Telegram Web Link
“ ጎሉ በራስ መተማመን ጨምሮልኛል “ ሜሪኖ

ስፔናዊው የመድፈኞቹ አማካይ ሚኬል ሜሪኖ ትላንት ምሽት ብሬንትፎርድ ላይ ያስቆጠረው ግብ በራስ መተማመኑን እንዳሳደገለት ተናግሯል።

ግቡ ከምንም በላይ ቡድኑ እንዲያሸንፍ በመረዳቱ መደሰቱን የገለፀው ሚኬል ሜሪኖ አክሎም “ ጎል ትልቅ በራስ መተማመን ሰጥቶኛል “ ሲል ተደምጧል።

“ አመቱን በጥሩ መንገድ የጀመርን ይመስላል በዚህ መንገድ መቀጠል አለብን “ ሲል ተጨዋቹ ጨምሮ ተናግሯል።

@Tikvahethsport    @kidusyoftahe
አስቶን ቪላ ተጨዋች ሊያስፈርም ነው !

የፕርሚየር ሊጉ ክለብ አስቶን ቪላ የቦርስያ ዶርትመንዱን የፊት መስመር ተጨዋች ዶንዬል ማለን ለማስፈረም ንግግር ላይ መሆናቸውን ዘ አትሌቲክ አስነብቧል።

አስቶን ቪላ ለተጨዋቹ ዝውውር 18 ሚልዮን ዩሮ የዝውውር ሒሳብ እና ታይቶ የሚጨመር ክፍያ ማቅረባቸው ተነግሯል።

ክለቡ ለ 25ዓመቱ ተጨዋች ማለን ያቀረበው የዝውውር ሒሳብ ዶርትመንድ ከሚጠብቀው ዋጋ ያነሰ ቢሆንም ሁለቱ ክለቦች ድርድር ላይ መሆናቸው ተዘግቧል።

በአሰልጣኝ ኡናይ ኤምሬ የሚመራው አስቶን ቪላ የፊት መስመሩን ለማጠናከር በመንቀሳቀስ ላይ መሆናቸው ተገልጿል።

@Tikvahethsport    @kidusyoftahe
የፕርሚየር ሊግ የወሩ ምርጥ ተጨዋች ማን ይሆናል ?

የእንግሊዝ ፕርሚየር ሊግ የ 2024/25 የውድድር ዘመን የወርሀ ታኅሣሥ የወሩ ምርጥ ተጨዋች ስምንት እጩዎች ይፋ ተደርገዋል።

በዚህም መሰረት :-

አሌክሳንደር አርኖልድ

ጊብስ ዋይት

ሁይጅሰን

አሌክሳንደር አይሳክ

ሙርፊ

ኮል ፓልመር

መሐመድ ሳላህ እና

ሮቢንሰን በእጩነት መቅረብ ችለዋል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
የፕርሚየር ሊግ የወሩ ምርጥ አሰልጣኝ ማን ይሆናል ?

የእንግሊዝ ፕርሚየር ሊግ የ 2024/25 የውድድር ዘመን የወርሀ ታኅሣሥ የወሩ ምርጥ አሰልጣኝ አራት እጩዎች ይፋ ተደርገዋል።

በዚህም መሰረት :-

አሰልጣኝ ኑኖ እስፕሪቶ ሳንቶ

አንዶኒ ኢራኦላ

አሰልጣኝ ኤዲ ሀው እና

አሰልጣኝ አርኔ ስሎት በእጩነት መቅረብ ችለዋል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
Forwarded from WANAW SPORT (Wanaw Sportswear)
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
“ እግርኳስ በጣም ቀላል ነገር ነው “ ሰርጂዮ ኮንሴሳኦ

" እኔ ፍልስፍና የለኝም ማሸነፍ ነው ፍላጎቴ “

ኤሲ ሚላንን በሀላፊነት የተረከቡት ፖርቹጋላዊው አሰልጣኝ ሰርጂዮ ኮንሴሳኦ የሚከተሉት ፍልስፍና አለመኖሩን በሰጡት አስተያየት ገልጸዋል።

“ እኔ ፈላስፋ አይደለሁም የምከተለው ፍልስፍናም የለም “ የሚሉት አሰልጣኝ ሰርጂዮ ኮንሴሳኦ “ እኔ ብቸኛ ፍላጎቴ ጨዋታዎችን ማሸነፍ ነው “ ብለዋል።

ከቀናት በፊት ቡድኑን በሀላፊነት የተረከቡት አሰልጣኝ ሰርጂዮ ኮንሴሳኦ “ ውጤት ማምጣት እፈልጋለሁ “ በማለት ተናግረዋል።

ሰርጂዮ ኮንሴሳኦ አክለውም “ እግርኳስ በጣም ቀላል ነገር ነው “ ያሉ ሲሆን “ ግብ እንድታስቆጥር አንድ ጎል ተቀምጦልሀል ግብ እንዳይቆጠርብህ ደግሞ ሌላ አንድ ጎል አለ ከባድ ነገር አይደለም።“ ብለዋል።

ነገ በሱፐር ኮፓ ኢጣልያ ጁቬንቱስን የሚገጥሙት አሰልጣኙ ሁለቱ ክለቦች ለመጨረሻ ጊዜ ባደረጉት ጨዋታ “ ሁለት መሸነፍ የፈለጉ ቡድኖች ናቸው የታዩኝ “ ሲሉ ገልጸዋል።

አሰልጣኙ ተጨዋቾቹን ወጣ ያለ ጠንካራ ልምምድ በቀን ሁለት ጊዜ በሳውዲ አረቢያ ሪያድ በማሰራት ላይ መሆናቸው ተገልጿል።

@Tikvahethsport    @kidusyoftahe
ፕርሚየር ሊጉ ለአራት ሳምንታት ሊራዘም ይችላል !

አዲሱ የአለም ክለቦች ዋንጫ ውድድር በሚቀጥለው ክረምት በአሜሪካ አዘጋጅነት እንደሚካሄድ ይጠበቃል።

ከእንግሊዝ ፕርሚየር ሊግ ክለቦች ማንችስተር ሲቲ እና ቼልሲ የውድድሩ ተካፋይ እንደሚሆኑም ይጠበቃል።

ቼልሲ ወይም ማንችስተር ሲቲ ለውድድሩ ፍፃሜ የሚደርሱ ከሆነ አዲሱ የእንግሊዝ ፕርሚየር ሊግ ውድድር መጀመሪያ ቀን እንደሚራዘም ተገልጿል።

የፕርሚየር ሊጉ ዋና ሀላፊ ሪቻርድ ማስተርስ “ ከሁለቱ ክለቦች አንዱ ለፍፃሜ የሚደርሱ ከሆኑ ፕርሚየር ሊጉ ከፍፃሜው በኋላ ለአራት ሳምንታት ይራዘማል “ ብለዋል።

አዲሱ የእንግሊዝ ፕርሚየር ሊግ መጀመሪያ ቀን ከአለም ክለቦች ዋንጫ ውድድር በኋላ አጭር የእረፍት ጊዜ በመሆን ማንችስተር ሲቲ እና ቼልሲ ቅሬታ ሲያቀርቡ ነበር።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
የጣልያን ሱፐር ካፕ አሸናፊ ስንት ያገኛል ?

የጣልያን ሱፐር ካፕ ውድድር በአራት ክለቦች መካከል በሳውዲ አረቢያ ሪያድ ዛሬ ምሽት ጀምሮ ይካሄዳል።

በውድድሩ የሴርያው እና ኮፓ ኢጣልያ ውድድሮችን አንደኛ እና ሁለተኛ ደረጃን በመያዝ ያጠናቀቁት

- ኢንተር ሚላን
- ጁቬንቱስ
- ኤሲ ሚላን
- አታላንታ ይሳተፋሉ።

የውድድሩ አሸናፊዎች ስንት ያገኛሉ ?

ከግማሽ ፍፃሜ የሚሰናበቱ :- 1.2 ሚልዮን ዩሮ
የፍፃሜ ተፋላሚ :- 5 ሚልዮን ዩሮ
የዋንጫ አሸናፊ :- 8 ሚልዮን ዩሮ እንደሚያገኙ ተገልጿል።

የጨዋታ መርሐግብሩ ምን ይመስላል ?

ዛሬ ምሽት 4:00 :- ኢንተር ሚላን ከ አታላንታ
አርብ ምሽት 4:00 :- ጁቬንቱስ ከ ኤሲ ሚላን

የፍፃሜ ጨዋታ :- ሰኞ ምሽት 4:00

ለአምስተኛ ጊዜ በሳውዲ አረቢያ የሚካሄደው የጣልያን ሱፐር ካፕ ውድድር ያለፉት ሶስት አመታት በኢንተር ሚላን አሸናፊነት መጠናቀቃቸው ይታወሳል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
ማርከስ ራሽፎርድ ወደ ሳውዲ አረቢያ ?

እንግሊዛዊው የማንችስተር ዩናይትድ የፊት መስመር ተጨዋች ማርከስ ራሽፎርድ ከሳውዲ አረቢያ ሊግ የዝውውር ጥያቄዎች እንደቀረበለት ዴይሊ ሜል ዘግቧል።

ማርከስ ራሽፎርድ ከሳውዲ አረቢያ የቀረቡለትን ሶስት የዝውውር ጥያቄዎች ውድቅ ማድረጉ ተያይዞ ተገልጿል።

የሳውዲ አረቢያ ክለቦች ለማርከስ ራሽፎርድ በአመት 35 ሚልዮን ፓውንድ የሚያስገኝለት ጥያቄ አቅርበውለት እንደነበር እየተዘገበ ይገኛል።

ራሽፎርድ በቀጣይ ማንችስተር ዩናይትድን የሚለቅ ከሆነ በትልቅ ሊግ የመጫወት ፍላጎት እንዳለው ተነግሯል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
“ አርኖልድ ጥፋተኛ ሊደረግ አይገባም “ አለን ሺረር

የቀድሞ እንግሊዛዊ ተጨዋች አለን ሺረር አሌክሳንደር አርኖልድ ሪያል ማድሪድን ለመቀላቀል ከወሰነ እጅ ሊቀሰርበት አይገባም በማለት አስተያየቱን ሰጥቷል።

“ ከሊቨርፑል ጋር ሁሉንም ነገር አሳክቷል ፤ አሁን ደግሞ ሪያል ማድሪድ ጥያቄ አቅርቦለታል ሁኔታውን በእሱ ቦታ ሆነን መመልከት አለብን “ ሲል አለን ሺረር ተናግሯል።

“ አርኖልድ በሚወስነው ውሳኔ ጣት ሊቀሰርበት እና ተጠያቂ ሊደረግ አይገባም “ የሚለው አለን ሺረር እሱ ላይ ምንም መጥፎ እሳቤዎች እንደማይኖሩ ተስፋ አደርጋለሁ ብሏል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
ኢንተር ሚላን ለፍፃሜ ደርሰዋል !

የጣልያን ሱፐር ካፕ ግማሽ ፍፃሜ ጨዋታ በሳውዲ አረቢያ ሪያድ ሲካሄድ ኢንተር ሚላን ለፍፃሜ መድረሳቸውን አረጋግጠዋል።

በአሰልጣኝ ሲሞን ኢንዛጊ የሚመራው ኢንተር ሚላን ከአታላንታ ጋር ያደረገውን ጨዋታ 2ለ0 በሆነ ውጤት መርታት ችሏል።

የኢንተር ሚላንን የማሸነፊያ ግቦች ዴንዜል ዱምፍሪስ 2x ከመረብ ማሳረፍ ችሏል።

ኢንተር ሚላን በፍፃሜው የፊታችን ሰኞ ምሽት 4:00 የጁቬንቱስ እና ኤሲ ሚላንን አሸናፊ የሚገጥሙ ይሆናል።

@Tikvahethsport    @kidusyoftahe
ተመላሽ እያደረግን ነው! 🔥
ሽንፈት? አይታሰብም!!!!!
በየቀኑ ለአምስት እድለኞች 500 ብር እየሸለምን ነው።
ውርርዱ ባይሳካም አምስት መቶ ብር የግልዎ ይሆናል። ይወራረዱ!
ቢሸነፉም በተመላሽ ያሸንፉ!
Forwarded from Can PlayStation (CAN PlayStation Manager)
ታላቅ የገና ስጦታ እስከ ጥር 4ሚቆይ ቅናሽ

Exchange Available (ባሎት PlayStation ላይ  ጨምረው መቀየር ይችላሉ)

PlayStation 4 Slim በቅናሽ ዋጋ ከCan PlayStation ይግዙ

Ps4 Slim
2 Orginal jestic
5 Game installed
Storage 500gb
HD quality resolution
Version 12.00
Full accessories
1 years guarantee

ዋጋ=35,000

አድራሻ፦
ቁጥር 1  መገናኛ ሱቅ የአድራሻ ለውጥ በቅርቡ ስለምናደርግ ከመምጣቶ በፊት አስቀድመው ይደውሉ
   
ቁጥር 2   ቦሌ Celavi burger አጠገብ ዘንባባ ህንፃ  ምድር ላይ


ስልክ፦ 0910529770 ወይም                  0977349492
0914646972  ይደውሉ
Telegram channel ፦
https://www.tg-me.com/CanPlaystation

                       👍Update Your Life
“ አርሰናልን ለማሸነፍ በድፍረት መጫወት አለብን “

የብራይተኑ ዋና አሰልጣኝ ፋብያን ሁርዜለር ቡድናቸው በፕርሚየር ሊጉ የትኛውንም ክለብ ማሸነፍ እንደሚችል ያሳየ መሆኑን ተናግረዋል።

“ አርሰናልን ለማሸነፍ ከፈለግን በሁሉም አጋጣሚዎች ያለንን አቅም በሙሉ መጠቀም ያስፈልጋል “ ያሉት አሰልጣኙ “ በድፍረት መጫወት አለብን ካልሆነ እድል አይኖረንም “  ብለዋል።

ባለፉት ጨዋታዎች ውጤቶች ጥሩ አይደሉም ነገርግን እንቅስቃሴያችን ጥሩ ነበር ፤ በዚህ ሊግ የትኛውንም ቡድን ማሸነፍ እንደምንችል አሳይተናል።“ ፋብያን ሁርዜለር

ብራይተን ነገ ምሽት 2:30 በሜዳው ከአርሰናል ጋር ተጠባቂ ጨዋታውን የሚያደርግ ይሆናል።

@Tikvahethsport    @kidusyoftahe
“ ከሻምፒየንስ ሊግ በላይ ሊጉን ማሸነፍ እፈልጋለሁ “ ሳላህ

የሊቨርፑሉ የፊት መስመር ተጨዋች መሐመድ ሳላህ በዚህ አመት ለእሱ የፕርሚየር ሊግ ዋንጫ ከሻምፒየንስ ሊግ የበለጠ ቦታ እንዳለው ተናግሯል።

“ በዚህ አመት ሊጉን ማሸነፍ እፈልጋለሁ “ የሚለው ሳላህ አክሎም “ እንደ ቡድንም አላማችን ነው ፤ በዚህ አመት ከሻምፒየንስ ሊግ በበለጠ ፕርሚየር ሊጉን ማሸነፍ እፈልጋለሁ “ ብሏል።

ስለ ባሎን ዶር ሀሳቡን የሰጠው ተጨዋቹ “ ባሎን ዶር ማሸነፍ እና የአለም ምርጥ መሆን ከባድ ነው ሰዎች የተለያየ ምርጫ ነው ያላቸው “ ሲል ተደምጧል።

ሳላህ አክሎም “ እኔ ሁልጊዜም ራሴን ምርጥ አድርጌ ነው የምመለከተው ለቡድኑ ያኝን ሁሉ መስጠት እፈልጋለሁ “ በማለት ተናግሯል።

@Tikvahethsport    @kidusyoftahe
ቶማስ ቱሄል የሊጉን ጨዋታ ይታደማሉ !

ጀርመናዊው አሰልጣኝ ቶማስ ቱሄል አሰልጣኝ ጋሪዝ ሳውዝጌትን በመተካት የእንግሊዝ ብሔራዊ ቡድን አሰልጣኝ በመሆን መሾማቸው ይታወቃል።

አሰልጣኝ ቶማስ ቱሄል ከሁለት ቀናት በፊት የሶስቱን አናብስት አሰልጣኝነት ሥራ በይፋ ጀምረዋል።

ቶማስ ቱሄል ነገ በምሳ ሰዓት መርሐ ግብር ቶተንሀም ከኒውካስል ዩናይትድ ጋር የሚያደርጉትን ጨዋታ ስታዲየም ተገኝተው ለመጀመሪያ ጊዜጰእንደሚከታተሉ ተገልጿል።

አሰልጣኝ ቶማስ ቱሄል በጨዋታው እንግሊዛዊዎቹን ጄምስ ማዲሰን ፣ ዶምኒክ ሶላንኬ ፣ አንቶኒ ጎርደን እና ሊዊስ ሀል የመመልከት እድል ያገኛሉ።

@Tikvahethsport    @kidusyoftahe
“ ተጨዋቾቹ ለዩናይትድ ለመጫወት ብቁ አይደሉም “ ጆን ኦቢ ሚኬል

የቀድሞ ናይጄሪያዊ የቼልሲ ተጨዋች ጆን ኦቢ ሚኬል ማንችስተር ዩናይትድ የገጠመው የአሰልጣኝ ችግር አለመሆኑን ገልጿል።

“ ደጋፊ ባይኮንም ማንችስተር ዩናይትድን መመልከት አስፈሪ ነው “ ጆን ኦቢ ሚኬል ነገርግን ችግሩ በፍፁም የአሰልጣኝ አይደለም በማለት ተናግሯል።

“ አሰልጣኝ ሩበን አሞሪም አስደናቂ ወጣት አሰልጣኝ ነው ችግሩ የእሱ አይደለም “ ሲል የቀድሞ ተጨዋቹ አክሎ ገልጿል።

የክለቡ ችግር ተጨዋቾች መሆናቸውን ከዚህ በፊት መናገሩን ያስታወሰው ጆን ኦቢ ሚኬል “ ለተጨዋቾቹ አዝናለሁ ነገርግን ለማንችስተር ዩናይትድ ለመጫወት ብቁ አይደሉም “ ብሏል።

@Tikvahethsport    @kidusyoftahe
ሊቨርፑል ተጫዋቾቹ ልምምድ ጀምረዋል !

የመርሲሳይዱ ክለብ ሊቨርፑል ፈረንሳዊ የተከላካይ ስፍራ ተጨዋች ኢብራሂም ኮናቴ ልምምድ መጀመሩን አሰልጣኝ አርኔ ስሎት አረጋግጠዋል።

ተጨዋቹ ክለቡ ከሪያል ማድሪድ ጋር በነበረው ጨዋታ ጉዳት አጋጥሞት ላለፉት ሳምንታት ከሜዳ ርቆ መቆየቱ የሚታወስ ነው።

በተጨማሪም ሌላኛው በጉዳት ላይ የሚገኘው ብራድሌይ በዛሬው እለት ልምምድ መስራት መጀመሩን አሰልጣኙ ገልጸዋል።

ጆ ጎሜዝ በበኩሉ በጥሩ ሁኔታ ላይ እንደማይገኝ የገለፁት አሰልጣኝ አርኔ ስሎት ለረጅም ጊዜ ከሜዳ ይርቃል ብለዋል።

@Tikvahethsport    @kidusyoftahe
ቤን ዋይት መቼ ወደ ሜዳ ይመለሳል ?

በጉዳት ላይ የሚገኘው የአርሰናሉ እንግሊዛዊ የተከላካይ ስፍራ ተጨዋች ቤን ዋይት ከአንድ ወር ባነሰ ጊዜ ውስጥ ወደ ጨዋታ ሊመለስ እንደሚችል ተገልጿል።

ስለ ተጨዋቹ ሁኔታ አስተያየታቸውን የሰጡት አሰልጣኝ ሚኬል አርቴታ “ ለመመለስ ጥቂት ሳምንት ብቻ ይቀሩታል ይህ ወር ሳይጠናቀቅ ይመለሳል “ ብለዋል።

ቶሚያሱ በበኩሉ ወደ ልምምድ መመለሱን ያረጋገጡት አሰልጣኝ ሚኬል አርቴታ ነገርግን ከረጅም ጉዳት እንደመመለሱ ጊዜ ያስፈልገዋል ሲሉ ተናግረዋል።

አሰልጣኝ ሚኬል አርቴታ አክለውም የፊት መስመር ተጨዋቹ ካይ ሀቨርትዝ ለነገው የብራይተን ጨዋታ ዝግጁ መሆኑን ገልጸዋል።

@Tikvahethsport    @kidusyoftahe
TIKVAH-SPORT
የዩናይትድ የወሩ ምርጥ ተጨዋች ማን ይሆናል በአሰልጣኝ ሩበን አሞሪም ማንችስተር ዩናይትዶች የወርሀ ታኅሣሥ የወሩ ምርጥ ተጨዋች #ሶስት እጩዎችን ይፋ አድርገዋል። በዚህም መሰረት :- አማድ ዲያሎ ሀሪ ማጓየር እና ማኑኤል ኡጋርቴ  የታኅሣሥ ወር የማንችስተር ዩናይትድ ምርጥ ተጨዋች እጩ ሆነው መቅረብ ችለዋል። የወሩ ምርጥ ተጨዋች ማን ይሆናል @tikvahethsport    …
የዩናይትድ የወሩ ምርጥ ተጨዋች ታውቋል !

በአሰልጣኝ ሩበን አሞሪም የሚመሩት ማንችስተር ዩናይትዶች የወርሀ ታኅሣሥ የወሩ ምርጥ ተጨዋቻቸውን ይፋ አድርገዋል።

በዚህም መሰረት ኮትዲቯራዊው የፊት መስመር ተጨዋች አማድ ዲያሎ የታኅሣሥ ወር የማንችስተር ዩናይትድ ምርጥ ተጨዋች ተብሎ መመረጥ ችሏል።

በተጨማሪም አማድ ዲያሎ ማንችስተር ሲቲ ላይ ያስቆጠረው ግብ የማንችስተር ዩናይትድ የታኅሣሥ ወር ምርጥ ግብ ተብሎ ተመርጧል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
2025/01/10 08:33:14
Back to Top
HTML Embed Code: