Telegram Web Link
እጥፍ ድርብ አሸናፊነት!

በቤቲካ ያሸነፉትን ገንዘብ በACCA እስከ 300% ከፍ ያድርጉ!

አሁኑኑ Betika.et ላይ አሸናፊነትን ይጀምሩ!

ቤቲካ የአሸናፊዎች ቤት!
Forwarded from HEY Online Market
Apple AirPods & Samsung Earbuds

Brand New:
AirPods 2 - 15,500 ETB
AirPods 3 - 24,000 ETB
AirPods Pro 2 - 29,000 ETB


Buds Pro 2 - 16,000ETB
Buds 2 - 11,000ETB

Contact us :
0953964175 @heymobile
0925927457

@Heyonlinemarket
“ የሀገሬ ሰዎች ጨከኑብኝ “ ገዛኸኝ አበራ

የ ኢትዮጵያ አትሌቲክስ ተቀዳሚ ምክትል ፕሬዝዳንት አትሌት ገዛኸኝ አበራ የፓሪስ ኦሎምፒክ “ የአመራረነት ባጅ “ መግቢያው ተሰርዞ እንደጠበቀው ተናግሯል።

በራሱ ወጪ ወደ ፓሪስ ማቅናቱን የገለፀው ገዛኸኝ “ አዲስ አበባ የተሰጠኝ የአመራርነት ባጅ ወደ አትሌቶች መንደር አስተዳደር ተቀይሮ ሰጡኝ “ ሲል ተደምጧል።

ገዛኸኝ ፓሪስ ላይ በተሰጠው የይለፍ መግቢያ ወደ አትሌቶች መንደር ብቻ የሚያስገባ መሆኑን ገልጷል።

“ ይህን ያደረገው የኦሎምፒክ ኮሚቴ ነው ፣ የጨከኑብኝ የሀገሬ ሰዎች ናቸው የሰጡኝን ባጅ አሰርዘው ጠበቁኝ “ ገዛኸኝ አበራ

የ ኦሎምፒክ ኮሚቴን ምርጫ የተቃወመው ገዛኸኝ ድርጊቱን “ የቂም በቀል “ ብሎታል።

የመረጃው ባለቤት ጋዜጠኛ ታምሩ አለሙ ነው።

@tikvahethsport @kidusyoftahe
የሜዳ ቴኒስ ፍፃሜ ተፋላሚዎች ታውቀዋል !

ሰርቢያዊው የሜዳ ቴኒስ ተጨዋች ኖቫክ ጆኮቪች ጣልያናዊውን ሎሬንዞ ሙሴቲ 6-4 እና 6-2 በማሸነፍ ለፍፃሜ መድረሱን አረጋግጧል።

የፊታችን እሁድ በሚደረገው የፓሪስ ኦሎምፒክ የነጠላ ሜዳ ቴኒስ የወርቅ ፍፃሜ ጨዋታ ኖቫክ ጆኮቪች ከስፔናዊው ኮከብ ካርሎስ አልካራዝ ጋር ተጠባቂ ፍልሚያቸውን ያደርጋሉ።

የ 37ዓመቱ ኖቫክ ጆኮቪች በኦሎምፒክ ቴኒስ ፍፃሜ የደረሰ በእድሜ ትልቁ ተጨዋች ሲሆን የ 21ዓመቱ ካርሎስ አልካራዝ በበኩሉ በእድሜ ትንሹ ተጨዋች ሆኖ ይቀርባል።

ሁለቱ ተጨዋቾች ከወር በፊት የተደረገውን ጨምሮ ያለፉት ሁለት አመታት የዌምበልደን ፍፃሜ ተፋላሚ የነበሩ ሲሆን ሁለቱም በካርሎስ አልካራዝ አሸናፊነት መጠናቀቃቸው አይዘነጋም።

ኖቫክ ጆኮቪች እና ካርሎስ አልካራዝ የመጀመሪያ የኦሎምፒክ ወርቅ ሜዳልያቸውን ለማሳካት ከፍተኛ ትንቅንቅ እንደሚያደርጉ ይጠበቃል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
TIKVAH-SPORT
#TeamEthiopia🇪🇹 የፓሪስ ኦሎምፒክ 10,000ሜ ፍፃሜ ውድድር ሲካሄድ ኢትዮጵያዊው አትሌት በሪሁ አረጋዊ ለሀገራችን ኢትዮጵያ የመጀመሪያውን የብር ሜዳልያ ማስመዝገብ ችሏል። ጠንካራ ፉክክር በታየበት ውድድር አትሌት በሪሁ አረጋዊ በጥሩ አጨራረስ ሁለተኛ ደረጃን በመያዝ ለሀገራችን ኢትዮጵያ የብር ሜዳልያ አስገኝቷል። በርቀቱ የተሳተፉት ሌሎች ኢትዮጵያዊያን አትሌቶች 6️⃣ኛ ዮሚፍ ቀጄልቻ…
“ ህዝቡ ወርቅ ቢጠብቅም ብር በማሳካቴ ደስተኛ ነኝ “ በሪሁ አረጋዊ

በፓሪሱ የ2024 ኦሎምፒክ ውድድር ለሀገራችን ኢትዮጵያ የመጀመሪያውን የብር ሜዳልያ ማስመዝገብ የቻለው አትሌት በሪሁ አረጋዊ በውጤቱ ደስተኛ መሆኑን ገልጿል።

“ በኢትዮጵያ የተለመደው ወርቅ ነው “ ያለው አትሌት በሪሁ አረጋዊ “ በቀነኒሳ ፣ ምሩፅ እና ኃይሌ ወርቅ ተለምዷል ነገርግን እኔ በግል ብር በማምጣቴ ደስ ብሎኛል ለእኔ ጥሩ ውጤት ነው “ ሲል ተናግሯል።

በመጨረሻው ሰዓት ስለነበረው ትንቅንቅ የተናገረው አትሌት በሪሁ አረጋዊ “ በአጨራረስ ላይ ዮሚፍ ሲመራ ነበር በኋላ ቼፕቴጌ ጥሎ ወጥቷል እኔ ባገኘሁት ክፍተት ወጥቼ ብር አስገኝቻለሁ በጣም ደስተኛ ነኝ።“ ብሏል።

አትሌት በሪሁ አረጋዊ በ10,000 ሜትር ኦሎምፒክ የወንዶች ውድድር ታሪክ ለኢትዮጵያ ሁለተኛውን የብር ሜዳልያ ማሳካት ችሏል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
TIKVAH-SPORT
“ የሀገሬ ሰዎች ጨከኑብኝ “ ገዛኸኝ አበራ የ ኢትዮጵያ አትሌቲክስ ተቀዳሚ ምክትል ፕሬዝዳንት አትሌት ገዛኸኝ አበራ የፓሪስ ኦሎምፒክ “ የአመራረነት ባጅ “ መግቢያው ተሰርዞ እንደጠበቀው ተናግሯል። በራሱ ወጪ ወደ ፓሪስ ማቅናቱን የገለፀው ገዛኸኝ “ አዲስ አበባ የተሰጠኝ የአመራርነት ባጅ ወደ አትሌቶች መንደር አስተዳደር ተቀይሮ ሰጡኝ “ ሲል ተደምጧል። ገዛኸኝ ፓሪስ ላይ በተሰጠው የይለፍ መግቢያ…
“ ደራርቱ አሳዛኝ ምላሽ ነው የሰጠችኝ “ ገዛኸኝ አበራ

“ ያዋረዱት ገዛኸኝን ሳይሆን ሀገርን ነው “ ኃይሌ ገብረስላሴ

የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ተቀዳሚ ምክትል ፕሬዝዳንት ገዛኸኝ አበራ ተጨማሪ ሀሳቦችን ለጋዜጠኛ ይሳቅ በላይ አካፍሏል።

“ ለሀገሬ ታሪክ የሰራሁ እንጂ ሀገሬን ያዋረድኩ ሰው አይደሉም “ ያለው ገዛኸኝ “ በሰው ሀገር ይህ አይነት ውርደት መፈፀሙ በጣም እንዳዝን አድርጎኛል “ ብሏል።

“ ዶክተር አሸብር በህገወጥ መንገድ ተመርጧል የህግ ያለህ “ ማለቱ ይህ ድርጊት እንዲፈፀምበት ምክንያት መሆኑን ጠቅሷል።

በፓሪስ ኦሎምፒክ የኦሎምፒኩ ቡድን መሪን ደራርቱ ቱሉን በጉዳዩ ላይ ማብራሪያ የጠየቀው ገዛኸኝ “ የይለፍ መግቢያ ከአትሌቶች ውሰድ “ የሚል ምላሽ እንደተሰጠው ገልፆል።

ገዛኸኝ አበራ የደረሰብኝን በደል የ ኢትዮጵያ ህዝብ ይፍረድ ሲል ቅሬታውን ገልጿል።

ሻለቃ አትሌት ኃይሌ ገብረ ስላሴ ስለ ጉዳዩ ምላሽ ሲሰጥ “ ከ 32ዓመታት በኋላ ማራቶን ወደ ሀገር ቤት የመለሰና ወርቅ ያመጣ አትሌት በገዛ ወገኑ ጥቃት ሲደርስበት ከማየት በላይ ህመም የለም “ ሲል ስሜቱን አጋርቷል።

ኃይሌ ገብረስላሴ አያይዞም ሀገር ተዋርዳለች ሲል “ ይህን ያደረጉ ሰዎች ያዋረዱት ገዛኸኝን ሳይሆን ሀገርን ነው ብሏል።

🔴 የዝግጅት ክፍላችን በጉዳዩ ላይ የኢትዮጵያ ኦሎምፒክ ኮሚቴ የሚመለከታቸውን አካላት አናግሮ ምላሽ የሚያቀርብ ይሆናል።

@tikvahethsport @kidusyoftahe
#TeamEthiopia 🇪🇹

በ2024 የፓሪስ ኦሎምፒክ ውድድር ኢትዮጵያን በውሀ ዋና ስፖርት የምትወክለው ሊና አለማየሁ በ50 ሜትር ሴቶች የነጻ ቀዘፋ ውድድር ወደ ግማሽ ፍጻሜ ለማለፍ የማጣሪያ ውድድሯን ዛሬ ታከናውናለች።

- ሊና አለማየሁ የመጀመሪያ የኦሎምፒክ ተሳትፎዋን ከቀኑ 6:00 ሰዓት በ " París La Défense Arena " ሁለገብ የስፖርት ማዕከል ታደርጋለች።

- በተጨማሪም በትላንትናው ዕለት በ1,500 ሜትር ወንዶች እና በ800 ሜትር ሴቶች ማጣሪያ ማለፍ ያልቻሉ አትሌቶች ዛሬ የ " repêchage " ማጣሪያ ውድድራቸውን ያደርጋሉ።

በዚህም መሰረት :-

- ቀን 6:10 :- 800 ሜትር ሴቶች " repêchage " ማጣሪያ ( አትሌት ሀብታም አለሙ )

- ምሽት 2:15 :- 1,500 ሜትር ወንዶች " repêchage " ማጣሪያ ( አትሌት አብዲሳ ፈይሳ )

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
#TeamEthiopia 🇪🇹

በፓሪስ 2024 ኦሎምፒክ ውድድር ኢትዮጵያን በውሀ ዋና ስፖርት ወክላ የተሳተፈችው ሊና አለማየሁ ውድድሯን በአራተኛነት ማጠናቀቅ ችላለች።

ይህንንም ተከትሎ ሊና አለማየሁ በ50 ሜትር ሴቶች የነጻ ቀዘፋ ውድድር ወደ ግማሽ ፍጻሜ ለማለፍ ሳትችል ቀርታለች።

በምድብ 2 የተወዳደረችው ሊና አለማየሁ በውድድሩ የገባችበት ሰዓት 31 ሴኮንድ ከ87 ማይክሮ ሴኮንድ  ነው።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
#Paris2024

የውሀ ዋና ተጣበቂ ውድድሮች ምሽት ሲደረጉ አራት የወርቅ ሜዳሊያዎች ሲበረከቱ ተጠባቂዋ አሜሪካዊት ኬቲ ሌድኪ ዘጠነኛ የወርቅ ሜዳሊያዋን በኦሎምፒኩ ለማሸነፍ ትጠበቃለች።

ኬቲ ሌድኪ በ 800ሜትር የነፃ ዉሀ ዋና ምሽቱን ስትወዳደር ለማሸነፍ ቅድሚያ ግምቱን አግኝታለች።

ሌድኪ ምሽቱን የምታሸንፍ ከሆነ በኦሎምፒኩ ብዙ የወርቅ ሜዳሊያዎችን ማሸነፍ የቻለች ኦሎምፒያን ለመሆነ ትበቃለች።

ይህ ተጠባቂ ውድድር ከምሽቱ 4:20 ሲል መካሄዱን ይጀምራል።

@tikvahethsport @kidusyoftahe
🎁 በተወዳጆቹ ሜጋ ጥቅሎች ለወራት ያለሃሳብ ዳታ እንጠቀም! ለ90 እና ለ180 ቀን የሚቆዩትን ልዩ የኢንተርኔት ጥቅሎች በM-PESA በመግዛት እስከ 500 ብር የሚደርስ ቅናሽ አግኝተን ፏ እንበል! 🌐🤳 ከሳፋሪኮም ጋር አንድ ወደፊት!⚡️

🤖 የቴሌግራም ቦታችንን https://www.tg-me.com/official_safaricomet_bot በመጠቀም የአየር ሰዓት ወይንም ልዩ ልዩ ጥቅሎችን እንግዛ!

🔗የM-PESA ሳፋሪኮም መተግበሪያ በዚህ ሊንክ እናዉርድ: https://play.google.com/store/apps/details?id=et.safaricom.mpesa.lifestyle

ስለ አገልግሎታችን ማንኛውንም ጥያቄ ወይም መረጃ በቴሌግራም ቻናላችን https://www.tg-me.com/Safaricom_Ethiopia_PLC 24/7 ማግኘት ይቻላል!

#MPESASafaricom
#SafaricomEthiopia
#1Wedefit
#Furtheraheadtogether
Forwarded from WANAW SPORT
🔊 ለማልያ ትጥቅ ፈላጊዎች ልዩ ዕድል #ከዋናው!

🔥 ይህ ዕድል #እንዳያመልጥዎ#ይዘዙን!

📌 ለበለጠ መረጃና ትዕዛዝ 📲 09011382830910851535 እና 0913586742 ላይ ይደውሉ።

👉🏾 እንዲሁም በቴሌግራም @Wanawsales ላይ የሽያጭ ሰራተኞቻችንን በቀጥታ በማናገር ወይም በቴሌግራም ቦት @WanawSportBot ይዘዙን።

🏅 ዋናው ወደፊት...

@wanawsportwear
#Paris2024

አሜሪካዊቷ ፈጣን የ 100ሜትር ሯጭ ሻ ካሪ ሪቻርድሰን ዛሬ ምሽት በሚደረገው የፍፃሜ ውድድር የማሸነፍ ትልቅ ግምትን አግኝታለች።

የኦሎምፒክ የመጀመሪያ ተሳትፎን እያደረገች የምትገኘው የአለም ሻምፒዮና ሻ ካሪ ማጣርያውን 10.94 በማግባት ማሸነፏ ይታወቃል።

የጃማይካ ተፎካካሪዋ ሼሪካ ጃክሰን በውድድሩ አለመኖር ሻ ካሪ በቀላሉ እንድታሸንፍ ከፍተኛ ግምትን አሰጥቷታል።

ሆኖም ግን ሻ ካሪ ከሶስት ጊዜ የ ኦሎምፒክ የወርቅ ሜዳሊያ አሸናፊዋ ሼሊ አን ፍሬዘር ፕራይስ ብርቱ ፉክክር ይጠብቃታል።

ሻ ካሪ ሪቻርድሰን በዘንድሮው የውድድር ዘመን በርቀቱ በተወዳደረችበት መድረክ አልተረታችም።

የ 100ሜትር ሴቶች ፍፃሜ ዛሬ ምሽት 4:15 ሲል ይጀምራል።

@tikvahethsport @kidusyoftahe
TIKVAH-SPORT
የኦሎምፒክ መክፈቻ ዝግጅት የእምነት ተቋማትን አስቆጣ ! ከቀናት በፊት አርብ ምሽት የተካሄደው የ2024 ፓሪስ ኦሎምፒክ ውድድር መክፈቻ ስነ ስርዓት ብዙ የእምነት ተቋማትን ማስቆጣቱ ተገልጿል። በመክፈቻ ዝግጅቱ ላይ የቀረበው ትዕይንት " የክርስትና እምነት ላይ ያፌዘ እና ክብረ ነክ ነው " በሚል የእምነቱን አባቶች ጨምሮ የሀገራት መሪዎችን አስቆጥቷል። በዝግጅቱ ላይ በክርስትና እምነት ተከታዮች…
#Paris2024

የ 2024 ፓሪስ ኦሎምፒክ መክፈቻ ዝግጅት ዳይሬክተር የነበሩት ቶማስ ጆሊ በማህበራዊ ሚዲያዎች የግድያ እና ማስፈራሪያ ዛቻ እንደደረሳቸው ተገልጿል።

የዝግጅቱ ዳይሬክተር ከመክፈቻው በኋላ ማስፈራሪያ እየደረሳቸው እንደሚገኝ ለፓሪስ መንግሥት ባለስልጣናት ማስታወቃቸው ተነግሯል።

የፓሪስ ከተማ ከንቲባ አኔ ሂዳልጎ በዚሁ ጉዳይ ላይ በሰጡት አስተያየት የሚመሩት ከተማ እንዲሁም በግላቸው የማስፈራሪያ ዛቻ ከደረሰባቸው የዝግጅቱ ዳይሬክተር ቶማስ ጆሊ ጎን መሆናቸውን ገልጸዋል።

በተጨማሪም በዳይሬክተሩ ላይ እየደረሱ የሚገኙ የጥላቻ ንግግሮች እና የግድያ እና የማስፈራሪያ ዛቻዎች ምርመራ እየተደረገባቸው እንደሚገኝ ተገልጿል።

በፓሪሱ ኦሎምፒክ መክፈቻ ስነ ስርዓት የተስተዋሉ ድርጊቶች የእምነት ተቋማትን ጨምሮ በርካቶችን ማስቆጣታቸው አይዘነጋም።

የዝግጅቱ ዳይሬክተር በስነ ስርዓቱ ላይ ስለተፈጠረው ድርጊት ባስረዱበት ወቅትም ማስተላለፍ የፈለጉትን መልዕክት በሚገባ ማስተላለፋቸውን ገልፀው ነበር።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
ፊሊፒንስ በፓሪስ ኦሎምፒክ አዲስ ታሪክ ፅፋለች  !

በ2024 ፓሪስ ኦሎምፒክ ውድድር እየተሳተፈች የምትገኘው ፊሊፒንስ በውድድሩ በወንዶች የተገኘ የመጀመሪያ የወርቅ ሜዳልያዋን አሳክታለች።

ፊሊፒናዊው ካርሎስ ኤድሪል ዩሎ በጂምናስቲክ ውድድር ለሀገሩ የመጀመሪያውን የኦሎምፒክ ወርቅ ሜዳልያ ማሳካት የቻለ የመጀመሪያው ወንድ ተወዳዳሪ መሆን ችሏል።

ፊሊፒንስ በኦሎምፒክ ጨዋታ ታሪክ ሁለተኛ የወርቅ ሜዳልያዋን አግኝታለች።

በአርቲስቲክ ጂምናስቲክስ ውድድር ታላቋ ብሪታንያ የብር እንዲሁም እስራኤል የነሐስ ሜዳልያ አስመዝግበዋል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
ሲሞን ባይልስ ሶስተኛ ወርቅ ሜዳልያዋን አሳካች !

ታሪካዊቷ አሜሪካዊ የጂምናስቲክ ተወዳዳሪ ሲሞን ባይልስ ሶስተኛውን የፓሪስ ኦሎምፒክ ወርቅ ሜዳልያዋን በጂምናስቲክ ውድድር ማሳካት ችላለች።

የ 27ዓመቷ የጂምናስቲክ ተወዳዳሪ ሲሞን ባይልስ በኦሎምፒክ ውድድር ታሪክ #ሰባተኛ የወርቅ ሜዳልያዋን ማስመዝገብም ችላለች።

ሲሞን ባይልስ አጠቃላይ በኦሎምፒክ ውድድር አስር ሜዳልያዎችን በማሳካት ስኬታማዋ አሜሪካዊ የጂምናስቲክ ተወዳዳሪ በመሆን ባለታሪክ ሆናለች።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
“ እንግሊዝ ብታሸንፍ አያስቀምጡኝም ነበር " ሮሜሮ

አርጀንቲናዊው የሰሜን ለንደኑ ክለብ ቶተንሀም ተጨዋች ክርስቲያን ሮሜሮ በጀርመኑ የአውሮፓ ዋንጫ ውድድር ፍፃሜ ስፔንን ሲደግፍ እንደነበርገልጿል።

“ በአውሮፓ ዋንጫ ፍፃሜ ከስፔን ጎን ነበርኩ “ የሚለው ክርስቲያን ሮሜሮ " እንግሊዝ ዋንጫውን ብታሸንፍ በጣም ስለሚኮሩ አመቱን ሙሉ አያስቀምጡኝም ነበር " በማለት ተናግሯል።

ክርስቲያን ሮሜሮ ቀጥሎም ቶተንሀም ትልቅ ክለብ መሆኑን በማስረዳት በቀጣይ ዋንጫ ማሸነፍ እንዳለባቸው ገልጿል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
ቻይናዊቷ ቴኒስ ተጨዋች አዲስ ታሪክ ፅፋለች !

ቻይናዊቷ የአለም ቁጥር ሰባት የሜዳ ቴኒስ ተጨዋች ቺንወን ዛንግ በነጠላ ቴኒስ ውድድር የፓሪስ ኦሎምፒክ ወርቅ ሜዳልያ ባለቤት መሆን ችላለች።

ቺንወን ዛንግ በፍፃሜው ክሮሽያዊቷን ዶና ቬኪች ምርጥ ብቃቷን በማሳየት በተከታታይ ዙር 6-2 እና 6-3 በመርታት የወርቅ ሜዳልያ ባለቤት ሆናለች።

ቺንወን ዛንግ በነጠላ የሜዳ ቴኒስ ውድድር ታሪክ የኦሎምፒክ ወርቅ ሜዳልያ ማሳካት የቻለች የመጀመሪያዋ ቻይናዊ ተጨዋች በመሆን አዲስ ታሪክ መፃፍ ችላለች።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
አትሌቲኮ ማድሪድ አልቫሬዝን ለማስፈረም ንግግር ላይ ነው !

የስፔን ላሊጋው ክለብ አትሌቲኮ ማድሪድ አርጀንቲናዊውን የፊት መስመር ተጨዋች ጁሊያን አልቫሬዝ ለማስፈረም ከማንችስተር ሲቲ ጋር በንግግር ላይ መሆኑ ተገልጿል።

በአሰልጣኝ ዲያጎ ሲሞኒ የሚመራው አትሌቲኮ ማድሪድ ተጫዋቹን የማስፈረም ከፍተኛ ፍላጎት እንዳለው ሲገለፅ ዝውውሩን በ46.8 ሚልዮን ፓውንድ እና ተጨማሪ ክፍያ ማጠናቀቅ ይፈልጋሉ ተብሏል።

ማንችስተር ሲቲ በበኩሉ ለተጨዋቹ ዝውውር 70 ሚልዮን ፓውንድ እና ተጨማሪ 20 ሚልዮን ፓውንድ ክፍያ እንደሚፈልግ ተዘግቧል።

ጁሊያን አልቫሬዝ ከቀናት በፊት በማንችስተር ሲቲ ስለሚኖረው የወደፊት ቆይታው ከኦሎምፒክ በኋላ ቁጭ ብሎ ማሰብ እንደሚፈልግ ተናሮ ነበር።

አሰልጣኝ ፔፕ ጋርዲዮላ በበኩላቸው “ አልቫሬዝ ያስብበት እና ምን ማድረግ እንደሚፈልግ በፍጥነት ያሳውቀን “ ሲሉ መናገራቸው አይዘነጋም።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
2024/10/05 13:18:22
Back to Top
HTML Embed Code: