Telegram Web Link
ሲቲ ሲያሸንፍ ቼልሲ ነጥብ ጥሏል !

በእንግሊዝ ፕርሚየር ሊግ መርሐግብር ማንችስተር ሲቲ ዌስትሀም ዩናይትድን 4ለ1 ሲያሸንፍ ቼልሲ ከክሪስታል ፓላስ 1ለ1 ተለያይተዋል።

የማንችስተር ሲቲን የማሸነፊያ ግቦች ኤርሊንግ ሀላንድ 2x ፊል ፎደን እና ኩፋል በራሱ ግብ ላይ እንዲሁም ለዌስትሀም ፉልክሩግ አስቆጥረዋል።

የቼልሲን ግብ ኮል ፓልመር ሲያስቆጥር ማቴታ ክሪስታል ፓላስን አቻ አድርጓል።

የማንችስተር ሲቲው የፊት መስመር ተጨዋች ኤርሊንግ ሀላንድ በውድድር ዘመኑ አስራ ስድስተኛ የሊግ ግቡን አስቆጥሯል።

ቼልሲ ያለፉትን አራት ጨዋታዎች ማሸነፍ አልቻሉም።

በሌሎች ጨዋታዎች

- አስቶን ቪላ ሌስተር ሲቲን 2ለ1
- በርንማውዝ ኤቨርተንን 1ለ0 እንዲሁም
- ብሬንትፎርድ ሳውዝሀምፕተንን 5ለ0 ማሸነፍ ችለዋል።

የሊግ ደረጃቸው ምን ይመስላል ?

4️⃣ ቼልሲ :- 36 ነጥብ
6️⃣ ማንችስተር ሲቲ :- 34 ነጥብ
7️⃣ በርንማውዝ :- 33 ነጥብ
8️⃣ አስቶን ቪላ :- 32 ነጥብ

በቀጣይ የሊጉ መርሐግብር ?

ማክሰኞ - ቼልሲ ከ በርንማውዝ

ማክሰኞ - ብሬንትፎርድ ከ ማንችስተር ሲቲ

@tikvahethsport            @kidusyoftahe
አርሰናል ተጨዋቾቹ ህመም አጋጥሟቸዋል !

የመድፈኞቹ ተጨዋቾች ካይ ሀቨርትዝ እና ማርቲን ኦዴጋድ ህመም እንዳጋጠማቸው አሰልጣኝ ሚኬል አርቴታ አረጋግጠዋል።

ጀርመናዊው የፊት መስመር ተጨዋች ካይ ሀቨርትዝ ለሁለተኛ ተከታታይ ጨዋታ ከቡድኑ ስብስብ ውጪ ሆኗል።

አምበሉ ማርቲን ኦዴጋርድ በበኩሉ ከህመሙ ሙሉ ለሙሉ ባለማገገሙ በዛሬው ጨዋታ ተጠባባቂ ሆኖ የሚጀምር ይሆናል።

ማርቲን ኦዴጋርድ ከጉዳት ከተመለሰ ወዲህ ለመጀመሪያ ጊዜ ለአርሰናል በሊጉ ቋሚ ሆኖ #የማይጀመር ይሆናል።

@Tikvahethsport    @kidusyoftahe
ይገምቱ ይሸለሙ

የባርሴሎና እና ባርባስትሮን ጨዋታ ውጤት ገምተው በትክክል ላወቁ ሶስት ቤተሰቦቻችን የአንድ መቶ ብር ካርድ የምንሸልምዎ ይሆናል።

የውድድሩ ህጎች ምን ይመስላሉ ?

√ ተሳታፊዎች ግምቶቻቸውን ከዚህ ፖስት ስር ባለው የሀሳብ መስጫ ሳጥን #ብቻ ማስቀመጥ ይኖርባቸዋል።

√ ኤዲት የተደረጉ ምላሾች በፍፁም ተቀባይነት አይኖራቸውም።

√ ግምትዎን መላክ የሚቻለው እስከ 3:00 ሰዓት ብቻ ነው።

🔴 ይነበብ

አንድ የቤተሰባችን አባል ግምት ማስቀመጥ የሚችለው #አንዴ ብቻ ነው። ከአንድ ጊዜ በላይ የመለሰ ቤተሰባችን ሽልማት አይደርሰውም።

መልካም ዕድል !

@tikvahethsport    
ተጀመረ

ብራይተን 0-0 አርሰናል

@Tikvahethsport    @kidusyoftahe
“ ይህንን ጨዋታ አለማሸነፍ ያበሳጫል “ ሳንቾ

የሰማያዊዎቹ የፊት መስመር ተጨዋች ጄደን ሳንቾ ቡድናቸው የዛሬውን ጨዋታ ማሸነፍ አለመቻሉ እንዳበሳጨው ገልጿል።

“ ከዚህ ጨዋታ ሶስት ነጥብ ይዘን መውጣት አለመቻላችን በጣም ያበሳጫል “ ሲል ጄደን ሳንቾ ከጨዋታው በኋላ ተናግሯል።

“ እዚህ ባሳየሁት መሻሻል በጣም ደስተኛ ነኝ ከመጀመሪያው ጀምሮ እዚህ ምቾት ተሰምቶኛል ያለኝን ሁሉ ለቡድኑ መስጠት አለብኝ።“ ጄደን ሳንቾ

@Tikvahethsport    @kidusyoftahe
17 '

ብራይተን 0-1 አርሰናል

ንዋኔሪ

@Tikvahethsport    @kidusyoftahe
30 '

ብራይተን 0-1 አርሰናል

             ንዋኔሪ

@Tikvahethsport    @kidusyoftahe
41'

ብራይተን 0-1 አርሰናል

             ንዋኔሪ

@Tikvahethsport    @kidusyoftahe
እረፍት

ብራይተን 0-1 አርሰናል

             ንዋኔሪ

@Tikvahethsport    @kidusyoftahe
“ ጥሩ እንቅስቃሴ አላደረግንም “ ጋርዲዮላ

የማንችስተር ሲቲው ዋና አሰልጣኝ ፔፕ ጋርዲዮላ ቡድናቸው ዛሬ ሶስት ነጥብ ቢያሳካም ያደረገው እንቅስቃሴ እንዳላስደሰታቸው ገልጸዋል።

ማንችስተር ሲቲ ወደ አቋሙ ተመልሷል የሚል እምነት እንደሌላቸው የገለፁት አሰልጣኙ “ ዛሬ ጥሩ እንቅስቃሴ አላደረግንም “ በማለት ተናግረዋል።

አሰልጣኝ ፔፕ ጋርዲዮላ አክለውም “ አቻ በወጣንበት የኤቨርተን ጨዋታ ዛሬ ካደረግነው ጨዋታ በጣም የተሻልን ነበርን ሲሉ ተደምጠዋል።

@Tikvahethsport    @kidusyoftahe
51 '

ብራይተን 0-1 አርሰናል

             ንዋኔሪ

@Tikvahethsport    @kidusyoftahe
62 '

ብራይተን 1-1 አርሰናል

ፔድሮ             ንዋኔሪ

@Tikvahethsport    @kidusyoftahe
ናፖሊ የሊጉን መሪነት ተረከበ !

በጣልያን ሴርያ የአስራ ዘጠነኛ ሳምንት መርሐ ግብር ናፖሊ ከፊዮሬንቲና ጋር ያደረጉትን ጨዋታ 3ለ0 በሆነ ውጤት በማሸነፍ የሴርያውን መሪነት ተረክበዋል።

የናፖሊን የማሸነፊያ ግቦች ኔሬስ ፣ ሮሜሉ ሉካኩ እና ስኮት ማክ ቶሚናይ አስቆጥረዋል።

የቡድኖቹ ደረጃ ምን ይመስላል ?

1⃣ ናፖሊ - 44 ነጥብ
6️⃣ ፊዮሬንቲና - 32 ነጥብ

ቀጣይ መርሐ ግብር ?

እሁድ - ናፖሊ ከ ሄላስ ቬሮና

ሰኞ - ሞንዛ ከ ፊዮሬንቲና

@Tikvahethsport    @kidusyoftahe
72 '

ብራይተን 1-1 አርሰናል

ፔድሮ             ንዋኔሪ

@Tikvahethsport    @kidusyoftahe
90 '

ብራይተን 1-1 አርሰናል

ፔድሮ             ንዋኔሪ

@Tikvahethsport    @kidusyoftahe
መድፈኞቹ ነጥብ ጥለዋል !

የሰሜን ለንደኑ ክለብ አርሰናል ከብራይተን ጋር ያደረጉትን የፕርሚየር ሊግ መርሐግብር 1ለ1 በሆነ አቻ ውጤት አጠናቀዋል።

የአርሰናልን የመሪነት ግብ ኢታን ንዋኔሪ ከመረብ ሲያሳርፍ ጇ ፔድሮ ብራይተንን አቻ ማድረግ ችሏል።

ብራይተን ያለፉትን ስምንት የፕርሚየር ሊግ ጨዋታዎች ማሸነፍ አልቻሉም ስድስቱን ጨዋታዎች በአቻ ውጤት አጠናቀዋል።

አርሰናል ከሶስት ተከታታይ የፕርሚየር ሊግ ድል በኋላ ነጥብ ጥለዋል።

የሊግ ደረጃቸው ምን ይመስላል ?

2️⃣ አርሰናል :- 40 ነጥብ
1️⃣0️⃣ ብራይተን :- 28 ነጥብ

በቀጣይ የሊጉ መርሐግብር ?

ረቡዕ - አርሰናል ከ ቶተንሀም

ሐሙስ - ኢፕስዊች ታውን ከ ብራይተን

@Tikvahethsport    @kidusyoftahe
ባርሴሎና ቀጣዩን ዙር ተቀላቀለ !

የካታላኑ ክለብ ባርሴሎና ከባርባስትሮ ጋር ያደረገውን የስፔን ኮፓ ዴላሬ ጨዋታ 4ለ0 በሆነ ሰፊ ውጤት ማሸነፍ ችሏል።

ለባርሴሎና የማሸነፊያ ግቦችን ሮበርት ሌዋንዶውስኪ 2x ፣ ጋርሺያ እና ፓብሎ ቶሬ ማስቆጠር ችለዋል።

ይህንንም ተከትሎ ባርሴሎና በስፔን ኮፓ ዴላሬ አስራ ስድስት ውስጥ መቀላቀል ችሏል።

ሮበርት ሌዋንዶውስኪ በዘንድሮው የውድድር ዘመን በሁሉም ውድድሮች ለባርሴሎና 2️⃣5️⃣ኛ ግቡን አስቆጥሯል።

የ 16ዓመቱ ተጨዋች ቶኒ ፈርናንዴዝ ከላሚን ያማል ቀጥሎ ለባርሴሎና ተሰልፎ መጫወት የቻለ ሁለተኛው በእድሜ ትንሹ ተጨዋች ሆኗል።

@Tikvahethsport    @kidusyoftahe
“ በህይወቴ እንደዚህ አይነት ውሳኔ አይቼ አላውቅም “ አርቴታ

የመድፈኞቹ ዋና አሰልጣኝ ሚኬል አርቴታ ቡድናቸው ዛሬ ምሽት የተሰጠበት ፍፁም ቅጣት ምት ውሳኔ ታይቶ የማይታወቅ ነው ሲሉ ገልጸዋል።

“ በህይወቴ እንደዚህ አይነት ውሳኔ አይቼ አላውቅም “ የሚሉት ሚኬል አርቴታ “ ተጨዋቾቹ አይተው ያውቁ እንደሆነ ጠይቄያቸው ነበር እነሱም አይተው አያውቁም “ ሲሉ ተናግረዋል።

አሰልጣኝ ሜኬል አርቴታ አክለውም “ በፍፁም ቅጣት ምቱ በጣም ተበሳጭተናል በጭራሽ አያሰጥም ነበር “ ሲሉ ተደምጠዋል።

የብራይተኑ ዋና አሰልጣኝ ፋብያን ሁርዜለር በበኩላቸው “ አርቴታ ለምን ያንን እንዳሉ አልገባኝም “ ያሉ ሲሆን “ ፍፁም ቅጣት ምቱ ግልጽ እና ትክክለኛ ነበር “ ብለዋል።

@Tikvahethsport    @kidusyoftahe
2025/01/05 02:07:25
Back to Top
HTML Embed Code: