Telegram Web Link
“ ሁሉም አጨዋወት ደካማ ጎን አለው “ ቴንሀግ

የቀያይ ሴጣኖቹ ዋና አሰልጣኝ ኤሪክ ቴንሀግ የዛሬ ተጋጣሚያቸው ቶተንሀምን የአጨዋወት ዘይቤ እንደሚወዱት ገልጸዋል።

“ የቶተንሀምን አጨዋወት እወደዋለሁ ጠንካራ እና የሚሰብ ጨዋታ ነው የሚያደርጉት ነገርግን ሁሉም አጨዋወት የራሱ ድክመቶች አሉት “ ሲሉ ኤሪክ ቴንሀግ ተናግረዋል።

“ በፈርናንዴዝ እተማመናለሁ በየአመቱ ተመሳሳይ ነው በአመቱ መጨረሻ ፈርናንዴዝ በሊጉ ከሁሉም በላይ የግብ እድል ፈጥሮ ብዙ ግብ ያስቆጥራል “ ቴንሀግ

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
3 ' ማንችስተር ዩናይትድ 0 - 1 ቶተንሀም

ጆንሰን

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
11 ' ማንችስተር ዩናይትድ 0 - 1 ቶተንሀም

                             ጆንሰን

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
42 ' ማንችስተር ዩናይትድ 0 - 1 ቶተንሀም

                             ጆንሰን

🟥 የማንችስተር ዩናይትዱ አምበል ብሩኖ ፈርናንዴዝ ቀይ ካርድ ተመልክቷል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
የእረፍት ሰዓት !

በሳምንቱ ተጠባቂ መርሐ ግብር ማንችስተር ዩናይትድ ከቶተንሀም ጋር እያደረጉ የሚገኙትን ጨዋታ 1ለ0 በሆነ ውጤት እየመሩ ወደ መልበሻ ቤት አምርተዋል።

የቶተንሀምን የመሪነት ግብ ጆንሰን ከመረብ አሳርፏል።

🟨 የቢጫና ቀይ ካርድ የተመለከቱ ተጫዋቾች እነማን ናቸው ?

- በመጀመሪያው አጋማሽ በማንችስተር ዩናይትድ በኩል ማዝራዊ ፣ ማውንት እና ዲያጎ ዳሎት በቶተንሀም በኩል ጆንሰን የማስጠንቀቂያ ካርድ ተመልክተዋል።

🟥 በተጨማሪም የማንችስተር ዩናይትዱ አምበል ብሩኖ ፈርናንዴዝ ቀይ ካርድ ተመልክቷል።

የጨዋታው የኳስ ቁጥጥር ምን ይመስላል ?

- በመጀመሪያው አጋማሽ ቶተንሀም 63% - 37% የኳስ ቁጥጥር ብልጫ ነበራቸው።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
ብሩኖ ፈርናንዴዝ ምን ያህል ጨዋታ ያመልጠዋል ?

የቀያይ ሴጣኖቹ አምበል ብሩኖ ፈርናንዴዝ ከቶተንሀም ጋር እየተደረገ በሚገኘው ጨዋታ የቀይ ካርድ መመልከቱ ይታወቃል።

ብሩኖ ፈርናንዴዝ በቀጣይ ክለቡ የሚያደርጋቸው ሶስት የሊጉ መርሐ ግብሮች እንደሚያመልጡት ይጠበቃል።

በዚህም መሰረት :-

- አስቶን ቪላ ከ ማንችስተር ዩናይትድ

- ማንችስተር ዩናይትድ ከ ብሬንትፎርድ

- ዌስትሀም ከ ማንችስተር ዩናይትድ በሚያደርጉት ጨዋታዎች ለቡድኑ ግልጋሎት የማይሰጥ ይሆናል።

@tikvahethsport @kidusyoftahe
47 ' ማንችስተር ዩናይትድ 0 - 2 ቶተንሀም

                             ጆንሰን
ኩሉሴቭስኪ

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
54 ' ማንችስተር ዩናይትድ 0 - 2 ቶተንሀም

                             ጆንሰን
                             ኩሉሴቭስኪ

- የቶተንሀም ተጓዥ ደጋፊዎች አሰልጣኝ ኤሪክ ቴንሀግን “ ጠዋት ትሰናበታለህ " የሚል ዝማሬ እያሰሙ ይገኛሉ።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
77 ' ማንችስተር ዩናይትድ 0 - 3 ቶተንሀም

                             ጆንሰን
                             ኩሉሴቭስኪ
ሶላንኬ

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
85 ' ማንችስተር ዩናይትድ 0 - 3 ቶተንሀም

                             ጆንሰን
                             ኩሉሴቭስኪ
                             ሶላንኬ

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
ማንችስተር ዩናይትድ ሽንፈት አስተናግዷል !

ማንችስተር ዩናይትድ ከቶተንሀም ጋር ያደረጉትን የፕርሚየር ሊግ ስድስተኛ ሳምንት መርሐ ግብር 3ለ0 በሆነ ውጤት ተሸንፈዋል።

የቶተንሀምን የማሸነፊያ ግቦች ዶምኒክ ሶላንኬ ፣ ብሬናን ጆንሰን እና ኩሉሴቭስኪ ከመረብ ማሳረፍ ችለዋል።

በአሰልጣኝ ኤሪክ ቴንሀግ የሚመራው ማንችስተር ዩናይትድ በውድድር ዘመኑ ሶስተኛ የሊግ ሽንፈቱን አስተናግዷል።

ፖርቹጋላዊው አማካይ ብሩኖ ፈርናንዴዝ በማንችስተር ዩናይትድ ቆይታው የመጀመሪያ ቀይ ካርድ ተመልክቷል።

የሊግ ደረጃቸው ምን ይመስላል ?

8️⃣ኛ ቶተንሀም :- 10 ነጥብ
1️⃣2️⃣ኛ ማንችስተር ዩናይትድ :- 7 ነጥብ

ቀጣይ ጨዋታዎች ?

እሁድ አስቶን ቪላ ከ ማንችስተር ዩናይትድ

እሁድ ብራይተን ከ ቶተንሀም

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
በአሰልጣኝ ኤሪክ ቴን ሀግ ስር ክለቡ ወደ ኃላ እየተጓዘ ነው “

የቀድሞ የማንችስተር ዩናይትድ ተጫዋቾች በዛሬው ጨዋታ ቡድኑ ካስመዘገበው ውጤት በኃላ ሀሳበቸውን አካፍለዋል።

የቀድሞ ተጫዋች አሽሊ ያንግ “ ዩናይትዶች በሜዳ ላይ ያላቸውን አልሰጡም “ ሲል “ ምንም አይነት ፍላጎት አላሳዩም “ ብሏል።

አሽሊ ያንግ በተጨማሪም “ ቡድኑን በሜዳ ላይ የሚመራ ተጫዋች የለም ፣ ቶተንሀም በሜዳው የሚጫወት ይመስል ነበር “ በማለት ተናግሯል።

ጋሪ ኔቭል በበኩሉ “ የመጀመሪያ አጋማሽ የቡደ‍ኑ እንቅስቃሴ መጥፎ ነበር “ ሲል ተደምጧል።

የቀድሞ የመሐል ተከላካይ ሚኬል ሲልቬስተር የክለቡን ወቅታዊ ሁኔታ ሲተች “ ክለቡ በአሰልጣኝ ኤሪክ ቴን ሀግ ስር ወደ ኃላ እየተጓዘ ነው “ ሲል ሁኔታውን ገልፆል።

@tikvahethsport @kidusyoftahe
“ ድሉ የሚገባን ነው “

የቶተንሀሙ ተጫዋች ቫን ዴ ቫን ቡድናቸው በማንችስተር ዩናይትድ ላይ ያስመዘገበው ድል “ የሚገባን ነው “ ሲል ገልፆታል።

“ ድሉ የሚገባን ነው “ ያለው ቫን ዴ ቫን “ ጥሩ እግር ኳስ እንደምንጫወት አሳይተናል ፣ ዛሬ ማሸነፍ ይገባን ነበር “ በማለት ተናግሯል።

ቫን ዴ ቨን በምሽቱ መርሐ ግብር የጨዋታው ኮከብ በመባል መመረጥ ችሏል።

@tikvahethsport @kidusyoftahe
ይገምቱ ይሸለሙ

የሪያል ማድሪድ እና አትሌቲኮ ማድሪድን ጨዋታ ውጤት ገምተው በትክክል ላወቁ ሶስት ቤተሰቦቻችን የአንድ መቶ ብር ካርድ የምንሸልምዎ ይሆናል።

የውድድሩ ህጎች ምን ይመስላሉ ?

√ ተሳታፊዎች ግምቶቻቸውን ከዚህ ፖስት ስር ባለው የሀሳብ መስጫ ሳጥን #ብቻ ማስቀመጥ ይኖርባቸዋል።

√ ኤዲት የተደረጉ ምላሾች በፍፁም ተቀባይነት አይኖራቸውም።

√ ግምትዎን መላክ የሚቻለው እስከ 4:00 ሰዓት ብቻ ነው።

መልካም ዕድል !

@tikvahethsport    
በጎዶሎ ተጫዋች መጫወት ቀላል አይደለም “

በምሽቱ ጨዋታ በቀይ ካርድ የወጣው የማንችስተር ዩናይትድ አምበል ቡሩኖ ፈርናንዴዝ ቡድኑ “ የተቻለውን ሞክሯል “ ሲል ተደምጧል።

“ ቡድኑ ተስፋ አለመቁረጥ አሳይቷል ፣ በቡድን አጋሮቼ ኮርቻለሁ ፣ በጎዶሎ ተጫዋች መጫወት ቀላል አይደለም “ ብሩኖ ፈርናንዴዝ

የቡድኑ አምበል ጥፋት መሰራቱን አምኖ ነገር ግን “ የቀይ ካርዱ አያሰጥም “ በማለት የተመለከተው ቀይ ካርድ እንደማያሰጥ ገልፆል።

“ ማዲሰንን ጠይቄው ቀይ ካርድ እንደማሰጥ ነግሮኛል ቫር ለምን ሊመለከተው እንዳልፈለገ ሊገባኝ አልቻለም “ ሲል ብሩኖ ፈርናንዴዝ ተናግሯል።

@tikvahethsport @kidusyoftahe
ነገ አዲስ ቀን ነው “ ኤሪክ ቴን ሀግ

የቀያይ ሴጣኖቹ ዋና አሰልጣኝ ኤሪክ ቴን ሀግ ብሩኖ ፈርናንዴዝ የተመለከተው ቀይ ካርድ “ ጨዋታውን ቀይሮታል “ ብለዋል።

“ ነገ አዲስ ቀን ነው ፣ የተሻለ ነገር መስራት እና መማር ይኖርብናል “ አሰልጣኝ ኤሪክ ቴን ሀግ

አሰልጣኙ አያይዘውም “ ሙሉ ትኩረታችን በፖርቶ ጨዋታ ላይ ነው “ በማለት ስለቀጣይ መርሐ ግብሮች ማሰብ እንደሚገባ ተናግረዋል።

@tikvahethsport @kidusyoftahe
“ ቀይ ካርዱ ጨዋታውን አልቀየረውም “ ፖስቴኮግሉ

የቶተንሀሙ ዋና አሰልጣኝ አንሄ ፖስቴኮግሉ በምሽቱ ጨዋታ የብሩኖ ፈርናንዴዝ ቀይ ካርድ ጨዋታውን እንዳልቀየረው ገልጸዋል።

በጨዋታው የተመዘዘው ቀይ ካርድ “ ጨዋታውን ለውጦታል ብዬ አላስብም “ ያሉት አሰልጣኙ እንደውም ከዛ በፊት የጨዋታውን የበላይነት ወስደን ነበር ብለዋል።

“ ጥሩ እንቅስቃሴ አድርገናል ጨዋታውን በጥሩ ሁኔታ ጀምረን ግብም አስቆጥረናል ተጨማሪ ግብ ማስቆጠር እንችልም ነበር።“ አንሄ ፖስቴኮግሉ

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
ኤሪክ ቴንሀግ ስለ ወደፊት ቆይታቸው ምን አሉ ?

በውጤት ማጣት ውስጥ የሚገኙት ማንችስተር ዩናይትድ ዋና አሰልጣኝ ኤሪክ ቴንሀግ በቀጣይ የመሰናበት ስጋት እንደሌለባቸው ገልጸዋል።

“ ስንብት የሚያሳስበኝ ጉዳይ አይደለም “ ሲሉ አሰልጣኝ ኤሪክ ቴንሀግ በቀጣይ የመሰናበተት ስጋት እንደሌለባቸው ተናግረዋል።

“ ክረምት ላይ በዚህ ጉዳይ በደንብ ተነጋግረን ነው አብረን ለመቀጠል በጋራ የወሰንነው ፣ ግልጽ ግምገማም አድርገናል ትንሽ ጊዜ እንደሚወስድ እናውቃለን አንድ ላይ ነን “ ቴንሀግ

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
#TikvahGoal

እረፍት | አትሌቲኮ ማድሪድ 0-0 ሪያል ማድሪድ

ጨዋታውን እና አጫጭር ቪዲዮች በጎል ቻናላችን መከታተል ይችላሉ።

የጎል ቻናላችን 👉 https://www.tg-me.com/+rbdEU4UaEdQxYWFk

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
73 ' አትሌቲኮ ማድሪድ 0-1 ሪያል ማድሪድ

ሚሊታኦ

- የአትሌቲኮ ማድሪድ ደጋፊዎች ቁሳቁስ ወደ ሜዳ ውስጥ መወርወራቸውን ተከትሎ በአሁኑ ሰዓት ጨዋታው ተቋርጧል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
2024/09/30 23:37:21
Back to Top
HTML Embed Code: