Telegram Web Link
አስቶን ቪላ ከቼልሲ ጋር ንግግር ጀመረ !

የአውሮፓ ሻምፒየንስ ሊግ ተሳታፊው ክለብ አስቶን ቪላ እንግሊዛዊውን የሰማያዊዎቹ የመሐል ሜዳ ተጨዋች ኮነር ጋላገር ለማስፈረም ከቼልሲ ንግግር መጀመራቸው ተገልጿል።

የምዕራብ ለንደኑ ክለብ ቼልሲ በክረምት የዝውውር መስኮት ተጫዋቹን በቋሚ ዝውውር ለመሸጥ ዝግጁ መሆኑ ተነግሯል።

አሰልጣኝ ኡናይ ኤምሬ የ 24ዓመቱ ተጨዋች ኮነር ጋላገር አድናቂ መሆናቸው የተገለፀ ሲሆን በቀጣይ ለማስፈረም ቅድሚያ ሰጥተው እንደሚሰሩ ተዘግቧል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
አርሰናል ከተጨዋቹ ጋር ሊለያይ ይችላል !

የሰሜን ለንደኑ ክለብ አርሰናል በክረምቱ የተጨዋቾች የዝውውር መስኮት ጥሩ ሒሳብ የሚቀርብለት ከሆነ ፖላንዳዊውን የመስመር ተጨዋች ያኩብ ኪውዮርን ሊሸጥ እንደሚችል ተገልጿል።

የጣልያን ሴርያው ክለብ ኤሲ ሚላን የ 24ዓመቱ ፖላንዳዊ የመስመር ተጨዋች ያኩብ ኪውዮር ፈላጊ መሆናቸው ተዘግቧል።

ፖላንዳዊው ተጨዋች ያኩብ ኪውዮር ከአመት በፊት ከጣልያኑ ክለብ ስፔዚያ አርሰናልን መቀላቀሉ ይታወሳል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
TIKVAH-SPORT
አርሰናል በቀጣይ ምን ማስፈረም ይፈልጋል ? የሰሜን ለንደኑ ክለብ አርሰናል በክረምቱ የተጨዋቾች የዝውውር መስኮት የፊት መስመራቸውን ለማጠናከር አጥቂ ለማስፈረም በዝግጅት ላይ መሆናቸው ተገልጿል። በተጨማሪም መድፈኞቹ የግራ መስመር ተጨዋች ለማስፈረም እየተመለከቱ መሆኑ ሲዘገብ ሶስተኛ ግብ ጠባቂም ለማስፈረም ከሚመለከቱት የሜዳ ክፍል አንዱ መሆኑ ተነግሯል። አርሰናል በቀጣይ ለማስፈረም የሚመለከተው…
የአርሰናል ባለቤቶች ለዝውውር ትልቅ ገንዘብ ያቀርባሉ !

የተጠናቀቀው የ2023/24 የውድድር ዘመን ለሰሜን ለንደኑ ክለብ አርሰናል ከሜዳው ውጪ ሌላኛው አትራፊ አመት እንደነበር ተገልጿል።

መድፈኞቹ በውድድር አመቱ በሊጉ ሁለተኛ ደረጃን ይዘው ሲያጠናቅቁ በአውሮፓ ሻምፒየንስ ሊግ ውድድር ሩብ ፍፃሜ መድረሳቸውም አይዘነጋም።

አርሰናሎች በተጠናቀቀው የውድድር አመት ከአውሮፓ ሻምፒየንስ ሊግ ውድድር ብቻ ከ90 ሚልዮን ዩሮ በላይ ገቢ ማግኘታቸው ተነግሯል።

ይህንንም ተከትሎ የመድፈኞቹ ባለቤቶች በዚህ ክረምት ቡድኑን ለማጠናከር ትልቅ የዝውውር ገንዘብ ያዘጋጃሉ ተብሎ እንደሚጠበቅ ተዘግቧል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
TIKVAH-SPORT
ቼልሲ ተጨዋች ለማስፈረም ተቃርበዋል ! የምዕራብ ለንደኑ ክለብ ቼልሲ እንግሊዛዊውን የተከላካይ ስፍራ ተጨዋች ቶሲን አዳራብዮ ከፉልሀም በነፃ ዝውውር ለማስፈረም መቃረባቸው ተገልጿል። ኒውካስል ዩናይትድ ተጫዋቹን ለማስፈረም በመስራት ላይ የሚገኙ ቢሆንም ሰማያዊዎቹ ዝውውሩን ለማጠናቀቅ መቃረባቸው ተዘግቧል። ቼልሲን በሀላፊነት ለመረከብ ከስምምነት የደረሱት አሰልጣኝ ኢንዞ ማሬስካ ቶሲን አዳራብዮ የክለቡ…
ፉልሀም ከተጨዋቹ ጋር መለያየቱን ይፋ አደረገ !

ፉልሀም በክለቡ ያለው ኮንትራቱ ከተጠናቀቀው እንግሊዛዊው የተከላካይ ስፍራ ተጨዋች ቶሲን አዳራብዮ ጋር መለያየታቸውን ይፋ አድርገዋል።

ቼልሲን ለመቀላቀል ከስምምነት የደረሰው ተጨዋቹ በትላንትናው ዕለት የህክምና ምርመራውን ማጠናቀቁ ተዘግቧል።

በአሰልጣኝ ኢንዞ ማሬስካ የሚመራው ቼልሲ ቶሲን አዳራብዮን በነፃ ዝውውር የክለቡ የመጀመሪያ ፈራሚያቸው የሚያደርጉ ይሆናል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
ቤንጃሚን ሴስኮ ወዴት ያመራ ይሆን ?

በታላላቅ ክለቦች እየተፈለገ የሚገኘው ስሎቬንያዊው የጀርመኑ ክለብ ሌፕዚግ የፊት መስመር አጥቂ ቤንጃሚን ሴስኮ በሚቀጥሉት ቀናት ቀጣይ ማረፊያውን እንደሚመርጥ ተገልጿል።

የጀርመኑ ክለብ ሌፕዚግ ተጨዋቹን በክለቡ ለማቆየት ጥረት በማድረግ ላይ መሆናቸው የተገለፀ ሲሆን አዲስ ኮንትራት እንዳቀረቡለት ተነግሯል።

በተጨማሪም የሳውዲ አረቢያ ክለቦች ተጫዋቹን ለማስፈረም ከታላላቅ ክለቦች ጋር በመፎካከር አመታዊ 30 ሚልዮን ዩሮ ክፍያ ቢያቀርቡለትም ውድቅ ማድረጉ ተነግሯል።

አርሰናል ፣ ማንችስተር ዩናይትድ እና ቼልሲ በክረምቱ የተጨዋቾች የዝውውር መስኮት ቤንጃሚን ሴስኮን ለማስፈረም ጥረት በማድረግ ላይ መሆናቸው ተዘግቧል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
" ራሽፎርድን አርሰናል ዉስጥ ብመለከተው ደስ ይለኛል " ሳኛ

የቀድሞ የመድፈኞቹ ተጨዋች ባካሪ ሳኛ እንግሊዛዊውን የማንችስተር ዩናይትዱን የፊት መስመር ተጨዋች ማርከስ ራሽፎርድ በአርሰናል ማልያ መመልከት እንደሚፈልግ ተናግሯል።

" ራሽፎርድን አርሰናል ዉስጥ ብመለከተው ደስ ይለኛል " የሚለው ባካሪ ሳኛ " የአርሰናል የፊት መስመር ማርከስ ራሽፎርድ ቢጨመርለት ለተጋጣሚው እችግ አስቸጋሪ እና አስፈሪ ሆኖ ይቀርባል።"በማለት ተናግሯል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
TIKVAH-SPORT
አሰልጣኝ አንቶኒዮ ኮንቴ ናፖሊን ሊረከቡ ነው ! የጣልያን ሴርያው ክለብ ናፖሊ ጣልያናዊውን አሰልጣኝ አንቶኒዮ ኮንቴን በሀላፊነት ለመሾም ከስምምነት መድረሳቸው ተገልጿል። አሰልጣኝ አንቶኒዮ ኮንቴ ናፖሊን እስከ 2027 ለሶስት የውድድር አመታት ለማሰልጠን ከስምምነት መድረሳቸው ይፋ ሆኗል። አሰልጣኝ አንቶኒዮ ኮንቴ ከቶተንሀም ጋር ከተለያዩ በኋላ ለቤተሰባቸው ቅርብ ለመሆን የጣልያን ክለብ የማሰልጠን…
ናፖሊ አሰልጣኝ አንቶኒዮ ኮንቴን በሀላፊነት ሾመ !

የጣልያን ሴርያው ክለብ ናፖሊ ጣልያናዊውን አሰልጣኝ አንቶኒዮ ኮንቴን የቡድኑ ዋና አሰልጣኝ አድርገው በሀላፊነት መሾማቸውን በይፋ አስታውቀዋል።

አሰልጣኝ አንቶኒዮ ኮንቴ ናፖሊን እስከ 2027 ለሶስት የውድድር አመታት ለማሰልጠን ፊርማቸውን ማኖራቸው ይፋ ሆኗል።

" የናፖሊ አሰልጣኝ በመሆኔ ደስታ ተሰምቶኛል ክለቡን ለማሳደግ እና ቡድኑን ለማሻሻል ያለኝን ሁሉ እንደምሰጥ ቃል እገባለሁ።"ሲሉ አሰልጣኝ አንቶኒዮ ኮንቴ ከፊርማው በኋላ ተናግረዋል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
" ቀጣዩ የሲቲ አላማ ለአምስተኛ ጊዜ ማሸነፍ ነው "

የማንችስተር ሲቲው ሊቀመንበር ኸልዱን አል ሙባረክ በክለቡ የውድድር አመት ሁኔታ ዙሪያ በክለቡ ሚዲያ ቃለ ምልልስ አድርገው ነበር።

ሊቀመንበሩ በቃለ ምልልሳቸው የማንችስተር ሲቲን ያለፉት አመታት ስኬትን ጨምሮ የተለያዩ ጉዳዮችን አንስተዋል።

ከእነዚህም መካከል :-

- " የፕርሚየር ሊግ ዋንጫውን እንደምናሸንፍ ያወቅኩት ነሀሴ ወር ላይ ከአርሰናል ጋር ኤምሬትስ ስታዲየም በተሸነፍንበት ጨዋታ ነው።

- በቀጣይ የውድድር አመት የማንችስተር ሲቲ አላማ የሚሆነው የፕርሚየር ሊግ ዋንጫውን ለተከታታይ አምስተኛ ጊዜ ማሸነፍ ነው።

- በእንግሊዝ እግርኳስ ታሪክ ባለፉት መቶ አመታት ውስጥ ሊጉን ለተከታታይ አራት ጊዜ ማሸነፍ የቻለ ክለብ የለም ይህንን ስታውቅ ማንችስተር ሲቲን ማድነቅ ትጀምራለህ።

- ስለ ፔፕ ጋርዲዮላ ቆይታ በጋራ የምንወስነው ውሳኔ ነው የሚሆነው ለእኛም ለጋርዲዮላም የሚስማማ ውሳኔ እንወስናለን።

- የቀረቡብን 115 ክሶች የሚያበሳጩ ናቸው ነገርግን ሰዎች በክስ ሂደቱ ሳይሆን ከመጨረሻው ውሳኔ በኋላ በእኛ ላይ እንዲፈርዱ እንፈልጋለን የመጨረሻው ፍርድ እስከሚታወቅ ረጅም ጊዜ ይወስዳል።

- በፕርሚየር ሊጉ ባለፉት አመታት በእኛ ደረጃ የሚገኝ ቡድን ፈልገህ ማግኘት አትችልም።" ሲሉ ተደምጠዋል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
Forwarded from WANAW SPORT
🔊 #ሁለት ቀናት ብቻ ቀሩት

⚽️ ለእግር ኳስ ቡድንዎ ልዩ የሽያጭ ብስራት ⚽️

🔥 #እንዳያመልጥዎ፣ ዛሬውኑ ይዘዙን!

📌 ለበለጠ መረጃና ትዕዛዝ 📲 09011382830910851535 እና 0913586742 ላይ ይደውሉ።

👉🏾 እንዲሁም በቴሌግራም @Wanawsales ላይ የሽያጭ ሰራተኞቻችንን በቀጥታ በማናገር ወይም በቴሌግራም ቦት @WANAWSbot በኩል ይዘዙን።

Instagram | Facebook | TikTok

🏅 ዋናው ወደፊት...

@wanawsportwear
ሽመልስ በቀለ 1⃣8⃣ ገስት ሀውስ

በውቢቷ ሀዋሳ ቆይታዎ የት ለማረፍ አስበዋል ? ንፁህ እና በደንበኞቻችን ተወዳጅ በሆነው የእንግዳ ማረፊያችን መጥተው የእረፍት ጊዜውን ያሳልፉ።

እንግዶቻችንን ተቀበልን ለእይታ ሳቢ በሆነው የእንግዳ ማረፊያችን ማስተናገድ ከጀመርን አመታትን አስቆጥረናል።

አድራሻችን :- ሀዋሳ አርቴፍሻል ስታዲየም መንገድ ላይ ያገኙናል።

ለተጨማሪ መረጃ እና ለትዕዛዝዎ ይደውሉልን :- 0928684848

#ShemelesBekele18
TIKVAH-SPORT
ኦማሪ ፎርሰን ዩናይትድን ሊለቅ ነው ! የማንችስተር ዩናይትዱ ወጣት የፊት መስመር ተጨዋች ኦማሪ ፎርሰን በዚህ ክረምት ኮንትራቱ ሲጠናቀቅ ክለቡን ሊለቅ መሆኑ ተገልጿል። በቅርቡ ለዋናው ቡድን ተሰልፎ በመጫወት ጥሩ እንቅስቃሴ ማሳየት የቻለው ኦማሪ ፎርሰን በነፃ ዝውውር ማንችስተር ዩናይትድን እንደሚለቅ ተነግሯል። የ 19ዓመቱን የፊት መስመር አጥቂ ኦማሪ ፎርሰንን በነፃ ዝውውር ለማስፈረም በርካታ…
ጆኒ ኢቫንስ በዩናይትድ ሊቆይ ነው !

ማንችስተር ዩናይትድ የተከላካይ ስፍራ ተጨዋቹን ጆኒ ኢቫንስ ኮንትራት ለተጨማሪ አመት ለማራዘም ንግግር ላይ መሆናቸውን አስታውቀዋል።

እንግሊዛዊው ግብ ጠባቂ ቶም ሂተን በተመሳሳይ ውሉን ለማራዘም ከክለቡ ጋር በንግግር ላይ መሆናቸው ተዘግቧል።

የክለቡ አካዳሚ ውጤት የሆነው ብራንደን ዊሊያምስ በበኩሉ ከክለቡ ጋር ከአመታት በኋላ መለያየቱ ይፋ ተደርጓል።

ማንችስተር ዩናይትድን ሊለቅ እንደሚችል ሲነገር የቆየው የፊት መስመር ተጨዋቹ ኦማሪ ፎርሰን በበኩሉ አዲስ ኮንትራት እንደቀረበለት ተገልጿል።

ይሁን እንጂ የ 19ዓመቱን የፊት መስመር አጥቂ ኦማሪ ፎርሰን የቀረበለትን ኮንትራት ውድቅ በማድረግ ክለቡን ሊለቅ እንደሚችል ተነግሯል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
ጁድ ቤሊንግሀም የአመቱ ምርጥ ተጨዋች ተባለ !

እንግሊዛዊው የመሐል ሜዳ ተጨዋች ጁድ ቤሊንግሀም የሪያል ማድሪድ የደጋፊዎች የአመቱ ምርጥ ተጨዋች በመሆን መመረጥ ችሏል።

ጁድ ቤሊንግሀም ሎስ ብላንኮዎቹ የላሊጋ ፣ ሻምፒየንስ ሊግ እና ስፔን ሱፐር ካፕ ዋንጫን ሲያሳኩ ሀያ ሶስት ግቦችን በማስቆጠር ለቡድኑ ጥሩ የሚባል ግልጋሎት መስጠት ችሏል።

" በመጀመሪያ አመቴ ይህንን ሽልማት በማሸነፌ ኩራት ተሰምቶኛል የመረጡኝን ደጋፊዎች ሁሉ አመሰግናለሁ።"ሲል ቤሊንግሀም ከሽልማቱ በኋላ ተናግሯል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
የሊቨርፑል የአመቱ ምርጥ ተጨዋች ታውቋል !

የመርሲሳይዱ ክለብ ሊቨርፑል የ2023/24 የውድድር አመት የደጋፊዎች የውድድር ዘመኑ ምርጥ ተጨዋች ይፋ አድርገዋል።

በዚህም መሰረት ግብፃዊው የፊት መስመር ተጨዋች መሐመድ ሳላህ የሊቨርፑል የውድድር ዘመኑ የደጋፊዎች ምርጥ ተጨዋች በመሆን በአብላጫ ድምፅ መመረጥ ችሏል።

መሐመድ ሳላህ በሊቨርፑል ቤት ባሳለፋቸው ሰባት አመታት የአመቱ ምርጥ ተጨዋች ተብሎ ሲመረጥ ለአራተኛ ጊዜ መሆኑ ተገልጿል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
ዊሊያም ሳሊባ ሶስተኛ ደረጃን ይዞ አጠናቋል !

ፈረንሳዊው የተከላካይ ስፍራ ተጨዋች ዊሊያም ሳሊባ የተጠናቀቀው የውድድር አመት የአርሰናል የአመቱ ምርጥ ተጨዋች ሽልማትን በሶስተኝነት ማጠናቀቅ ችሏል።

ዊሊያም ሳሊባ ከተሰጠው አጠቃላይ ድምፅ ሀያ በመቶውን በማግኘት ሶስተኛ ደረጃን ይዞ ማጠናቀቁ ተገልጿል።

በቀጣይ የዘንድሮው የውድድር አመት የአርሰናል የአምቱ ምርጥ ተጨዋች እና ሁለተኛ ደረጃን በመያዝ ያጠናቀቀው ተጨዋች ይፋ ይደረጋል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
የኤፌ ካፕ የአመቱ ምርጥ ተጨዋች ታውቋል !

በማንችስተር ዩናይትድ አሸናፊነት የተጠናቀቀው የዘንድሮው የ2023/24 የውድድር አመት የእንግሊዝ ኤፌ ካፕ ውድድር የውድድሩ ምርጥ ተጨዋች ይፋ ተደርጓል።

በዚህም መሰረት እንግሊዛዊው የማንችስተር ዩናይትድ የመሐል ሜዳ ተጨዋች ኮቢ ማይኖ የእንግሊዝ ኤፌ ካፕ ምርጥ ተጨዋች ተብሎ በአብላጫ ድምፅ መመረጥ ችሏል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
TIKVAH-SPORT
የሊጉ ክለቦች ቫር እንዲቀር ድምፅ ሊሰጡ ነው ! የእንግሊዝ ፕርሚየር ሊግ ክለቦች ከሚቀጥለው የውድድር አመት ጀምሮ ቫር ከሊጉ እንዲቀር ድምፅ ሊሰጡ መሆኑ ተገልጿል። ሀሳቡን ዎልቭስ ማምጣቱ እና ክለቦቹ በሚቀጥለው ወር በሚያደርጉት አመታዊ ስብሰባ ላይ በአጀንዳነት በመያዙ ድምፅ ለመስጠት መስማማታቸው ተነግሯል። በድምፅ አሰጣጥ ሂደቱ ውስጥ ከሀያው ክለቦች መካከል አስራ አራቱ ከተስማሙ ቫር በሚቀጥለው…
የሊጉ ክለቦች በቫር ዙሪያ ነገ ድምፅ ይሰጣሉ !

የእንግሊዝ ፕርሚየር ሊግ ክለቦች ከሚቀጥለው የውድድር አመት ጀምሮ #ቫር ከሊጉ እንዲቀር በዎልቭስ በቀረበው ሀሳብ ላይ ነገ በሚኖራቸው አመታዊ ስብሰባ ድምፅ ይሰጣሉ።

ይሁን እንጂ አብዛኞቹ የእንግሊዝ ፕርሚየር ሊግ ክለቦች ሀሳቡን አለመቀበላቸው እና ቫር እንዲቀጥል እንደሚፈልጉ የሀገሪቱ መገናኛ ብዙሀን ዘግበዋል።

ማንችስተር ሲቲ ፣ አርሰናል እና ቶተንሀም ቫር እንዲቀጥል ከሚፈልጉ ክለቦች ጎራ እንደሆኑ መታወቁ ተጠቁሟል።

በድምፅ አሰጣጥ ሂደቱ ውስጥ ከሀያው ክለቦች መካከል አስራ አራቱ ከተስማሙ ቫር በሚቀጥለው አመት ተግባራዊ እንደማይሆን ተዘግቧል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
ሚሎስ ኬርኬዝ ወደ ማንችስተር ዩናይትድ ?

ማንችስተር ዩናይትድ በክረምቱ የተጨዋቾች የዝውውር መስኮት የግራ መስመር ተጨዋች ለማስፈረም ወደ ዝውውር ገባያው እንደሚገቡ ተነግሯል።

ቀያዮቹ ሴጣኖች በተጨማሪም በዚህ ክረምት የመሐል ተከላካይ እና የፊት መስመር አጥቂ ለማስፈረም ቅድሚያ ሰጥተው እንደሚሰሩ ይጠበቃል።

ማንችስተር ዩናይትድ ለማስፈረም ከተመለከቷቸው የግራ መስመር ተጨዋቾች አንዱ የበርንማውዙ ተጨዋች ሚሎስ ኬርኬዝ አንዱ መሆኑ ተገልጿል።

ይሁን እንጂ ማንችስተር ዩናይትድ እስካሁን ሀንጋራዊውን ተጫዋች ሚሎስ ኬርኬዝ ለማስፈረም ንግግር አለመጀመሩ ተዘግቧል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
ሮናልዶ የወሩ ምርጥ ተጨዋች ተብሏል !

በአል ሂላል አሸናፊነት የተጠናቀቀው የሳውዲ ሮሽን ሊግ የ2023/24 የውድድር አመት የወርሀ ግንቦት የወሩ ምርጥ ተጨዋች ይፋ ተደርጓል።

በዚህም መሰረት ፖርቹጋላዊው የአል ናስር የፊት መስመር ተጨዋች ክርስቲያኖ ሮናልዶ የሳውዲ ሊግ የግንቦት ወር ምርጥ ተጨዋች በመሆን በአብላጫ ድምፅ መመረጥ ችሏል።

ክርስቲያኖ ሮናልዶ በዘንድሮው የውድድር ዘመን ለአምስተኛ ጊዜ የሳውዲ ሊግ የወሩ ምርጥ ተጫዋች በመባል መመረጥ ችሏል።

የአምስት ጊዜ ባሎን ዶር አሸናፊው ተጨዋች ክርስቲያኖ ሮናልዶ በተጠናቀቀው የውድድር አመት ባደረጋቸው ሰላሳ አንድ የሊጉ ጨዋታዎች ሰላሳ አምስት ግቦች ማስቆጠር ችሏል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
Stock Clearance Discount

📞 0925927457 @eBRO4
📞
0953964175 @heymobile

• iPhone X, White, 256 GB/ 100%    
   19,000 ETB
• iPhone Max, White, 64GB/ 89%     
   24,000 ETB
• iPhone Max, Black, 256 GB/ 89%
   28,000 ETB
• iPhone Max, Golden, 256 GB/ 92%
   29,000 ETB
• iPhone 11,  Red,  64 GB/ 75%  
   27,000 ETB
• iPhone 11, Black, 128 GB/ 91%  
   33,000 ETB
• iPhone 11 Pro, Black, 64 GB/ 63%
   35,000 ETB
• iPhone 11 Pro, Black, 256 GB/88%  
  39,000 ETB
•11 Pro Max, Black, 64 GB/ 77%  
  36,000 ETB
• iphone 12 mini, Red, 64 GB/ 98%  
  22,000 ETB
• iPhone 12 Pro, Blue, 128 GB/ 83%  
   47,000 ETB
• iPhone 12 Pro, Blue, 128 GB/ 89% 
  48,000 ETB
• iPhone 12 Pro, Black,256 GB/ 85%  
   51,000 ETB
• 12 Pro Max, Golden, 128 GB/ 85%
   59,000 ETB
• 12 Pro Max, Blue, 128 GB/ 86%
   43,000 ETB ⚠️

Exchange Available!
Free Delivery 🚚

@heyonlinemarket
❇️SMART ያልሆኑ TV SMART ለማድረግ ምን መግዛት እንዳለብዎ ካላወቁ  ይሄን እቃ ምርጫው ያድርጉ።

❇️የራሱ የሆነ BLUETOOTH ሪሞት ያለው ትክክለኛ 4K ምስል ጥራት ያለው

❇️የተለያዩ የፊልም እና የኳስ ቻናሎች የተጫኑበት በአጭር ጊዜ በሚቆ ይ ቅናሽ 3200 ብር ብቻ

Inbox Us 📩Admin @Sadikethio
Call 📱 +251 91 178 5693

የተለያዩ ነፃ የኳስ ቻናሎች የሚያገኙበት የዲሽ ቻናል 👇👇 https://www.tg-me.com/joinchat-AAAAAEnaa5LpZrcwQ-E0Tw
2024/10/04 19:22:52
Back to Top
HTML Embed Code: