Telegram Web Link
“ እዚህ ማሸነፍ አለብን “ ሩበን አሞሪም

አዲሱ የማንችስተር ዩናይትድ አሰልጣኝ ሩበን አሞሪም ቡድኑን በሀላፊነት ከተረከቡ በኋላ ለመጀመሪያ ጊዜ ኦልድትራፎርድ ስታዲየምን ጎብኝተዋል።

አሰልጣኙ በጉብኝታቸው ወቅት የክለቡን መልበሻ ቤት የተመለከቱ ሲሆን “ የአለም ምርጥ ክለብ “ ሲል አዲሱን ክለባቸውን ገልጸዋል።

“ እዚህ ማሸነፍ አለብን “ ያሉት አሰልጣኝ ሩበን አሞሪም ይህንንም ሁሉም ሰው ያውቀዋል በማለት አስተያየታቸውን ስጥተዋል።

@Tikvahethsport    @kidusyoftahe
Forwarded from HEY Online Market
Tab A9+ , 128GB, 29,999 Birr
Tab A8, 64GB , 31,000 Birr
Tab S6 lite, 64GB, 40,000 Birr

Contact us:
0936222222 @heymobile1
0925927457 @eBRO4

@Heyonlinemarket
ዶች ከመቼውም ጊዜ በላይ ከፍ ተደርገዋል።
ታዲያ ምን ይጠብቃሉ? ለማሸነፍ በተመቻቹ ኦዶች ይወራረዱ!
አሁኑኑ Betika.et ላይ ብቻ!
ቤቲካ የአሸናፊዎች ቤት!
#CONMEBOLWorldCupQ

በደቡብ አሜሪካ የአለም ዋንጫ ማጣሪያ ጨዋታዎች አርጀንቲና ስትሸነፍ ብራዚል ነጥብ ተጋርታ ወጥታለች።

ምድቡን እየመራ የሚገኘው የአርጀንቲና ብሔራዊ ቡድን ከፓራጓይ ጋር ያደረገውን ጨዋታ 2ለ1 በሆነ ውጤት ተሸንፏል።

አርጀንቲና በ 2024 ከሜዳዋ ውጪ ያደረገቻቸውን የአለም ዋንጫ ማጣሪያ ጨዋታዎች ማሸነፍ አልቻለችም በሁለቱ ስትሸነፍ በአኔዱ አቻ ወጥታለች።

አርጀንቲና በ 2023 ያደረገቻቸውን ሁሉንም የማጣሪያ የሜዳ ውጪ ጨዋታዎች በአሸናፊነት አጠናቃ ነበር።

ሊዮኔል ሜሲ በእግርኳስ ህይወቱ ለሶስተኛ ጊዜ በተከታታይ ያደረጋቸውን ሶስት ጨዋታዎች ተሸንፏል።

የብራዚል ብሔራዊ ቡድን በበኩሉ ከቬንዙዌላ ጋር ጨዋታውን አድርጎ 1ለ1 በሆነ አቻ ውጤት አጠናቋል።

በጨዋታው ቪንሰስ ጁኒየር ያገኘውን የፍፁም ቅጣት ምት መጠቀም ሳይችል ሲቀር ለብራዚል ለአቻነት ግብ ራፊንሀ አስቆጥሯል።

የምድብ ደረጃቸው ምን ይመስላል ?

1️⃣ አርጀንቲና :- 22 ነጥብ

2️⃣ ኮሎምቢያ :- 19 ነጥብ

3️⃣ ብራዚል :- 17 ነጥብ

4️⃣ ዩራጓይ :- 16 ነጥብ

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
ቦትስዋና ፕሬዝዳንቷ ስታዲየም ይገኛሉ !

የቦትስዋና ብሔራዊ ቡድን ዛሬ ከሞሪታንያ ብሔራዊ ቡድን ጋር ወሳኝ የአፍሪካ ዋንጫ ማጣሪያ ጨዋታዋን ታደርጋለች።

በጨዋታው የሀገሪቱ ፕሬዝዳንት ዱማ ቦኮ በስታዲየሙ ተገኝተው ብሔራዊ ቡድኑን ለማበረታታት ማሰባቸውን በማህበራዊ ትስስር ገፃቸው አሳውቀዋል።

ቦትስዋና ጨዋታውን የምታሸንፍ ከሆነ በሞሮኮ አዘጋጅነት ለሚካሄደው የአፍሪካ ዋንጫ ማለፏን ታረጋግጣለች።

ጨዋታው ዛሬ 10:00 ሰዓት ቦትስዋና ላይ የሚደረግ ይሆናል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
ክላውዲዮ ራኔሪ በሮማ በአዲስ ሚና ይቀጥላሉ !

እስከ ውድድር አመቱ መጨረሻ በሚቆይ ኮንትራት ሮማን በሀላፊነት የተረከቡት አሰልጣኝ ክላውዲዮ ራኔሪ በቀጣይ በክለቡ አዲስ ሚና እንደሚሰጣቸው ተገልጿል።

ጣልያናዊው አሰልጣኝ ከቀጣዩ የውድድር አመት ጀምሮ በሴርያው ክለብ የስፖርታዊ ጉዳዮች አማካሪ ሆነው እንደሚያገለግሉ  ተዘግቧል።

የ 73ዓመቱ አሰልጣኝ ክላውዲዮ ራኔሪ ክለቡ በቀጣይ በሚሾመው የረጅም ጊዜ አሰልጣኝ ምርጫ ሂደት ውስጥ እንደሚሳተፉ ተመላክቷል።

@Tikvahethsport        @kidusyoftahe
ሰርጂዮ ራሞስ ወደ ሪያል ማድሪድ ?

ስፔናዊው የተከላካይ ስፍራ ተጨዋች ሰርጂዮ ራሞስ ወደ ቀድሞ ክለቡ ሪያል ማድሪድ ቢመለስ ደስተኛ እንደሚሆኑ ተገልጿል።

ተጨዋቹ ከሲቪያ ጋር ከተለያየ በኋላ ያለ ክለብ የሚገኝ ሲሆን አሁን ላይ በነፃ ዝውውር አዲስ ክለብ መቀላቀል ይችላል።

ሎስ ብላንኮዎቹ በበኩላቸው ተከላካዮቻቸው ጉዳት ያጋጠማቸው መሆኑን ተከትሎ ወደ ዝውውር ገበያው ሊወጡ እንደሚችሉ እየተገለፀ ይገኛል።

ሪያል ማድሪድ አሁን ላይ ሰርጅዮ ራሞስን በድጋሜ ለማስፈረም ምንም ንግግር አለመጀመሩን የዝውውር ጉዳዮችን የሚዘግበው ጋዜጠኛ ፋብሪዝዮ ሮማኖ አረጋግጧል።

@Tikvahethsport        @kidusyoftahe
“ በማድሪድ መፈለግ ለእኔ ክብር ነው “ ማርዮ ሄርሞሶ

ስፔናዊው የሮማ የተከላካይ ስፍራ ተጨዋች ማርዮ ሄርሞሶ ስሙ ከሪያል ማድሪድ ጋር መያያዙ ለእሱ ክብር መሆኑን ተናግሯል።

ስሙ ከሪያል ማድሪድ ጋር ተያይዞ መነሳቱን እንዳነበበ የገለፀው ማርዮ ሄርሞሶ “ በትልቅ ክለብ መፈለግ ትልቅ ነገር ነው ይሄ ለእኔ ክብር ነው።“ ሲል ተደምጧል።

በሪያል ማድሪድ አካዳሚ ተጫውቶ ያሳለፈው ተጨዋቹ ክለብ ለእሱ ባደረገው አስተዋጽኦ አመስጋኝ መሆኑን ገልጿል።

@Tikvahethsport        @kidusyoftahe
" ጥሩ ተጨዋቾች እና ጥሩ ቡድን አለን " ጋብሬል ማርቲኔሊ

ብራዚላዊው የመድፈኞቹ የፊት መስመር ተጨዋች ጋብሬል ማርቲኔሊ ቡድናቸው አመቱን በስኬት ለማጠናቀቅ ዝግጁ መሆኑን ገልጿል።

" በድንቅ ተጨዋቾች የተሟላ ጥሩ ቡድን አለን " የሚለው ተጨዋቹ " ያለፉትን አመታት በሊጉ ሁለተኛ ሆነ አጠናቀናል ዘንድሮ ዋንጫውን ለማሸነፍ ዝግጁ ነን።" ብሏል።

የውድድር አመቱ "ረጅም ነው" ሲል የገለፀው ማርቲኔሊ "በራሳችን እምነት አለን የምንፈልገውን ነገር ለማሳካት ቁርጠኛ ነንደ" በማለት ተናግሯል።

@Tikvahethsport    @kidusyoftahe
የቀድሞ የአርሰናል ተጨዋች ጫማውን ሰቀለ !

የቀድሞ የአርሰናል እና የደቡብ ኮርያ ብሔራዊ ቡድን የፊት መስመር ተጨዋች ፓርክ ቹ ያንግ በ 39ዓመቱ ጫማውን እንደሰቀለ ይፋ አድርጓል።

ፓርክ ቹ ያንግ በአርሰናል መለያ መጫወት የቻለ ብቸኛው ደቡብ ኮርያዊ እግርኳስ ተጨዋች መሆኑ ተነግሯል።

ተጨዋቹ በአርሰናል ቤት ባሳለፈባቸው አራት አመታት ብዙም የመሰለፍ እድል ያላገኘ ሲሆን ስድስት ጨዋታዎች እና አንድ ግብ ማስቆጠር ችሏል።

@Tikvahethsport    @kidusyoftahe
#Ethiopia 🇪🇹

የ 2017 የሶፊ ማልት ታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ የአለም አቀፍ የ 10 ኪሎ ሜትር ውድድር የፊታችን እሁድ ይካሄዳል።

ለሀያ አራተኛ ጊዜ በሚካሄደው በዘንድሮው ውድድር 50,000 ተሳታፊዎች እንደሚካፈሉ ይጠበቃል።

በእሁዱ ውድድር የታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ የአለምአቀፍ 10 ኪሎ ሜትር የሶስት ጊዜ አሸናፈው አቤ ጋሻሁን ወደ ውድድር እንደሚመለስ ተገልጿል።

የአምናው የውድድሩ አሸናፊ ቢኒያም መሃሪም በውድድሩ የሚካፈል ሲሆን ባለፈው አመት የውድድሩን ክብረ ወሰን ለመስበር በአንድ ሰከንድ ዘግይቶ ጠንካራ ፉክክር አድርጎ ነበር።

በሴቶች ውድድር እጅግ ከባድ ፉክክር የሚጠበቅ ሲሆን መታየት ካለባቸው አትሌቶች መካከል በመስከረም ወር በአምስተርዳም ዳም ቱ ዳም የ 10 ማይል አሸናፊ የሆነችው አሳየች አይቸው ትገኝበታለች፡፡

የዚህ ዓመት ውድድር ለሽልማት የሚቀርበው ሚዳሊያ በኢትዮጵያ ከተገኘች 50 ዓመት የሞላትን ድንቅነሽን (ሉሲ) የሚያስታውስ ቅርፅ እንደሚኖረው ተገልጿል።

የአዋቂ አትሌቶች ውድድር ከሌሎች ተሳታፊዎች ውድድር በአምስት ደቂቃዎች ቀድሞ እንደሚጀምር አዘጋጆቹ አሳውቀዋል።

@Tikvahethsport    @kidusyoftahe
ኒውካስል ተጨዋቹ ቤቱ መዘረፉን ገለፀ !

ብራዚላዊው የኒውካስል ዩናይትድ የመሐል ሜዳ ተጨዋች ጆኢሊንተን መኖሪያ ቤቱ በዘራፊዎች መዘረፉን በማህበራዊ ትስስር ገፁ ገልጿል።

ተጨዋቹ መኖሪያ ቤቱ ሲዘረፍ ከአመት ባነሰ ጊዜ ውስጥ ለሁለተኛ ጊዜ መሆኑ ተነግሯል።

ተጨዋቹ በማህበራዊ ገፁ ባሰፈረው መልዕክትም “ በድጋሜ ለማድረግ ላሰባቸሁ ምንም ሳይዘረፍ የቀረ ነገር እንደሌለ እወቁ ” ብሏል።

ተጨዋቹ አክሎም ቤተሰቦቻችን ያለፍርሀት በሰላም እንዲኖሩ እንፈልጋለን መብታችን እንዲከበር እንጠይቃለን በሰላም መኖር እንፈልጋለን በማለት ተናግሯል።

@Tikvahethsport    @kidusyoftahe
“ ለድጋፋችሁ አመሰግናለሁ " ቫን ኔስትሮይ

ከማንችስተር ዩናይትድ ጋር የተለያየው አሰልጣኝ ሩድ ቫን ኔስትሮይ ባስተላለፈው የስንብት መልዕክት ለተደረገለት ድጋፍ ምስጋናውን አቅርቧል።

“ በዩናይትድ ውስጥ ላሉ ሁሉ ላደረጋችሁልኝ ድጋፍ እና አብሮነት ከልብ አመሰግናለሁ " ሲል ቫን ኔስትሮይ በመልዕክቱ ገልጿል።

“ ማንችስተር ዩናይትድን መምራት ክብር ነበር አብረን የነበረንን ጊዜ ስደሰትበት እኖራለሁ “ ያለው ቫን ኔስትሮይ “ ማንችስተር ዩናይትድ ሁልጊዜም በልቤ ውስጥ የተለየ ቦታ ይኖረዋል “ ብሏል።

አሰልጣኝ ሩድ ቫን ኔስትሮይ ማንችስተር ዩናይትድን በጊዜያዊ አሰልጣኝነት ለአራት ጨዋታዎች ሲመራ በሶስቱ አሸንፎ በአንዱ አቻ ተለያይቷል።

@Tikvahethsport    @kidusyoftahe
" ዩናይትድን በመልቀቄ አልፀፀትም " ማክ ቶሚናዬ

ናፖሊን የተቀላቀለው ስኮትላንዳዊው የመሐል ሜዳ ተጨዋች ስኮት ማክ ቶሚናይ ከማንችስተር ዩናይትድ ጋር በመለያየቱ እንደማይፀፀት ተናግሯል።

ተጨዋቹ ማንችስተር ዩናይትድን በመልቀቁ ይፀፀት እንደሆነ ሲጠየቅ " በእግር ኳስ ህይወቴ የምፀፀትበት ነገር የለም።" በማለት ምላሹን ሰጥቷል።

ስኮት ማክ ቶሚናይ አክሎም " አንዳንዴ ትልልቅ ውሳኔዎች ማሳለፍ ይኖርብሀል ቀጥሎም ወደ ኋላ መመልከት አያስፈልግም።" ሲል ተደምጧል።

@Tikvahethsport     @kidusyoftahe
" በጥሩ ሁኔታ ላይ አንገኝም " ኮቫቺች

የማንችስተር ሲቲው የመሐል ሜዳ ተጨዋች ማትዮ ኮቫቺች ቡድናቸው በዚህ ሰአት በጥሩ ሁኔታ ላይ #እንደማይገኝ በሰጠው አስተያየት ገልጿል።

" በጥሩ ሁኔታ ላይ አንገኝም " ሲል የተደመጠው ኮቫቺች ሆኖም ከምንገኝበት የውጤት ቀውስ የመውጣቱ ሀላፊነት የሁላችንም ነው። " ሲል ቡድኑን አሳስቧል።

አሁን የምንገኝበት የእረፍት ጊዜ ለቡድናችን ጥሩ ይሆናል ሲል የገለፀው ተጨዋቹ "ይበልጥ ጠንካራ ሆነን እንድንመለስ ይረዳናል።" ብሏል።

@Tikvahethsport    @kidusyoftahe
ብዙ ጉዳት ያጋጠማቸው ክለቦች የትኞቹ ናቸው ?

የሰሜን ለንደኑ ክለብ ቶተንሀም በዘንድሮው የውድድር ዘመን በሊጉ ተጨዋቾቹን በጉዳት ብዙ ጊዜ ለማጣት የተገደደ ቀዳሚው ክለብ መሆኑ ተገልጿል።

ቶተንሀም በውድድር ዘመኑ ተጨዋቾቹን አስራ ሶስት ጊዜ በጉዳት ምክንያት በፕርሚየር ሊግ ጨዋታዎች ማጣቱ ተነግሯል።

ብዙ ጉዳት ያጋጠማቸው ክለቦች የትኞቹ ናቸው ?

  ቶተንሀም :- 13 ጉዳቶች

ብራይተን :- 12 ጉዳቶች

ኢፕስዊች ታውን :- 12 ጉዳቶች

አስቶን ቪላ :- 11 ጉዳቶች

ክሪስታል ፓላስ :- 11 ጉዳቶች

አርሰናል :- 10 ጉዳቶች

ማንችስተር ሲቲ :- 10 ጉዳቶች

ዌስትሀም ዩናይትድ በውድድር ዘመኑ በሁለት ጉዳቶች አነስተኛ ጉዳት ያጋጠመው ክለብ መሆኑ ተጠቁሟል።

@Tikvahethsport           @kidusyoftahe
🔊 🌟የሳፋሪኮም #1ወደፊት  የሙዚቃ ስልጠናችን እንደቀጠለ ነው!

ምርጥ 10 ኮከቦቻችን በ#1Wedefit የሙዚቃ ስልጠና ልምድ እያገኙ ነው! ሙሉ ቆይታቸውን በቅርቡ...📽️

#SafaricomEthiopia
#1Wedefit
#FurtherAheadTogether #DigitalMusicChallenge
ውጤቱን ይገምቱ

ሀገራችን ኢትዮጵያን ወክለው የዓምናው የሴቶች የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ አሸናፊ የሆኑት የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ቡድን ነገ ከምሽቱ 02፡00 ሰዓት ከሞሮኮዎቹ ኤፍ ሲ ማስር ጋር ይጋጠማሉ!

ይህንን ደማቅ ፍልሚያ በቀጥታ በSS Liyu 2 በጎጆ ፓኬጅ

ደንብና ሁኔታዎች ተፈፀሚነት አላቸው! ለበለጠ መረጃ
👇
www.dstv.com/en-et

የዲኤስቲቪ የተለያዩ አገልግሎቶችን ለማግኘት ከታች ያለውን የMyDStv Telegram ሊንክ ይጫኑ!
👇
https://bit.ly/3yBcOHc

#ሁሉምያለውእኛጋርነው #DStvEthiopia
Forwarded from WANAW SPORT
#Wanaw_sportswear
🎉 Congrats to our partners, the Liberia National Team, on your well-deserved victory! Keep your eyes on the target, and let success be your reward. 🏆⚽️

Contact us!
📞 8289


Follow Us
Website|Instagram|Facebook |TikTok |X|Youtube|Telegram

🌍Made In Africa 🌍
🏅 ዋናው ወደፊት...
2024/11/15 16:41:50
Back to Top
HTML Embed Code: