Telegram Web Link
ማንችስተር ዩናይትድ ነጥብ ጥሏል !

በእንግሊዝ ፕርሚየር ሊግ አምስተኛ ሳምንት መርሐ ግብር ማንችስተር ዩናይትድ ከክሪስታል ፓላስ ጋር ያደረገውን ጨዋታ 0ለ0 በሆነ አቻ ውጤት አጠናቋል።

ማንችስተር ዩናይትድ በውድድር አመቱ ካደረጋቸው አምስት የሊግ ጨዋታዎች በሁለቱ ሲሸነፍ በሁለቱ አሸንፎ በአንዱ አቻ ተለያይቷል።

የሊግ ደረጃቸው ምን ይመስላል ?

1️⃣1️⃣ኛ ማንችስተር ዩናይትድ :- 7 ነጥብ
1️⃣6️⃣ኛ ክሪስታል ፓላስ :- 3 ነጥብ

ቀጣይ ጨዋታዎች ?

እሁድ ማንችስተር ዩናይትድ ከ ቶተንሀም

ቅዳሜ ኤቨርተን ከክሪስታል ፓላስ

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
“ በትክክለኛው መንገድ ላይ ነን “ ማሬስካ

የምዕራብ ለንደኑ ክለብ ቼልሲ ዋና አሰልጣኝ ኢንዞ ማሬስካ ቡድናቸው በትክክለኛው መንገድ ላይ መሆኑን ከዛሬው ድል በኋላ ተናግረዋል።

“ በትክክለኛው መንገድ ላይ እንገኛለን “ ሲሉ የተደመጡት አሰልጣኝ ኢንዞ ማሬስካ የተወሰኑ ነገሮችን ግን ልናሻሽል ይገባል በማለት ገልጸዋል።

ሆኖም ቡድናቸው ሶስት ነጥቡን ማሳካቱ አስፈላጊ መሆኑን አሰልጣኝ ኢንዞ ማሬስካ ደረጃቸውን ካሻሻሉበት ድል በኋላ ተናግረዋል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
“ ወደ ማንችስተር መመለስ ከባድ ነው “ ኦናና

የቀያይ ሴጣኖቹ ግብ ጠባቂ አንድሬ ኦናና በምሽቱ ጨዋታ ወሳኝ የግብ እድሎችን ማዳን ቢችልም ትርጉም አልባ እንደሆነበት ገልጿል።

“ ሁለቱን ኳሶች ማዳኔ ምንም ለውጥ አላመጣም ማሸነፍ አልቻልንም ፤ አሁን ወደ ማንችስተር መመለስ ከባድ ነው “ ሲል አንድሬ ኦናና ተናግሯል።

“ በሀዘን ነው ወደ ቤቴ የምሄደው “ ሲል ያለበትን ሁኔታ የገለፀው ኦናና ሶስት ነጥብ ማግኘት ነበረብን አንድ ነው ያገኘነው ሲል ተደምጧል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
አሸናፊዎች ተለይተዋል።

ትክክለኛ ምላሽ ቀድመው የሰጡት ከስር የተገለፁት የቤተሰባችን አባላት ናቸው።

ትክክለኛ ምላሽ የሰጡትን በመፈለጉ ሂደት የተዘለለ እና ያልታየ ካለ ማሳወቅ ይቻላል። Edit የተደረገ መልስ ተቀባይነት አይኖረውም።

ስጦታ የሚበረከትላቸው ቀድመው የመለሱ ሶስት አሸናፊዎች ብቻ ናቸው።

የሊቨርፑል እና በርንማውዝ ጨዋታ :-

1ኛ. @Abelabera12
2ኛ. @abulala10
3ኛ. @RG_81014

የጁቬንቱስ እና ናፖሊ ጨዋታ :-

1ኛ. @Mo0m67
2ኛ. Jo
3ኛ. @Neba63

የማንችስተር ዩናይትድ እና ክሪስታል ፓላስ ጨዋታ :-

1ኛ. @abulala10
2ኛ. @pavel2446
3ኛ. Mc alister

@tikvahethsport
“ ደስተኛ አይደለሁም ማሸነፍ ነበረብን “ ቴንሀግ

የማንችስተር ዩናይትዱ ዋና አሰልጣኝ ኤሪክ ቴንሀግ ቡድናቸው ያስመዘገበው ውጤት እንዳላስደሰታቸው ከጨዋታው በኃላ ገልጸዋል።

“ ደስተኛ አይደለሁም ማሸነፍ ነበረብን “ ያሉት አሰልጣኝ ኤሪክ ቴንሀግ “ ከእረፍት በፊት ቢያንሰ አንድ ወይም ሁለት ግብ ማስቆጠር ነበረብን “ በማለት ተናግረዋል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
አል ሂላል በአሸናፊነቱ ቀጥሏል !

በሰዑዲ ዓረቢያ ሊግ የአራተኛ ሳምንት መርሐግብር አል ሂላል ከአል ኢትሀድ ጋር ያደረገውን ጨዋታ 3ለ1 በሆነ ውጤት ማሸነፍ ችሏል።

የአል ሂላልን የማሸነፊያ ግቦች ሚትሮቪች 2x እና አል ዳውሳሪ ከመረብ ማሳረፍ ሲችሉ ለአል ኢትሀድ ካሪም ቤንዜማ አስቆጥሯል።

አል ሂላል በዘንድሮው የውድድር አመት ያደረጋቸውን አራት የሊግ ጨዋታዎች በአሸናፊነት መወጣት ችሏል።

የሊግ ደረጃቸው ምን ይመስላል ?

1️⃣ኛ አል ሂላል :- 12 ነጥብ
2️⃣ኛ አል ኢትሀድ :- 9 ነጥብ

ቀጣይ ጨዋታዎች ?

አርብ አል ኢትሀድ ከ አል ካሊጅ

ቅዳሜ አል ሂላል ከ አል ኮሉድ

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
ኢንተር ሚያሚ ነጥብ ተጋርቷል !

በአሜሪካ ሜጀር ሊግ ሶከር የሊዮኔል ሜሲው ቡድን ኢንተር ሚያሚ ከኒውዮርክ ሲቲ ጋር ያደረገውን ጨዋታ 1ለ1 በሆነ አቻ ውጤት አጠናቋል።

የኢንተር ሚያሚን ግብ ሊዮናርዶ ካምፓና ሲያስቆጥር ጄምስ ሳንድስ ኒውዮርክ ሲቲን አቻ አድርጓል።

የሊግ ደረጃቸው ምን ይመስላል ?

1️⃣ኛ ኢንተር ሚያሚ :- 64 ነጥብ
6️⃣ኛ ኒውዮርክ ሲቲ :- 41 ነጥብ

ቀጣይ ጨዋታዎች ?

ቅዳሜ ሌሊት ኢንተር ሚያሚ ከ ቻርሎቴ

ቅዳሜ ሌሊት  ኒውዮርክ ሬድ ቡልስ ከ ኒውዮርክ ሲቲ

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
ሎስ ብላንኮዎቹ ድል አድርገዋል !

በስፔን ላሊጋ የስድስተኛ ሳምንት መርሐ ግብር ሪያል ማድሪድ ከእስፓኞል ጋር ያደረገውን ጨዋታ 4ለ1 በሆነ ውጤት አሸንፏል።

የሪያል ማድሪድን የማሸነፊያ ግቦች ካርቫል ፣ ሮድሪጎ ፣ ቪንሰስ ጁኒየር እና ኪሊያን ምባፔ በፍፁም ቅጣት ምት ከመረብ ማሳረፍ ችለዋል።

ብራዚላዊው የፊት መስመር ተጨዋች ቪንሰስ ጁኒየር ባለፉት ስድስት የላሊጋ ጨዋታዎች ሶስት ግብ አስቆጥሮ አራት አመቻችቶ ማቀበል ችሏል።

በሊጉ ደረጃ ሰንጠረዥ ስንተኛ ናቸው ?

2️⃣ኛ. ሪያል ማድሪድ :- 14 ነጥብ
1️⃣3️⃣ኛ. እስፓኞል :- 7 ነጥብ

ቀጣይ ጨዋታቸው ምን ይመስላል ?

ማክሰኞ ሪያል ማድሪድ ከ ዲፖርቲቮ አላቬስ

ማክሰኞ እስፓኞል ከ ቪያሪያል

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
Forwarded from HEY Online Market
iPhone 16 Promax
iPhone 16 Pro
iPhone 16 Plus
iPhone 16
Available Now!

0925927457 @eBRO4
0953964175 @heymobile
@heyonlinemarket
ተጠባቂ የዛሬ መርሐ ግብሮች !

10:00 ብራይተን ከ ኖቲንግሀም ፎረስት

10:00 ኢትዮ ኤሌክትሪክ ከ ወላይታ ድቻ

10:30 ባየር ሌቨርኩሰን ከ ዎልፍስበርግ

12:30 ማንችስተር ሲቲ ከ አርሰናል

1:00 ቅዱስ ጊዮርጊስ ከ ፋሲል ከነማ

1:30 ቪያሪያል ከ ባርሴሎና

3:45 ኢንተር ሚላን ከ ኤሲ ሚላን

3:45 ሊዮን ከ ማርሴይ

🔴 የዛሬው የይግምቱ ሽልማታችን የማንችስተር ሲቲ ከ አርሰናል ፣ ባርሴሎና እና ኢንተር ሚላን ጨዋታዎች ናቸው።

🔴 የዛሬ ሶስት ሽልማቶቻችን 11:00 ፣ 12:00 ፣ 2:15 ሰዓት ላይ ወደ ቤተሰቦቻችን የሚደርሱ ይሆናል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
አሸናፊዎች ተለይተዋል።

የሪያል ማድሪድ እና እስፓኞልን ጨዋታ ትክክለኛ ምላሽ ቀድመው የሰጡት ከስር የተገለፁት የቤተሰባችን አባላት ናቸው።

ትክክለኛ ምላሽ የሰጡትን በመፈለጉ ሂደት የተዘለለ እና ያልታየ ካለ ማሳወቅ ይቻላል። Edit የተደረገ መልስ ተቀባይነት አይኖረውም።

ስጦታ የሚበረከትላቸው ቀድመው የመለሱ ሶስት አሸናፊዎች ብቻ ናቸው።

1️⃣ኛ Yesl.D
2️⃣ኛ Mac Alister
3️⃣@Gunne_rs

@tikvahethsport
“ 0ለ0 የምትወጣው ተጋጣሚህ ሲበልጥህ ነው “ ጋርዲዮላ

የማንችስተር ሲቲው ዋና አሰልጣኝ ፔፕ ጋርዲዮላ ቡድናቸውን “ ስራን ወደ ውጤት መቀየር የሚችል ነው “ ሲሉ ገልጸዋል።

ማንችስተር ሲቲ በአለም ላይ የተዋጣለት ቡድን ነው በማለት የተናገሩት አሰልጣኝ ፔፕ ጋርዲዮላ “ እኛ የሰራነውን ወደ ውጤት መቀየር የምንችል ቡድን ነን “ ብለዋል።

“ 0ለ0 የምትወጣው ደካማ ሆነህ ስትጫወት ወይም ተጋጣሚህ ሲበልጥህ ነው “ ያሉት አሰልጣኝ ፔፕ ጋርዲዮላ እኔ ለ 0ለ0 እንደማልጫወት አርቴታ ያውቃል እሱም እንደማይጫወት አውቃለሁ “ ሲሉ ተናግረዋል።

ጨዋታዎችን የማደርገው ለመዝናናት ሳይሆን ለማሸነፍ እና ገንዘብ ለማግኘት ነው ሲሉ አሰልጣኝ ፔፕ ጋርዲዮላ ተናግረዋል።

“ ሁለት ሪኮ ሌዊስ ቢኖረኝ ጥሩ ነበር አንዱ ትንሽ ረዘም ያለ ቢሆን ነገርግን ምን ላድርግ ጉዳዩ የእናት እና አባቱ ነው።“ ጋርዲዮላ

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
“ ወደዛ ሄደን ለማሸነፍ ዝግጁ ነን “ ዴክላን ራይስ

የመድፈኞቹ የመሐል ሜዳ ተጨዋች ዴክላን ራይስ አርሰናል ዛሬ ከማንችስተር ሲቲ ጋር የሚያደርገው ጨዋታ ከባድ እንደሚሆን ገልጿል።

“ ከባድ ጨዋታ ይሆናል “ ያለው ዴክላን ራይስ ምን ይዘው እንደሚመጡ እናውቃለን በምናደርገው ነገር እና እያደረግን ባለነው ነገር እምነት አለን በማለት ተናግሯል።

ዴክላን ራይስ አክሎም ቡድናቸው በኢትሀድ ስታዲየም በተጋጣሚው ላይ የበላይነቱን ወስዶ ለማሸነፍ ዝግጁ መሆኑን ገልጿል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
ኢንተር ሚያሚ ተቃውሞ ገጥሞታል !

የአሜሪካ ሜጀር ሊግ ሶከሩ ክለብ ኢንተር ሚያሚ ትላንት ከኒውዮርክ ሲቲ ጋር አቻ በተለያዩበት ጨዋታ የቡድን ባሳቸው በተቃራኒ ደጋፊ ተቃውሞ ሲገጥመው ነበር።

የሊዮኔል ሜሲው ቡድን ኢንተር ሚያሚ ከሜዳው ውጪ ጨዋታውን ሲያደርግ ለመጀመሪያ ጊዜ በተጋጣሚው ደጋፊዎች ተቃውሞዎች ገጥመውታል።

በጨዋታው ኒውዮርክ ሲቲ ከፍተኛ የሆነ የተመልካች ቁጥር ማስመዝገቡን አሳውቋል።

ኢንተር ሚያሚ በጨዋታው በመጨረሻ ደቂቃ በተቆጠረበት ግብ 1ለ1 ለመለያየት መገደዱ ይታወሳል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
“ ባለፈው አመት ሀላንድን ማቆም ችለናል “ ሳሊባ

የሰሜን ለንደኑ ክለብ አርሰናል የኋላ መስመር ተጨዋች ዊሊያም ሳሊባ የማንችስተር ሲቲው አጥቂ ኤርሊንግ ሀላንድ አሰቸጋሪ አጥቂ መሆኑን ገልጿል።

"ኤርሊንግ ሀላንድ በጣም ጥሩ ተጨዋች ነው አለም ላይ ካሉ ምርጥ የፊት መስመር አጥቂዎች አንዱ ነው።"ሲል ዊሊያም ሳሊባ ተናግሯል።

“ ከሀላንድ ጋር መጫወት አስቸጋሪ ነው ነገርግን ባለፈው አመት እሱ ግብ እንዳያስቆጥር ለመከላከል የቻልነውን ሁሉ አድርገናል እናም አልተሳካለትም።“ ሳሊባ

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
“ ሁሉም ሰው ሲቲ እንዲወርድ ይፈልጋል “ ጋርዲዮላ

የማንችስተር ሲቲው ዋና አሰልጣኝ ፔፕ ጋርዲዮላ በዚህ በሰለጠነ ዘመን ሁሉም ሰው እኛ እንድንወርድ እየጠየቀ ነው በማለት ተናግረዋል።

“ ለቡድኔ መከላከል እፈልጋለሁ “ ያሉት አሰልጣኝ ፔፕ ጋርዲዮላ " በዚህ በሰለጠነ ዘመን ሁሉም ሰው እኛ እንድንወርድ እና ከምድረ ገፅ እንድንጠፋ ይፈልጋል " በማለት ቅሬታቸውን ገልጸዋል።

" አሰልጣኝ መሆን የምትፈልግ ከሆነ የእኔን የአሰልጣኝ ቡድን ተቀላቀል ያን ጊዜ ምናልባት ምርጥ ቡድን የማሰልጠን እድል ታገኛለህ።" ጋርዲዮላ

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
ኢትሃድ የሳምንቱን ታላቅ ጨዋታ ያስተናግዳል

ሁለቱም ክለቦች ያለወሳኝ ተጫዋቾቻቸው የሳምንቱን ፈታኝ ጨዋታ ያደርጋሉ።
ሲቲ ያለ ዴብርዩነ፣ አርሰናል ያለ ኦዴጋርድ።
በጨዋታው ማን የበላይ ሆኖ ይጨርሳል?

ከፍ በተደረጉ ኦዶች የጨዋታውን አሸናፊ ይገምቱ!
አሁኑኑ ለመወራረድ ሊንኩን ይጫኑ https://shorturl.at/bmqEp
ቤቲካ የአሸናፊዎች ቤት!
⚡️ በዕለታዊ የዳታ ጥቅሎች ቀኑን ሙሉ ፈታ እንበል! 🥳

በM-PESA ላይ ስንገዛ ሁሉም ቅናሽ አላቸው!

በልዩ ልዩ አማራጮች የቀረበልንን የሳፋሪኮም የኢንተርኔት ጥቅል የM-PESA Appን በመጠቀም አሁኑኑ እንግዛ! በፈጣን ዳታ እንንበሽበሽ!

🔗የM-PESA ሳፋሪኮም መተግበሪያ በዚህ ሊንክ እናዉርድ:
https://play.google.com/store/apps/details?id=et.safaricom.mpesa.lifestyle

የቴሌግራም ቦታችንን
https://www.tg-me.com/official_safaricomet_bot በመጠቀም የአየር ሰዓት ወይንም ልዩ ልዩ ጥቅሎችን እንግዛ!

ስለ አገልግሎታችን ማንኛውንም ጥያቄ ወይም መረጃ በቴሌግራም ቻናላችን
https://www.tg-me.com/Safaricom_Ethiopia_PLC 24/7 ማግኘት ይቻላል!

#MPESASafaricom
#SafaricomEthiopia
#1wedefit
#Furtheraheadtogether
2024/09/28 21:27:16
Back to Top
HTML Embed Code: