Telegram Web Link
#እረፍት

ዎልቭስ 0 - 1 ሊቨርፑል

                  ኮናቴ

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
51 '

ዎልቭስ 0 - 1 ሊቨርፑል

                  ኮናቴ

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
58 '

ዎልቭስ 1 - 1 ሊቨርፑል

  ኑሪ                 ኮናቴ

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
62 '

ዎልቭስ 1 - 2 ሊቨርፑል

  ኑሪ                 ኮናቴ
ሳላህ

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
71 '

ዎልቭስ 1 - 2 ሊቨርፑል

  ኑሪ                 ኮናቴ
                              ሳላህ

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
ድሬዳዋ ከተማ ተከታታይ ድሉን አስመዘገበ !

በኢትዮጵያ ፕርሚየር ሊግ የሁለተኛ ሳምንት መርሐ ግብር ድሬዳዋ ከተማ ከወላይታ ድቻ ጋር ያደረጉትን ጨዋታ 4ለ1 በሆነ ውጤት ማሸነፍ ችለዋል።

የድሬዳዋ ከተማን የማሸነፊያ ግቦች ቻርልስ ሙሴጌ 2x እና መሐመድ ኑር ናስር 2x  ከመረብ ማሳረፍ ሲችሉ ለወላይታ ድቻ ያሬድ ዳርዛ አስቆጥሯል።

ቻርልስ ሙሴጌ እና መሐመድ ኑር ናስር በውድድር አመቱ በሁለት ጨዋታዎች ሶስተኛ ግባቸውን አስቆጥረዋል።

ድሬዳዋ ከተማ የመጀመሪያ ሁለት የሊግ ጨዋታዎችን በማሸነፍ ሊጉን በስድስት ነጥብ መምራት ጀምረዋል።

ቀጣይ መርሐ ግብራቸው ምን ይመስላል ?

እሮብ ⏩️ መቻል ከ ወላይታ ድቻ

⏩️ ድሬዳዋ ከተማ በዚህ ዙር አራፊ ክለብ ይሆናል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
ይገምቱ ይሸለሙ

የባርሴሎና እና ኦሳሱናን ጨዋታ ውጤት ገምተው በትክክል ላወቁ ሶስት ቤተሰቦቻችን የአንድ መቶ ብር ካርድ የምንሸልምዎ ይሆናል።

የውድድሩ ህጎች ምን ይመስላሉ ?

√ ተሳታፊዎች ግምቶቻቸውን ከዚህ ፖስት ስር ባለው የሀሳብ መስጫ ሳጥን #ብቻ ማስቀመጥ ይኖርባቸዋል።

√ ኤዲት የተደረጉ ምላሾች በፍፁም ተቀባይነት አይኖራቸውም።

√ ግምትዎን መላክ የሚቻለው እስከ 4:00 ሰዓት ብቻ ነው።

መልካም ዕድል !

@tikvahethsport    
85 '

ዎልቭስ 1 - 2 ሊቨርፑል

  ኑሪ                 ኮናቴ
                              ሳላህ

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
#Bundesliga 🇩🇪

በጀርመን ቡንደስሊጋ አምስተኛ ሳምንት መርሐ ግብር የሊጉ መሪ ባየር ሙኒክ ከባየር ሌቨርኩሰን ጋር ያደረጉትን ጨዋታ 1ለ1 በሆነ አቻ ውጤት አጠናቀዋል።

የባየር ሌቨርኩሰንን ግብ ሮበርት አንድሪክ ሲያስቆጥር አሌክሳንደር ፓቭሎቪች ባየር ሙኒክን አቻ አድርጓል።

የሊግ ደረጃቸው ምን ይመስላል ?

1️⃣ኛ ባየር ሙኒክ :- 13 ነጥብ
3️⃣ኛ ባየር ሌቨርኩሰን :- 10 ነጥብ

ቀጣይ ጨዋታዎች ?

እሁድ ፍራክፈርት ከ ባየር ሙኒክ

ቅዳሜ ባየር ሌቨርኩሰን ከ ሆልስቴን ኬል

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
ሊቨርፑል የሊጉ መሪ ሆነዋል !

የመርሲሳይዱ ክለብ ሊቨርፑል ከዎልቭስ ጋር ያደረገውን የእንግሊዝ ፕርሚየር ሊግ ስድስተኛ ሳምንት መርሐ ግብር 2ለ1 በሆነ ውጤት ማሸነፍ ችሏል።

የሊቨርፑልን የማሸነፊያ ግቦች ኮናቴ እና መሐመድ ሳላህ ከመረብ ሲያሳርፉ የዎልቭስን ግብ ኑሪ አስቆጥሯል።

ሊቨርፑል በአስራ አምስት ነጥቦች የሊጉ መሪ ሆነው የስድስተኛ ሳምንት ውድድራቸውን አጠናቀዋል።

የሊግ ደረጃቸው ምን ይመስላል ?

1️⃣ኛ ሊቨርፑል :- 15 ነጥብ
2️⃣0️⃣ኛ ዎልቭስ :- 1 ነጥብ

ቀጣይ ጨዋታዎች ?

ቅዳሜ ክሪስታል ፓላስ ከ ሊቨርፑል

ቅዳሜ ብሬንትፎርድ ከ ዎልቭስ

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
“ ቡድኑ ባሳየው ብቃት ተደስቻለሁ “ አርቴታ

የመድፈኞቹ ዋና አሰልጣኝ ሚኬል አርቴታ ቡድናቸው ዛሬ ባሳየው እንቅስቃሴ መደሰታቸውን በሰጡት አስተያየት ገልጸዋል።

“ በቡድኑ እንቅስቃሴ በጣም ተደስቻለሁ “ ያሉት አሰልጣኝ ሚኬል አርቴታ “ ዛሬ ድንቅ ነበርን ብዬ አስባለሁ በተጨማሪ ብዙ ግብ ማሸነፍ ይገባናል “ ሲሉ ተናግረዋል።

ሲቲ ነጥብ በመጣሉ ድሉን የበለጠ አስፈላጊ ያደርገው እንደሆነ የተጠየቁት ሚኬል አርቴታ “ ገና ስድስተኛ ሳምንት ነው መስከረም ላይ ነን “ ሲሉ መልሰዋል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
ባርሴሎና ሽንፈት አስተናግዷል !

የካታላኑ ክለብ ባርሴሎና የስፔን ላሊጋ የስምንተኛ ሳምንት መርሐ ግብሩን ከኦሳሱና ጋር አድርጎ 4ለ2 በሆነ ውጤት ተሸንፏል።

የኦሳሱናን የማሸነፊያ ግቦች አንቲ ቡዲሚር 2x ፣ ዛራጎዛ እና ኤቤል ብሬቶንስ ከመረብ ሲያሳርፉ ለባርሴሎና ፓው ቪክቶር እና ላሚን ያማል አስቆጥረዋል።

ባርሴሎና ከተከታታይ ሰባት ድሎች በኋላ የውድድር ዘመኑ መጀመሪያ ሽንፈታቸውን አስተናግደዋል።

ስፔናዊው ተጨዋች ላሚን ያማል በዚህ አመት ባደረጋቸው ዘጠኝ ጨዋታዎች አምስት ግቦች አስቆጥሮ አምስት አመቻችቶ ማቀበል ችሏል።

የሊግ ደረጃቸው ምን ይመስላል ?

1️⃣ኛ ባርሴሎና :- 21 ነጥብ
6️⃣ኛ ኦሳሱና :- 14 ነጥብ

ቀጣይ ጨዋታቸው ምን ይመስላል ?

እሁድ ዲፖርቲቮ አላቬዝ ከ ባርሴሎና

ቅዳሜ ሄታፌ ከ ኦሳሱና

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
Forwarded from HEY Online Market
iPhone 16 Promax
iPhone 16 Pro
iPhone 16 Plus
iPhone 16
Available Now!

0925927457 @eBRO4
0953964175 @heymobile
@heyonlinemarket
የዛሬ ተጠባቂ ጨዋታዎች !

10:00 ኢፕስዊች ከ አስቶን ቪላ

10:00 ሮማ ከ ቬኔዝያ

12:30 ማንችስተር ዩናይትድ ከ ቶተንሀም

3:45 ናፖሊ ከ ሞንዛ

4:00 አትሌቲኮ ማድሪድ ከ ሪያል ማድሪድ

🔴 የዛሬው የይግምቱ ሽልማታችን የማንችስተር ዩናይትድ እና ሪያል ማድሪድ ጨዋታዎች ናቸው።

🔴 የዛሬ ሽልማቶቻችን 11:00 ፣ 3:00 ሰዓት ላይ ወደ ቤተሰቦቻችን የሚደርሱ ይሆናል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
“ ለዋንጫዎች መፎካከር እንደምንችል ማሳየት አለብን “ አርኔ ስሎት

የሊቨርፑሉ ዋና አሰልጣኝ አርኔ ስሎት የሊጉን አሸናፊነት ግምት አሁን ባለው የሊጉ ደረጃ መገመት እንደማይቻል ገልጸዋል።

“ የሊጉ መሪ መሆናችን ጥሩ ነው ሁልጊዜም መሆን የምንፈልግበት ቦታ ነው ነገርግን በአሁን ሰዓት ምንም የሚገልፀው ነገር የለም “ ሲሉ አርኔ ስሎት ተናግረዋል።

ከአስራ ዘጠኝ ጨዋታዎች በኋላ የሊጉን አሸናፊነት በመጠኑ መገመት ይቻል ይሆናል አሁን በስድስት ሳምንት ግን መገመት አይቻልም ሲሉ አሰልጣኙ ገልጸዋል።

አሰልጣኝ አርኔ ስሎት አክለውም ቡድናቸው ለእንግሊዝ ፕርሚየር ሊግ እና ሻምፒየንስ ሊግ ዋንጫዎች መፎካከር እንደሚችል ማሳየት እንዳለበት ተናግረዋል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
TIKVAH-SPORT
“ አርቴታ ለተናገረው ነገር ማብራሪያ መስጠት አለበት “ ጋርዲዮላ የማንችስተር ሲቲው ዋና አሰልጣኝ ፔፕ ጋርዲዮላ  አሰልጣኝ ሜኬል አርቴታ ከቀናት በፊት የተናገሩትን “ ግልጽ ማድረግ አለባቸው “ ሲሉ አሳስብዋል። ሚኬል አርቴታ ከቀናት በፊት በሲቲ ጨዋታ በተከተሉት አጨዋወት ምክንያት ለቀረበባቸው ትችት ምላሽ ሲሰጡ “ ሲቲ በነበርኩበት አራት አመት ስለ እነሱ ሁሉንም መረጃ አውቃለሁ “ ብለው ነበር።…
" አውቃለሁ ያልኩት ጠንክረው እንደሚሰሩ ነው “ አርቴታ

የሰሜን ለንደኑ ክለብ አርሰናል ዋና አሰልጣኝ ሚኬል አርቴታ ከቀናት በፊት ስለ ማንችስተር ሲቲ አውቃለሁ ያልኩት “ ጠንካራ ሰራተኝነታቸውን ነው “ ብለዋል።

ሚኬል አርቴታ በቅርቡ ስለ ሲቲ እዛ በነበርኩበት ሰዓት “ ሁሉም መረጃ አለኝ “ ማለታቸውን ተከትሎ አሰልጣኝ ፔፕ ጋርዲዮላ ምን ማለት እንደፈለጉ ማብራሪያ ይስጡ ብለው ነበር።

“ እኔ እነሱን አውቃቸዋለሁ ስል ለማለት የፈለግኩት  ጠንካራ ሰራተኛ መሆናቸውን አውቃለሁ ነው “ ሲሉ አሰልጣኝ ሚኬል አርቴታ ተናግረዋል።

“ አሰልጣኝ ፔፕ ጋርዲዮላን እወደዋለሁ እየሰራ ያለው ነገር እወዳለሁ እሱን እንደ ጓደኛዬ ነው የማስበው “ ሚኬል አርቴታ

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
አሸናፊዎች ተለይተዋል።

ትክክለኛ ምላሽ ቀድመው የሰጡት ከስር የተገለፁት የቤተሰባችን አባላት ናቸው።

ትክክለኛ ምላሽ የሰጡትን በመፈለጉ ሂደት የተዘለለ እና ያልታየ ካለ ማሳወቅ ይቻላል። Edit የተደረገ መልስ ተቀባይነት አይኖረውም።

ስጦታ የሚበረከትላቸው ቀድመው የመለሱ ሶስት አሸናፊዎች ብቻ ናቸው።

የማንችስተር ሲቲ እና ኒውካስል

1ኛ. @abulala10
2ኛ. @smokealchemist
3ኛ. @U77681202

የአርሰናል እና ሌስተር ሲቲ

1ኛ. @Nalosmigad
2ኛ. @yoniyeasme
3ኛ. @MussieTT

የቼልሲ እና ብራይተን

1ኛ. @U77681202
2ኛ. @Nalosmigad
3ኛ. @Hamido505

የሊቨርፑል እና ዎልቭስ

1ኛ. @U77681202
2ኛ.@Fatilong
3ኛ. @Bdfyb

የባርሴሎና እና ኦሳሱና

1ኛ. Yusuf Kemal
2ኛ. @Dirsha_ye

አሸናፊዎች @Kidusyoftahe መልዕክት በማስቀመጥ ሽልማታቸውን መውሰድ ይችላሉ።

@tikvahethsport
TIKVAH-SPORT
ወልቂጤ ከተማ በተከታታይ ጨዋታ ሳይገኝ ቀርቷል ! የወልቂጤ ከተማ እግር ኳስ ክለብ ለአዲሱ የውድድር ዘመን የሚጠበቅበትን ህጋዊ መስፈርት አለሟሟላቱን ተከትሎ በተከታታይ መርሐግብር ጨዋታውን ሳያደርግ ቀርቷል። ዛሬ ምሽት ከኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ጋር የሁለተኛ ሳምንት መርሐግብር የወጣለት ወልቂጤ ከተማ ተገቢውን የምዝገባ ሂደት ባለሟሟላቱ ጨዋታው በፎርፌ ለንግድ ባንክ ተሰጥቷል። ወልቂጤ ከተማ ባለፈው…
ወልቂጤ ከተማ ከሊጉ መሰረዙ ይፋ ሆነ !

የወልቂጤ ከተማ እግር ኳስ ክለብ አስፈላጊው የመወዳደሪያ መስፈርት ባለሟሟላቱ በሊጉ የመጀመሪያ ሳምንታት ሁለት መርሐ ግብሮች ላይ ሳይካፈሉ ቀርተዋል።

የኢትዮጵያ ፕርሚየር ሊግ አክስዮን ማህበር የውድድር ስነ-ስርዓት ኮሚቴ ባስተላለፈው ውሳኔ ክለቡ “ ከ 2017 የ ኢትዮጵያ ፕርሚየር ሊግ እንዲሰረዝ “ ወስኛለሁ ብሏል።

የወልቂጤ ከተማ ክለብ ለውድድር ዓመቱ የሚያስፈልገውን የክለብ ላይሰንሲንግ የምዝገባ ሂደት ማሟላት ሳይችሉ መቅረታቸው የሚታወስ ነው።

የወልቂጤ ከተማን ከሊጉ መሰረዝ ተከትሎ የኢትዮጵያ ፕርሚየር ሊግ በቀጣይ በአስራ ስምንት ክለቦች መካከል የሚካሄድ ይሆናል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
“ የትኛውንም ክለብ አንፈራም “ ሶላንኬ

የሰሜን ለንደኑ ክለብ ቶተንሀም የፊት መስመር ተጨዋች ዶምኒክ ሶላንኬ ቡድናቸው የትኛውንም ክለብ እንደማይፈራ ገልጿል።

“ ወደ ኦልድትራፎርድ ስታዲየም ሄደን በራሳችን መንገድ እንጫወታለን “ ያለው ዶምኒክ ሶላንኬ እኛ የትኛውንም ቡድን አንፈራም በማለት ተናግሯል።

ለቶተንሀም በርካታ ግቦችን ማስቆጠር እንደሚፈልግ የገለፀው ሶላንኬ “ በተጨማሪ ከቶተንሀም ጋር የተወሰኑ ዋንጫዎችን ማሸነፍ እፈልጋለሁ “ ብሏል።

ቶተንሀም ዛሬ ምሽት 12:30 ከማንችስተር ዩናይትድ ጋር በኦልድትራፎርድ ተጠባቂ የሊግ ጨዋታቸውን ያደርጋሉ።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
2024/09/30 14:21:20
Back to Top
HTML Embed Code: