

🏅 ዋናው ወደፊት...

@wanawsportwear
የኢትዮጵያ  ቡና ይፋዊ አጋር የሆነው ቤቲካ - የኢትዮጵያ ቡናን  22ኛ የጨዋታ ቀን የዲጂታል መፅሄት ይዞ ቀርቧል።
በመፅሄቱ ላይ የዕለቱ ጨዋታን የተመለከቱና ሌሎች የተለያዩ መረጃዎች የሚቀርቡ ይሆናል፡፡

መፅሄቱን በተከታዩ ሊንክ ማግኘት ይችላሉ

https://www.tg-me.com/betikaethiopia/5329

የጨዋታ መፅሄት ቁጥር 22
ወልቂጤ ከተማ ከ ኢትዮጵያ ቡና
ዛሬ 12:00

ቤቲካ - የኢትዮጵያ ቡና ይፋዊ አጋር
#EthiopianPL 🇪🇹

በኢትዮጵያ ፕርሚየር ሊግ የሀያ ሰባተኛ ሳምንት መርሐ ግብር የሊጉ መሪ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ከባሕር ዳር ከተማ ጋር ያደረጉትን ጨዋታ 2ለ2 በሆነ አቻ ውጤት ተለያይተዋል።

የጣና ሞገዶቹቹን ግቦች የአብስራ ተስፋዬ እና ፀጋዬ አበራ ከመረብ ማሳረፍ ሲችሉ ለንግድ ባንክ የአቻነት ግቦችን አዲስ ግደይ 2x አስቆጥሯል።

የፕርሚየር ሊጉ መሪ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ #ሲመራ ቢቆይም በጨዋታው መጠናቀቂያ ከ86ኛው ደቂቃ በኋላ ባስቆጠረው ሁለት ግብ ነጥብ መጋራት ችሏል።

የኢትዮጵያ ንግድ ባንኩ ተጨዋች አዲስ ግደይ በውድድር ዘመኑ አስራ አንደኛ የሊግ ግቡን ከመረብ ማሳረፍ ችሏል።

የሊጉ ደረጃ ሰንጠረዥ ምን ይመስላል ? 

1️⃣ ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ :- 57 ነጥብ

3️⃣ ባሕር ዳር ከተማ :- 46 ነጥብ

ቀጣይ መርሐ ግብር ምን ይመስላል ?

- አዳማ ከተማ ከ ባሕር ዳር ከተማ

- ቅዱስ ጊዮርጊስ ከ ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
ቼልሲ ኦሊሴን ለማስፈረም ንግግር ጀመሩ !

የምዕራብ ለንደኑ ክለብ ቼልሲ በፈረንሳዊው ተጨዋች ሚሼል ኦሊሴ ዝውውር ዙሪያ ክለቡ ክሪስታል ፓላስን ማነጋገራቸው ተገልጿል።

ሰማያዊዎቹ ፈረንሳዊውን የፊት መስመር ተጨዋች ሚሼል ኦሊሴን በግል ጥቅማጥቅም ዙሪያ ለማነጋገር ከክሪስታል ፓላስ ፍቃድ መጠየቃቸው ተነግሯል።

ባየር ሙኒክ እና ኒውካስል ዩናይትድ በበኩላቸው ተጫዋቹን ለማስፈረም ክሪስታል ፓላስን ማነጋገራቸው ተገልጿል።

እንዲሁም ማንችስተር ዩናይትድ እና ማንችስተር ሲቲ የ 22ዓመቱን የፊት መስመር ተጨዋች ሚሼል ኦሊሴ ለማስፈረም ከፍተኛ ፍላጎት እንዳላቸው ተጠቁሟል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
ባየር ሙኒክ ተጨዋች አስፈርመዋል !

የጀርመን ቡንደስሊጋው ክለብ ባየር ሙኒክ ጃፓናዊውን የተከላካይ ስፍራ ተጨዋች ሂሮኪ ኢቶ ከስቱትጋርት ማስፈረማቸውን ይፋ አድርገዋል።

ባየር ሙኒክ የ 25ዓመቱን የተከላካይ ስፍራ ተጨዋች ሂሮኪ ኢቶ በሶስት አመት ኮንትራት ማስፈረማቸውን አስታውቀዋል።

ባየር ሙኒክ ለተጨዋቹ ውል ማፍረሻ ለስቱትጋርት 30 ሚልዮን ዩሮ መክፈላቸው ተዘግቧል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
ኪሊያን ምባፔ መቼ አቀባበል ይደረግለታል ?

በቅርቡ በይፋ ሪያል ማድሪድን የተቀላቀለው ፈረንሳዊው የፊት መስመር ተጨዋች ኪሊያን ምባፔ በክለቡ ደማቅ አቀባበል እንደሚደረግለት ተገልጿል።

ሎስ ብላንኮዎቹ ለኪሊያን ምባፔ ሐምሌ 9/2016 ዓ.ም ይፋዊ አቀባበል በሳንቲያጎ በርናቦ ስታዲየም ማዘጋጀታቸው ተነግሯል።

ከአውሮፓ ዋንጫው ፍፃሜ ሁለት ቀናት በኋላ በሚደረገው ይፋዊ አቀባበል ክርስቲያኖ ሮናልዶ ከአመታት በፊት በ80,000 ደጋፊዎች ፊት የተደረገለት አቀባበል አይነት እንደሚሆን ተጠቁሟል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
" ጀርመንን ለመግጠም ዝግጁ ነን ማንንም አንፈራም " ስቴቭ ክላርክ

የውድድሩ የመክፈቻ ጨዋታቸውን ከአዘጋጇ ሀገር ጀርመን ጋር የሚያደጉት ስኮትላንድ ብሔራዊ ቡድን አሰልጣኝ ስቴቭ ክላርክ ከአንዲ ሮበርሰን ጋር በመሆን አስተያየታቸውን ሰጥተዋል።

አሰልጣኝ ስቴቭ ክላርክ በሰጡት አስተያየትም " በአውሮፓ ዋንጫው በመሳተፋችን ደስተኞች ነን ለውድድሩም ዝግጁ ነን " ያሉ ሲሆን በእንዲህ አይነት ውድድሮች ብዙም ልዩነት የለም ጀርመንን ለመግጠም ዝግጁ ነን ብለዋል።

አሰልጣኝ ስቴቭ ክላርክ አያይዘውም የጀርመን ብሔራዊ ቡድን ውድድሩን ያሸንፋሉ ተብለው ከታጩ ቡድኖች አንዱ መሆኑን ጠቅሰው ቡድናቸው መጠንቀቅ እንዳለበት አሳስበዋል።

" ሁሉንም ቡድኖች በተገቢው መልኩ እናከብራለን ነገርግን የትኛውንም ብሔራዊ ቡድኝ አንፈራም።" ስቴቭ ክላርክ

አንዲ ሮበርትሰን በበኩሉ " የውድድሩን አሸናፊ እጩ መግጠም አስቸጋሪ እንደሚሆን እናውቃለን ፣ በመጀመሪያ ጨዋታችን ጥሩ ውጤት ለማስመዝገብ ያለንን ሁሉ መስጠት አለብን " ሲል ተደምጧል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
ቡናማዎቹ ድል አድርገዋል !

በኢትዮጵያ ፕርሚየር ሊግ የሀያ ሰባተኛ ሳምንት መርሐ ግብር ኢትዮጵያ ቡና ከወልቂጤ ከተማ ጋር ያደረጉትን ጨዋታ 4ለ0 በሆነ ሰፊ ውጤት ማሸነፍ ችለዋል።

የቡናማዎቹን የማሸነፊያ ግቦች አማኑኤል አድማሱ መሐመድ ናስር ፣ ስንታየሁ ወለጬ እና አንተነህ ተፈራ ከመረብ ማሳረፍ ችለዋል።

ኢትዮጵያ ቡና አራተኛ ተከታታይ ድሉን በማሳካት ደረጃውን ማሻሻል ችሏል።

ወልቂጤ ከተማ ሰባተኛ ተከታታይ ሽንፈቱን አስተናግዷል።

ኢትዮጵያ ቡና ባለፉት ሁለት ጨዋታዎች በተጋጣሚዎቹ ላይ አስር ግቦችን ማስቆጠር ችሏል።

የሊጉ ደረጃ ሰንጠረዥ ምን ይመስላል ? 

3️⃣ ኢትዮጵያ ቡና :- 47 ነጥብ

1️⃣4️⃣ ወልቂጤ ከተማ :- 16 ነጥብ

ቀጣይ መርሐ ግብር ምን ይመስላል ?

- ሀዋሳ ከተማ ከ ወልቂጤ ከተማ

- ኢትዮጵያ መድን ከ ኢትዮጵያ ቡና

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
ሌኒ ዮሮ ወዴት ሊያመራ ይችላል ?

ጥሩ የውድድር አመት ማሳለፍ የቻለው ፈረንሳዊው የሊል የተከላካይ ስፍራ ተጨዋች ሌኒ ዮሮ አሁን ላይ በአውሮፓ ታላላቅ ክለቦች እየተፈለገ ይገኛል።

አሁን ላይ የእንግሊዝ ፕርሚየር ሊጎቹ ሊቨርፑል እና ማንችስተር ዩናይትድ ተጫዋቹን ለማስፈረም በንቃት እየተከታተሉ እንደሚገኙ ተገልጿል።

ሌኒ ዮሮን ለማስፈረም ቀደም ብሎ እንቅስቃሴ የጀመረው ሪያል ማድሪድ የተሻለ እድል እንዳለው ሲገለፅ ተጨዋቹ በበኩሉ ለሎስ ብላንኮዎቹ ቅድሚያ ሊሰጥ እንደሚችል ተዘግቧል።

የ 19ዓመቱ የመሐል ተከላካይ ሌኒ ዮሮ የዝውውር ሒሳብ 50 ሚልዮን ዩሮ ሊደርስ እንደሚችል ተነግሯል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
ናቾ ወደ ሳውዲ አረቢያ ሊያመራ ነው !

ስፔናዊው የሪያል ማድሪድ የተከላካይ ስፍራ ተጨዋች ናች ፈርናንዴዝ የሳውዲ አረቢያውን ክለብ አል ኢትሀድ ለመቀላቀል ንግግር ላይ መሆኑ ተገልጿል።

ሪያል ማድሪድን በዚህ ክረምት እንደሚለቅ የሚጠበቀው ናቾ ዝውውሩን ባያጠናቀቅም ከአል ኢትሀድ ጋር እያደረገ የሚገኘው ንግግር በጥሩ ሁኔታ መቀጠሉ ተዘግቧል።

የሳውዲ አረቢያው ክለብ አል ኢትሀድ ለናቾ 40 ሚልዮን ዩሮ የሚያስገኝለትን የሁለት አመት ኮንትራት ማቅረባቸው ተገልጿል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
Forwarded from HEY Online Market
Play More and Spend less!

•PS4 Slim, 34,999 Birr
•PS4 PRO, 41,999 Birr
•Original Controller 6,499 Birr

Contact Us
0953964175 @heymobile

@heyonlinemarket
ሽመልስ በቀለ 1⃣8⃣ ገስት ሀውስ

በውቢቷ ሀዋሳ ቆይታዎ የት ለማረፍ አስበዋል ? ንፁህ እና በደንበኞቻችን ተወዳጅ በሆነው የእንግዳ ማረፊያችን መጥተው የእረፍት ጊዜውን ያሳልፉ።

እንግዶቻችንን ተቀበልን ለእይታ ሳቢ በሆነው የእንግዳ ማረፊያችን ማስተናገድ ከጀመርን አመታትን አስቆጥረናል።

አድራሻችን :- ሀዋሳ አርቴፍሻል ስታዲየም መንገድ ላይ ያገኙናል።

ለተጨማሪ መረጃ እና ለትዕዛዝዎ ይደውሉልን :- 0928684848

#ShemelesBekele18
TIKVAH-SPORT
" ጀርመንን ለመግጠም ዝግጁ ነን ማንንም አንፈራም " ስቴቭ ክላርክ የውድድሩ የመክፈቻ ጨዋታቸውን ከአዘጋጇ ሀገር ጀርመን ጋር የሚያደጉት ስኮትላንድ ብሔራዊ ቡድን አሰልጣኝ ስቴቭ ክላርክ ከአንዲ ሮበርሰን ጋር በመሆን አስተያየታቸውን ሰጥተዋል። አሰልጣኝ ስቴቭ ክላርክ በሰጡት አስተያየትም " በአውሮፓ ዋንጫው በመሳተፋችን ደስተኞች ነን ለውድድሩም ዝግጁ ነን " ያሉ ሲሆን በእንዲህ አይነት ውድድሮች…
" የመጀመሪያ ጨዋታችንን ማሸነፍ አለብን " ኔግልስማን

የጀርመን ብሔራዊ ቡድን ዋና አሰልጣኝ ጁሊያን ኔግልስማን ከአውሮፓ ዋንጫው መክፈቻ ጨዋታ በፊት ከአምበሉ ኢልካይ ጉንዶጋን ጋር በመሆን ከጋዜጠኞች ጋር ቆይታ አድርገዋል።

አሰልጣኝ ጁሊያን ኔግልስማን ምን አሉ ?

- " ከፓቭሎቪች ውጪ ሁሉም ተጨዋቾች በመልካም ጤንነት ላይ ይገኛሉ ቡድናችን በሙሉ ጥንካሬ ላይ ነው ለምሽቱ ጨዋታ ጓጉተናል።

- ስኮትላንድ በጣም ጥሩ ቡድን ነው በስብሰባቸው ውስጥ አራት ወይም አምስት ወሳኝ ተጨዋቾች ይዘዋል፣ እኛ ከእነሱ በበለጠ በጫና ውስጥ ሆነን እንጫወታለን የመጀመሪያ ጨዋታችንን ማሸነፍ አለብን።

- ስላለፈው አቋማችን ማውራት አልፈልግም ሁሉም ነገር  አሁን ስላለንበት ሁኔታ ነው ካለፈው የተሻለ ስኬት ማስመዝገብ እንፈልጋለን ዛሬ በጥሩ ውጤት መጀመር አለብን።

- ቶኒ ክሩስ ወሳኝ ተጨዋቻችን ነው በተለይ ለወጣት ተጨዋቾች ወደ ብሔራዊ ቡድኑ እንዲመለስ ስጠይቀው ከእሱ ጋር ዋንጫ እንደምናሳካ ካመነ ብቻ እንደሚመለስ ነግሮኝ ነበር።" ሲሉ ተናግረዋል።

ኢልካይ ጉንዶጋን በበኩሉ :-

- " ከስኮትላንድ አስቸጋሪ ጨዋታ መጠበቅ አለብን አብዛኞቹን ተጨዋቾች ፕርሚየር ሊግ ውስጥ አውቃቸዋለሁ ልምድ ያለው ቡድን ነው።

- እነሱን አሳንሰን መመልከት የለብንም ለእነሱ ክብር አለን ነገርግን በጥሩ አቋማችን ላይ ከሆንን ጨዋታውን የማሸነፍ ጥሩ እድል አለን።"ብሏል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
ኢትዮጵያን በኦሎምፒክ የሚወክሉ አትሌቶች ዛሬ ይለያሉ !

ዛሬ ምሽት በስፔን ኔርጃ ሀገራችን ኢትዮጵያን በቀጣዩ የፓሪስ ኦሎምፒክ ውድድር በ10,000 ሜትር የሚወክሉ አትሌቶችን ለመለየት የመምረጫ ውድድር እንደሚደረግ ተገልጿል።

ከምሽቱ የመምረጫ ውድድር በኋላ ኢትዮጵያን በፓሪስ ኦሎምፒክ ውድድር 10,000 ሜትር የሚወክሉ አትሌቶች ተለይተው ይታወቃሉ ተብሎ ይጠበቃል።

ከዚህ በተጨማሪም ዛሬ ምሽት የ800ሜ እና 1500ሜ ወንዶች የኦሎምፒክ ሚኒማ ለማሟላት የሙከራ ውድድሮች እንደሚደረጉ ታውቋል።

ውድድሮቹ ስንት ሰዓት ይደረጋሉ ?

ምሽት 2:25 - 800ሜ ወንዶች

ምሽት 2:40 - 10000ሜ ሴቶች

ምሽት 3:15 - 10000ሜ ወንዶች

ምሽት 3:50 - 1500 ወንዶች

ምንጭ :- ብዙአየሁ ዋጋው

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
#EURO2024

ተጠባቂው የ2024 አውሮፓ ዋንጫ ውድድር ዛሬ ምሽት 4:00 ሰዓት አዘጋጇ ሀገር ጀርመን ከስኮትላንድ ጋር በምታደርገው የመክፈቻ ጨዋታ ይጀመራል።

- በውድድሩ የስኮትላንድ ብሔራዊ ቡድን በአማካይ 28.2 እድሜ ትልቅ እድሜ ያለው ብሔራዊ ቡድን በመሆን የሚቀርብ ይሆናል።

- የቼክ ሪፐብሊክ ብሔራዊ ቡድን በበኩሉ በ25.3 አመት በአማካይ የውድድሩ ወጣት እድሜ ያለው የቡድን ስብስብ ይዞ የሚካፈሉ ይሆናል።

- የ 17ዓመቱ ስፔናዊው የባርሴሎና ተጨዋች ላሚን ያማል በውድድሩ ተሰልፎ የሚጫወት ከሆነ በአውሮፓ ዋንጫው ታሪክ በእድሜ ትንሹ ተጨዋች በመሆን አዲስ ታሪክ ይፅፋል።

- የ 41ዓመቱ ፖርቹጋላዊው ተከላካይ ፔፔ በውድድሩ ተሰልፎ የሚጫወት ከሆነ በአውሮፓ ዋንጫ ታሪክ በእድሜ ትልቁ ተጨዋች በመሆን አዲስ ሪከርድ ያስመዘግባል።

- ከፔፔ የተሻለ ግብ የማስቆጠር እድል ያለው ክርስቲያኖ ሮናልዶ በአውሮፓ ዋንጫው ታሪክ በትልቅ እድሜው ግብ ማስቆጠር የቻለ ተጨዋች መሆን ይችላል።

- ሮሜሎ ሉካኩ ለሀገሩ በሚያደርጋቸው ጨዋታዎች ከሌሎች ተጨዋቾች የበለጠ ግብ የማስቆጠር ሪከርድ አለው ሉካኩ በጨዋታ በአማካይ 0.74 ግብ ያስቆጥራል።

- የአውሮፓ ዋንጫውን ከሚያስተናግዱ የጀርመን ስታዲየሞች ግማሹ የጀርመን ሁለተኛ ሊግ ክለቦች መሆናቸው ተገልጿል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
TIKVAH-SPORT
በኢትዮጵያ የአፍሪካ ዋንጫን ለማዘጋጀት ቅድመ ዝግጅት መጀመሩ ተገለጸ !

ኢትዮጵያ በሚቀጥሉት አመታት የአፍሪካ ዋንጫ ውድድርን እንድታዘጋጅ በተያዘው እቅድ መሠረት የቅድመ ዝግጅት ስራዎች እየተከናወኑ መሆኑን የባህልና ስፖርት ሚኒስትር አቶ ቀጄላ መርዳሳ ገልጸዋል።

አቶ ቀጄላ መርዳሳ ከዚህ በፊት በሀገራችን ኢትዮጵያ የአፍሪካ ዋንጫን እ.ኤ.አ በ2029 ወይም በ2031 ለማዘጋጀት እየተሰራ መሆኑን ማስታወቃቸው አይዘነጋም።

አሁን ላይ ውድድሩን ለማዘጋጀት የሚያስችሉ የጥናት ስራዎች በመሰራት ላይ መሆናቸው የተገለፀ ሲሆን ውድድሩ በኢትዮጵያ ያለውን ታሪካዊ ዳራ በተጠበቀ መልኩ ለማዘጋጀት መታቀዱም ተነግሯል።

መሟላት ስለሚገባቸው ስታዲየሞች ያስረዱት ሚኒስትሩ ብሔራዊ ስታዲየም እና ባሕር ዳር ስታዲየምን ጨምሮ ሌሎች እንቅስቃሴዎች መጀመራቸውን ጠቁመዋል።

ምንጭ :- EBC

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
#EURO2024 🇩🇪

በአሰልጣኝ ጁሊያን ኔግልስማን የሚመራው የጀርመን ብሔራዊ ቡድን ዛሬ ምሽት ከስኮትላንድ ጋር በሀገሪቱ ሁለተኛ ግዙፍ ስታዲየም የባየር ሙኒኩ አሊያንዝ አሬና የአውሮፓ ዋንጫ መክፈቻ ጨዋታውን ያደርጋል።

አሰልጣኝ ጁሊያን ኔግልስማን ዶርትመንድን ለሻምፒየንስ ሊግ ፍፃሜ ያደረሱትን ማትስ ሁሜልስ እና ካሪም አዴይሚን ባልተጠበቀ መልኩ በስብሰባቸው ሳያካትቱ ለውድድሩ ቀርበዋል።

አሰልጣኙ በባየር ሙኒክ ቤት ያሰለጠኑት የመሐል ሜዳ ተጨዋቹ ሊዮን ጎሬዝካን እንዲሁ በስብስባቸው ውስጥ ያላከተቱ ሌላኛው ተጨዋች ነው።

ጁሊያን ኔግልስማን የመሐል ሜዳውን እንዲመሩ የብራይተኑን ፓስካል ግሮስ እና የባየር ሊቨርኩሰኑን ሮበርት አንድሪችን መርጠዋል።

አሰልጣኙ በተጨማሪም ቁልፍ በሆኑ የሜዳ ክፍሎች በቡንደስሊጋው ሁለተኛ ደረጃን ይዞ ካጠናቀቀው ስቱትጋርት ተከላኩዩን ዋልዴማር አንቶን እና የክንፍ ተጫዋቹን ክሪስ ፉሪች በስብሰባቸው አካተዋል።

የአውሮፓ ዋንጫው ውድድር ፍፃሜ ከአንድ ወር በኋላ በርሊን በሚገኘው የሀገሪቱ ግዙፍ ስታዲየም ኦሎምፒያስታዲዮን የሚደረግ ይሆናል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
2024/10/02 20:34:03
Back to Top
HTML Embed Code: