Telegram Web Link
“ አል ነስር ትልቅ ነገር የማሳካት አቅም አለው “ ስቴፋኖ ፒዮሊ

ፖርቹጋላዊውን አሰልጣኝ ሉዊስ ካስትሮን ያሰናበተው የሰዑዲ ዓረቢያው ክለብ አል ነስር ጣልያናዊውን አሰልጣኝ ስቴፋኖ ፒዮሊ በይፋ በአሰልጣኝነት ሾሟል።

በአል ነስር ቤት የሶስት አመት ውል የፈረሙት አሰልጣኝ ስቴፋኖ ፒዮሊ “ አል ነስር ጥሩ ነገር ማሳካት የሚችል አቅም አለው “ ሲሉ ተናግረዋል።

“ በዚህ አመት የአል ነስርን ሁሉንም ጨዋታዎች ተመልክቻለሁ “ ያሉት አሰልጣኙ “ በቀጣይ የወደፊቱ ላይ ማተኮር አለብን “ ብለዋል።

“ ከዚህ በፊት ከሰዑዲ ዓረቢያ ጥያቄ ቀርቦልኛል ነገርግን እንድቀበል ያደረገኝ የአል ነስር ጥያቄ ነው በዚህ ደስተኛ ነኝ “ አሰልጣኝ ስቴፋኖ ፒዮሊ

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
የኢትዮጵያ ኦሎምፒክ ኮሚቴ በድጋሜ እግድ ተጣለበት !

የኢትዮጵያ ኦሎምፒክ ኮሚቴ ተነስቶለት የነበረው እገድ በተጠየቀ ይግባኝ በድጋሜ በፍርድ ቤት መታገዱ ይፋ ተደርጓል።

የኢትዮጵያ ኦሎምፒክ ኮሚቴ ላይ ከተላለፉት እግዶች ለአብነትም :-

- ኦሎምፒክ ኮሚቴው በአስራ አንድ ባንኮች ያሉት ገንዘብ ከደሞዝ ውጪ በድጋሜ እንዲታገድ።

- ግንቦት 6/2016 ዓ.ም እና ሰኔ 4/2016 ዓ.ም የተደረጉ ጉባኤ እና ምርጫዎች ታግደው እንዲቆዩ መወሰኑ ተገልጿል።

የኢትዮጵያ ኦሎምፒክ ኮሚቴ የ 2024 ፓሪስ ኦሎምፒክ ውድድር የእውቅናና የሽልማት ስነ ስርዓት በዛሬው ዕለት ለማካሄድ ቀጠሮ መያዙ ይታወቃል።

ሙሉ መረጃው ከላይ በምስሉ ላይ ተያይዟል።

ምንጭ :- ጋዜጠኛ ይስሀቅ በላይ

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
“ 500,000 ዶላር ያለ አግባብ ጠፍቷል “ አቶ እያሱ ወሰን

የአፍሪካ ቦክስ ኮንፌዴሬሽን ፕሬዝዳንት አቶ እያሱ ወሰን የኢትዮጵያ ኦሎምፒክ ኮሚቴን ለመቃወም

- ከሻለቃ ኃይሌ ገብረሥላሴ ፣

- አትሌት ገዛኸኝ አበራ እና

- ታምራት በቀለ ጋር በመሆን አቋም መያዛቸውን ገልፀዋል።

በ " X " የማህበራዊ ትስስር ገፃቸው መልዕክታቸውን ያጋሩት አቶ እያሱ ወሰን ከፍተኛው ፍርድ ቤት “ አስደንጋጭ “ ባሏቸው ክሶች የኦሎምፒክ ኮሚቴውን የባንክ ሒሳብ ማገዱን አረጋግጠዋል።

ኦሎምፒክ ኮሚቴው ላይ ከቀረቡ ክሶች መካከልም :-

- 156 ሚልዮን ብር ለቶኪዮ ኦሎምፒክ ያለአግባብ የተወሰደ

- 47 ሚልዮን ብር ከ " ANOCA " የተገኘ በተገቢ ሁኔታ ጥቅም ላይ ያልዋለ

- 500,000 ዶላር ከአፍሪካ ጨዋታዎች የተገኘ ገንዘብ በቀላሉ መጥፋቱን አቶ እያሱ ወሰን ገልጸዋል።

ፕሬዝዳንቱ “ የኢትዮጵያ ስፖርት ታማኝነት አደጋ ላይ ወድቋል “ ሲሉ “ ግልፀኝነትና ተጠያቂነት እንዲኖር እንጠይቃለን “ በማለት መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
Forwarded from WANAW SPORT
🌼 ልዩ የአዲስ ዓመት ስጦታ እስከ ጥቅምት 15 ብቻ! 🌼

📌 ለበለጠ መረጃና ትዕዛዝ 📲 09011382830910851535 እና 0913586742 ላይ ይደውሉ።

👉🏾 እንዲሁም በቴሌግራም @Wanawsales ላይ የሽያጭ ሰራተኞቻችንን በቀጥታ በማናገር ወይም በቴሌግራም ቦት @WanawSportBot ይዘዙን።

Instagram | Facebook | TikTok

🏅ዋናው ወደፊት...

@wanawsportwear
ኦሎምፒክ ኮሚቴ የሽልማት መርሐ ግብር አካሄደ !

የኢትዮጵያ ኦሎምፒክ ኮሚቴ በ 2024 የፓሪስ ኦሎምፒክ ውድድር ጥሩ ውጤት ላስመዘገቡ አትሌቶች የእውቅና ሽልማት መርሐ ግብር በዛሬው ዕለት አከናውኗል።

በዚህም መሰረት በማራቶን ውድድር የኦሎምፒክን ክብረወሰን በማሻሻል ያሸነፈው አትሌት ታምራት ቶላ የሁለት ሚሊየን ብር ሽልማት ተበርክቶለታል።

በውድድሩ የብር ሜዳልያ አሸናፊ የሆኑት

- ትግስት አሰፋ ፣

- በሪሁ አረጋዊ እና

- ጽጌ ድጉማ የአንድ ሚሊየን ብር ተሸላሚ ሆነዋል።

አሰልጣኝ ገመዶ ደደፎ በበኩሉ የሚያሰለጥናቸው አትሌቶች የወርቅ እና የብር ሜዳልያ ማስገኘታቸውን ተከትሎ 1.8 ሚሊየን ብር ሽልማት ተበርክቶለታል።

ከዚህ በተጨማሪም :-

- አትሌት ለሜቻ ግርማ ፣
- አትሌት ቀነኒሳ በቀለ ፣
- አሰልጣኝ ቶሌራ ዲንቃ ፣
- አሰልጣኝ ሀጂ አዴሎ ፣
- ኮማንደር ደራርቱ ቱሉ ደግሞ ልዩ ተሸላሚ በመሆን በምሽቱ እውቅና ተሰጥቷቸዋል።

መረጃው የኢቢኤስ ቴሌቪዥን ነው።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
የሊቨርፑል የወሩ ምርጥ ተጨዋች ታውቋል !

በአሰልጣኝ አርኔ ስሎት የሚመራው የመርሲሳይዱ ክለብ ሊቨርፑል የወርሀ ነሐሴ የወሩ ምርጥ ተጨዋቻቸውን ይፋ አድርገዋል።

በዚህም መሰረት ግብፃዊው የፊት መስመር ተጨዋች መሐመድ ሳላህ የሊቨርፑል የወርሀ ነሐሴ የወሩ ምርጥ ተጨዋች በመሆን በአብላጫ ድምፅ መመረጥ ችሏል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
#Ethiopia 🇪🇹

የ 2016ዓ.ም የኢትዮጵያ ፕርሚየር ሊግ የአመቱ የኮከቦች ሽልማት በድሬዳዋ በመካሄድ ላይ ይገኛል።

የሊጉ ክለቦች ከቀጥታ ስርጭት የሚያገኙትን ክፍያ ሲቀበሉ በሻምፒዮኑ ንግድ ባንክ እና ወራጁ ሀምበሪቾ መካከል የ 10ሚልዮን ብር ልዩነት መኖሩ ተገልጿል።

ይህንንም ተከትሎ :-

1ኛ ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ - 18,372,924 ብር
2ኛ መቻል - 17,190,949 ብር
3ኛ ኢትዮጵያ ቡና - 16,068,481 ብር

4ኛ ባህርዳር ከተማ - 15,059,520 ብር
5ኛ ቅዱስ ጊዮርጊስ - 14,110,065 ብር
6ኛ ፋሲል ከተማ - 13,238,116 ብር
7ኛ አዳማ ከተማ 12,443,674 ብር

8ኛ ሀድያ ሆሳዕና - 11,726,739 ብር
9ኛ ሀዋሳ ከተማ - 11,887,310 ብር

10ኛ ኢትዮጵያ መድን - 10,525,387 ብር
11ኛ ሲዳማ ቡና - 10,040,971 ብር

12ኛ ድሬዳዋ ከተማ - 9,634,062 ብር
13ኛ ወላይታ ድቻ - 9,316,159 ብር
14ኛ ወልቂጤ ከተማ - 9,052,763 ብር

15ኛ ሻሸመኔ ከተማ - 8,878,373 ብር
16ኛ ሀምበሪቾ ዱራሜ - 8,781,490 ብር ገቢ ማግኘት ችለዋል።

ይህ ገቢ ክለቦቹ ከቴሌቪዥን መብት ሽያጭ እንዲሁም ከተለያዩ ገቢዎች ተቀንሶ ለክለቦች የሚደርስ ክፍያ መሆኑ ተገልጿል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
#Ethiopia 🇪🇹

የተጠናቀቀው የውድድር ዘመን ( 2016ዓ.ም ) የኢትዮጵያ ፕርሚየር ሊግ የአመቱ ኮከቦች ሽልማት በድሬዳዋ ተካሂዷል።

የሊጉ ሻምፒዮን ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በአመቱ የኮከቦች ሽልማት በሶስት ዘርፎች አሸናፊ መሆን ችለዋል።

በዚህም መሰረት :-

➡️ የአመቱ ኮከብ ተጫዋች - ባሲሩ ኡመር

- ጋናዊው የመሐል ሜዳ ተጫዋች ባሲሩ ኡመር በኢትዮጵያ ፕርሚየር ሊግ ታሪክ የአመቱ ኮከብ ሽልማትን ያሸነፍ የውጭ ሀገር ተጫዋች ሆኗል።

- ባሲሩ ኡመር 210,000 ብር ተሸላሚ መሆን ችሏል።

➡️ የአመቱ ተስፈኛ (ወጣት) ተጫዋች - ቢንያም አይተን

- ቢንያም አይተን የ 105,000 ብር ተሸላሚ ሆኗል።

- አዳማ ከተማ እግር ኳስ ክለብ በዚህ የሽልማት ዘርፍ ለተከታታይ አመት ተጫዋች ማስመረጥ ችለዋል።

➡️ የአመቱ ምርጥ አሰልጣኝ - አሰልጣኝ በፀሎት ልዑል ሰገድ

- አሰልጣኝ በፀሎት ልዑል ሰገድ የ 200,000ሺህ ብር ሽልማት ተበርክቶላቸዋል።

➡️ የአመቱ ኮከብ ግብ አስቆጣሪ - አሊ ሱሌማን ( ሀያ ጎል )

- ኤርትራዊው የሀዋሳ ከተማ አጥቂ አሊ ሱሌማን የ 200,000ሺህ ብር ተሸላሚ ሆኗል።

➡️ የአመቱ ኮከብ ግብ ጠባቂ - ፍሬው ጌታሁን

- ፍሬው ጌታሁን 150,000 ብር የገንዘብ ሽልማት ተበርክቶለታል።

➡️ የአመቱ ምርጥ ምስጉን ረዳት ዳኛ - ኢንተርናሽናል ረዳት ዳኛ ፋሲካ ዮኋላሸት

- ኢንተርናሽናል ረዳት ዳኛ ፋሲካ የኋላሸት የ 105,000 ብር ተሸላሚ ሆነዋል።

➡️ የአመቱ ምርጥ ኮከብ ዋና ዳኛ - ኢንተርናሽናል ባምላክ ተሰማ

- ኢንተርናሽናል ባምላክ ተሰማ 105,000 ብር የገንዘብ ሽልማት ተበርክቶላቸዋል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
የጨዋታ አሰላለፎች !

4:00 አታላንታ ከ አርሰናል

4:00 ሞናኮ ከ ባርሴሎና

@tikvahethsport @kidusyoftahe
Forwarded from TIKVAH-SPORT
#UCL

የአውሮፓ ሻምፒየንስ ሊግ የመጀመሪያ ጨዋታዎች ሲደረጉ ባየር ሌቨርኩሰን እና ቤኔፊካ ተጋጣሚዎቻቸውን መርታት ችለዋል።

ባየር ሌቨርኩሰን ፊኖርድን 4ለ0 በሆነ ሰፊ ውጤት ሲያሸንፍ ግቦቹን ፍሎሪያን ቨርትዝ 2x ፣ ግሪማልዶ እና ዌለንሩተር ከመረብ አሳርፈዋል።

ቤኔፊካ በበኩሉ የሰርቢያውን ክለብ ሬድ ስታር ቤልግሬድ 2ለ1 በሆነ ውጤት ማሸነፍ ችሏል።

ለቤኔፊካ የማሸነፊያ ግቦችን አክቱርኮግሉ እና ኮክቹ ከመረብ ሲያሳርፉ ለሬድ ስታር ቤልግሬድ ሚልሰን አስቆጥሯል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
“ ጄሱስ በሻምፒየንስ ሊግ ጥሩ ልምድ አለው “ አርቴታ

የመድፈኞቹ ዋና አሰልጣኝ ሚኬል አርቴታ የማንችስተር ሲቲን ጨዋታ ከማሰባቸው በፊት በዛሬው ጨዋታ ትኩረት ማድረግ እንደሚፈልጉ ገልጸዋል።

" ጋብሬል ጄሱስ ጥሩ ልምምድ ሰርቷል በአውሮፓ ሻምፒየንስ ሊግም ጥሩ ልምድ አለው።" ሲሉ ሚኬል አርቴታ በቋሚ አሰላለፍ ስላካተቱበት ምክንያት አስረድተዋል።

" ትኩረት የምናደርገው የዛሬው ጨዋታ ላይ ብቻ ነው ፣ ቀጥለን ሴለ ማንችስተር ሲቲ ጨዋታ ማሰብ እንጀምራለን።"አርቴታ

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
16 '

ሞናኮ 1-0 ባርሴሎና

አታላንታ 0-0 አርሰናል

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
#TikvahGoal

በአሁን ሰዓት እየተካሄዱ የሚገኙ ጨዋታዎች ጎሎች እና አጫጭር ቪዲዮች በጎል ቻናላችን መመልከት ይችላሉ።

የጎል ቻናላችን 👉 https://www.tg-me.com/+rbdEU4UaEdQxYWFk

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
27 '

ሞናኮ 1-1 ባርሴሎና

አክልዮች ላሚን ያማል

አታላንታ 0-0 አርሰናል

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
እረፍት

ሞናኮ 1-1 ባርሴሎና

አክልዮች               ላሚን ያማል

አታላንታ 0-0 አርሰናል

አትሌቲኮ ማድሪድ 1-1 ሌፕዚግ

ግሪዝማን ሴስኮ

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
72 '

ሞናኮ 2-1 ባርሴሎና

አክልዮች        ላሚን ያማል
ኤኒኬና

አታላንታ 0 - 0 አርሰናል

አትሌቲኮ ማድሪድ 1-1 ሌፕዚግ

ግሪዝማን           ሴስኮ

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
2024/09/30 19:30:58
Back to Top
HTML Embed Code: