Telegram Web Link
መልካም ዕድል!
ከፍ የተደረጉ ኦዶችን አይተዋል ? እንግዲያውስ ተወራረዱባቸው!
Godoy Cruz - Rosario Central
ለተሻለ ውርርድ ቤቲካን ይጠቀሙ! አሁኑኑ Betika.et ላይ /በቴሌግራም ቦታችን - @BetikaETBot ይወራረዱ!
ሽመልስ በቀለ 1⃣8⃣ ገስት ሀውስ

በውቢቷ ሀዋሳ ቆይታዎ የት ለማረፍ አስበዋል ? ንፁህ እና በደንበኞቻችን ተወዳጅ በሆነው የእንግዳ ማረፊያችን መጥተው የእረፍት ጊዜውን ያሳልፉ።

እንግዶቻችንን ተቀበልን ለእይታ ሳቢ በሆነው የእንግዳ ማረፊያችን ማስተናገድ ከጀመርን አመታትን አስቆጥረናል።

አድራሻችን :- ሀዋሳ አርቴፍሻል ስታዲየም መንገድ ላይ ያገኙናል።

ለተጨማሪ መረጃ እና ለትዕዛዝዎ ይደውሉልን :- 0928684848

#ShemelesBekele18
" ኦስትሪያን አቅልለን መመልከት የለብንም "

የፈረንሳይ ብሔራዊ ቡድን የተከላካይ ስፍራ ተጨዋች ዳዮት አፕሜካኖ ቡድናቸው ከኦስትሪያ ጋር የሚያደርገው ጨዋታ አስቸጋሪ እንደሚሆን አውቆ እንዲዘጋጅ አሳስቧል።

ዳዮት አፕሜካኖ በንግግሩም " ኦስትሪያ ቀላል የሚባል ቡድን አይደለም በሜዳ ላይ ሁሉንም የሚሰጥ ቡድን ነው " ያለ ሲሆን ባለፉት ሰባት ጨዋታዎች አልተሸነፉም አስቸጋሪ ጨዋታ መጠበቅ አለብን ብሏል።

ፈረንሳይ የአውሮፓ ዋንጫ የመጀመሪያ ጨዋታዋን ከኦስትሪያ ጋር ሰኞ ምሽት 4:00 ሰዓት የምታደርግ ይሆናል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
የቫር ውሳኔ ማብራሪያ ለተመልካች ሊቀርብ ነው !

በቀጣዩ የ2024 ጀርመን አውሮፓ ዋንጫ ውድድር ላይ የሚተላለፉ የቫር ውሳኔዎች ለተመልካች ማብራሪያ እንደሚሰጥባቸው ተገልጿል።

በጨዋታዎቹ የሚተላለፉ የቫር ውሳኔዎች ማብራሪያ በስታዲየሙ በሚገኙ ስክሪኖች ለጨዋታው ተመልካቾች እንደሚገለጽ ተነግሯል።

በተጨማሪም ጨዋታውን በቴሌቪዥን ለሚከታተሉ ተመልካቾች በቀጥታ በቴሌቪዥን ማብራሪያው እንደሚቀርብ ተጠቁሟል።

ይህ ሂደት ጨዋታውን የሚከታተሉ ተመልካቾች ዳኛው ቫርን ተመልክተው የሚወስኑትን ውሳኔ በደንብ እንዲረዱ ያግዛል ተብሎ ይጠበቃል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
TIKVAH-SPORT
" በእግርኳስ ብዙ አመት አይቀረኝም " ሮናልዶ ፖርቹጋላዊው የፊት መስመር ተጨዋች ክርስቲያኖ ሮናልዶ በእግርኳስ ብዙ አመታት ስለማይቀሩት አሁን ላይ በሚያደርጋቸው ጨዋታዎች መደሰት እንደሚፈልግ ተናግሯል። ሮናልዶ በንግግሩም " በእግርኳስ ውስጥ ብዙ አመታት አይቀሩኝም ስለዚህ አሁን መደሰት አለብኝ ፣ ለእግርኳስ ልዩ ፍቅር አለኝ ሁሉም ጨዋታዎች ልዩ ናቸው። በአውሮፓ ዋንጫ ውድድር ፖርቹጋልን መወከል…
" መጨረሻው ሰዓት እየደረሰ መሆኑን አውቃለሁ " ሜሲ

አርጀንቲናዊው የፊት መስመር ተጨዋች ሊዮኔል ሜሲ የአሜሪካው ክለብ ኢንተር ሚያሚ ከዚህ በኋላ የመጨረሻው ክለብ እንደሚሆን በሰጠው አስተያየት ገልጿል።

" እግርኳስን ለመሰናበት ዝግጁ አይደለሁም " ያለው ሊዮኔል ሜሲ ህይወቴን ሁሉ ያሳለፍኩበት ነው መጫወት ልምምድ መስራት ሁልጊዜም የምወደው ነገር ነው " ሲል ተደምጧል።

ሊዮኔል ሜሲ ቀጥሎም " መጨረሻው ሰዓት እየደረሰ ስለመሆኑ ሁልጊዜም ፍርሀት አለኝ " ያለ ሲሆን ሰዓቱ እየደረሰ መሆኑን አውቃለሁ አሁን ጥሩ ጊዜ እያሳለፍኩ ነው ብሏል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
ጁቬንቱስ በይፋ አሰልጣኝ ሾመዋል !

በውድድር አመቱ መጨረሻ ከአሰልጣኝ ማሲሚላኖ አሌግሪ ጋር የተለያየው የጣልያኑ ክለብ ጁቬንቱስ አዲስ አሰልጣኝ በሀላፊነት መሾማቸውን ይፋ አድርገዋል።

ጁቬንቱስ የቀድሞ የቦሎኛ አሰልጣኝ ቲያጎ ሞታን በሶስት አመት ኮንትራት በሀላፊነት መሾማቸውን በይፋ አስታውቀዋል።

አሰልጣኝ ቲያጎ ሞታ ከሹመቱ በኋላ " እንደ ጁቬንቱስ ባለ ትልቅ ክለብ አዲስ ምዕራፍ በመጀመሬ ተደስቻለሁ እምነታቸውን ስለ ሰጡኝ አመሰግናለሁ እኔም ያለኝን ሁሉ እንደምሰጥ አረጋግጣለሁ " ብለዋል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
አስቶን ቪላ የኩቲንሆን ኮንትራት ሊያቋርጥ ነው !

አስቶን ቪላ የብራዚላዊውን የመሐል ሜዳ ተጨዋች ፊሊፔ ኩቲንሆ ኮንትራት ለማቋረጥ በንግግር ላይ መሆናቸው ተገልጿል።

ያለፈውን የውድድር አመት በውሰት በኳታሩ ክለብ አል ዱሀይሊ ያሳለፈው ፊሊፔ ኩቲንሆ በአስቶን ቪላ ቤት እስከ 2026 የሚያቆይ ኮንትራት አለው።

የ 32ዓመቱ ተጨዋች ፊሊፔ ኩቲንሆ በቀጣይ ወደ ቀድሞ ክለቡ የብራዚሉ ክለብ ቫስኮ ዳጋማ ለማምራት በንግግር ላይ መሆኑ ተዘግቧል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
TIKVAH-SPORT
" ከአለም ዋንጫ አውሮፓ ዋንጫ ከባድ ነው " ምባፔ የፈረንሳይ ብሔራዊ ቡድን አምበል እና አዲሱ የሪያል ማድሪድ ተጨዋች ኪሊያን ምባፔ የአውሮፓ ዋንጫ ውድድር ለማሸነፍ አስቸጋሪ መሆኑን በሰጠው አስተያየት ገልጿል። አንድ ጊዜ የአለም ዋንጫን ያሳካው ኪሊያን ምባፔ ሲናገርም " ከአለም ዋንጫ ውድድር ይልቅ የአውሮፓ ዋንጫ ውድድር ለማሸነፍ እጅግ አስቸጋሪ ነው።"በማለት ተናግሯል። ስለ ሪያል ማድሪድ…
" ምባፔ የአለም ሻምፒዮኖቹን አላካተተም " ሊዮኔል ሜሲ

አርጀንቲናዊው የስምንት ጊዜ ባሎን ዶር አሸናፊ ሊዮኔል ሜሲ ፈረንሳዊው ተጨዋች ኪሊያን ምባፔ በአለም ዋንጫ ውድድር ዙሪያ የሰጠው አስተያየት ትክክል አለመሆኑን ተናግሯል።

ፈረንሳዊው ተጨዋች ኪሊያን ምባፔ በቅርቡ በሰጠው አስተያየት የአውሮፓ ዋንጫ ውድድር ከአለም ዋንጫ ይልቅ ከባድ መሆኑን ተናግሮ ነበር።

ስለኪሊያን ምባፔ ንግግር አስተያየት የሰጠው ሊዮኔል ሜሲ " አውሮፓ ዋንጫ ጥሩ ውድድር ነው ነገርግን ሁሉም ራሱ የሚጫወትበትን ነው ከፍ የሚያደርገው።

ምባፔ አውሮፓ ዋንጫ የበለጠ ከባድ ነው ብሎ ሲናገር በርካታ የአለም ሻምፒዮን የደቡብ አሜሪካ ሀገራትን አሶጥቶ ነው ፣ ምርጥ ቡድኖች ያሉት በአለም ዋንጫ ነው።

ሁሉም የአለም ሻምፒዮን ሀገራት የሚገኙት እዛ ነው ሁሉም ሰው አለም ዋንጫን ማሸነፍ የሚፈልገውም ለዚሁ ነው።"ሲል ተደምጧል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
Forwarded from HEY Online Market
Play More and Spend less!

•PS4 Slim, 34,999 Birr
•PS4 PRO, 41,999 Birr
•Original Controller 6,499 Birr

Contact Us
0953964175 @heymobile

@heyonlinemarket
ሽመልስ በቀለ 1⃣8⃣ ገስት ሀውስ

በውቢቷ ሀዋሳ ቆይታዎ የት ለማረፍ አስበዋል ? ንፁህ እና በደንበኞቻችን ተወዳጅ በሆነው የእንግዳ ማረፊያችን መጥተው የእረፍት ጊዜውን ያሳልፉ።

እንግዶቻችንን ተቀበልን ለእይታ ሳቢ በሆነው የእንግዳ ማረፊያችን ማስተናገድ ከጀመርን አመታትን አስቆጥረናል።

አድራሻችን :- ሀዋሳ አርቴፍሻል ስታዲየም መንገድ ላይ ያገኙናል።

ለተጨማሪ መረጃ እና ለትዕዛዝዎ ይደውሉልን :- 0928684848

#ShemelesBekele18
" ዋንጫውን ማሳካት እንፈልጋለን " ኮማን

የኔዘርላንድ ብሔራዊ ቡድን ዋና አሰልጣኝ ሮናልድ ኮማን ቡድናቸው የአውሮፓ ዋንጫ ውድድሩን ማሸነፍ እንደሚፈልግ በሰጡት አስተያየት ተናግረዋል።

አሰልጣኝ ሮናልድ ኮማን በንግግራቸውም " የአውሮፓ ዋንጫውን ማሸነፍ እንፈልጋለን የምናሳካ ከሆነ ስኬታማ ውድድር ይሆንልናል የማናሳካው ከሆነ ለእኛ ስኬታማ አይሆንም።"ሲሉ ተደምጠዋል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
በአውሮፓ ዋንጫው ማን ብዙ ተጨዋች ያሳትፋሉ ?

በነገው ዕለት በሚጀምረው የ2024 የጀርመን አውሮፓ ዋንጫ ውድድር የእንግሊዝ ፕርሚየር ሊግ ዘጠና ስድስት ተጨዋቾችን በማሳተፍ ቀዳሚው ሊግ መሆን ችሏል።

በክለቦች ደረጃ የጣልያን ሴርያ አሸናፊው ክለብ ኢንተር ሚላን እና የፕርሚየር ሊጉ አሸናፊ ማንችስተር ሲቲ አስራ አራት ተጨዋቾችን ለውድድሩ በመላክ በቀዳሚነት መቀመጥ ችለዋል።

ብዙ ተጨዋቾች ያሳተፉ ሊጎች የትኞቹ ናቸው ?

- የእንግሊዝ ፕርሚየር ሊግ :- 96 ተጨዋቾች

- የጣልያን ሴርያ :- 92 ተጨዋቾች

- የጀርመን ቡንደስሊጋ :- 75 ተጨዋቾች

- የስፔን ላሊጋ :- 57 ተጨዋቾች

- የፈረንሳይ ሊግ :- 29 ተጨዋቾች

- የቱርክ ሱፐር ሊግ :- 26 ተጨዋቾች

ብዙ ተጨዋቾች ያሳተፉ ክለቦች የትኞቹ ናቸው ?

- ኢንተር ሚላን :- 14 ተጨዋቾች

- ማንችስተር ሲቲ :- 14 ተጨዋቾች

- ሪያል ማድሪድ :- 13 ተጨዋቾች

- ባርሴሎና :- 11 ተጨዋቾች

- ፒኤስጂ :- 11 ተጨዋቾች

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
ዳኛን ማነጋገር የሚችለው የትኛው ተጨዋች ነው ?

በነገው ዕለት በሚጀምረው የጀርመን አውሮፓ ዋንጫ ውድድር የመሐል ዳኛውን ማነጋገር የሚችሉት የብሔራዊ ቡድን አምበሎች ብቻ መሆናቸው ተገልጿል።

ሌሎች ተጨዋቾች ዳኛውን ለማነጋገር እንደማይችሉ እና ለማነጋገር የሚሞክሩ ከሆነ እንዲሁም አላስፈላጊ ባህሪ ሲያሳዩ ከተስተዋሉ የማስጠንቀቂያ ካርድ እንደሚመለከቱ ተነግሯል።

የብሔራዊ ቡድኑ አምበል ግብ ጠባቂ የሚሆን ከሆነ በሜዳ ውስጥ ዳኛውን ማነጋገር የሚችል ተጨዋች እንደሚመረጥ ተዘግቧል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
#EURO2024

በቀጣዩ የ2024 የጀርመን አውሮፓ ዋንጫ ውድድር ሀምሳ ስምንት የአፍሪካ የዘር ሀረግ ያላቸው ተጨዋቾች በተለያዩ ብሔራዊ ቡድኖች ተሰልፈው በውድድሩ ይጫወታሉ።

በፈረንሳይ ብሔራዊ ቡድን ታላላቅ ተጨዋቾቿን ጨምሮ አስራ አራት ተጨዋቾቿ የአፍሪካ የዘር ሀረግ ያላቸው መሆናቸው ተገልጿል።

በተጨማሪም የቤልጅየም ብሔራዊ ቡድን ዘጠኝ ተጨዋቾቹ የዘር ሀረጋቸው ከአፍሪካ የሚመዘዝ መሆኑ ተነግሯል።

እንዲሁም ስዊዘርላንድ ( ስምንት ) ፣ እንግሊዝ ( ስድስት ) ፣ ጀርመን ( አምስት ) ፣ ኔዘርላንድ ( አራት ) ፣ ፖርቹጋል ( አራት ) ፣ ጣልያን ( ሁለት ) ፣ ስፔን ( ሁለት ) ተጨዋቾችን ያሳትፋሉ።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
ዋልያዎቹ የምድብ ተጋጣሚያቸውን መቼ ያውቃሉ ?

በሞሮኮ አዘጋጅነት ለሚካሄደው የ 2025 አፍሪካ ዋንጫ ውድድር የማጣርያ ጨዋታ ምድብ ድልድል የሚካሄድበት ቀን ታውቋል።

ብሔራዊ ቡድኖች የምድብ ተጋጣሚያቸውን ሐሙስ ሰኔ 27/2016 ዓ.ም በደቡብ አፍሪካ ጆሀንስበርግ በሚደረገው የእጣ ማውጣት ስነ ስርዓት እንደሚያውቁ ይፋ ተደርጓል።

በምድብ ድልድሉ የቅድመ ማጣሪያውን ያለፉ አራት ሀገራትን ጨምሮ አርባ ስምንት ብሔራዊ ቡድኖች እንደሚካተቱ ተገልጿል።

በአስራ ሁለት ምድብ ተክፈለው የማጣሪያ ጨዋታቸውን የሚያደርጉት ብሔራዊ ቡድኖቹ የምድብ አንደኛ እና ሁለተኛ የመጀመሪያ ሀያ አራት ቡድኖች ለአፍሪካ ዋንጫው የሚያልፉ ይሆናል።

የማጣሪያ ጨዋታዎቹ ከሚቀጥለው አመት መስከረም ወር ጀምሮ መካሄዳቸውን እንደሚጀምሩ ተጠቁሟል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
TIKVAH-SPORT
ኤሲ ሚላን ከአሰልጣኙ ጋር ተለያየ ! የጣልያን ሴርያው ክለብ ኤሲ ሚላን በውድድር አመቱ መጨረሻ ከአሰልጣኝ ስቴፋኖ ፒዮሊ ጋር ለመለያየት መወሰኑን በይፋ አስታውቋል። አሰልጣኝ ስቴፋኖ ፒዮሊ ኤሲ ሚላን ነገ በስታዲዮ ጁሴፔ ሜዛ ከሳለርኒታና ጋር በሚያደርገው የሊግ የመጨረሻ ሳምንት መርሐ ግብር ክለቡን ይሰናበታሉ። ከ 2019 ጀምሮ ኤሲ ሚላንን በሀላፊነት የመሩት አሰልጣኝ ስቴፋኖ ፒዮሊ ክለቡን የሴርያ…
ኤሲ ሚላን በይፋ አሰልጣኝ ሾመ !

በውድድር አመቱ መጨረሻ ከአሰልጣኝ ስቴፋኖ ፒዮሊ ጋር የተለያየው የጣልያን ሴርያው ክለብ ኤሲ ሚላን አሁን ላይ አዲስ አሰልጣኝ መሾማቸውን ይፋ አድርገዋል።

ኤሲ ሚላን ፖርቹጋላዊውን የቀድሞ የሊል እና ሮማ አሰልጣኝ የነበሩትን ፓውሎ ፎንሴካን በሀላፊነት መሾማቸውን በይፋ አስታውቀዋል።

ፖርቹጋላዊው አሰልጣኝ ፓውሎ ፎንሴካ ኤሲ ሚላንን ለሚቀጥሉት ሶስት የውድድር አመታት ለማሰልጠን ፊርማቸውን ማኖራቸው ተገልጿል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
አሰልጣኝ ኤዲን ቴርዚች ከሀላፊነታቸው ለቀቁ !

ጀርመናዊው የቡንደስሊጋው ክለብ ቦርስያ ዶርትመንድ ዋና አሰልጣኝ ኤዲን ቴርዚች ከክለቡ አሰልጣኝነታቸው መልቀቃቸው ይፋ ተደርጓል።

አሰልጣኝ ኤዲን ቴርዚች ከቦርስያ ዶርትመንድ ጋር በጋራ ስምምነት መለያየታቸውን በይፋ አስታውቀዋል።

የ 41ዓመቱ አሰልጣኝ ኤዲን ቴርዚች ቦርስያ ዶርትመንድን እየመሩ የዘንድሮው የአውሮፓ ሻምፒየንስ ሊግ ፍፃሜ ተፋላሚ እንደነበሩ ይታወሳል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
ሮቤርቶ ዲ ዘርቢ ወደ ማርሴይ ሊያመሩ ነው !

ጣልያናዊው የቀድሞ የብራይተን አሰልጣኝ ሮቤርቶ ዲ ዘርቢ የፈረንሳዩን ክለብ ኦሎምፒክ ማርሴይ ለመረከብ ንግግር ላይ መሆናቸው ተገልጿል።

አሰልጣኝ ሮቤርቶ ዲ ዘርቢ ከማርሴይ የሶስት አመት ኮንትራት እንደቀረበላቸው ተነግሯል።

አሰልጣኙ ማርሴይን ለመረከብ አሁን ላይ ሙሉ ስምምነት ላይ ባይደርሱም ንግግሮች በጥሩ መልኩ መቀጠላቸው ተዘግቧል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
ዌስትሀም ዩናይትድ ተጨዋች አስፈርመዋል !

ዌስትሀም ዩናይትድ ብራዚላዊውን የመሐል ሜዳ ተጨዋች ሉዊስ ጉልሄርሜ ከፓልሜይራስ ማስፈረማቸውን ይፋ አድርገዋል።

የ 18ዓመቱ ተጨዋች ሉዊስ ጉልሄርሜ ለዌስትሀም ዩናይትድ ለአንድ ተጨማሪ አመት የመቆየት አማራጭ ያካተተ የአምስት አመት ኮንትራት መፈረሙ ተገልጿል።

ዌስትሀም ዩናይትድ ለተጨዋቹ ዝውውር 30 ሚልዮን ዩሮ የዝውውር ሒሳብ ማውጣታቸው ተገልጿል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
Forwarded from WANAW SPORT
🔥 #እንዳያመልጥዎ፣ ይዘዙን!

📌 ለበለጠ መረጃና ትዕዛዝ 📲 09011382830910851535 እና 0913586742 ላይ ይደውሉ።

👉🏾 እንዲሁም በቴሌግራም @Wanawsales ላይ የሽያጭ ሰራተኞቻችንን በቀጥታ በማናገር ይዘዙን።

Instagram | Facebook | TikTok

🏅 ዋናው ወደፊት...

@wanawsportwear
2024/09/30 20:20:00
Back to Top
HTML Embed Code: