Telegram Web Link
በአሸናፊነቷ የቀጠለችው ጃፓን !

የጃፓን ብሔራዊ ቡድን ከኢንዶኔዥያ ጋር ያደረገውን የእስያ የአለም ዋንጫ ማጣሪያ ጨዋታ 4ለ0 በሆነ ውጤት ማሸነፍ ችሏል።

ጃፓን ከሶስተኛው ዙር አምስት ማጣሪያ ጨዋታዎች አራቱን በአሸናፊነት ስተወጣ በአንዱ አቻ ተለያይታለች።

ብሔራዊ ቡድኑ ባደረጋቸው አምስት የአለም ዋንጫ ማጣሪያ ጨዋታዎች አስራ ዘጠኝ ግቦችን ሲያስቆጥር የተቆጠረበት አንድ ግብ ነው።

ቡድኑ በአማካይ በጨዋታ 3.8 ግቦችን ማስቆጠር ችሏል።

ጃፓን ምድቡን በአስራ ሶስት ነጥብ ስትመራ ከሶስተኛ ደረጃው ያላት ነጥብ ወደ ሰባት መስፋቱን ተከትሎ የምድቡ መሪ ሆና ለአለም ዋንጫው ለማለፍ ተቃርባለች።

ጃፓን በ 2024 ካደረገቻቸው አስራ ስድስት ጨዋታዎች መካከል በአስሩ ከሶስት በላይ ግቦችን አስቆጥራ ማሸነፍ ችላለች።

@Tikvahethsport    @kidusyoftahe
ኢንተር ሚላን የተጫዋቹን ውል አራዝሟል !

የጣልያን ሴርያው ክለብ ኢንተር ሚላን የጀርመናዊውን የተከላካይ ስፍራ ተጨዋች ያን ቢሴክ ኮንትራት ለተጨማሪ አመት ማራዘማቸውን ይፋ አድርገዋል።

የ 23ዓመቱ ተከላካይ ያን ቢሴክ በኢንተር ሚላን ቤት እስከ 2029 የሚያቆየውን የተጨማሪ አንድ አመት ውል መፈረሙ ተገልጿል።

ተጨዋቹ የነበረው ውል 2028 የሚጠናቀቅ የነበረ ሲሆን በአዲሱ የአስራ ሁለት ወራት ኮንትራት የክፍያ ጭማሬ ማግኘቱ ተነግሯል።

@Tikvahethsport    @kidusyoftahe
ክላውዲያ ራኔሪ ወደ እግርኳስ እንዴት ተመለሱ ?

በይፋ ራሳቸውን ከእግርኳስ አግልለው የነበሩት ጣልያናዊው አሰልጣኝ ክላውዲያ ራኔሪ በድጋሜ በመመለስ ሮማን መረከባቸው ይታወቃል።

አሰልጣኙ ራሳቸውን ከእግርኳስ ሲያገሉ ሮማ ወይም ካግሊያሪ ጥያቄ ካቀረቡላቸው ወደ እግርኳስ ለመመለስ አስበው እንደነበር ገልጸዋል።

ክላውዲዮ ራኔሪ ሲናገሩም “ ሌስተርን ይዤ ዋንጫ ካሸነፍኩበት ጊዜ በበለጠ ከእግርኳስ ከተገለልኩ በኋላ በርካታ ጥያቄዎች ቀርበውልኝ አልተቀበልኩም ነበር “ ብለዋል።

" ሮማ ወይም ካግሊያሪ “ ካልሆኑ አልቀበልም ማለታቸውን ያስረዱት አሰልጣኙ አሁን ላይ ሮማ ደርሻለሁ በማለት ተናግረዋል።

የ 73ዓመቱ አንጋፋ አሰልጣኝ የሆኑት ክላውዲዮ ራኔሪ በ እግር ኳስ ከ 51ዓመታት በላይ መስራት ችለዋል።

@Tikvahethsport    @kidusyoftahe
“ ባሎን ዶር ማሸነፍ እፈልጋለሁ “ ፓልመር

የሰማያዊዎቹ የፊት መስመር ተጨዋች ኮል ፓልመር በቀጣይ ቼልሲ ውስጥ ባሎን ዶር ማሸነፍ እንደሚፈልግ ገልጿል።

በቼልሲ ማሳካት ስለሚፈልገው ነገር የተጠየቀው ፓልመር “ ከቼልሲ ጋር ዋንጫዎችን እና ባሎን ዶር ማሸነፍ እፈልጋለሁ “ በማለት ተናግሯል።

የዋይን ሩኒን ግብ የማስቆጠር ክህሎት ሲመለከት ማደጉን የሚገልጸው ፓልመር “ እሱ በየጨዋታው ግብ ሲያስቆጥር እኔም እንደምችል ለማየት ወጥቼ እሞክር ነበር።“ ብሏል።

@Tikvahethsport    @kidusyoftahe
የአለም ክለቦች ውድድር ዋንጫ ምን ይመስላል ?

ፊፋ በቀጣይ በአዲስ መልክ የሚጀምረውን የአለም ክለቦች ዋንጫ ውድድር ያዘጋጀውን በወርቅ የተለበጠ የዋንጫ ሽልማት ትላንት አስተዋውቋል።

በዋንጫው ላይ የ 54ዓመቱ የፊፋው ፕሬዝዳንት ጂያኒ ኢንፋቲኖ ስም ሁለት ጊዜ ተቀርጾ እንደሚገኝ ተገልጿል።

በተጨማሪም ትልቅ የእግርኳስ ታሪኮች እና የሁሉም 2️⃣1️⃣1️⃣ የፊፋ አባል ሀገራት ስም በዋንጫው ላይ ተቀርፆ እንደሚገኝ ተነግሯል።

የ 2025 የአለም ክለቦች ዋንጫ ውድድር በሚቀጥለው ክረምት በአሜሪካ በ 3️⃣2️⃣ ክለቦች መካከል እንደሚካሄድ ይጠበቃል።

በውድድሩ ከእንግሊዝ ክለቦች ማንችስተር ሲቲ እና ቼልሲ የሚሳተፉ ይሆናል።

የሊዮኔል ሜሲው ቡድን ኢንተር ሚያሚ እንዲሁ ከውድድሩ አዘጋጅ አሜሪካ የበውድድሩ የሚሳተፍ ክለብ ነው።

@Tikvahethsport    @kidusyoftahe
" ሁልጊዜም ከማድሪድ ጎን እቆማለሁ " ቶኒ ክሩስ

የቀድሞ የሎስ ብላንኮዎቹ የመሐል ሜዳ ተጨዋች ቶኒ ክሩስ ወደፊት ክለቡን በአዲስ ሚና ሊያገለግል እንደሚችል ፍንጭ ሰጥቷል።

" ሁልጊዜም ከማድሪድ ጎን እቆማለሁ " ያለው ቶኒ ክሩስ " ሪያል ማድሪድ ለኔ ትልቅ ትርጉም አለው እስከመጨረሻው ከክለቡ ጋር ጥብቅ ግንኙነት ይኖረኛል።" ብሏል።

ክሩስ በቀጣይ በሌላ ሀላፊነት ወደ ክለቡ ሊመለስ እንደሚችል ለተነሳለት ጥያቄ "ስለወደፊቱ ምንም ማለት አልችልም ሆኖም እድሎች ካሉ ወደ ምወደው ክለብ ከመመለስ ወደኋላ አልልም።" ሲል ምላሽ ሰጥቷል።

@Tikvahethsport    @kidusyoftahe
2024/11/15 18:30:18
Back to Top
HTML Embed Code: