Telegram Web Link
#MatchDay 🇪🇹

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ዛሬ ምሽት የአለም ዋንጫ ማጣሪያ የምድብ ሶስተኛ ጨዋታውን ከጊኒ ቢሳው ብሔራዊ ቡድን ጋር የሚያደርግ ይሆናል።

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን በጨዋታው ሙሉ ቢጫ ማልያ ለብሶ ወደ ሜዳ እንደሚገባ ተገልጿል።

የሁለቱ ብሔራዊ ቡድኖች ጨዋታ ዛሬ በኢትዮጵያ ሰዓት አቆጣጠር ምሽት 1:00 ሰዓት በስታዲዮ 24 ዴ ሴቴምብሮ የሚደረግ ይሆናል።

ጨዋታውን ማን ይመራዋል ?

ጨዋታውን ቤኒናውያን ዳኞች ጂንዶ ልዊስ በመሐል ዳኝነት አይማር ኤሪክ እና ጆ ኮርቴል በረዳት ዳኝነት እንዲሁም ሙሐመድ ኢሳ በአራተኛ ዳኝነት ይመሩታል።

ጨዋታውን በምን መመልከት ይቻላል ?

ጨዋታውን ከአንድ ሰዓት ጀምሮ በተከታዩ ሊንክ መከታተል ይችላሉ።

https://www.plus.fifa.com/en/content/guinea-bissau-v-ethiopia-caf-qualifiers-first-round-group-a-fifa-world-cup-26tm-live-stream-2024/acccd313-94dc-4a1d-ba44-2dbf97a5b894

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
TIKVAH-SPORT
እንግሊዝ ስብስቧን ይፋ አድርጋለች ! በአሰልጣኝ ጋሪዝ ሳውዝጌት የሚመራው የእንግሊዝ ብሔራዊ ቡድን ለቀጣዩ የ2024 አውሮፓ ዋንጫ ውድድር የሚጠቀመውን ስብስብ ይፋ አድርጓል። ማርከስ ራሽፎርድ ከስብስቡ ውጪ የሆነው በእሱ ቦታ የተሻለ አመት ያሳለፉ ተጨዋቾች መኖራቸውን ተከትሎ መሆኑን አሰልጣኝ ጋሪዝ ሳውዝጌት ገልጸዋል። ብሔራዊ ቡድኑ በቀጣይ ከሚያደርጋቸው የወዳጅነት ጨዋታዎች በኋላ ሰባት ተጨዋቾችን…
ጄምስ ማዲሰን ከእንግሊዝ ስብስብ ተቀነሰ !

እንግሊዛዊው የቶተንሀም የመሐል ሜዳ ተጨዋች ጄምስ ማዲሰን ከቀጣዩ የ2024 አውሮፓ ዋንጫ ውድድር ውጪ መሆኑ ተገልጿል።

ከእንግሊዝ ብሔራዊ ቡድን አሰልጣኝ ጋሪዝ ሳውዝጌት ጥሪ ቀርቦለት የነበረው ጄምስ ማዲሰን አሁን ላይ ከስብስቡ መቀነሱ ተነግሯል።

ብሔራዊ ቡድኑ ለወዳጅነት ጨዋታዎች እና ዝግጅት ጥሪ ካደረገላቸው ተጨዋች ውስጥ ከጄምስ ማዲሰን በተጨማሪ ስድስት ተጨዋቾችን ቀንሶ ወደ አውሮፓ ዋንጫው ያመራል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
TIKVAH-SPORT
#MatchDay 🇪🇹 የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ዛሬ ምሽት የአለም ዋንጫ ማጣሪያ የምድብ ሶስተኛ ጨዋታውን ከጊኒ ቢሳው ብሔራዊ ቡድን ጋር የሚያደርግ ይሆናል። የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን በጨዋታው ሙሉ ቢጫ ማልያ ለብሶ ወደ ሜዳ እንደሚገባ ተገልጿል። የሁለቱ ብሔራዊ ቡድኖች ጨዋታ ዛሬ በኢትዮጵያ ሰዓት አቆጣጠር ምሽት 1:00 ሰዓት በስታዲዮ 24 ዴ ሴቴምብሮ የሚደረግ ይሆናል። ጨዋታውን ማን ይመራዋል…
" አስቸጋሪ ቡድን እንደምንገጥም እናውቃለን " ሉዊስ ቦ ሞርቴ

የዛሬ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ተጋጣሚ ጊኒ ቢሳው ብሔራዊ ቡድን ዋና አሰልጣኝ ሉዊስ ቦ ሞርቴ ኢትዮጵያ ጠንካራ ተጋጣሚ መሆኗን ከጨዋታው በፊት በሰጡት አስተያየት ተናግረዋል።

" የምንገጥመው ነጥብ ማግኘት የሚፈልግ ለማሸነፍ አስቸጋሪ የሆነ ቡድን መሆኑን እናውቃለን " ያሉት አሰልጣኝ ሉዊስ ቦ ሞርቴ " ነገርግን በሜዳችን እንደመጫወታችን አሸንፈን ሶስት ነጥቡን ማሳካት እንፈልጋለን።"ብለዋል።

ጊኒ ቢሳው በምድቡ አራት ነጥቦችን ሰብስባ ሶስተኛ ደረጃ ላይ ስትቀመጥ ኢትዮጵያ በአንድ ነጥብ አምስተኛ ደረጃን ይዛለች።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
" በሜዳችን መጫወታችን መነሳሳት ይጨምርልናል
" ማማ ባልዴ

የጊኒ ቢሳው ብሔራዊ ቡድን የፊት መስመር አጥቂ ማማ ባልዴ ቡድናቸው ዛሬ ከኢትዮጵያ ጋር በሚያደርገው ጨዋታ ደጋፊያቸው የአፍሪካ ዋንጫውን ክስተት ረስቶ ድጋፍ እንዲያደርግላቸው ጠይቋል።

ከምሽቱ ጨዋታ በፊት አስተያየቱን የሰጠው የሊዮን ተጨዋች ማማ ባልዴ " በሜዳችን እና ደጋፊያችን ፊት ነው የምንጫወተው ይህ ደግሞ መነሳሳት ይጨምርልናል።

በአፍሪካ ዋንጫው የተፈጠረውን ነገር መርሳት እና በቀጣይ የምናደርጋቸው ሁለት ጨዋታዎች ማተኮር አለብን ፣ ደጋፊው ከጎናችን እንደሚሆን ተስፋ እናደርጋለን።"ብሏል።

ጊኒ ቢሳው በቅርቡ በተደረገው የኮትዲቯር አፍሪካ ዋንጫ ውድድር ያደረገቻቸውን ሶስት የምድብ ጨዋታዎች ተሸንፋ ከምድቧ መሰናበቷ ይታወሳል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
ሉካኩ ወደ ሳውዲ መሄድ እንደሚፈልግ ገለጸ !

ቤልጂየማዊው የፊት መስመር አጥቂ ሮሜሎ ሉካኩ የሳውዲ አረቢያ እግርኳስ በከፍተኛ ደረጃ እያደገ መሆኑን በሰጠው አሰሰተያየት ገልጿል።

" አንድ ቀን ሳውዲ አረቢያ መጫወት እፈልጋለሁ " የሚለው ሮሜሎ ሉካኩ እዛ እግርኳስ ከፍተኛ ደረጃ ላይ እንደሚደርስ አውቃለሁ ብዙ ተጨዋቾች ወደዛ መሄድ ይፈልጋሉ።"በማለት ተናግሯል።

" የሳውዲ አረቢያ እግርኳስ በፍጥነት እያደገ ነው የሚገኘው አሁን ካለበት ደረጃም ከፍ ይላል ፣ ሁሉም የአውሮፓ ክለቦች ሳውዲ ጠንካራ ሆና እንደምትመጣ ያውቃሉ።"ሉካኩ

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
ቼልሲ ተጨዋቾቹን ወደ ኦሎምፒክ አይልክም !

የምዕራብ ለንደኑ ክለብ ቼልሲ ተጨዋቾቹን ወደ ቀጣዩ የፈረንሳይ ፓሪስ የ2024 ኦሎምፒክ ውድድር ለብሔራዊ ቡድኖቻቸው እንደማይልክ ተገልጿል።

ሰማያዊዎቹ አርጀንቲናዊው ኢንዞ ፈርናንዴዝ እና ዩክሬናዊው ማይካሎ ሙድሪክ ወደ ኦሎምፒክ ውድድር እንዳይሄዱ ማድረጋቸው ተነግሯል።

ክለቡ ተጨዋቾቹ በኦሎምፒክ ውድድር እንዳይሳተፉ ያደረገው ከአውሮፓ እና ኮፓ አሜሪካ ውድድር ሲመለሱ ከአዲሱ አሰልጣኝ ጋር በቂ ጊዜ እንዲኖራቸው መሆኑ ተጠቁሟል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
Forwarded from WANAW SPORT
🔊 #አንድ ቀን ብቻ ቀረው

🔥 #እንዳያመልጥዎ፣ አሁኑኑ ይዘዙን!

📌 ለበለጠ መረጃና ትዕዛዝ 📲 0901138283፣ 0910851535 እና 0913586742 ላይ ይደውሉ።

👉🏾 እንዲሁም በቴሌግራም @Wanawsales ላይ የሽያጭ ሰራተኞቻችንን በቀጥታ በማናገር ወይም በቴሌግራም ቦት @WANAWSbot በኩል ይዘዙን።

Instagram | Facebook | TikTok

🏅 ዋናው ወደፊት...

@wanawsportwear
Celtics VS Mavericks ( ሐሙስ ሌሊት 9:30)

በአሜሪካ ቅርጫት ኳስ ውድድር የኢስተርን ኮንፈረንስ ደረጃ ሰንጠረዥ መሪው " Boston Celtics " ከዌስተርን ኮንፈረንሱ " Dallas Mavericks " ጋር ተጠባቂ የፍፃሜ የመጀመሪያ ጨዋታቸውን ያደርጋሉ።

የኢስተርን ኮንፈረንሱ መሪ " Boston Celtics " እንዲሁም በዌስተርን ኮንፈረንስ ደረጃ ሰንጠረዥ አምስተኛ ላይ የሚገኘው " Dallas Mavericks "
ካለፉት አስር ጨዋታዎች በተመሳሳይ ሰባቱን በአሸናፊነት ተወጥተዋል።

ጨዋታው ሐሙስ ሌሊት 9:30 ይደረጋል።
TIKVAH-SPORT
ጄምስ ማዲሰን ከእንግሊዝ ስብስብ ተቀነሰ ! እንግሊዛዊው የቶተንሀም የመሐል ሜዳ ተጨዋች ጄምስ ማዲሰን ከቀጣዩ የ2024 አውሮፓ ዋንጫ ውድድር ውጪ መሆኑ ተገልጿል። ከእንግሊዝ ብሔራዊ ቡድን አሰልጣኝ ጋሪዝ ሳውዝጌት ጥሪ ቀርቦለት የነበረው ጄምስ ማዲሰን አሁን ላይ ከስብስቡ መቀነሱ ተነግሯል። ብሔራዊ ቡድኑ ለወዳጅነት ጨዋታዎች እና ዝግጅት ጥሪ ካደረገላቸው ተጨዋች ውስጥ ከጄምስ ማዲሰን በተጨማሪ…
ከርትስ ጆንስ ወደ አውሮፓ ዋንጫ አያመራም !

የመርሲሳይዱ ክለብ ሊቨርፑል የመሐል ሜዳ ተጨዋች ከርትስ ጆንስ ከእንግሊዝ ብሔራዊ ቡድን የአውሮፓ ዋንጫ ስብስብ መቀነሱ ተገልጿል።

ተጨዋቹ የብሔራዊ ቡድኑ አሰልጣኝ ጋሪዝ ሳውዝጌት በመጀመሪያ ባሳወቁት የሰላሳ ሶስት ተጨዋቾች ስብስብ ውስጥ መካተት ችሎ ነበር።

እንግሊዝ ከጄምስ ማዲሰን እና ከርትስ ጆንስ በተጨማሪ አምስት ተጨዋቾችን በመቀነስ በነገው ዕለት የመጨረሻ ሀያ ስድስት ተጨዋቾችን ለውድድሩ ታስመዘግባለች።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
ሀሪ ማጓየር ለአውሮፓ ዋንጫ ይደርሳል ?

እንግሊዛዊው የማንችስተር ዩናይትድ የተከላካይ ስፍራ ተጨዋች ሀሪ ማጓየር በጉዳት ምክንያት በቀጣዩ የአውሮፓ ዋንጫ ውድድር ብሔራዊ ቡድኑን መወከሉ አጠራጣሪ መሆኑ ተገልጿል።

ሀሪ ማጓየር የእንግሊዝ ብሔራዊ ቡድን ነገ ምሽት ከአይስላንድ ጋር ላለበት የወዳጅነት ጨዋታ ያደረገው ልምምድ እንዳመለጠው ተነግሯል።

የብሔራዊ ቡድኑ አሰልጣኝ ጋሪዝ ሳውዝጌት በአውሮፓ ዋንጫ የሚጠቀሟቸውን ሀያ ስድስት ተጨዋቾች እስከ ነገ እኩለ ሌሊት ለዩኤፋ ማሳወቅ ይኖርባቸዋል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
የባሎን ዶር ሽልማት ስነስርዓት መቼ ይካሄዳል ?

በፍራንስ ፉትቦል አዘጋጅነት የሚካሄደው እና በጉጉት የሚጠበቀው የባሎን ዶር ሽልማት የሚካሄድበት እና እጩዎች የሚገለፁበት ቀን ይፋ ተደርጓል።

በዚህም መሰረት የባሎን ዶር ሽልማት ስነ-ስርዓቱ ሰኞ ጥቅምት 18/2017 ዓ.ም እንደሚካሄድ የሽልማቱ አዘጋጆች ይፋ አድርገዋል።

የ2023/24 የውድድር አመትን የሚያካትተው የባሎን ዶር የሽልማት የእጩዎች ዝርዝር ዕሮብ ነሀሴ 29/2016 ዓ.ም ይፋ እንደሚደረግ ተገልጿል ።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
ሴስክ ፋብሪጋስ ውሉን ሊያራዝም ነው !

የጣልያኑን ክለብ ኮሞ በሀላፊነት እየመራ የሚገኘው ስፔናዊው አሰልጣኝ ሴስክ ፋብሪጋስ በክለቡ የረጅም ጊዜ ኮንትራት ለመፈረም መቃረቡ ተገልጿል።

ሴስክ ፋብሪጋስ ቡድኑን እየመራ በዚህ አመት ከሀያ ሁለት አመታት በኋላ ለመጀመሪያ ጊዜ ወደ ጣልያን ሴርያ ውድድር ማሳደጉ አይዘነጋም።

የቀድሞ የአርሰናል እና ቼልሲ ተጨዋች ሴስክ ፋብሪጋስ በተጨማሪም በክለቡ የአክስዮን ድርሻ እንዳለው ተነግሯል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
TIKVAH-SPORT
የሊጉ ክለቦች በቫር ዙሪያ ነገ ድምፅ ይሰጣሉ ! የእንግሊዝ ፕርሚየር ሊግ ክለቦች ከሚቀጥለው የውድድር አመት ጀምሮ #ቫር ከሊጉ እንዲቀር በዎልቭስ በቀረበው ሀሳብ ላይ ነገ በሚኖራቸው አመታዊ ስብሰባ ድምፅ ይሰጣሉ። ይሁን እንጂ አብዛኞቹ የእንግሊዝ ፕርሚየር ሊግ ክለቦች ሀሳቡን አለመቀበላቸው እና ቫር እንዲቀጥል እንደሚፈልጉ የሀገሪቱ መገናኛ ብዙሀን ዘግበዋል። ማንችስተር ሲቲ ፣ አርሰናል እና…
የፕርሚየር ሊጉ ክለቦች ቫር እንዲቆይ ወሰኑ !

የእንግሊዝ ፕርሚየር ሊግ ክለቦች #ቫር ከሊጉ እንዲቀር በሚጠይቀው የዎልቭስ ሀሳብ ላይ ዛሬ ባደረጉት አመታዊ ስብሰባ ላይ ድምፅ መስጠታቸው ተገልጿል።

በተሰጠው ድምፅ መሰረትም ቫር በሚቀጥለው የውድድር አመት በእንግሊዝ ፕርሚየር ሊግ እንዲቀጥል እንዲሁም ማሻሻያዎች እንዲደረጉበት መወሰኑ ተነግሯል።

በድምፅ አሰጣጡ ሂደትም ሀሳቡን ካቀረበው ዎልቭስ ውጪ አስራ ዘጠኙም የፕርሚየር ሊግ ክለቦች ቫር እንዲቀጥል ድምፅ መስጠታቸው ተገልጿል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
TIKVAH-SPORT
ሀሪ ማጓየር ለአውሮፓ ዋንጫ ይደርሳል ? እንግሊዛዊው የማንችስተር ዩናይትድ የተከላካይ ስፍራ ተጨዋች ሀሪ ማጓየር በጉዳት ምክንያት በቀጣዩ የአውሮፓ ዋንጫ ውድድር ብሔራዊ ቡድኑን መወከሉ አጠራጣሪ መሆኑ ተገልጿል። ሀሪ ማጓየር የእንግሊዝ ብሔራዊ ቡድን ነገ ምሽት ከአይስላንድ ጋር ላለበት የወዳጅነት ጨዋታ ያደረገው ልምምድ እንዳመለጠው ተነግሯል። የብሔራዊ ቡድኑ አሰልጣኝ ጋሪዝ ሳውዝጌት በአውሮፓ…
እንግሊዝ ተጨዋቾቿ ከአውሮፓ ዋንጫ ውጪ ሆኑ !

የማንችስተር ዩናይትድ እና እንግሊዝ ብሔራዊ ቡድን የተከላካይ ስፍራ ተጨዋች ሀሪ ማጓየር በጉዳት ምክንያት ከጀርመኑ አውሮፓ ዋንጫ ውድድር ውጪ መሆኑ ተገልጿል።

የማንችስተር ሲቲው የፊት መስመር ተጨዋች ጃክ ግሪሊሽ በበኩሉ የመጀመሪያ ስብስብ ውስጥ ቢካተትም ከአውሮፓ ዋንጫው የእንግሊዝ የመጨረሻ ስብስብ መቀነሱ ተነግሯል።

እስካሁን ጄምስ ማዲሰን ፣ ከርትስ ጆንስ ፣ ሀሪ ማጓየር ፣ ጃክ ግሪሊሽ እና ጄምስ ትራፎርድ ከአውሮፓ ዋንጫው ውጪ መሆናቸው ተረጋግጧል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
የጨዋታ አሰላለፍ !

1:00 ጊኒ ቢሳው ከ ኢትዮጵያ ( የአለም ዋንጫ ማጣሪያ )

ጨዋታውን በተከታዩ ሊንክ መከታተል ይቻላል።

https://www.plus.fifa.com/content/acccd313-94dc-4a1d-ba44-2dbf97a5b894

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
2 ' ጊኒ ቢሳው 0 - 0 ኢትዮጵያ ( የአለም ዋንጫ ማጣሪያ )

ጨዋታውን በተከታዩ ሊንክ መከታተል ይቻላል።

https://www.plus.fifa.com/content/acccd313-94dc-4a1d-ba44-2dbf97a5b894

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
10 '  ጊኒ ቢሳው 0 - 0 ኢትዮጵያ ( የአለም ዋንጫ ማጣሪያ )

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
20 '  ጊኒ ቢሳው 0 - 0 ኢትዮጵያ ( የአለም ዋንጫ ማጣሪያ )

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
30 '  ጊኒ ቢሳው 0 - 0 ኢትዮጵያ ( የአለም ዋንጫ ማጣሪያ )

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
38 '  ጊኒ ቢሳው 0 - 0 ኢትዮጵያ ( የአለም ዋንጫ ማጣሪያ )

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
2024/10/04 17:15:08
Back to Top
HTML Embed Code: