Telegram Web Link
ሊቨርፑል ግብ ጠባቂው ወደ ሜዳ ይመለሳል !

የመርሲሳይዱ ክለብ ሊቨርፑል ቁጥር አንድ ግብ ጠባቂ አሊሰን ቤከር ልምምድ መስራቱን አሰልጣኝ አርኔ ስሎት ገልጸዋል።

“ አሊሰን ልምምድ ሰርቷል ለጨዋታ ብቁ ነው ብለን እናስባለን እሱን በድጋሜ በማግኘታችን ደስተኞች ነን “ ሲሉ አሰልጣኝ አርኔ ስሎት ተናግረዋል።

ብራዚላዊው ግብ ጠባቂ አሊሰን ቤከር በጉዳት ምክንያት ባለፉት ሁለት ጨዋታዎች ለሊቨርፑል ግልጋሎት እንዳልሰጠ ይታወሳል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
ባርሴሎና ከዩኤፋ ቅጣት ተጥሎባቸዋል !

የካታላኑ ክለብ ባርሴሎና ከሞናኮ በነበረ የሻምፒየንስ ሊግ ጨዋታ ደጋፊዎቹ የዘረኝነት ባህሪ አሳይተዋል በሚል ከአውሮፓ እግርኳስ ማህበር ቅጣት እንደተጣለባቸው ተገልጿል።

በዚህም መሰረት ባርሴሎና በቀጣይ ከሜዳው ውጪ ለሚያደርገው አንድ የሻምፒየንስ ሊግ ጨዋታ ትኬቶች እንዳይሸጥ እና 10,000 ዩሮ ቅጣት እንደተጣለበት ተነግሯል።

ይህንንም ተከትሎ ባርሴሎና በቀጣይ ከሜዳው ውጪ ከሬድ ስታር ቤልግሬድ ጋር የሚያደርገውን የሻምፒየንስ ሊግ ጨዋታ ያለ ተጓዥ ደጋፊ ለማድረግ ይገደዳል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
TIKVAH-SPORT
ኒውካስል የተጫዋቹን ውል ማራዘም ይፈልጋል ! ኒውካስል ዩናይትድ የእንግሊዛዊውን የፊት መስመር ተጨዋች አንቶኒ ጎርደን ኮንትራት ማራዘም እንደሚፈልጉ ተገልጿል። በአሰልጣኝ ኤዲ ሀው የሚመራው ኒውካስል ዩናይትድ አንቶኒ ጎርደን ከእረፍት ሲመለስ ኮንትራቱን ለማራዘም ንግግር ለመጀመር ማሰባቸው ተነግሯል። ኒውካስል ዩናይትድ ተጨዋቹ በመጀመሪያ አመቱ በክለቡ ላሳየው ጥሩ ብቃት መሸለም እንደሚፈልጉ ተዘግቧል።…
ኒውካስል የተጫዋቹን ውል ለማራዘም ተስማማ !

ኒውካስል ዩናይትድ የእንግሊዛዊውን የፊት መስመር ተጨዋች አንቶኒ ጎርደን ኮንትራት ለማራዘም ከስምምነት መድረሳቸው ተገልጿል።

በአሰልጣኝ ኤዲ ሀው የሚመራው ኒውካስል ዩናይትድ የአንቶኒ ጎርደንን ኮንትራት እስከ 2029 ለማራዘም መስማማቱ ተነግሯል።

እንግሊዛዊው የፊት መስመር ተጨዋች አንቶኒ ጎርደን በአዲሱ ውል መሰረት የኒውካስል ዩናይትድ ከፍተኛ ተከፋይ እንደሚሆን ተገልጿል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
“ የገጠምናቸው ቡድኖች ከሊጉ ግርጌ የነበሩ ናቸው “ አርኔ ስሎት

የመርሲሳይዱ ክለብ ሊቨርፑል ዋና አሰልጣኝ አርኔ ስሎት ቡድናቸው እስካሁን የገጠማቸው ክለቦች አቋሙን በደንብ የፈተሹ አለመሆናቸውን ገልጸዋል።

“ የገጠምናቸው ቡድኖች በሊጉ ደረጃ ከወገብ በታች ያሉ ነበሩ “ ያሉት አሰልጣኝ አርኔ ስሎት አሁንም ገና ልናረጋግጠው የሚገባን ብዙ ነገር አለ ብለዋል።

አሰልጣኝ አርኔ ስሎት አያይዘውም “ ይህንን የቡድን ስብስብ ከየርገን ክሎፕ መረከብ ትልቅ ክብር ነው “ ሲሉ ተናግረዋል።

“ ጥሩ የውድድር አመት ጅማሬ ነው ነገርግን ፍፁም አይደለም፣ አጨዋወታችን ለአመታት በሊቨርፑል የነበረ ነው ጥሩውን ውጤት ማስቀጠል አለብን።“ አርኔ ስሎት

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
አትሌቲኮ ማድሪድ የአቀንቃኟን ዝግጅት ሰረዘ !

አትሌቲኮ ማድሪድ እሁድ በሚደረገው ተጠባቂው የማድሪድ ደርቢ ጨዋታ እንድታቀነቅን ጋብዟት የነበረችውን አቀንቃኝ ዝግጅት መሰረዙ ተገልጿል።

ሜክሲኳዊቷ አቀንቃኝ ዳና ፓኦላ በእሁዱ የማድሪድ ደርቢ ጨዋታ በእረፍት ሰዓት ዝግጅቷን እንደምታቀርብ ተገልጾ ነበር።

አትሌቲኮ ማድሪድ የአቀንቃኟን ዝግጅት የሰረዘው ከጨዋታው አስቀድሞ የሪያል ማድሪድ ደጋፊ መሆኗን ስታናገር በመደመጧ መሆኑ ተነግሯል።

አቀንቃኟ ጨዋታውን ሪያል ማድሪድ 2ለ1 ያሸንፋል ስትልም ግምቷን አስቀምጣለች።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
“ ፕርሚየር ሊግ መሄድ አልፈልግም “ ቦንፌስ

ናይጄሪያዊው የባየር ሌቨርኩሰን የፊት መስመር አጥቂ ቪክቶር ቦኒፌስ የእንግሊዝ ፕርሚየር ሊግ ምርጫው እንዳልሆነ ተናግሯል።

በባየር ሌቨርኩሰን ቤት ጥሩ ጊዜ በማሳለፍ ላይ የሚገኘው ቪክቶር ቦኒፌስ አንድ ቀን ወደ ፕርሚየር ሊግ ማምራት ይፈልግ እንደሆን ሲጠየቅ “ በፍጹም “ ሲል መልሷል።

ከልጅነቱ ፕርሚየር ሊግ መጫወት ህልሙ እንዳልነበረ የሚገልጸው ተጨዋቹ “ ፕርሚየር ሊግን አልወድም የስፔን እና ጀርመንን እግርኳስ እመርጣለሁ “ ብሏል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
ቼልሲ ተጨዋቹ ወደ ሜዳ ይመለሳል !

ቤልጂየማዊው የቼልሲ የመሐል ሜዳ ተጨዋች ሮሚዮ ላቪያ ካጋጠመው ጉዳት በማገገም ወደ ሜዳ እንደሚመለስ አሰልጣኝ ኢንዞ ማሬስካ ገልጸዋል።

ሮሚዮ ላቪያ በቡድናቸው ስብስብ እንደሚካተት የገለፁት አሰልጣኝ ኢንዞ ማሬስካ መሰለፉን በቀሪ ልምምድ አይተነው እንወስናለን ብለዋል።

እንግሊዛዊው የመስመር ተጨዋች ሬስ ጄምስ በበኩሉ አሁንም ከስብስቡ ውጪ መሆኑን አሰልጣኙ አረጋግጠዋል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
“ ራያ ዝግጁ መሆኑን ለማወቅ ተጨማሪ ጊዜ ያስፈልገናል “ ሚኬል አርቴታ

የመድፈኞቹ ዋና አሰልጣኝ ሚኬል አርቴታ ቤን ዋይት እና ጁሪየን ቲምበር ልምምድ መስራታቸውን እና ለጨዋታ ዝግጁ መሆናቸውን ገልጸዋል።

አሰልጣኙ አያይዘውም አዲስ ፈራሚያቸው ሚኬል ሜሪኖ በሚቀጥለው ሳምንት ወደ ሜዳ ሊመለስ እንደሚችል ጠቁመዋል።

ግብ ጠባቂው ዴቪድ ራያ በበኩሉ “ በጥሩ ጤንነት ላይ መሆን አለመሆኑን ለማወቅ ተጨማሪ 24 ሰዓት መጠበቅ አለብን “ ሲሉ ሚኬል አርቴታ ተናግረዋል።

በነገው የሌስተር ሲቲ ጨዋታ ዴቪድ ራያ መድረስ አለመድረሱን ነገ አይተው እንደሚወስኑ ሚኬል አርቴታ ገልጸዋል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
TIKVAH-SPORT
ሮድሪ ከባድ ጉዳት አጋጥሞታል ! ስፔናዊው አማካይ ሮድሪ በሳምንቱ መጨረሻ ከአርሰናል በነበረው ጨዋታ ያጋጠመው ጉዳት የ “ ACL “ ጉዳት መሆኑን ማንችስተር ሲቲ በይፋ አረጋግጧል። ተጨዋቹ በቀኝ ጉልበቱ ላይ ጉዳቱ እንዳጋጠመው የገለፀው ክለቡ ለተሻለ የህክምና ምርመራ ስፔን እንደሚገኝም አስታውቋል። ሮድሪ በቀጣይ ለምን ያህል ጊዜ ከሜዳ እንደሚርቅ ለማወቅ የህክምና ምርመራዎች መቀጠላቸውን ክለቡ…
ሮድሪ ከውድድር አመቱ ውጪ ሆነ !

ስፔናዊው የማንችስተር ሲቲ አማካይ ሮድሪ በቅርቡ ባጋጠመው ከባድ ጉዳት ምክንያት ከውድድር አመቱ ውጪ መሆኑን አሰልጣኝ ፔፕ ጋርዲዮላ አረጋግጠዋል።

ተጨዋቹ ባለፈው ሳምንት ማንችስተር ሲቲ ከአርሰናል ባደረገው ጨዋታ “ ACL “ ጉዳት እንዳጋጠመው ይታወቃል።

የሮድሪ ጉዳት “ በጣም አስከፊ እና ከባድ ነው በዚህ አመት አንመለከተውም “ሲሉ አሰልጣኝ ፔፕ ጋርዲዮላ በይፋ አሳውቀዋል።

አሰልጣኝ ፔፕ ጋርዲዮላ አያይዘውም ኬቨን ዴብሮይን ከነገው የኒውካስል ዩናይትድ ጨዋታ ውጪ መሆኑን ገልጸዋል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
“ ለማሸነፍ ልክ ነው ያልኩትን አድርጌያለሁ “ አርቴታ

የመድፈኞቹ ዋና አሰልጣኝ ሚኬል አርቴታ ቡድናቸው ነገ ከሌስተር ሲቲ ጋር ከሚያደርገው ጨዋታ በፊት አስተያየታቸውን ሰጥተዋል።

አሰልጣኝ ሚኬል አርቴታ ምን አሉ ?

- “ በማንችስተር ሲቲ ጨዋታ ለመፎካከር እና ጨዋታውን ለማሸነፍ ልክ ነው ብዬ ያሰብኩትን አድርጌያለሁ።

- ስለ ቡድኑ ብዙ ጥሩ አስተያየቶችን ስምቻለሁ በመጨረሻው ጨዋታ ባደረግነው ነገር ትችቶች ካሉ ከዚህ ቡድን ስለሚጠበቀው ነገር ይነግረናል።

- ቶሚያሱ ዛሬ በነበረን ልምምድ በከፊል ተሳትፏል በጥሩ ሁኔታ እየተሻሻለ ይገኛል።

- በነበረን አጨዋወት ምክንያት ዩቲዩብ ላይ መተቸት አልፈልግም ግንቦት ላይ የሆነ ነገር ስለማሸንፍ እዛ መሆን እፈልጋለሁ።“ ሲሉ ተደምጠዋል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
TIKVAH-SPORT
ሮድሪ ከውድድር አመቱ ውጪ ሆነ ! ስፔናዊው የማንችስተር ሲቲ አማካይ ሮድሪ በቅርቡ ባጋጠመው ከባድ ጉዳት ምክንያት ከውድድር አመቱ ውጪ መሆኑን አሰልጣኝ ፔፕ ጋርዲዮላ አረጋግጠዋል። ተጨዋቹ ባለፈው ሳምንት ማንችስተር ሲቲ ከአርሰናል ባደረገው ጨዋታ “ ACL “ ጉዳት እንዳጋጠመው ይታወቃል። የሮድሪ ጉዳት “ በጣም አስከፊ እና ከባድ ነው በዚህ አመት አንመለከተውም “ሲሉ አሰልጣኝ ፔፕ ጋርዲዮላ…
“ ወደ ፍልሚያ ለመሄድ መዘጋጀት አለብን “ ጋርዲዮላ

የማንችስተር ሲቲው ዋና አሰልጣኝ ፔፕ ጋርዲዮላ በቀጣይ በቡድናቸው ሮድሪን መተካት የሚችል አማራጭ እንዳላቸው ገልፀዋል።

ፔፕ ጋርዲዮላ ከተናገሯቸው ሌሎች አስተያየቶች መካከል :-

- " ኒውካስል ከጠንካራ እና አስቸጋሪ ቡድኖች አንዱ ነው በተለይ በሜዳው ወደ ትልቅ ፍልሚያ ለመሄድ መዘጋጀት አለብን።

- የምናሸንፍ ከሆነ ያለ ሮድሪ መፎካከር እንችላለን ማለት ነው የማናሸንፍ ከሆነ ግን ሮድሪ ስላጎደለን ነው።

- በሮድሪ ቦታ ሪኮ ሌዊስ እና ማቲኦ ኮቫቺች እንጠቀማለን ኢልካይ ጉንዶጋንም መጫወት ይችላል ጆን ስቶንስ እና አካንጂም መጫወት ይችላሉ አማራጭ አለን።

- ለሮድሪ ተተኪ በጥር ማስፈረም የሚያስፈልገን ከሆነ እንነጋገርበታለን ገና ለዛ ብዙ ጊዜ አለን።" ሲሉ ተደምጠዋል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
መልካም ዕድል!
ከፍ የተደረጉ ኦዶችን አይተዋል ? እንግዲያውስ ተወራረዱባቸው!
ለተሻለ ውርርድ ቤቲካን ይጠቀሙ! አሁኑኑ Betika.et ላይ /በቴሌግራም ቦታችን - @BetikaETBot ይወራረዱ!
Forwarded from WANAW SPORT
📞 8289 📞

ወደ ዋናው የጥሪ ማዕከል በቀላሉ ይደውሉ፣ #ትዕዛዝዎን ያድርሱን!

📞 8289 📞

Instagram | Facebook | TikTok

🏅ዋናው ወደፊት...

@wanawsportwear
“ የሮናልዶ መፈረም መልበሻ ቤቱ ላይ ተፅዕኖ ያሳደረ ይመስለኛል “ ሶልሻየር

የቀድሞው የቀያይ ሴጣኖቹ አሰልጣኝ ኦሌ ገነር ሶልሻየር ከአመታት በፊት ሮናልዶን ማስፈረማቸው መልበሻ ቤቱ ላይ ተፅዕኖ አሳድሯል የሚል እምነት እንዳላቸው ገልጸዋል።

“ ምናልባት ሌሎች ተጨዋቾች ሮናልዶ ሲመጣ ያን ያህል እንደማያስፈልጉ ተሰምቷቸው ነበር " ያሉት ሶልሻየር “ ምክንያቱም እሱ ከአለም ምርጥ ኮከቦች አንዱ ነበር “ ብለዋል

“ ሮናልዶ ጥሩ ስራ ሰርቶ ነበር በዛ አመቱ ሀያ አራት ጎል አስቆጥሮ የቡድኑ ከፍተኛ ጎል አስቆጣሪ ሆኗል ነገርግን ከአስር ሳምንት በኋላ እኔ ስራዬን አጣሁ “ ሲሉ ሶልሻየር ተናግረዋል።

ክርስቲያኖ ሮናልዶ ምናልባት በማንችስተር ሲቲ ሀላንድ እያደረገ ከሚገኘው የበለጠ ማድረግ ይችል ነበር የሚል እምነት እንዳላቸው አሰልጣኝ ሶልሻየር ጨምረው ገልጸዋል።

አሰልጣኙ አክለውም “ የክርስቲያኖ ሮናልዶ መፈረም ሙሉ መልበሻ ቤቱ ላይ ተፅዕኖ ያደረገ ይመስለኛል “ ብለዋል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
ፈረሰኞቹ የመጀመሪያ ድላቸውን አሳክተዋል !

በኢትዮጵያ ፕርሚየር ሊግ ሁለተኛ ሳምንት መርሐ ግብር ቅዱስ ጊዮርጊስ ከወልዋሎ አዲግራት ዩኒቨርስቲ ጋር ያደረጉትን ጨዋታ 2ለ1 በሆነ ውጤት ማሸነፍ ችለዋል።

የፈረሰኞቹን የማሸነፊያ ግቦች ፍፁም ጥላሁን እና አማኑኤል ኤርቦ ከመረብ ሲያሳርፉ ለወልዋሎ አዲግራት ዩኒቨርስቲ ኪሩቤል ወንድሙ አስቆጥሯል።

ቀጣይ መርሐግብር ምን ይመስላል ?

ሰኞ ቅዱስ ጊዮርጊስ ከ መቐለ 70 እንደርታ

ሐሙስ ⏩️ ወልዋሎ አዲግራት ዩኒቨርስቲ ከ ሲዳማ ቡና

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
አል ነስር ድል አድርጓል !

በሰዑዲ ዓረቢያ ሊግ የአምስተኛ ሳምንት መርሐ ግብር አል ነስር ከአል ዌህዳ ጋር ያደረገውን ጨዋታ 2ለ0 በሆነ ውጤት ማሸነፍ ችሏል።

የአል ነስርን የማሸነፊያ ግቦች አንሄሎ ጋብሬል እና ክርስቲያኖ ሮናልዶ ከመረብ ማሳረፍ ችለዋል።

ክርስቲያኖ ሮናልዶ በሰባ ግቦች ለአል ናስር ብዙ ግብ ያስቆጠረ በታሪክ አራተኛው የውጪ ሀገር ተጨዋች መሆን ችሏል።

ፖርቹጋላዊው ተጨዋች ክርስቲያኖ ሮናልዶ በእግርኳስ ህይወቱ 903 ኛ ግቡን ማስቆጠር ችሏል።

የሊግ ደረጃቸው ምን ይመስላል ?

2️⃣ኛ. አል ነስር :- 11 ነጥብ
1️⃣4️⃣ኛ. አል ዌህዳ :- 4 ነጥብ

ቀጣይ ጨዋታቸው ምን ይመስላል ?

ቅዳሜ አል ነስር ከ አል ኦሮባህ

ሐሙስ አል ዌህዳ አል ፋይሀ

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
አዳማ ከተማ ድል አድርጓል !

በኢትዮጵያ ፕርሚየር ሊግ ሁለተኛ ሳምንት መርሐ ግብር አዳማ ከተማ ከባሕር ዳር ከተማ ጋር ያደረጉትን ጨዋታ 1ለ0 በሆነ ውጤት ማሸነፍ ችለዋል።

የአዳማ ከተማን የማሸነፊያ ግቦች ስንታየሁ መንግሥቱ ከመረብ ማሳረፍ ችሏል።

ባሕር ዳር ከተማ የመጀመሪያ ሽንፈቱን ሲያስተናግድ አዳማ ከተማ የመጀመሪያ ድሉን አሳክቷል።

ቀጣይ መርሐግብር ምን ይመስላል ?

ማክሰኞ ወልቂጤ ከተማ ከ አዳማ ከተማ

ማክሰኞ ⏩️  ባሕር ዳር ከተማ ከ ሀድያ ሆሳዕና

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
#SaudiLeague 🇸🇦

በሰዑዲ ዓረቢያ ሊግ የአምስተኛ ሳምንት መርሐ ግብር አል ኢትሐድ አል ካሊጅን 4ለ1 ሲያሸንፍ አል አህሊ በአል ቃዲሲያ 1ለ0 በሆነ ውጤት ተሸንፏል።

የአል ኢትሀድን የማሸነፊያ ግቦች ካሪም ቤንዜማ ፣ ጋምዲ ፣ ስቴቨን ቤርግዊን እና ሁሴም ኡራ ከመረብ ማሳረፍ ችለዋል።

የአል ቃዲሲያን ብቸኛ የማሸነፊያ ግብ ፔር ኤምሪክ ኦባምያንግ ማስቆጠር ችሏል።

ፈረንሳዊው የፊት መስመር አጥቂ ካሪም ቤንዜማ በውድድር ዘመኑ ስድስተኛ የሊግ ግቡን ማስቆጠር ችሏል።

በሊጉ ደረጃ ሰንጠረዥ ስንተኛ ናቸው ?

1️⃣ኛ አል ኢትሀድ :- 12 ነጥብ
4️⃣ኛ አል ቃዲሲያ :- 10 ነጥብ
7️⃣ኛ አል አህሊ :- 7 ነጥብ

ቀጣይ ጨዋታቸው ምን ይመስላል ?

ሐሙስ ⏩️ አል አክዱድ ከ አል ኢትሀድ

ቅዳሜ ⏩️ አል አህሊ ከ አል ሂላል

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
ኤሲ ሚላን ድል አድርጓል !

በጣልያን ሴርያ የስድስተኛ ሳምንት መርሐ ግብር ኤሲ ሚላን ከሊቼ ጋር ያደረጉትን ጨዋታ 3ለ0 በሆነ ውጤት ማሸነፍ ችለዋል።

የኤሲ ሚላንን የማሸነፊያ ግቦች አልቫሮ ሞራታ ፣ ቲኦ ሄርናንዴዝ እና ክርስቲያን ፑልሲች ከመረብ ማሳረፍ ችለዋል።

የሊግ ደረጃቸው ?

2️⃣ኛ ኤሲ ሚላን :- 11 ነጥብ
1️⃣7️⃣ኛ ሊቼ :- 5 ነጥብ

ቀጣይ ጨዋታቸው ምን ይመስላል ?

እሁድ ፊዮሬንቲና ከ ኤሲ ሚላን

ቅዳሜ ዩዲኔዜ ከ ሊቼ

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
2024/09/27 00:13:58
Back to Top
HTML Embed Code: