Telegram Web Link
13 '

ብሬንትፎርድ 1-0 አርሰናል

ምቤሞ

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
27 '

ብሬንትፎርድ 1-0 አርሰናል

ምቤሞ

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
30'

ብሬንትፎርድ 1-1 አርሰናል

ምቤሞ ጄሱስ

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
40 '

ብሬንትፎርድ 1 - 1 አርሰናል

ምቤሞ       ጄሱስ

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
የእረፍት ሰዓት !

በፕርሚየር ሊግ የአስራ ዘጠነኛ ሳምንት መርሐ ግብር አርሰናል ከብሬንትፎርድ ጋር እያደረጉ የሚገኙትን ጨዋታ 1ለ1 በሆነ አቻ ውጤት ወደ መልበሻ ቤት አምርተዋል።

ግቦችን ለብሬንትፎርድ ምቤሞ እንዲሁም ለአርሰናል ጋብሬል ጄሱስ ማስቆጠር ችለዋል።

🟨 የቢጫ ካርድ የተመለከቱ ተጫዋቾች እነማን ናቸው ?

- በመጀመርያው አጋማሽ በአርሰናል በኩል ጁሪየን ቲምበር እንዲሁም በብሬንትፎርድ በኩል ኖርጋርድ የማስጠንቀቂያ ካርድ ተመልክተዋል።

የጨዋታው የኳስ ቁጥጥር ምን ይመስላል ?

- በመጀመሪያው አጋማሽ አርሰናል 62% - 38% የኳስ ቁጥጥር ብልጫ ነበራቸው።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
የሊቨርፑል እና ዩናይትድን ጨዋታ ማን ይመራዋል ?

የፊታችን እሁድ የሚጠበቀውን የሊቨርፑል እና ማንችስተር ዩናይትድ የፕርሚየር ሊግ መርሐ ግብር የሚመሩት ዳኛ ታውቀዋል።

በአንፊልድ ስታዲየም የሚካሄደውን ተጠባቂ ጨዋታ ማይክል ኦሊቨር በመሐል ዳኝነት እንደሚመሩት ይፋ ተደርጓል።

ጨዋታውን ክሪስ ካቫናህ በቫር ዳኝነት የሚመሩት ይሆናል።

ተጠባቂው ጨዋታ እሁድ ምሽት 1:30 በአንፊልድ ስታዲየም የሚደረግ ይሆናል።

ጨዋታውን ማን ያሸንፋል ?

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
50 '

ብሬንትፎርድ 1 - 2 አርሰናል

ምቤሞ       ጄሱስ
ሜሪኖ

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
53 '

ብሬንትፎርድ 1 - 3 አርሰናል

ምቤሞ       ጄሱስ
                        ሜሪኖ
ማርቲኔሊ

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
65 '

ብሬንትፎርድ 1 - 3 አርሰናል

ምቤሞ       ጄሱስ
                        ሜሪኖ
                         ማርቲኔሊ

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
78 '

ብሬንትፎርድ 1 - 3 አርሰናል

ምቤሞ       ጄሱስ
                        ሜሪኖ
                         ማርቲኔሊ

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
90 '

ብሬንትፎርድ 1 - 3 አርሰናል

ምቤሞ       ጄሱስ
                        ሜሪኖ
                         ማርቲኔሊ

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
መድፈኞቹ ወሳኝ ድል አሳክተዋል !

የሰሜን ለንደኑ ክለብ አርሰናል ከብሬንትፎርድ ጋር ያደረገውን የሊግ መርሐ ግብር 3ለ1 በሆነ ውጤት ማሸነፍ ችሏል።

የመድፈኞቹን የማሸነፊያ ግቦች ጋብሬል ጄሱስ ፣ ሜሪኖ እና ማርቲኔሊ ከመረብ ሲያሳርፉ ለብሬንትፎርድ ምቤሞ አስቆጥሯል።

አርሰናል በዘንድሮው የውድድር ዘመን በፕርሚየር ሊጉ #አስር ከማዕዘን ምት የተሻሙ ግቦችን ማስቆጠር ችሏል።

ብራዚላዊው የአርሰናል የፊት መስመር አጥቂ ጋብርል ጄሱስ ባለፉት አራት ጨዋታዎች ስድስት ግቦችን አስቆጥሯል።

ጁሪየን ቲምበር በጨዋታው ቢጫ ካርድ መመልከቱን ተከትሎ አርሰናል ቅዳሜ ከብራይተን ጋር የሚያደርገው ጨዋታ በቅጣት ምክንያት የሚያመልጠው ይሆናል።

መድፈኞቹ ማሸነፋቸውን ተከትሎ ከሊጉ መሪ ሊቨርፑል ያላቸውን የነጥብ ልዩነት ወደ ስድስት ማጥበብ ችለዋል።

የሊግ ደረጃቸው ምን ይመስላል ?

2️⃣ አርሰናል :- 39 ነጥብ
1️⃣2️⃣ ብሬንትፎርድ :- 24 ነጥብ

ቀጣይ መርሐግብር ?

ቅዳሜ - ብራይተን ከ አርሰናል
ቅዳሜ - ሳውዝሀምፕተን ከ ብሬንትፎርድ

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
ይቅናዎት!
ኦዶች ከመቼውም ጊዜ በላይ ከፍ ተደርገዋል።
ታዲያ ምን ይጠብቃሉ? ለማሸነፍ በተመቻቹ ኦዶች ይወራረዱ!
አሁኑኑ Betika.et ላይ ብቻ!
ቤቲካ የአሸናፊዎች ቤት!
እውነትም ቅመም! ቅመም Itel Proን ዛሬውኑ ገዝተን ያለ ባትሪ ስጋት በሽ በሽ እንበል! ዛሬውኑ ወደ ሳፋሪኮም ሱቆች በማቅናት ስልካችንን ገዝተን ለ90 ቀናት በሚቆይ 5ጊባ ወርሃዊ ጥቅል እና 1000 የሳፋሪኮም ደቂቃ ጉርሻ እናግኝ!

የቴሌግራም ቦታችንን https://www.tg-me.com/official_safaricomet_bot በመጠቀም የአየር ሰዓት ወይም ልዩ ልዩ ጥቅሎችን እንግዛ!

🔗 የM-PESA ሳፋሪኮም መተግበሪያ በዚህ ሊንክ እናውርድ፦ https://play.google.com/store/apps/details?id=et.safaricom.mpesa.lifestyle

ስለ አገልግሎታችን ማንኛውንም ጥያቄ ወይም መረጃ በቴሌግራም ቻናላችን https://www.tg-me.com/Safaricom_Ethiopia_PLC 24/7 ማግኘት ይቻላል!

#MPESASafaricom #SafaricomEthiopia #1Wedefit #Furtheraheadtogether
“ ለሊጉ ዋንጫ መፋለም አለብን “ ጄሱስ

የመድፈኞቹ የፊት መስመር ተጨዋች ጋብሬል ጄሱስ ለአርሰናል አይነት ትልቅ ቡድን መጫወት ቀላል አለመሆኑን ተናግሯል።

“ እንደ አርሰናል ላለ ትልቅ ክለብ መጫወት ቀላል አይደለም “ የሚለው ጄሱስ ባለፉት ጊዜያት ጥሩ ብጫወትም ግብ አላስቆጥርም ነበር ብሏል።

ጋብሬል ጄሱስ አክሎም “ በቀጣይ ለፕርሚየር ሊጉ ዋንጫ መፋለም አለብን “ ሲል ቡድኑን አሳስቧል።

በጨዋታው ብራዚላዊው ተጨዋች ጋብሬል ማርቲኔሊ የጨዋታው ኮከብ በመባል መመረጥ ችሏል።

@Tikvahethsport    @kidusyoftahe
“ ማድረግ የምንችለው የራሳችንን የቤት ስራ መስራት ብቻ ነው “ አርቴታ

የአርሰናሉ ዋና አሰልጣኝ ሚኬል አርቴታ ቡድናቸው ትላንት ምሽት አስቸጋሪ ከሆነ ቦት ሶስት ነጥብ አሳክቶ መውጣቱን ገልጸዋል።

“ አስቸጋሪ ቦታ መጥተን አሸንፈናል እዚህ ጥሩ ሪከርድ ነው ያላቸው 1-0 ስንመራ ሁኔታው የባሰ አስቸጋሪ ነበር “ ሲሉ ሜኬል አርቴታ ተናግረዋል።

" በህመም እና ጉዳት ምክንያት የተወሰኑ ተጨዋቾች አጥተን ነበር በተለያዩ ተጨዋቾች መጫወት ነበረብን “ አርቴታ

ስለ ዋንጫ ፉክክሩ ያነሱት ሚኬል አርቴታ “ እኛ ማድረግ የምንችለው የራሳችንን የቤት ስራ መስራት ብቻ ነው ሌላ ነገር ማድረግ አንችልም “ ሲሉ አስረድተዋል።

“ በዚህ ሰዓት ትኩረት የምናደርገው ያሉን ተጨዋቾች መጠቀም ላይ ነው ነገርግን ጥሩ እድሎች ካገኘን እንመለከታለን “ ሲሉ አርቴታ ስለ ጥር የዝውውር መስኮት ሀሳባቸውን ሰጥተዋል።

@Tikvahethsport    @kidusyoftahe
አሸናፊዎች ተለይተዋል።

የአርሰናል ብሬንትፎርድን ጨዋታ ትክክለኛ ምላሽ ቀድመው የሰጡት ከስር የተገለፁት የቤተሰባችን አባላት ናቸው።

ትክክለኛ ምላሽ የሰጡትን በመፈለጉ ሂደት የተዘለለ እና ያልታየ ካለ ማሳወቅ ይቻላል። Edit የተደረገ መልስ ተቀባይነት አይኖረውም።

ስጦታ የሚበረከትላቸው ቀድመው የመለሱ ሶስት አሸናፊዎች ብቻ ናቸው።

1ኛ. @Mha0232
2ኛ. @Hamido505
3ኛ. Mac Alister55

🔴 አሸናፊዎች @Kidusyoftahe ስልክ ቁጥር በማስቀመጥ ሽልማታቸውን መውሰድ ይችላሉ።

@tikvahethsport
ጁቬንቱስ ከተጨዋቹ ጋር ሊለያይ ነው !

የጣልያን ሴርያው ክለብ ጁቬንቱስ ከብራዚላዊው የተከላካይ ስፍራ ተጨዋች ዳኒሎ ጋር በጥር እንደሚለያዩ የክለቡ ዳይሬክተር አረጋግጠዋል።

ዳይሬክተሩ በአስተያየታቸውም “ ዳኒሎን በዚህ ወር ለመሸጥ እየሰራን ነው እቅዳችን ይሄ ነው ለክለቡ እና ለተጨዋቹ የሚጠቅመውን ወስነናል “ ብለዋል።

የ 33ዓመቱ ብራዚላዊ የተከላካይ ስፍራ ተጨዋች ዳኒሎ በጁቬንቱስ የወደፊት እቅድ ውስጥ አለመኖሩ እንደተነገረው ተዘግቧል።

ጁቬንቱስ ከአምበሉ ጋር ለመለያየት የወሰነበት ምክንያት ከእምነት ማጣት ጋር በተያያዘ ሳይሆን እንዳልቀረ ተዘግቧል።

በሚቀጥለው ክረምት ውሉ የሚጠናቀቀው ዳኒሎ ከናፖሊ ጋር ግንኙነት በማድረጉ እንደ አንበል የተጣለበትን እምነት ጥሷል በሚል በክለቡ መወቀሱ ተገልጿል።

የኋላ መስመሩ በጉዳት ምክንያት የሳሳው ጁቬንቱስ በቀጣይ ሁለት ተከላካዮችን ለማስፈረም ጥረት እንደሚያደርግ ተዘግቧል።

@Tikvahethsport    @kidusyoftahe
TIKVAH-SPORT
“ ባሎን ዶር ፍትሀዊ አልነበረም “ ሮናልዶ ፖርቹጋላዊው ተጨዋች ክርስቲያኖ ሮናልዶ ሮድሪ ያሸነፈው የዘንድሮው የባሎን ዶር ሽልማት ፍትሀዊ አልነበረም በማለት ተናግሯል። “ ቪኒሰስ ጁኒየር ባሎን ዶሩን ማሸነፍ ነበረበት “ የሚለው ሮናልዶ ሽልማቱ ፍትሀዊ እንዳልነበረ በሁሉም ፊት እናገራለሁ በማለት አስተያየቱን ሰጥቷል። " የግሎብ ሶከር አዋርድን የምወደው በዚህ ምክንያት ነው እነሱ እውነተኛ ታማኞች…
“ ሮናልዶ የሰጠው አስተያየት አስገርሞኛል “ ሮድሪ

ስፔናዊው የባሎን ዶር አሸናፊ ተጨዋች ሮድሪ ክርስቲያኖ ሮናልዶ የዘንድሮው የባሎን ዶር ሽልማት “ ፍትሀዊ አልነበረም “ ማለቱ እንዳስገረመው ተናግሯል።

ክርስቲያኖ ሮናልዶ ከቀናት በፊት የዘንድሮው የባሎን ዶር ሽልማት ፍትሐዊ እንዳልነበረ እና ለቪኒሰስ ጁኒየር ይገባው እንደነበር ገልፆ ነበር።

“ ሮናልዶ ያንን መናገሩ አስገርሞኛል “ የሚለው ሮድሪ በበኩሉ “ ምክንያቱም እሱ ከሁሉም በላይ ሽልማቱ እንዴት እንደሚሰራ እና አሸናፊው እንዴት እንደሚመረጥ ያውቃል “ ብሏል።

" ጋዜጠኞቹ በዚህ አመት እኔ እንዳሸንፍ መርጠዋል ፤ ምናልባት ሮናልዶ እንዲያሸንፍ መርጠው የነበሩ ይሆናሉ በእሱ ግን ይስማማል ብዬ አስባለሁ።" ሮድሪ

@Tikvahethsport    @kidusyoftahe
2025/01/10 12:57:29
Back to Top
HTML Embed Code: