Telegram Web Link
🚀 የአቪዬተር ሻሞ - በረራ በነጻ! 🤩

⭐️የአቪዬተር ሻሞ ሽጦታዎች ዛሬም ቀጥለዋል!

💸እስከ 4ሺብር ዋጋ ያላቸው ነጻ የመወራረጃ እጣዎች እርስዎን እየጠበቁ ነው።

አሁኑኑ የራስዎ ያርጓቸው - 👉ln.run/k_QQW
ቤቲካ - የአሸናፊዎች ቤት!"
ላውረንት ኮስሎኒ በሀላፊነት ተሾሟል !

ከአመት በፊት በይፋ ራሱን ከፕሮፌሽናል እግርኳስ ያገለለው የቀድሞ ፈረንሳዊ የተከላካይ ስፍራ ተጨዋች ላውረንት ኮስሎኒ በአዲስ ሀላፊነት መሾሙ ተገልጿል።

የቀድሞ የሰሜን ለንደኑ ክለብ አርሰናል ተከላካይ ላውረንት ኮስሎኒ የፈረንሳዩ ክለብ ሎርየንት ስፖርቲንግ ዳይሬክተር በመሆን በሀላፊነት መሾሙ ይፋ ተደርጓል።

የ 38ዓመቱ ላውረንት ኮስሎኒ ከዚህ በፊት የሎርየንት ታዳጊ ቡድንን በማሰልጠን ላይ ይገኝ ነበር።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
ኢንተር ሚላን የተጫዋቹን ውል አራዝሟል !

የጣልያን ሴርያው ክለብ ኢንተር ሚላን የመሐል ሜዳ ተጨዋቻቸው ኒኮሎ ባሬላን ኮንትራት ለተጨማሪ አመታት ማራዘማቸውን ይፋ አድርገዋል።

የ 27ዓመቱ የመሐል ሜዳ ተጨዋች ኒኮሎ ባሬላ በኢንተር ሚላን ቤት ለተጨማሪ አምስት አመታት መቆየት የሚያስችለውን ኮንትራት መፈረሙ ይፋ ሆኗል።

ጣልያናዊው ተጨዋች ኒኮሎ ባሬላ በአዲሱ ኮንትራት በአመት ሰባት ሚልዮን ዩሮ የሚደርስ ክፍያ እንደሚያገኝ ተገልጿል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
ክርስቲያኖ ሮናልዶ አዲስ ታሪክ ፅፏል !

ፖርቹጋል ከአየርላንድ ጋር ያደረገችውን የወዳጅነት ጨዋታ 3ለ0 በሆነ ውጤት ስታሸንፍ ክርስቲያኖ ሮናልዶ ሁለት ግቦችን እንዲሁም ጇ ፊሊክስ ቀሪውን ጎል አስቆጥረዋል።

ፖርቹጋላዊው የፊት መስመር ተጨዋች ክርስቲያኖ ሮናልዶ በተከታታይ ለሀያ አንድ አመታት ለብሔራዊ ቡድኑ ግብ ማስቆጠር የቻለ በታሪክ የመጀመሪያው ተጨዋች መሆን ችሏል።

ክርስቲያኖ ሮናልዶ እ.ኤ.አ. ከ2004 ጀምሮ ላለፉት ሀያ አንድ አመታት በየአመቱ ለፖርቹጋል ብሔራዊ ቡድን ግቦችን ማስቆጠር ችሏል።

ሮናልዶ ለፖርቹጋል ብሔራዊ ቡድን ያስቆጠራቸውን ግቦች አንድ መቶ ሰላሳ ማድረስ ችሏል።

ክርስትያኖ ሮናልዶ በዘንድሮው የውድድር አመት ባደረጋቸው ሀምሳ ስምንት ጨዋታዎች ሀምሳ ሰባት ግቦችን አስቆጥሯል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
TIKVAH-SPORT
ዩናይትድ በሚቀጥለው ሳምንት ግምገማ ያደርጋል ! የኤፌ ካፕ ዋንጫን ያሳካው ማንችስተር ዩናይትድ በሚቀጥለው ሳምንት የድህረ የውድድር ዘመን ግምገማ ለማድረግ እቅድ መያዛቸው ተገልጿል። ክለቡ በአሰልጣኝ ኤሪክ ቴንሀግ የወደፊት ቆይታ ዙሪያ የመጨረሻ ውሳኔ ከማሳለፉ በፊት አሰልጣኙ የሰሩትን ስራ ለመገምገም ማሰቡ ተነግሯል። አሰልጣኙ ከኤፌ ካፕ ዋንጫ ድላቸው በኋላ በሰጡት አስተያየት ጨዋታው የመጨረሻቸው…
ኤሪክ ቴንሀግ በዩናይትድ ቤት ይቆያሉ !

ኔዘርላንዳዊው አሰልጣኝ ኤሪክ ቴንሀግ በሚቀጥለው የውድድር አመት በማንችስተር ዩናይትድ ቤት እንደሚቀጥሉ ተገልጿል።

ማንችስተር ዩናይትድ ካደረገው የድህረ ውድድር አመት ግምገማ በኋላ አሰልጣኝ ኤሪክ ቴንሀግ በክለቡ እንዲቀጥሉ ከውሳኔ መድረሱ ተዘግቧል።

በሚቀጥለው አመት ውላቸው የሚጠናቀቀው አሰልጣኝ ኤሪክ ቴንሀግ በበኩላቸው የክለቡን ውሳኔ መቀበላቸው እና በሀላፊነት ለመቀጠል መስማማታቸው ተነግሯል።

በተጨማሪም ማንችስተር ዩናይትድ የአሰልጣኝ ኤሪክ ቴንሀግን ኮንትራት ለተጨማሪ አመታት ለማራዘም በዛሬው ዕለት ንግግር መጀመራቸው ተገልጿል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
❇️SMART ያልሆኑ TVዎን  SMART ለማረግ  ምን መግዛት እንዳለብዎ ካላወቁ  ይሄን እቃ ምርጫው ያድርጉ

❇️የራሱ የሆነ BLUETOOTH ሪሞት ያለው
ትክክለኛ 4K ምስል ጥራት ያለው

❇️የለያዩ የፊል የኳስ ቻናሎች እላዩ ላይ የተጫነበት በአጭር ጊዜ በሚቋይ ቅናሽ
3200 ብር ብቻ

Inbox Us 📩Admin @Sadikethio
Call 📱 +251 91 178 5693

የተለያዩ ነፃ የኳስ ቻናሎች የሚያገኙበት የዲሽ ቻናል 👇👇 https://www.tg-me.com/joinchat-AAAAAEnaa5LpZrcwQ-E0Tw
Forwarded from HEY Online Market
Play More and Spend less!

•PS4 Slim, 34,999 Birr
•PS4 PRO, 41,999 Birr
•Original Controller 6,499 Birr

Contact Us
0953964175 @heymobile

@heyonlinemarket
ሊቨርፑል ምን አይነት ተጨዋች ሊያስፈርም ይችላል ?

አሰልጣኝ አርኔ ስሎትን በሀላፊነት የሾመው የመርሲሳይዱ ክለብ ሊቨርፑል በዚህ ክረምት የዝውውር መስኮት ለማስፈረም ቅድሚያ የሚሰጠው ለመሐል ተከላካይ መሆኑ ተገልጿል።

ሊቨርፑሎች በመቀጠልም የፊት መስመራቸውን ለማጠናከር ጥሩ የአጥቂ ስፍራ ተጨዋች የሚያገኙ ከሆነ ለማስፈረም እንደሚሰሩ ተነግሯል።

በሌላ በኩል ሊቨርፑል በቅድመ ውድድር ዝግጅት ወቅት ተጨማሪ የወዳጅነት ጨዋታዎችን ለማድረግ ማቀዳቸው ሲገለፅ ከአሜሪካ ጉዞ በኋላ አንፊልድ ላይ ለመጫወት ማሰባቸው ተጠቁሟል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
" በእግርኳስ ብዙ አመት አይቀረኝም " ሮናልዶ

ፖርቹጋላዊው የፊት መስመር ተጨዋች ክርስቲያኖ ሮናልዶ በእግርኳስ ብዙ አመታት ስለማይቀሩት አሁን ላይ በሚያደርጋቸው ጨዋታዎች መደሰት እንደሚፈልግ ተናግሯል።

ሮናልዶ በንግግሩም " በእግርኳስ ውስጥ ብዙ አመታት አይቀሩኝም ስለዚህ አሁን መደሰት አለብኝ ፣ ለእግርኳስ ልዩ ፍቅር አለኝ ሁሉም ጨዋታዎች ልዩ ናቸው።

በአውሮፓ ዋንጫ ውድድር ፖርቹጋልን መወከል የተለየ ኮራት ይሰማሃል በሀያ እድሜዎች ላይ እንዳለሁ ሁሉ አሁንም ህልሜ ነው።"ሲል ተደምጧል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
በእንግሊዝ ጨዋታ አነስተኛ አልኮል ያለው መጠጥ ይቀርባል !

የእንግሊዝ ብሔራዊ ቡድን በአውሮፓ ዋንጫው መጀመሪያ እሁድ ከሰርቢያ ጋር በሚያደርገው ጨዋታ በስታዲየሙ አነስተኛ የአልኮል መጠን ያለው መጠጥ እንደሚቀርብላቸው ተገልጿል።

በውድድሩ ከሚደረጉት ጨዋታዎች ሁሉ አነስተኛ የአልኮል መጠን ያለው መጠጥ የሚቀርብበት ብቸኛው ጨዋታ እንደሚሆንም ተነግሯል።

ይህ የሆነው 40,000 ገደማ የእንግሊዝ ብሔራዊ ቡድን ደጋፊዎች ይታደማሉ ተብሎ በሚጠበቅበት ጨዋታ ከተቃራኒ ደጋፊዎች ጋር አለመግባባት ይፈጠራል በሚል ፍራቻ መሆኑ ተዘግቧል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
" በውድድሩ አሻራዬን ማስቀመጥ እፈልጋለሁ " ምባፔ

የፈረንሳይ ብሔራዊ ቡድን አምበል ኪሊያን ምባፔ ቡድናቸው በበቀጣዩ የአውሮፓ ዋንጫ ውድድር ታሪክ ለመፃፍ ጀርመን መድረሱን በሰጠው አስተያየት ተናግሯል።

" በአውሮፓ ዋንጫው አሻራዬን ሜዳ ላይ ማስቀመጥ እፈልጋለሁ " የሚለው ኪሊያን ምባፔ ታሪክ ለመፃፍ ጀርመን ደርሰናል ምን ማድረግ እንዳለብን እናውቃለን ለውድድሩ ዝግጁ ነን በማለት ተናግሯል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
✈️ አውሮፓ እንሂድ

🏆 የአውሮፓ ታላላቅ ተጫዋቾች ለሃገራችው ዋንጫ ለማሸነፍ ጉዞ ወደ ጀርመን ጀምረዋል!

በጀርመን የሚደረጉትን ደማቅ ጨዋታዎች በቀጥታ በዲኤስቲቪ ሱፐርስፖርት በወር ከ350 ብር ጀምሮ በጎጆ ፓኬጅ ይከታተሉ!

የዲኤስቲቪ ዲኮደር በ1,999 ብር ከ1 ወር ነፃ ሜዳ ፓኬጅ ጋር ያገኛሉ።

የዲኤስቲቪ አገልግሎቶችን ለማግኘት ከታች ያለውን የMyDStv Telegram bot ሊንክ ይጫኑ!
👇
https://bit.ly/3XdLqsP

#Euro2024 #ሁሉምያለውእኛጋርነው #DStvEthiopia
Forwarded from WANAW SPORT
📯 አስቀድመው ተዘጋጅተው የሚወስዷቸው ማልያዎች ከ #ዋናው!

🏃🏾‍♂ #ይዘዙን፣ አማራጩን ይጠቀሙ!

📌 ለበለጠ መረጃና ትዕዛዝ 📲 09011382830910851535 እና 0913586742 ላይ ይደውሉ።

👉🏾 እንዲሁም በቴሌግራም @Wanawsales ላይ የሽያጭ ሰራተኞቻችንን በቀጥታ በማናገር ይዘዙን።

Instagram | Facebook | TikTok

🏅 ዋናው ወደፊት...

@wanawsportwear
ፈርናንዶ ሳንቶስ በሀላፊነት ተሾመዋል !

ፖርቹጋላዊ አሰልጣኝ ፈርናንዶ ሳንቶስ የ አዘርባጃን ብሔራዊ ቡድን ዋና አሰልጣኝ በመሆን በሀላፊነት መሾማቸው ይፋ ተደርጓል።

የ 69ዓመቱ አሰልጣኝ ፈርናንዶ ሳንቶስ በቅርቡ ከቱርኩ ክለብ ቤሺክታሽ አሰልጣኝነታቸው መሰናበታቸው አይዘነጋም።

ከፖርቹጋል ብሔራዊ ቡድን ሀላፊነታቸው መነሳት በኋላ የፖላንድ ብሔራዊ ቡድን እና ቤሺክታሽ አሰልጣኝ በመሆን ተሾመው የነበሩት አሰልጣኝ ፈርናንዶ ሳንቶስ በሀላፊነት ብዙም ሳይቆዩ ተሰናብተዋል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
የአውሮፓ ዋንጫውን መክፈቻ ጨዋታ ማን ይመራዋል ?

የፊታችን አርብ የሚደረገውን ተጠባቂ የ2024 አውሮፓ ዋንጫ ውድድር መክፈቻ ጨዋታ የሚመሩት ዳኛ ታውቀዋል።

በጀርመን እና ስኮትላንድ ብሔራዊ ቡድኖች መካከል የሚደረገውን ተጠባቂ ጨዋታ ፈረንሳዊው ዳኛ ክሌመንት ቱርፒን በመሐል ዳኝነት እንደሚመሩት ይፋ ሆኗል።

የመክፈቻ ጨዋታው አርብ ምሽት 4:00 ሰዓት በባየር ሙኒኩ ፉባል አሬና ስታዲየም የሚደረግ ይሆናል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
አርሰናል ወጣት ተጨዋች ሊያስፈርም ነው !

የሰሜን ለንደኑ ክለብ አርሰናል ወጣቱን እንግሊዛዊ የፊት መስመር አጥቂ ሪያን ማክአይዶን ከቼልሲ ለማስፈረም ጥያቄ ማቅረባቸው እና ዝውውሩን እያጠናቀቁ እንደሚገኙ ተገልጿል።

የ 16ዓመቱ አጥቂ ሪያን ማክአይዶ በክረምቱ የተጨዋቾች የዝውውር መስኮት ቼልሲን ይለቃል ተብሎ እንደሚጠበቅ ተነግሯል።

ተጨዋቹ አሁን ላይ በእንግሊዝ ከ 17ዓመት በታች ብሔራዊ ቡድን ውስጥ በመሳተፍ ላይ ይገኛል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
" ያነጋገረኝ ክለብ እንኳን ባለመኖሩ አዝኛለሁ " ሳሪ

ከላዚዮ ጋር ከተለያዩ በኋላ ያለ ሀላፊነት የሚገኙት ጣልያናዊው አሰልጣኝ ማውሪዝዮ ሳሪ በዚህ ክረምት ምንም የጣልያን ክለብ ለአሰልጣኝነት እንዳልፈለጋቸው ገልፀዋል።

" ከጣልያን ክለቦች ምንም አይነት የአሰልጣኝነት ጥያቄ ስላልቀረበልኝ ትንሽ አዝኛለሁ " ያሉት አሰልጣኝ ማውሪዝዮ ሳሪ " ለማነጋገር እንኳን የፈለገ ክለብ የለም ይህ እንኳን ይገባኝ ነበር ብለዋል።

አሰልጣኝ ማውሪስዮ ሳሪ በንግግራቸው በዚህ አመት ኤስ ሚላን ወይም ፊዮረንቲናን የማሰልጠን ፍላጎት እንደነበራቸው ተናግረዋል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
ኤምሪ ቻን ለብሔራዊ ቡድኑ ጥሪ ቀርቦለታል !

የጀርመን ብሔራዊ ቡድን የመሐል ሜዳ ተጨዋች አሌክሳንደር ፓቭሎቪች በጉዳት ምክንያት ከቀጣዩ የአውሮፓ ዋንጫ ውድድር ውጪ ሆኗል።

በምትኩም የቦርስያ ዶርትመንዱ የመሐል ሜዳ ተጨዋች ኤምሪ ቻን ለጀርመን ብሔራዊ ቡድን ጥሪ ቀርቦለታል።

የጀርመን ብሔራዊ ቡድን የውድድሩ መክፈቻ ጨዋታውን አርብ ምሽት 4:00 ከስኮትላንድ አቻው ጋር የሚያደርግ ይሆናል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
የፖርቹጋል ልምምድ ትኬቶች ለሽያጭ ቀረቡ !

የፖርቹጋል ብሔራዊ ቡድን የአውሮፓ ዋንጫ ውድድሩን ከመጀመሩ አስቀድሞ ጀርመን የሚያደርገውን ልምምድ ለመታደም በርካታ ተመልካቾች ጥያቄ ማቅረባቸው ተገልጿል።

የብሔራዊ ቡድኑን ልምምድ ለመመልከት ለህዝብ የቀረቡ 6,000 ነፃ ትኬቶች በአንድ ደቂቃ ውስጥ ለተመልካች ደርሰው መጠናቀቃቸው ተነግሯል።

የፖርቹጋል ብሔራዊ ቡድን የፊታችን አርብ ጀርመን ውስጥ የሚያደርገውን ልምምድ ለመከታተል ከ50,000 በላይ ጥያቄዎች መቅረባቸው ተዘግቧል።

አሁን ላይ አስቀድመው የነፃ ትኬቶችን ያገኙ ተመልካቾች የልምምድ መግቢያ ትኬቶቹን በበይነ መረብ እስከ 1,000 ዩሮ እየሸጡ እንደሚገኙ ተገልጿል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
TIKVAH-SPORT
ቶተንሀም ከተጫዋቹ ጋር ሊለያይ ነው ! የሰሜን ለንደኑ ክለብ ቶተንሀም ከፈረንሳዊው አማካይ ታንጎይ ንዶምቤሌ ጋር ያላቸውን ኮንትራት ለማቋረጥ በንግግር ላይ መሆናቸው ተገልጿል። ያለፈውን የውድድር አመት በውሰት በቱርኩ ክለብ ጋላታሳራይ ያሳለፈው ታንጎይ ንዶምቤሌ በቶተንሀም ቤት የአንድ አመት ውል ይቀረዋል። የ 27ዓመቱ ተጨዋች ታንጎይ ንዶምቤሌ ከአምስት አመታት በፊት ከፈረንሳዩ ክለብ ሊዮን በ55…
ቶተንሀም ከተጫዋቹ ጋር በይፋ ተለያየ !

ቶተንሀም ከፈረንሳዊው የመሐል ሜዳ ተጨዋች ታንጎይ ንዶምቤሌ ጋር ያላቸውን ኮንትራት በስምምነት ማቋረጣቸውን ይፋ አድርገዋል።

ያለፈውን የውድድር አመት በውሰት በቱርኩ ክለብ ጋላታሳራይ ቤት ያሳለፈው ታንጎይ ንዶምቤሌ በቶተንሀም ቤት የአንድ አመት ውል ይቀረው ነበሩ።

የ 27ዓመቱ ተጨዋች ታንጎይ ንዶምቤሌ ከአምስት አመታት በፊት ከፈረንሳዩ ክለብ ሊዮን በ55 ሚልዮን ፓውንድ ቶተንሀምን መቀላቀሉ አይዘነጋም።

@tikvahethsport      @kidusyoftahe
2024/09/30 22:14:59
Back to Top
HTML Embed Code: