Telegram Web Link
ኢንተር ሚላን ሁለተኛ ቡድን ሊገነባ ነው !

የጣልያኑ ክለብ ኢንተር ሚላን በሚቀጥለው የውድድር ዘመን ከዋናው ቡድን በተጨማሪ አዲስ ቡድን ለመመስረት ማሰቡ ተገልጿል።

ኢንተር ሚላን የሚመሰርተው አዲስ ቡድን በሚቀጥለው የውድድር ዘመን በጣሊያን ሴሪ ሲ እንደሚወዳደር ተነግሯል።

የክለቡ ውሳኔ ለዋናው ቡድን የሚያድጉ ተጨዋቾች ትልቅ ፉክክር ባለው ውድድር ላይ በደንብ አድገው እንዲመጡ እንዲረዳቸው መሆኑ ተዘግቧል።

ከዚህ በፊት ጁቬንቱስ ፣ አታላንታ እና ኤሲ ሚላን ተጨማሪ ቡድን ያላቸው ክለቦች መሆናቸው ተገልጿል።

@Tikvahethsport   @kidusyoftahe
" ሳውዲ አረቢያ መሄዴ ትክክለኛ ውሳኔ ነበር " ላፖርት

ስፔናዊው የአል ነስር ተከላካይ አይመሪክ ላፖርቴ የሳውዲ አረቢያ ፕሮ ሊግ ጠንካራ ፉክክር የሚታይበት ውድድር እየሆነ መምጣቱን ተናግሯል።

ተጨዋቹ በአስተያየቱም " የሳውዲ ሊግ አሁን ላይ የበለጠ ተፎካካሪ እየሆነ ነው " ያለ ሲሆን " ተጨዋቾች ከአውሮፓ ወደ ሳውዲ እየመጡ ነው።" ሲል ተደምጧል።

ላፖርቴ አክሎም ለአል ነስር ለመፈረም ውሳኔ ላይ ሲደርስ ቀላል እንዳልነበር ገልፆ " እዚህ ከመጣሁ በኋላ ውሳኔዬ ትክክለኛ እንደነበር አረጋግጫለሁ።" ብሏል።

"እንደ እኔ ሀሳብ በአሁኑ ሰአት የአለማችን ምርጡ ክለብ ማንችስተር ሲቲ ነው" ኤምሪክ ላፖርት

@Tikvahethsport    @kidusyoftahe
አንሱ ፋቲ ለሳምንታት ከሜዳ ይርቃል !

የባርሴሎናው የፊት መስመር ተጨዋች አንሱ ፋቲ ባስተናገደው ጉዳት ምክንያት ለሳምንታት ከሜዳ እንደሚርቅ ክለቡ ይፋ አድርጓል።

የ22 አመቱ ተጨዋች ጉዳቱ ያጋጠመው በዛሬው እለት ከቡድኑ ጋር መደበኛ ልምምዱን እያከናወነ በነበረበት ወቅት መሆኑ ተዘግቧል።

በዚህም ተጨዋቹ በተደረግለት ምርመራ "የሀምስትሪንግ" ጉዳት እንዳጋጠመው የታወቀ ሲሆን ለቀጣዮች አራት ሳምንታት ከሜዳ እንደሚርቅ ተገልጿል።

@Tikvahethsport    @kidusyoftahe
ዴክላን ራይስ በሮድሪ ደረጃ ይገኛል “ አጉዬሮ

የቀድሞ የማንችስተር ሲቲ የፊት መስመር ተጫዋች ሰርጅዮ አጉዬሮ ለመድፈኞቹ የመሐል ሜዳ ተጫዋች ዴክላን ራያስ ያለውን አድናቆት ገልፆል።

“ ከአለማችን ምርጥ የተከላካይ አማካዮች መካከል አንዱ ነው “ ያለው አጉዬሮ “ በካሴሚሮ ፣ ቡስኬት እና ሮድሪ ደረጃ ላይ ይገኛል “ ሲልም ተደምጧል።

@tikvahethsport @kidusyoftahe
TIKVAH-SPORT
ሮማ አሰልጣኙን በይፋ አሰናበተ ! የጣልያን ሴርያው ክለብ ሮማ የቡድኑን ዋና አሰልጣኝ ኢቫን ጁሪች ከሀላፊነት ማሰናበቱን በይፋ አስታውቋል። አሰልጣኝ ዳንኤል ዲ ሮሲን ተክተው ለአንድ አመት ሮማን የተረከቡት አሰልጣኝ ኢቫን ጁሪች ከ 5️⃣3️⃣ ቀናት በኋላ ተሰናብተዋል። ሮማ አሰልጣኙን ለማሰናበት የወሰነው ዛሬ በሜዳው በቦሎኛ ከደረሰበት የ 3ለ2 ሽንፈት በኋላ ነው። ሮማ ካለፉት አምስት የጣልያን…
ክላውዲዮ ራኔሪ ወደ አሰልጣኝነት ሊመለሱ ነው !

ከሌስተር ሲቲ ጋር የፕርሚየር ሊግ ዋንጫን ማሳካት የቻሉት ጣልያናዊው አሰልጣኝ ክላውዲዮ ራኔሪ ሮማን በሀላፊነት ሊረከቡ መሆኑ ተገልጿል።

የ 73ዓመቱ አሰልጣኝ ክላውዲዮ ራኔሪ ራሳቸውን ከእግር ኳስ የስልጠና አለም ማግለላቸውን ይፋ አድርገው እንደነበረ ይታወቃል።

ክላውዲዮ ራኔሪ አሁን ላይ ወደ አሰልጣኝነት በመመለስ ሮማን ለሁለት አመታት ለማሰልጠን ከስምምነት መድረሳቸውን የጣልያን መገናኛ ብዙሀን ዘግበዋል።

ሮማ ከቀናት በፊት አሰልጣኝ ኢቫን ጁሪችን ከሾማቸው ወራት በኋላ ከሀላፊነት ማሰናበቱ አይዘነጋም።

@Tikvahethsport    @Kidusyoftahe
Forwarded from HEY Online Market
Tab A9+ , 128GB, 29,999 Birr
Tab A8, 64GB , 31,000 Birr
Tab S6 lite, 64GB, 40,000 Birr

Contact us:
0936222222 @heymobile1
0925927457 @eBRO4

@Heyonlinemarket
የሩበን አምሪምን በረራ በርካቶች ተከታትለዋል !

የማንችስተር ዩናይትዱ ዋና አሰልጣኝ ሩበን አሞሪም ከፖርቹጋል ወደ እንግሊዝ ያደረገውን በረራ በርካቶች መከታተላቸው ተገልጿል።

አሰልጣኙ በግል ጄት ያደረጉትን በረራ 11,000 የሚጠጉ ሰዎች መከታተላቸውን ዴይሊ ሜል አስነብቧል።

የአሰልጣኙ የአውሮፕላን በረራም በአለም ከፍተኛ ቁጥር ያለው ህዝብ የተከታተለው በረራ በመሆን መመዝገቡ ተነግሯል።

@Tikvahethsport    @kidusyoftahe
" ቴንሀግ እድለኛ አልነበረም " ማትያስ ዴሊት

የቀያይ ሴጣኖቹ ተከላካይ ማትያስ ዴሊት አሰልጣኝ ኤሪክ ቴንሀግ በማንችስተር ዩናይትድ በነበረው ቆይታ እድለኛ እንዳልነበር ገልጿል።

" ቴንሀግ እድለኛ አልነበረም " ያለው ዴሊት " በአመቱ መጀመርያ ጥሩ እንቅስቃሴ ስናሳይ ነበር ነገር ግን የፈጠርናቸውን እድሎች አለመጠቀማችን ነገሮች በዚህ መንገድ እንዲሄዱ አድርጓል" ብሏል።

ተጨዋቹ አያይዞም ወደ ማንችስተር ዩናይትድ የተዘዋወረው በኤሪክ ቴንሀግ ምክንያት እንዳልሆነ በመግለፅ "ከእሱ ጋር በዩናይትድ ስኬታማ ለመሆን ፍላጎት ነበረኝ።" ሲል ተደምጧል።

@Tikvahethsport    @kidusyoftahe
“ ሊጉን የማናሸንፍበት ምክንያት የለም “ ሳላህ

የመርሲሳይዱ ክለብ ሊቨርፑል የፊት መስመር ተጨዋች መሐመድ ሳላህ ሊቨርፑል በዚህ አመት ዝቅተኛ ግምት የሚሰጠው ቡድን አለመሆኑን ተናግሯል።

ግብፃዊው ተጨዋች መሐመድ ሳላህ በንግግሩም ሊቨርፑል ከአለም ምርጥ ቡድኖች አንዱ መሆኑን ገልጿል።

" በቡድናችን ሁሉም የሜዳ ክፍሎች ከአለም ምርጥ ሶስት ውስጥ የሚካተት ተጨዋች ታገኛላችሁ “ የሚለው ሳላህ ሊጉን የማናሸንፍበት ምክንያት የለም ብሏል።

@Tikvahethsport    @kidusyoftahe
ሊቨርፑል በጥር ተጨዋች ያስፈርማል ?

የመርሲሳይዱ ክለብ ሊቨርፑል በጥር የተጨዋቾች የዝውውር መስኮት አዲስ ተጨዋች ላያስፈርሙ እንደሚችሉ ተገልጿል።

የሊቨርፑሉ አሰልጣኝ አርኔ ስሎት አሁን ላይ በሁሉም የሜዳ ክፍል ያላቸው የተጨዋቾች ስብስብ ለመፎካከር በቂ ነው የሚል እምነት እንዳላቸው ዘ አትሌቲክ ዘግቧል።

ሊቨርፑል ሚቀጥለው የውድድር አመት ግብፃዊውን ተጨዋች መሐመድ ሳላህን በክለቡ ማቆየት እንደሚፈልግ ተነግሯል።

በሌላ በኩል ሊቨርፑል ኦማር ማራሙሽን ለማስፈረም ንግግር ላይ ነው ተብሎ መነገሩ ሀሰተኛ መሆኑ ተዘግቧል።

@Tikvahethsport    @kidusyoftahe
ባርሴሎና ከናይኪ ስንት ያገኛል ?

የካታላኑ ክለብ ባርሴሎና ከማልያ ስፖንሰሩ ናይኪ ጋር ያለውን ኮንትራት ለተጨማሪ አመታት ማራዘማቸው ተገልጿል።

ባርሴሎና ከናይኪ የገባው አዲስ የውል ስምምነት ለአስራ አራት አመታት መሆኑ ሲገለፅ ለባርሴሎና 1.7 ቢልዮን ዩሮ የሚያስገኝ መሆኑን ዘ አትሌቲክ አስነብቧል።

የውል ስምምነቱ በአለም እግርኳስ የማልያ ስምምነት ታሪክ ከፍተኛ ክፍያ ያስገኘው ሆኖ መመዝገቡ ተገልጿል።

የማልያ ስምምነቱ በፋይናንሻል ፌር ፕሌይ ችግር ውስጥ ለሚገኘው ባርሴሎና ትልቅ እርዳታ እንደሚያደርግለት ተነግሯል።

ናይኪ እ.አ.አ ከ1998 ጀምሮ የካታላኑ ክለብ ባርሴሎና ታሪካዊ ዋና የማልያ ስፖንሰር ነው።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
" ቼልሲን ለመቀላቀል ተቃርቤ ነበር " ጎርደን

እንግሊዛዊው የፊት መስመር ተጨዋች አንቶኒ ጎርደን አሰልጣኝ ቶማስ ቱሄል በነበሩበት ወቅት ቼልሲን ለመቀላቀል ተቃርቦ እንደነበር ተናግሯል።

" ቱሄል እያለ ቼልሲን ለመቀላቀል ተቃርቤ ነበር " ሲል የተደመጠው ተጨዋቹ " እኔ የምጫወትበት መንገድ ለእሱ አጨዋወት እንደሚመች ይሰማኝ ነበር።" ብሏል።

ተጨዋቹ አክሎም ከቶማስ ቱሄል ጋር ለመስራት ከፍተኛ ጉጉት እንደነበረው በማስታወስ "ለቼልሲ ለመፈረም ስቃረብ ደስተኛ ሆኜ ነበር" በማለት ተናግሯል።

@Tikvahethsport    @kidusyoftahe
አንድሬስ ኢኔስታ የክለብ ባለቤት ሆኗል !

የቀድሞ ስፔናዊ የመሐል ሜዳ ተጨዋች አንድሬስ ኢኔስታ በዴንማርክ ሁለተኛ ሊግ የሚወዳደረውን ሄልሲንጎር ክለብ መግዛቱ ተገልጿል።

አንድሬስ ኢኔስታ በስሩ በሚተዳደር ተቋም አማካኝነት የክለቡን ከፍተኛ የአክሲዮን ድርሻ መግዛቱ ተነግሯል።

ኢኔስታ በሰጠው አስተያየትም " ከዚህ ክለብ ጋር ረጅም ርቀት መጓዝ እንዲሁም ማደግ እንፈልጋለን።" ሲል ተደምጧል።

በአንድሬስ ኢኔስታ የተያዘው ክለብ ሄልሲንጎር ባለፈው አመት ከዴንማርክ ሊግ ወደ ሁለተኛው ሊግ የወረደ ነው።

@Tikvahethsport     @kidusyoftahe
TIKVAH-SPORT
ክላውዲዮ ራኔሪ ወደ አሰልጣኝነት ሊመለሱ ነው ! ከሌስተር ሲቲ ጋር የፕርሚየር ሊግ ዋንጫን ማሳካት የቻሉት ጣልያናዊው አሰልጣኝ ክላውዲዮ ራኔሪ ሮማን በሀላፊነት ሊረከቡ መሆኑ ተገልጿል። የ 73ዓመቱ አሰልጣኝ ክላውዲዮ ራኔሪ ራሳቸውን ከእግር ኳስ የስልጠና አለም ማግለላቸውን ይፋ አድርገው እንደነበረ ይታወቃል። ክላውዲዮ ራኔሪ አሁን ላይ ወደ አሰልጣኝነት በመመለስ ሮማን ለሁለት አመታት ለማሰልጠን…
ሮማ ክላውዲዮ ራኔሪን በሀላፊነት ሾመ !

የጣልያን ሴርያው ክለብ ሮማ ጣልያናዊውን አሰልጣኝ ክላውዲዮ ራኔሪ በዋና አሰልጣኝነት መሾሙ ይፋ ተደርጓል።

የ 73ዓመቱ አሰልጣኝ ክላውዲዮ ራኔሪ ሮማን እስከ 2025 የውድድር አመት መጨረሻ ለማሰልጠን ከስምምነት መድረሳቸው ይፋ ሆኗል።

ሮማ ከቀናት በፊት አሰልጣኝ ኢቫን ጁሪችን ከሾማቸው ወራት በኋላ ከሀላፊነት ማሰናበቱ አይዘነጋም።

አሰልጣኙ ከፊርማው በኋላ በሰጡት አስተያየት "ወደ ምወደው ሙያ እና ሊግ ተመልሻለሁ" ሲሉ ተደምጠዋል።

@Tikvahethsport    @Kidusyoftahe
Forwarded from WANAW SPORT
🤩 እንኳን ለ2017 ዓ ም አንደኛ ሊግ የውድድር ዘመን አደረሳችሁ! 🤩

📌 ዋናው የስፖርት
ትጥቅ አምራች ለ2017 ውድድር የሚሆኑ በፋሽናቸው እና በምቾታቸው ተመራጭ የሆኑ የስፖርት ትጥቆችን አዘጋጅቶ ይጠብቃቹሃል።

👉🏾 1 ሙሉ Home & Away ትጥቅ ከነካሶተኒው #በ1199_ብር ሲገዙ፦

• 2 የአሰልጣኝ ስታፍ ፖሎ ቲሸርት በነፃ፣
• 1 ባንዲራ በነፃ፣
• ነፃ ያልተገደበ የዲዛይን ምርጫ፣ ከነፃ ዴሊቨሪ አገልግሎት ጋር ያገኛሉ።

Call us!
📞 8289

📞 +251901138283
📞 +251910851535
📞
+251913586742
🤖 Wanaw Bot

Follow Us
Website | Instagram | Facebook | TikTok | X | Youtube | Telegram

🏅 ዋናው ወደፊት...
ኦዶች ከመቼውም ጊዜ በላይ ከፍ ተደርገዋል።
ታዲያ ምን ይጠብቃሉ? ለማሸነፍ በተመቻቹ ኦዶች ይወራረዱ!
አሁኑኑ Betika.et ላይ ብቻ!
ቤቲካ የአሸናፊዎች ቤት!
ሀሪ ኬን የወሩ ምርጥ ተጨዋች ተብሏል !

አስረኛ ሳምንቱ ላይ የደረሰው የጀርመን ቡንደስሊጋ የወርሀ ጥቅምት የወሩ ምርጥ ተጨዋች ይፋ ተደርጓል።

በዚህም መሰረት እንግሊዛዊው የፊት መስመር አጥቂ ሀሪ ኬን የቡንደስሊጋ የጥቅምት ወር ምርጥ ተጨዋች በመሆን መመረጥ ችሏል።

ሀሪ ኬን በወሩ ለባየር ሙኒክ ባደረጋቸው ሶስት ጨዋታዎች አራት ግቦችን ማስቆጠር ችሏል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
የሴርያ የወሩ ምርጥ ተጨዋች ታውቋል !

አስራ አንደኛ ሳምንቱ ላይ የደረሰው የጣልያን ሴርያ የወርሀ ጥቅምት የወሩ ምርጥ ተጨዋችን ይፋ አድርጓል።

በዚህም መሰረት የአታላንታው የፊት መስመር ተጨዋች ማትዮ ሬቴጉይ የጥቅምት ወር የሴርያው ምርጥ ተጨዋች በመባል ተመርጧል።

ተጨዋቹ በወሩ ለአታላንታ ባደረጋቸው አራት ጨዋታዎች ስድስት ግቦችን አስቆጥሮ ሶስት አመቻችቶ ማቀበል ችሏል።

@Tikvahethsport     @kidusyoftahe
ጋና ለአፍሪካ ዋንጫው ታልፍ ይሆን ?

የሱዳን ብሔራዊ ቡድን ከኒጀር ብሔራዊ ቡድን ጋር ያደረገውን የአፍሪካ ዋንጫ ማጣሪያ ጨዋታ 4ለ0 በሆነ ውጤት ተሸንፏል።

ይህንንም ተከትሎ የጋና ብሔራዊ ቡድን ለአፍሪካ ዋንጫ ያለው ጠባብ የማለፍ ተስፋ አሁንም ቀጥሏል።

ሱዳን በቀጣይ አንድ ነጥብ የምታሳካ ከሆነ ለአፍሪካ ዋንጫው ማለፏን ታረጋግጣለች።

ጋና በበኩሏ በአፍሪካ ዋንጫው ለማለፍ ቀሪ ሁለት ጨዋታዎችን ማሸነፍ እና የሱዳንን መሸነፍ የምትጠባበቅ ይሆናል።

በሌላ ጨዋታዎች

ናይጄሪያ ፣
ደቡብ አፍሪካ
ቱኒዚያ
ዩጋንዳ
ጋቦን ለአፍሪካ ዋንጫው ማለፋቸውን ያረጋገጡ ቡድኖች ሆነዋል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
ዩናይትድ የሚያደርገውን ድጋፍ ሊቀንስ ነው !

የእንግሊዙ ክለብ ማንችስተር ዩናይትድ ለክለቡ አካል ጉዳተኛ ደጋፊዎች ማኅበር የሚያደርገውን የገንዘብ ድጋፍ ሊቀንስ መሆኑ ተገልጿል።

ቀያይ ሰይጣኖቹ ለማኅበሩ የሚለግሱትን አመታዊ የ 40,000 ፓውንድ የገንዘብ ድጋፍ ወደ 20,000 ለመቀነስ ከውሳኔ መድረሳቸውን ዴይሊ ሜል ዘግቧል።

ይህ የክለቡ ውሳኔ ቀያይ ሰይጣኖቹ ከቅርብ ጊዜያት ወዲህ በጀመሯቸው የወጪ ቅነሳ ተግባራት ውስጥ የሚካተት መሆኑ ተመላክቷል።

@Tikvahethsport    @kidusyoftahe
2024/11/15 18:58:37
Back to Top
HTML Embed Code: