Telegram Web Link
TIKVAH-SPORT
ሮናልዶ ናዛሪዮ ለፕሬዝዳንትነት ሊወዳደር ይችላል ! የቀድሞ የብራዚል ብሔራዊ ቡድን እና ሪያል ማድሪድ ታሪካዊ ተጨዋች ሮናልዶ ናዛሪዮ ለብራዚል እግርኳስ ፌዴሬሽን ፕሬዝዳንትነት ለመወዳደር እያሰበ እንደሚገኝ ተነግሯል። ሮናልዶ ናዛሪዮ በዋናነት ሀላፊነቱን የፈለገው አሰልጣኝ ፔፕ ጋርዲዮላ የብራዚል ብሔራዊ ቡድን አሰልጣኝ አድርጎ ለመሾም እንደሆነ የሀገሪቱ መገናኛ ብዙሀን አስነብበዋል። የብራዚል…
" የብራዚላዊያንን እግርኳስ ክብር መመለስ እፈልጋለሁ “ ሮናልዶ ናዛሪዮ

የቀድሞ የብራዚል ብሔራዊ ቡድን እና ሪያል ማድሪድ ታሪካዊ ተጨዋች ሮናልዶ ናዛሪዮ ለብራዚል እግርኳስ ፌዴሬሽን ፕሬዝዳንትነት እንደሚወዳደር በይፋ አስታውቋል።

ሮናልዶ ናዛሪዮ በቀጣይ የብራዚል ብሔራዊ ቡድን እና የሀገሪቱን እግርኳስ ክለቦች ለማገዝ በፕሬዝዳንታዊ ምርጫው ለመሳተፍ ወስኛለሁ ሲል አረጋግጧል።

" የብራዚላዊያንን የእግርኳስ ክብር ወደነበረበት መመለስ እፈልጋለሁ “ ሲል ሮናልዶ ናዛሪዮ በሰጠው አስተያየት ተናግሯል።

ሮናልዶ ናዛሪዮ ምርጫውን ካሸነፈ ፔፕ ጋርዲዮላን የብራዚል ብሔራዊ ቡድን አሰልጣኝ አድርጎ ለመሾም ጥረት ሊያደርግ እንደሚችል ተገልጿል።

የብራዚል እግርኳስ ፌዴሬሽን ፕሬዝዳንት ምርጫ በቀጣይ አመት 2025 መጀመሪያ ላይ ይካሄዳል ተብሎ እንደሚጠበቅ ተነግሯል።

@tikvahethsport            @kidusyoftahe
“ ቼልሲ ትልቅ ቡድኖች ማሸነፍ አለበት “ ቴሪ ሄንሪ

የቀድሞ ፈረንሳዊ ተጨዋች ቴሪ ሄንሪ ቼልሲ እንደ ዋንጫ ተፎካካሪ እንዲታሰብ ትልቅ ቡድኖችን ማሸነፍ እንዳለበት በሰጠው አስተያየት ተናግሯል።

" ቼልሲ እስካሁን ትልቅ ቡድን ማሸነፍ አልቻለም “ የሚለው ቴሪ ሄንሪ ሊቨርፑል ፣ አርሰናል እና ማንችስተር ሲቲን ማሸነፍ እንደምትችሉ አሳዩን ሲል ተደምጧል።

በስካይ ስፖርት ተንታኝነት እያገለገለ የሚገኘው ሌላኛው የቀድሞ ተጨዋች ጄሚ ካራገር በበኩሉ “ ቼልሲ በዚህ አመት ሊጉን ማሸነፍ አይችልም “ ሲል ተናግሯል።

ክለቡ ያለበት የግብ ጠባቂ እና የመሐል ተከላካይ ክፍተት ዋንጫውን ከማለም እንደሚያግደው ጄሚ ካራገር ጨምሮ ገልጿል።

@tikvahethsport            @kidusyoftahe
ዳኒ ኦልሞ ባርሴሎናን በነፃ ሊለቅ ይችላል !

ስፔናዊው የመሐል ሜዳ ተጨዋች ዳኒ ኦልሞ ባርሴሎና ያለበትን የፋይናንስ ችግር ማስተካከል የማይችል ከሆነ ከጥር በኋላ በሊጉ መመዝገብ እንደማይችል ተገልጿል።

ባርሴሎና ባለፈው ክረምት ከሊጉ የፋይናንስ ህግ ጋር በተያያዘ ተጫዋቹን ለማስመዝገብ ተቸግረው እንደነበር የሚታወስ ነው።

ባርሴሎና በወቅቱ ተጨዋቾቹ መጎዳታቸውን ተከትሎ ዳኒ ኦልሞን እስከ ጥር ወር ማስመዝገብ መቻላቸው አይዘነጋም።

አሁን ላይ ባርሴሎና ባለፈው የፋይናንስ ሁኔታ ዳኒ ኦልሞ ከ 2025 በኋላ በላሊጋው የተጨዋቾች ዝርዝር ውስጥ ማካተት እንደማይችል ተነግሯል።

ዩኤፋ በበኩሉ በሀገር ውስጥ ሊግ ውድድር በክለቦቻቸው ስር ያልተመዘገቡ ተጨዋች በሚያዘጋጃቸው ውድድሮች እንዲሰለፉ እንደማይፈቅድ ተነግሯል።

ይህንንም ተከትሎ 60 ሚልዮን ዩሮ ወጥቶበት ባርሴሎናን የተቀላቀለው ዳኒ ኦልሞ በነፃ ክለቡን ሊለቅ እንደሚችል ዘ አትሌቲክ ዘግቧል።

@tikvahethsport      @kidusoyoftahe
ሊቨርፑል ተጨዋቹ ልምምድ አልሰራም !

የመርሲሳይዱ ክለብ ሊቨርፑል የፊት መስመር ተጨዋች ዲያጎ ጆታ ትላንት ልምምድ መስራት እንዳልቻለ አሰልጣኝ አርኔ ስሎት ተናግረዋል።

ተጨዋቹ ከረጅም ጊዜ ጉዳት ወደ ሜዳ ተመልሶ በሳምንቱ መጨረሻ ለሊቨርፑል ግብ ማስቆጠር መቻሉ ይታወሳል።

“ ጆታ ከፉልሀም ጨዋታ በኋላ የህመም ስሜት ነበረው ትላንት ልምምድ አልሰራም ዛሬ ከሰራ እናየዋለን ነገርግን በቋሚነት ጨዋታውን መጀመር አይችልም።"ሲሉ አርኔ ስሎት ተናግረዋል።

አሰልጣኙ አያይዘውም ሲሚካስ ልምምድ መጀመሩን ገልፀው ብራድሌይ እና ኢብራሂም ኮናቴ ወደ ልምምድ አለመመለሳቸውን ተናግረዋል።

ሊቨርፑል ነገ ምሽት 5:00 ከሳውዝሀምፕተን ጋር የካራባኦ ካፕ ሩብ ፍፃሜ ጨዋታውን የሚያደርግ ይሆናል።

@Tikvahethsport    @kidusyoftahe
ሙድሪክ በጊዜያዊነት ከእግርኳስ ታገደ !

ዩክሬናዊው የምዕራብ ለንደኑ ክለብ ቼልሲ የፊት መስመር ተጨዋች ማይካሎ ሙድሪክ ያልተፈቀደ አበረታች ንጥረ ነገር በውስጡ መገኘቱ ተገልጿል።

የእንግሊዝ እግርኳስ ማህበር ባደረገው ምርመራ " positive " ሆኖ መገኘቱ የተገለጸው ተጨዋቹ በጊዜያዊነት ከእግርኳስ መታገዱን ክለቡ አሳውቋል።

ማይካሎ ሙድሪክ እያወቀ የተከለከለ ንጥረ ነገር አለመውሰዱን ማረጋገጡን ቼልሲ ባወጣው መግለጫ አስታውቀዋል።

ቼልሲ በመግለጫው አክሎም ማይካሎ ሙድሪክ እና ክለባችን ጉዳዩን በተመለከተ ከሚመለከተው አካል ጋር በትብብር ለመስራት ዝግጁ ነን ብሏል።

ተጨዋቹ ያለፉት አምስት የክለቡ ጨዋታዎች እንዳመለጡት የሚታወስ ሲሆን አሰልጣኝ ኢንዞ ማሬስካ በህመም እንደሆነ ገልፀው ነበር።

@Tikvahethsport    @kidusyoftahe
TIKVAH-SPORT
ሙድሪክ በጊዜያዊነት ከእግርኳስ ታገደ ! ዩክሬናዊው የምዕራብ ለንደኑ ክለብ ቼልሲ የፊት መስመር ተጨዋች ማይካሎ ሙድሪክ ያልተፈቀደ አበረታች ንጥረ ነገር በውስጡ መገኘቱ ተገልጿል። የእንግሊዝ እግርኳስ ማህበር ባደረገው ምርመራ " positive " ሆኖ መገኘቱ የተገለጸው ተጨዋቹ በጊዜያዊነት ከእግርኳስ መታገዱን ክለቡ አሳውቋል። ማይካሎ ሙድሪክ እያወቀ የተከለከለ ንጥረ ነገር አለመውሰዱን ማረጋገጡን…
“ ምንም የተከለከለ ነገር አልተጠቀምኩም " ሙድሪክ

የቼልሲው ተጨዋች ማይካሎ ሙድሪክ የተከለከለ ንጥረነገር አለመጠቀሙን በማህበራዊ ትስስር ገፁ ባሰፈረው መልዕክት ገልጿል።

የሰጠው ናሙና የተከለከለ ንጥረነገር መጠቀሙን እንደሚያሳይ የእንግሊዝ ኤፍኤ እንዳሳወቀው ያረጋገጠው ሙድሪክ “ እኔ ግን ተጠቅሜ አላውቅም " ሲል ተናግሯል።

የተነገረው ነገር እንዳስደነገጠው የገለፀው ተጨዋቹ “ እንዴት ሊሆን እንደቻለ ለማጣራት ከክለቤ ጋር በቅርበት እየሰራሁ ነው " ብሏል።

አሁን እየደረገ ያለው ምርመራ ሚስጥራዊ በመሆኑ ምንም ተጨማሪ ነገር መናገር አልችልም ነገርግን በቅርቡ ይሆናል ሲል ተጨዋቹ ተናግሯል።

“ ምንም የተሳሳተ ነገር የሰራሁት እንደሌለ አውቃለሁ ስለዚህ በቅርቡ ወደ እግርኳስ እንደምመለስ ሙሉ ተስፋ አለኝ።" ሙድሪክ

@Tikvahethsport    @kidusyoftahe
የሊቨርፑል እና ቶተንሀምን ጨዋታ ማን ይመራዋል ?

የፊታችን እሁድ በሊቨርፑል እና ቶተንሀም መካከል የሚደረገውን ተጠባቂ የፕርሚየር ሊግ መርሐ ግብር የሚመሩት ዳኛ ታውቀዋል።

እሁድ ምሽት 1:30 በቶተንሀም ሆትስፐርስ ስታዲየም የሚደረገውን ተጠባቂ ጨዋታ ሳም ባሮት በመሐል ዳኝነት እንደሚመሩት ይፋ ተደርጓል።

ጨዋታውን ማን ያሸንፋል

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
TIKVAH-SPORT
ቶተንሀም በይፋ ይግባኝ ጠየቁ ! የሰሜን ለንደኑ ክለብ ቶተንሀም ተጨዋቻቸው ሮድሪጎ ቤንታንኩር ላይ የተላለፈው ቅጣት ተገቢ አይደለም በሚል ይግባኝ መጠየቃቸውን አስታውቀዋል። ሮድሪጎ ቤንታንኩር ከመገናኛ ብዙሀን ጋር በነበረው ቆይታ በቡድን አጋሩ ላይ ያልተገባ ነገር ተናግሯል በሚል የሰባት ጨዋታዎች እገዳ ቅጣት እንደተጣለበት ይታወቃል። ክለቡ አሁን ላይ ባወጣው መግለጫ የተጨዋቹ ድርጊት ጥፋተኝነት…
ቶተንሀም ያቀረበው ይግባኝ ውድቅ ሆነ !

የሰሜን ለንደኑ ክለብ ቶተንሀም ተጨዋቻቸው ሮድሪጎ ቤንታንኩር ላይ የተላለፈው ቅጣት ተገቢ አይደለም በሚል ያቀረቡት ይግባኝ ውድቅ መሆኑ ተገልጿል።

ሮድሪጎ ቤንታንኩር በቡድን አጋሩ ሰን ሁንግ ሚን ላይ ያልተገባ ነገር ተናግሯል በሚል የሰባት ጨዋታዎች እገዳ ቅጣት እንደተጣለበት ይታወቃል።

የእንግሊዝ ኤፍኤ አሁን ላይ የቀረበውን ይግባኝ ውድቅ በማድረግ ቅጣቱን ማፅናቱ ተገልጿል።

ይህንንም ተከትሎ ሮድሪጎ ቤንታንኩር በቀጣይ ሐሙስ የማንችስተር ዩናይትድ እና እሁድ የሊቨርፑል ጨዋታዎች የሚያመልጡት ይሆናል።

@Tikvahethsport    @kidusyoftahe
💥የካራባው ካፕ ሩብ ፍፃሜ ጨዋታዎች ረቡዕ ታህሳስ 9 ይጀመራል

⚽️ ከአርሰናል ፣ ሊቨርፑል ፣ ቶተንሃም እና ማን ዩናይትድ ማን ወደ ቀጣዩ ዙር የሚያል ይመስላችኋል?

👉 ጨዋታዎችን ከትንታኔ ፣ ከተጫዋች ብቃት እስከ ቡድን ወኔ በሱፐርስፖርት ለመከታተል ዛሬውኑ ደንበኝነትዎን ያራዝሙ!

ዲኤስቲቪ ያስገቡ ፣ ደንበኝነትዎን ያራዝሙ!
👇
https://bit.ly/3RFtEvh

#PremierLeagueAllonDStv #ሁሉምያለውእኛጋርነው #DStvEthiopia
Forwarded from WANAW SPORT
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
አርሰናል የተጫዋቾቹን ግልጋሎት አያገኝም !

አርሰናል ነገ ከክሪስታል ፓላስ ጋር በሚያደርገው ጨዋታ የተጫዋቾቹን ግልጋሎት እንደማያገኝ አሰልጣኝ ሚኬል አርቴታ ተናግረዋል።

አሌክሳንደር ዚንቼንኮ እና ሪካርዶ ካላፊዮሪ ከጨዋታው ውጪ መሆናቸውን አሰልጣኝ ሚኬል አርቴታ አረጋግጠዋል።

የመሐል ሜዳ ተጨዋቹ ዴክላን ራይስ በበኩሉ በጥሩ ሁኔታ ላይ እንደሚገኝ እና በጨዋታው መሰለፉን ገና እንዳልወሰኑ አሰልጣኙ ገልፀዋል።

አርሰናል ነገ ምሽት 4:30 የካራባኦ ካፕ ሩብ ፍፃሜ ጨዋታውን ከክሪስታል ፓላስ ጋር የሚያደርግ ይሆናል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
" ሶስት ዋንጫ ነው ያሳካሁት " አርቴታ

ስፔናዊው አሰልጣኝ ሚኬል አርቴታ በተጨዋችነት ያሳለፉበትን አርሰናል ተረክበው ማሰልጠን ከጀመሩ አምስት አመታትን አስቆጥረዋል።

አሰልጣኙ መድፈኞቹን ጠንካራ የዋንጫ ተፎካካሪ ማድረግ ቢችሉም ትልቅ ዋንጫ ባለማሳካታቸው ጥያቄዎች ሲነሱባቸው ይደመጣል።

ሚኬል አርቴታ ዛሬ ከጋዜጠኞች ጋር በነበራቸው ቆይታ በዚህ ጉዳይ ከጋዜጠኞች ጥያቄ ቀርቦላቸው ነበር።

ባለፉት 5️⃣ አመታት አርሰናልን የዋንጫ ተፎካካሪ ማድረግ ብትችልም በመጀመሪያ አመት አንድ ዋንጫ ነው ያሳካኸው ተብለው የተጠየቁት አርቴታ " ትክክል አይደለም " ሲሉ ምላሽ ሰጥተዋል።

“ የኤፌ ካፕ ዋንጫ ብቻ አይደለም ያመጣሁት " ያሉት ሚኬል አርቴታ “ ሁለት የኮሚኒቲ ሺልድ ዋንጫም አሸንፌያለሁ አጠቃላይ ሶስት ዋንጫ ነው “ ሲሉ አስረድተዋል።

@Tikvahethsport    @kidusyoftahe
" አርሰናልን እንደማናሸንፍ ካመንን ባንሄድ ይሻላል "

የክሪስታል ፓላሱ ዋና አሰልጣኝ ኦሊቬር ግላስነር ቡድናቸው ነገ አርሰናልን ስለ ማሸነፍ ማሰብ እንዳለበት አሳስበዋል።

“ አርሰናልን ማሸነፍ እንደምንችል ካለመንን ወደዛ ባንሄድ ይመረጣል “ ሲሉ አሰልጣኝ ኦሊቬር ግላስነር ተናግረዋል።

አሰልጣኙ አክለውም ቡድናቸው አርሰናልን ማሸነፍ እንደሚችል ካላመነ ወደ ኤምሬትስ ከመሄድ ይልቅ ወደ በዓል ገበያ ቢወጡ እንደሚመርጡ ገልጸዋል።

ክሪስታል ፓላስ ነገ ምሽት 4:30 ከአርሰናል ጋር የካራባኦ ካፕ ሩብ ፍፃሜ ጨዋታውን የሚያደርግ ይሆናል።

@Tikvahethsport    @kidusyoftahe
የ ፊፋ ፑሽካሽ አዋርድ አሸናፊ ታወቀ !

አርጀንቲናዊው የማንችስተር ዩናይትድ ተጨዋች አሌሀንድሮ ጋርናቾ የ ፊፋ የ 2024 የአመቱ ምርጥ ግብ ፑሽካሽ ተሸላሚ ሆኗል።

አሌሀንድሮ ጋርናቾ ባለፈው አመት ኤቨርተን ላይ ባስቆጠራት የመቀስ ምት ግብ ሽልማቱን ማሸነፉ ተገልጿል።

የአመቱን ምርጥ ግብ በጎል ቻናላችን መመልከት ይችላሉ።

የጎል ቻናላችን 👉 https://www.tg-me.com/+rbdEU4UaEdQxYWFk

@Tikvahethsport     @kidusyoftahe
የአመቱ ምርጥ ግብ ጠባቂ ይፋ ተደርጓል !

የፊፋ የ2024 የአመቱ ምርጦች የሽልማት ስነ-ስርዐት ይፋ በመደረግ ላይ ሲሆን ከደቂቃዎች በፊት የፊፋ የአመቱ ምርጥ ግብ ጠባቂ ታውቋል።

በዚህም መሰረት የፊፋ የአመቱ ምርጥ ግብ ጠባቂ በመሆን አርጀንቲናዊው የአስቶን ቪላ ግብ ጠባቂ ኤሚሊያኖ ማርቲኔዝ መመረጡ ይፋ ተደርጓል።

አርጀንቲናዊው አስቶን ቪላ ግብ ጠባቂ ኤሚሊያኖ ማርቲኔዝ ከአርጀንቲና ጋር የኮፓ አሜሪካ ዋንጫ ማሳካቱ ይታወሳል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
የአመቱ ምርጥ አሰልጣኝ ይፋ ሆነ !

የ2024 የውድድር ዘመን የፊፋ የአመቱ ምርጥ አሰልጣኝ በአሁኑ ሰአት በዶሀ ከተማ እየተደረገ በሚገኘው ስነ ስርአት ላይ ይፋ ተደርጓል።

በዚህም የሪያል ማድሪዱ አለቃ ካርሎ አንቾሎቲ የአመቱ ምርጥ አሰልጣኝ ተብለው በአብላጫ ድምፅ ተመርጠዋል።

አሰልጣኝ ካርሎ አንቾሎቲ ከሽልማቱ በኋላ " ይህንን ሽልማት በማሸነፌ ክብር ይሰማኛል ሽልማቱን የአለም ምርጥ ክለብ አሰልጣኝ እንድሆን ካደረጉኝ ፍሎሬንቲኖ ፔሬዝ እና ሪያል ማድሪድ ጋር እጋራለሁ " ብለዋል።

ጣልያናዊው አሰልጣኝ ካርሎ አንቾሎቲ በአምናው የውድድር አመት ሪያል ማድሪድን የላሊጋ እና ሻምፒየንስ ሊግ ዋንጫ ባለ ክብር ማድረጋቸው የሚታወስ ነው።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
ቪኒሰስ ጁኒየር የአመቱ ምርጥ ተጨዋች ተባለ !

የ 2024 የፊፋ የዓመቱ ምርጥ ተጨዋች በኳታር ርዕሰ መዲና ዶሃ እየተደረገ በሚገኘው የአመቱ ምርጥ አሸናፊዎች ስነ-ስረዓት ላይ ከደቂቃዎች በፊት ይፋ ተደርጓል።

በዚህም መሰረት ብራዚላዊው የፊት መስመር ተጨዋች ቪንሰስ ጁኒየር የፊፋ የ2024 የአለም ምርጥ ተጨዋች በመባል መመረጥ ችሏል።

ብራዚላዊው የሪያል ማድሪድ የፊት መስመር ተጨዋች ቪንሰስ ጁኒየር የፊፋ የአመቱ ምርጥ ተጨዋች ክብርን ለመጀመሪያ ጊዜ መቀዳጀት ችሏል።

ቪንሰስ ጁኒየር በአመቱ ውስጥ ምን አሳካ ?

- የስፔን ላሊጋ አሸናፊ

- የአውሮፓ ሻምፒየንስ ሊግ አሸናፊ

- የአውሮፓ ሻምፒየንስ ሊግ የአመቱ ምርጥ ተጨዋች

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
TIKVAH-SPORT
ቪኒሰስ ጁኒየር የአመቱ ምርጥ ተጨዋች ተባለ ! የ 2024 የፊፋ የዓመቱ ምርጥ ተጨዋች በኳታር ርዕሰ መዲና ዶሃ እየተደረገ በሚገኘው የአመቱ ምርጥ አሸናፊዎች ስነ-ስረዓት ላይ ከደቂቃዎች በፊት ይፋ ተደርጓል። በዚህም መሰረት ብራዚላዊው የፊት መስመር ተጨዋች ቪንሰስ ጁኒየር የፊፋ የ2024 የአለም ምርጥ ተጨዋች በመባል መመረጥ ችሏል። ብራዚላዊው የሪያል ማድሪድ የፊት መስመር ተጨዋች ቪንሰስ ጁኒየር…
“ እዚህ መገኘት ለእኔ የማይቻል ይመስል ነበር “ ቪኒሰስ

የፊፋ የአመቱ ምርጥ ተጨዋች የተሰኘው ቪኒሰስ ጁኒየር ከሽልማቱ በኋላ ለእሱ የማይቻል ይመስል የነበረውን ክብር መቀዳጀቱን ተናግሯል።

“ የመጣሁት ለመኖር አስቸጋሪ ከሆነ ትንሽ መንደር ነው “ የሚለው ቪኒሰስ ጁኒየር “ እዚህ ቦታ መገኘት ለእኔ የማይችል ይመስል ነበር አሁን ግን እዚህ ነኝ “ ሲል ተደምጧል።

“ ማመስገን ያለብኝ በጣም ብዙ ሰዎች አሉ ፤ የመረጡኝን አሰልጣኞች ፣ ተጨዋቾች እና ደጋፊዎች ማመስገን እፈልጋለሁ “ ሲል ቪኒሰስ ተናግሯል።

“ በአለም ምርጡ ክለብ ሪያል ማድሪድ ውስጥ ለረጅም ጊዜ መቆየት እፈልጋለሁ “ ቪኒሰስ ጁኒየር

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
የ ፊፋ የአመቱ ምርጥ ደረጃ ምን ይመስላል ?

የ 2024 የፊፋ የአመቱ ምርጥ ሽልማት ስነስርዓት ከደቂቃዎች በፊት በኳታር ዶሀ በይፋ ተካሂዷል።

ብራዚላዊው የሪያል ማድሪድ ተጨዋች ቪኒሰስ ጁኒየር በ 4️⃣8️⃣ ነጥቦች የአመቱ ምርጥ ተጨዋች በመሆን በአብላጫ ድምፅ አሸንፏል።

ቪኒሰስ ጂኒየርን በመከተል ስፔናዊው የባሎን ዶር አሸናፊ ሮድሪ በ 4️⃣3️⃣ ነጥቦች ሁለተኛ ደረጃን ይዞ አጠናቋል።

አርጀንቲናዊው የኢንተር ሚያሚ ተጨዋች ሊዮኔል ሜሲ ስድስተኛ ደረጃን በመያዝ አጠናቋል።

የአመቱ ምርጥ ደረጃ ምን ይመስላል ?

1️⃣ ቪኒሰስ ጁኒየር

2️⃣ ሮድሪ

3️⃣ ጁድ ቤሊንግሀም

4️⃣ ዳኒ ካርቫል

5️⃣ ላሚን ያማል

6️⃣ ሊዮኔል ሜሲ በመሆን አጠናቀዋል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
TIKVAH-SPORT
ቪኒሰስ ጁኒየር የአመቱ ምርጥ ተጨዋች ተባለ ! የ 2024 የፊፋ የዓመቱ ምርጥ ተጨዋች በኳታር ርዕሰ መዲና ዶሃ እየተደረገ በሚገኘው የአመቱ ምርጥ አሸናፊዎች ስነ-ስረዓት ላይ ከደቂቃዎች በፊት ይፋ ተደርጓል። በዚህም መሰረት ብራዚላዊው የፊት መስመር ተጨዋች ቪንሰስ ጁኒየር የፊፋ የ2024 የአለም ምርጥ ተጨዋች በመባል መመረጥ ችሏል። ብራዚላዊው የሪያል ማድሪድ የፊት መስመር ተጨዋች ቪንሰስ ጁኒየር…
ኢትዮጵያ በፊፋ የአመቱ ምርጥ ማንን መረጠች ?

ከደቂቃዎች በፊት በተደረገው የፊፋ የአመቱ ምርጥ ሽልማት ሀገራችን ኢትዮጵያ በምርጫው ምርጥ ሶስት ተጫዋቾችን መመርጧን ለመመልከት ተችሏል።

ሀገራችንን የወከሉት እነማን ነበሩ ?

1️⃣. ያሬድ ባየህ ( አምበል )  :- ቪኒሰስ ጁኒየር ፣ ዳኒ ካርቫል እና ጁድ ቤሊንግሀም

2️⃣. አሰልጣኝ መሳይ ተፈሪ ( የብሔራዊ ቡድን አሰልጣኝ ) :- ሮድሪ ፣ ቪኒሰስ ጁኒየር እና ጁድ ቤሊንግሀም

3️⃣. ሁሴን አብድልቀኒ ( ጋዜጠኛ ) :- ሮድሪ ፣ ቪኒሰስ ጁኒየር እና ዳኒ ካርቫልን በቅደም ተከተል መምረጣቸው ይፋ ሆኗል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
2025/01/07 18:05:23
Back to Top
HTML Embed Code: