Telegram Web Link
ሞሮኮ ግማሽ ፍፃሜውን ተቀላቀለች !

በ2024 የፓሪስ ኦሎምፒክ ውድድር እግርኳስ ጨዋታ አፍሪካዊቷ ሀገር ሞሮኮ አሜሪካን በመርታት ግማሽ ፍፃሜውን ተቀላቅላለች።

ሞሮኮ ከአሜሪካ ያደረገችውን የሩብ ፍፃሜ እግርኳስ ጨዋታ በሀኪሚ ፣ ራሂሚ ፣ አኮማች እና ማኦቡብ ግቦች 4ለ0 በሆነ ሰፊ ውጤት ማሸነፍ ችላለች።

የሞሮኮ ኦሎምፒክ እግርኳስ ብሔራዊ ቡድን በታሪኩ ለመጀመሪያ ጊዜ ለኦሎምፒክ ግማሽ ፍፃሜ መድረስ ችሏል።

ሞሮኮ በግማሽ ፍፃሜው የስፔን እና ጃፓን ብሔራዊ ቡድን አሸናፊን የምትገጥም ይሆናል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
#TeamEthiopia 🇪🇹

በ2024 ፓሪስ ኦሎምፒክ 5,000ሜ ሴቶች ማጣሪያ ውድድር በመጀመሪያው ዙር የተሳተፉት ኢትዮጵያዊያን አትሌቶች ጉዳፍ ፀጋይ እና እጅጋየሁ ታዬ ለፍፃሜ ማለፋቸውን አረጋግጠዋል።

አትሌት ጉዳፍ ፀጋይ በማጣሪያ ውድድሩ 14:57.84 በሆነ ሰዓት #አምስተኛ ደረጃን በመያዝ ማጠናቀቅ ችላለች።

እጅጋየሁ ታዬ በበኩሏ 14:57.97 በሆነ ሰዓት #ስድስተኛ ደረጃን በመያዝ ማጠናቀቅ ችላለች።

የመጀመሪያውን ዙር የማጣሪያ ውድድር ኬኒያዊቷ ኪፕዬጎን አንደኛ ኔዘርላንዳዊቷ ሲፋን ሀሰን ሁለተኛ በመሆን አጠናቀዋል።

በቀጣይ በመጨረሻው ዙር ኢትዮጵያዊቷ አትሌት መዲና ኢሳ የማጣሪያ ውድድሯን የምታደርግ ይሆናል።

የ 5,000ሜ ሴቶች ፍፃሜ ውድድር ሰኞ ሐምሌ 29/2016 ዓ.ም ምሽት 4:10 ሰዓት ይካሄዳል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
#TeamEthiopia 🇪🇹

በ2024 ፓሪስ ኦሎምፒክ 5,000ሜ ሴቶች ማጣሪያ ውድድር በሁለተኛ ዙር የተሳተፈችው ኢትዮጵያዊያን አትሌት መዲና ኢሳ ለፍፃሜ ማለፏን አረጋግጣለች።

አትሌት መዲና ኢሳ በማጣሪያ ውድድሩ 15:00.82 በሆነ ሰዓት በመግባት #ሁለተኛ ደረጃን በመያዝ ማጠናቀቅ ችላለች።

አስቀድሞ በመጀመሪያው ዙር የተወዳደሩት አትሌቶች ጉዳፍ ፀጋዬ እና እጅጋየሁ ታዬ ለፍፃሜው ማለፋቸውን ማረጋገጣቸው ይታወቃል።

የ 5,000ሜ ሴቶች ፍፃሜ ውድድር ሰኞ ሐምሌ 29/2016 ዓ.ም ምሽት 4:10 ሰዓት ይካሄዳል።

@tikvahethsport @kidusyoftahe
#Paris2024

በ2024 የፓሪስ ኦሎምፒክ ውድድር እግርኳስ ጨዋታ የስፔን ኦሎምፒክ ብሔራዊ ቡድን የጃፓን አቻውን በመርታት አግማሽ ፍፃሜውን ተቀላቅለዋል።

ስፔን ከጃፓን ያደረገችውን የሩብ ፍፃሜ ጨዋታ በፌርሚን ሎፔዝ 2x እና አቤል ሩይዝ ግቦች 3ለ0 በሆነ ውጤት ማሸነፍ ችለዋል።

የስፔን ኦሎምፒክ ብሔራዊ ቡድን በግማሽ ፍፃሜው የሞሮኮ ብሔራዊ ቡድንን የፊታችን ሰኞ የሚገጥም ይሆናል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
" እየሰራሁ የቆየሁት ወርቅ ለማሸነፍ ነው " ሰለሞን ባረጋ

በፓሪስ ኦሎምፒክ በ10,000ሜትር ለወርቅ ሜዳልያ ከሚጠበቁት አትሌቶች መካከል አንዱ የሆነው ሰለሞን ባረጋ የቶኪዮ ኦሎምፒክን ድል መድገም እንደሚፈልግ ተናግሯል።

" የቶኪዮን ድል ዘንድሮም እደግመዋለሁ ብዬ ዝግጅቴን ሳደርግ ቆይቻለሁ " ያለው ሰለሞን ባረጋ " የሰው ልጅ ያስባል እግዚአብሔር ነው የሚፈጽመው " ሲል ስለ ውድድሩ ተናግሯል።

ሰለሞን ባረጋ አያይዞም አላማው ወርቅ ማሸነፍ እንደሆነ ሲገልፅ " የወርቅ ሜዳልያውን ወደ ሀገሬ ይዤ ለመመለስ ከሌሎች ውድድሮች ራሴን ቆጥቤ ለኦሎምፒክ ስዘጋጅ ነበር" ብሏል።

ሰለሞን ባረጋ በቶኪዮ ኦሎምፒክ ጆሽዋ ቼፕቴጊ እና ጃኮብ ኪፕሊሞን በማስከተል በ10,000ሜትር ወርቅ አሸናፊ መሆኑ አይዘነጋም።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
#TeamEthiopia 🇪🇹

በ 800ሜ ሴቶች ማጣርያ በሶስተኛ ምድብ የምትገኘው ወርቅነሽ መሰለ #አንደኛ ደረጃን በመያዝ ግማሽ ፍፃሜውን ተቀላቅላለች።

በ2024 ፓሪስ ኦሎምፒክ 800ሜ ሴቶች ማጣሪያ ውድድር የተሳተፈችው አትሌት ሀብታም አለሙ ቀጣዩን ዙር መቀላቀል አልቻለችም።

አትሌት ሀብታም አለሙ በማጣሪያ ውድድሩ 2:02.19 በሆነ ሰዓት ሰባተኛ ደረጃን በመያዝ ማጠናቀቅ ችላለች።

አትሌት ሀብታም አለሙ በቀጣይ " repêchage " በተባለው የአለም አትሌቲክስ አዲስ ህግ ሌላ ውድድር የምታደርግ ይሆናል።

ቀጣዩን ዙር መቀላቀል ያልቻሉ አትሌቶች ግማሽ ፍፃሜውን ለመቀላቀል ነገ የ " repêchage " ማጣሪያ ውድድራቸውን ቀን 6:10 የሚያደርጉ ይሆናል።

የ800ሜ ሴቶች ግማሽ ፍፃሜ ውድድር የፊታችን እሁድ ሐምሌ 28/2016 ዓ.ም ምሽት 3:35 የሚደረግ ይሆናል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
#TeamEthiopia 🇪🇹

በፓሪስ ኦሎምፒክ 800ሜ ሴቶች ማጣርያ በአምስተኛ ምድብ የተካፈለችው አትሌት ፅጌ ዱጉማ #አንደኛ ደረጃን በመያዝ ግማሽ ፍፃሜውን ተቀላቅላለች።

አትሌት ፅጌ ዱጉማ የማጣሪያ ውድድሯን 1:57.90 በሆነ ሰዓት በመግባት በበላይነት ማጠናቀቅ ችላለች።

ቀድመው በተደረጉ የማጣሪያ ውድድሮች አትሌት ወርቅነሽ መሰለ #አንደኛ ደረጃን በመያዝ ግማሽ ፍፃሜውን ስትቀላቀል አትሌት ሀብታም አለሙ ቀጣዩን ዙር #በቀጥታ መቀላቀል ሳትችል ቀርታለች።

ቀጣዩን ዙር መቀላቀል ያልቻሉ አትሌቶች ግማሽ ፍፃሜውን ለመቀላቀል ነገ የ " repêchage " ማጣሪያ ውድድራቸውን ቀን 6:10 ጀምሮ የሚያደርጉ ይሆናል።

የ800ሜ ሴቶች ግማሽ ፍፃሜ ውድድር የፊታችን እሁድ ሐምሌ 28/2016 ዓ.ም ምሽት 3:35 የሚደረግ ይሆናል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
TIKVAH-SPORT
ኒኪታህ ማርሴይን ለመቀላቀል ተስማማ ! እንግሊዛዊ የፊት መስመር ተጨዋች ኤዲ ኒኪታህ አርሰናልን በመልቀቅ የፈረንሳዩን ክለብ ማርሴይ ለመቀላቀል ከስምምነት መድረሱ ተገልጿል። ማርሴይ በበኩሉ በተጨዋቹ ዝውውር ሒሳብ ዙሪያ ከአርሰናል ጋር ከስምምነት ለመድረስ በንግግር ላይ መሆናቸው ተዘግቧል። አሰልጣኝ ሮቤርቶ ዲ ዘርቢን በሀላፊነት የሾመው ማርሴይ ቡድኑን ለማጠናከር በዝውውር መስኮቱ ንቁ ተሳትፎ…
አርሰናል የቀረበለትን ጥያቄ ውድቅ አደረገ !

የሰሜን ለንደኑ ክለብ አርሰናል ለኤዲ ኒኪታህ ከፈረንሳዩ ክለብ ማርሴይ ለሶስተኛ ጊዜ የቀረበለትን 23 ሚልዮን ፓውንድ የዝውውር ሒሳብ ውድቅ ማድረጉ ተገልጿል።

መድፈኞቹ እንግሊዛዊ የፊት መስመር ተጨዋች ኤዲ ኒኪታህ ከ30 ሚልዮን የዝውውር ሒሳብ በታች መሸጥ እንደማይፈልጉ ተነግሯል።

እንግሊዛዊ የፊት መስመር ተጨዋች ኤዲ ኒኪታህ በግሉ አርሰናልን በመልቀቅ የፈረንሳዩን ክለብ ማርሴይ ለመቀላቀል ከስምምነት መድረሱ አይዘነጋም።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
የ 10,000ሜ ወንዶች ፍፃሜ ውድድር ጀምሯል !

ኢትዮጵያውያን አትሌቶች የሚጠበቁበት የፓሪስ ኦሎምፒክ 10,000ሜ ወንዶች ፍፃሜ ውድድር መደረጉን ጀምሯል።

ሀገራችን ኢትዮጵያ በርቀቱ በአትሌት ሰለሞን ባረጋ ፣ ዮሚፍ ቀጀልቻ እና በሪሁ አረጋዊ ተወክላለች።

መልካም እድል ለአትሌቶቻችን 🇪🇹 🇪🇹 🇪🇹

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
18 ዙሮች ይቀራሉ።

1ኛ በሪሁ አረጋዊ
2ኛ ዮሚፍ ቀጀልቻ
3ኛ ሰለሞን ባረጋ

@tikvahethsport @kidusyoftahe
15 ዙሮች ይቀራሉ።

1ኛ
ዮሚፍ ቀጀልቻ
2ኛ
ሰለሞን ባረጋ
3ኛ በ
ሪሁ አረጋዊ

@tikvahethsport @kidusyoftahe
10 ዙሮች ይቀራሉ።

1ኛ ሰለሞን ባረጋ
3ኛ ዮሚፍ ቀጀልቻ
5ኛ በሪሁ አረጋዊ

@tikvahethsport @kidusyoftahe
4 ዙሮች ይቀራሉ።

ስር አትሌቶች ተነጥለው በመቅረት ሜዳሊያ ውስጥ ለማጠናቀቅ ብርቱ ፉክክር እያደረጉ ይገኛሉ።

@tikvahethsport @kidusyoftahe
የ 10,000ሜትር ፍፃሜውን ሲያገኝ ዩጋንዳ የወርቅ ሜዳሊያ አሸናፊ ሆናለች።

🥇ኛ ቼፕቴጋይ ( ኦሎምፒክ ሪከርድ )
🥈ኛ በሪሁ አረጋዊ
🥉ኛ ፊሸር

@tikvahethsport @kidusyoftahe
#TeamEthiopia🇪🇹

የፓሪስ ኦሎምፒክ 10,000ሜ ፍፃሜ ውድድር ሲካሄድ ኢትዮጵያዊው አትሌት በሪሁ አረጋዊ ለሀገራችን ኢትዮጵያ የመጀመሪያውን የብር ሜዳልያ ማስመዝገብ ችሏል።

ጠንካራ ፉክክር በታየበት ውድድር አትሌት በሪሁ አረጋዊ በጥሩ አጨራረስ ሁለተኛ ደረጃን በመያዝ ለሀገራችን ኢትዮጵያ የብር ሜዳልያ አስገኝቷል።

በርቀቱ የተሳተፉት ሌሎች ኢትዮጵያዊያን አትሌቶች

6️⃣ኛ ዮሚፍ ቀጄልቻ
7️⃣ኛ ሰለሞን ባረጋ ደረጃን በመያዝ አጠናቀዋል።

ውድድሩን ዩጋንዳዊው አትሌት ጆሽዋ ቼፕቴጌ የ ኦሎምፒክ ሪከርድ በመስበር በአንደኝነት ማጠናቀቅ ሲችል አሜሪካዊው ፊሸር ሶስተኛ ደረጃን ይዞ አጠናቋል።

ኢትዮጵያ በ10,000ሜ የኦሎምፒክ ውድድር በታሪክ አራተኛው የብር ሜዳልያ በመሆን መመዝገብ ችሏል።

@tikvahethsport @kidusyoftahe
2024/10/06 04:25:40
Back to Top
HTML Embed Code: