Telegram Web Link
TIKVAH-SPORT
“ በይፋ ራሴን ከኦሎምፒክ ኮሚቴ አግልያለሁ “ ሻለቃ ኃይሌ ገብረ ሥላሴ “ የተከበሩ ዶክተር አሸብር የትም ሂዱ ብለውናል የትም እንሄዳለን “ የኢትዮጵያ ኦሎምፒክ ኮሚቴ አባል የነበረው ሻለቃ ኃይሌ ገብረ ሥላሴ በወረቀት ላይ ብቻ ከተካተትኩበት የኦሎምፒክ የኮሚቴ አባልነት በይፋ መልቀቄን ህዝብ ይወቅልኝ ሲል ተናግሯል። አሁን ያለው የኢትዮጵያ ኦሎምፒክ ኮሚቴ አባል የስራ ዘመኑ ሊጠናቀቅ ስምንት ወይም…
ኦሎምፒክ ኮሚቴ ለኃይሌ ጥሪ አቀረበ !

የኢትዮጵያ ኦሎምፒክ ኮሚቴ በዛሬው ዕለት በፅ/ቤት ኃላፊው በአቶ ዳዊት አስፋው ተፈርሞ በወጣ ደብዳቤ ሻለቃ አትሌት ኃይሌ ገብረ ሥላሴን ለውይይት መጥራቱ  ተገልጿል።

የኢትዮጵያ ኦሎምፒክ ኮሚቴ በደብዳቤው ሻለቃ አትሌት ኃይሌ ገብረ ሥላሴን ከሰሞኑ በተፈጠሩ አለመግባባቶች ዙሪያ " እንወያይ " ሲል መጠየቁን ለመመልከት ተችሏል።

ሻለቃ ኃይሌ ገብረ ሥላሴ ትላንት ለሸገር ኤፍ ኤም በሰጠው አስተያየት በቅርቡ በዝግ በተደረገው የኦሎምፒክ ኮሚቴ ምርጫ ዙሪያ የጀመረውን ሂደት አጠናክሮ እንደሚቀጥል መግለፁ አይዘነጋም።

የኢትዮጵያ ኦሎምፒክ ኮሚቴ ዛሬ ለኃይሌ በላከው ደብዳቤ " ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ከኦሎምፒክ ኮሚቴ ጋር መግባባት #እንደሌልዎትና በአሰራሩም ቅሬታ እንዳልዎት ለእኛ በቀጥታ በፅሁፍ ፣ ወይንም በተለመደ አሰራር ያቀረቡት ነገር ባይኖርም ከሚዲያ እየሰማን እንገኛለን።

ይህንን ተከትሎ ጀግናውን አትሌታችንን ማዳመጥ #አለብን ብለን ስላመንን ዓርብ ሐምሌ 12/11/16 ዓ.ም ከቀኑ 9:00 በኦሎምፒክ ፅ/ቤት ተገኝተው እንድንወያይ በአክብሮት ጥሪያችንን እናስተላልፋለን " ብሏል።

ሻለቃ ኃይሌ ገብረ ሥላሴ ትላንት ከሸገር ኤፍ ኤም ጋር በነበረው ቆይታ " የተከበሩ ዶክተር አሸብር የትም ሂዱ ብለውናል የትም እንሄዳለን ፣ በኋላ ግን ለምን ሄዳችሁ እንዳይሉ እፈራለሁ" ማለቱ ይታወሳል።

ፎቶ :- ሀትሪክ ስፖርት

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
መልካም ዕድል!
ከፍ የተደረጉ ኦዶችን አይተዋል ? እንግዲያውስ ተወራረዱባቸው!
Maribor - Botev Plovdiv
ለተሻለ ውርርድ ቤቲካን ይጠቀሙ! አሁኑኑ Betika.et ላይ /በቴሌግራም ቦታችን - @BetikaETBot ይወራረዱ!
Forwarded from HEY Online Market
•PlayStation 5, 73,000 Birr
•Playstaion 5 Slim, 78,000 Birr

•PlayStation 4 Slim, 35,000 Birr
•PlayStation 4 Pro, 43,000 Birr

•Playstaion portal, 35,000 Birr
•Meta Quest 2, 55,000 Birr
•Meta Quest 3, 83,000 Birr

Contact
0953964175 @heymobile

@heyonlinemarket
ግሪንውድ በማርሴይ ደማቅ አቀባበል ተደርጎለታል !

የ 22ዓመቱ የፊት መስመር ተጫዋች ሜሰን ግሪንውድ ወደ ፈረንሳዩ ክለብ ማርሴይ የሚያደርገው ዝውውር ለማጠናቀቅ ምሽቱን ከቤተሰቡ ጋር ማርሴይ ከተማ ደርሷል።

ብዙ የፈረንሳዩ ክለብ ማርሴይ ደጋፊዎች በአየር ማረፊያ በመገኘት ለሜሰን ግሪንውድ ደማቅ አቀባበል አድርገዋል ደጋፊዎቹ በተደጋጋሚ ስሙን ስጠሩም ተስተውሏል።

ሜሰን ግሪንውድ ወደ ማርሴይ በሚያደርገው ዝውውር ዙሪያ ውዝግቦች መኖራቸው ሲገለፅ ከቀናት በፊት የማርሴይ ከንቲባ ቤኖይት ፓያን በዝውውር አለመደሰታቸውን ገልፀው ነበር።

ሜሰን ግሪንውድ የ2023/24 የውድድር ዘመን በስፔኑ ክለብ ሄታፌ ያሳለፈ ሲሆን በቆይታውም ስምንት የላሊጋ ጎሎችን ማስቆጠር ችሏል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
ቪንሰስ ጁኒየር ገቢ ማሰባሰቢያ አዘጋጅቷል !

የሪያል ማድሪዱ የፊት መስመር ተጫዋች ቪንሰስ ጁኒየር በብራዚል ለተቸገሩ ህፃናት የሚሆን የእርዳታ ገቢ ማሰባሰቢያ የጨረታ ዝግጅት ማካሄዱ ተገልጿል።

በብራዚል በተካሄደው ዝግጅት ላይ የቡድን አጋሮቹ ፌርላንድ ሜንዲ ፣ ኤደር ሚሊታኦ እና ኤድዋርዶ ካማቪንጋ መገኘታቸው ታውቋል።

በዝግጅቱ ላይ ኪሊያን ምባፔ የተፈረመበት ማልያውን እንዲሁም ጁድ ቤሊንግሀም በአውሮፓ ሻምፒየንስ ሊግ ግማሽ ፍፃሜ የተጫወተባቸውን ጫማዎች ለጨረታ መለገሳቸው ተገልጿል።

በተጨማሪም ሉካ ሞድሪች የተፈረመበት ማልያ መስጠቱ ሲገለፅ ሌላኛው የቡድን አጋሩ ኤደር ሚሊታኦ በበኩሉ ለገቢ ማሰባሰቢያው 35,000 ዩሮ መለገሱ ተገልጿል።

ቪንሰስ ጁኒየር በሀገሩ የሚገኙ ህፃናት ትምህርታቸውን እንዳያቋርጡ እገዛ የሚያደርግ ሲሆን ባለፈው አመት የበጎ አድራጎት ስራን የሚያበረታታውን የባሎን ዶር የሶክራተስ አዋርድ ማሸነፉ ይታወሳል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
አርጀንቲና ደረጃዋን አስጠብቃለች !

የፊፋ የአለም ብሔራዊ ቡድኖች ወርሀዊ ደረጃ ይፋ ሲደረግ የኮፓ አሜሪካ አሸናፊው የአርጀንቲና ብሔራዊ ቡድን የአንደኝነትን ደረጃውን አስጠብቋል።

የአውሮፓ ዋንጫን ያሸነፈው የስፔን ብሔራዊ ቡድን አምስት ደረጃዎችን በማሻሻል ሶስተኛ ደረጃ ላይ መቀመጥ ችሏል።

በአውሮፓ ዋንጫው ጥሩ ጉዞ ማድረግ የቻለው የቱርክ ብሔራዊ ቡድን አስራ ስድስት ደረጃዎች በማሻሻል ሀያ ስድስተኛ ደረጃ ላይ ተቀምጠዋል።

በኮፓ አሜሪካ ካደረጋቸው አራት ጨዋታዎች ሶስቱን አሸንፎ ከሩብ ፍፃሜ በመለያ ምት የተሰናበተው የቬንዙዌላ ብሔራዊ ቡድን በበኩሉ አስራ ሰባት ደረጃዎች በማሻሻል ሰላሳ ሰባተኛ ደረጃን ይዟል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
የኢብራሂሞቪች ልጅ ለኤሲ ሚላን ፈርሟል !

የስዊድናዊው የቀድሞ ተጨዋች ዝላታን ኢብራሂሞቪች ልጅ ማክሲሚሊያን ኢብራሂሞቪች በኤሲ ሚላን ቤት የመጀመሪያ ፕሮፌሽናል ኮንትራቱን መፈረሙ ተገልጿል።

የ 18ዓመቱ ተጨዋች ማክሲሚሊያን ኢብራሂሞቪች በጣልያን ሴርያ ሲ ለሚወዳደረው የኤሲ ሚላን ሁለተኛ ቡድን በመጫወት እንደሚጀመር ተነግሯል።

ባለፈው አመት በይፋ ጫማውን የሰቀለው ዝላታን ኢብራሂሞቪች በአሁኑ ሰዓት በኤሲ ሚላን ቤት በአዲስ ሚና እያገለገለ ይገኛል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
TIKVAH-SPORT
ማድሪድ የተጫዋቹን ውል ሊያራዝም ነው ! በአሰልጣኝ ካርሎ አንቾሎቲ የሚሰለጥኑት ሪያል ማድሪዶች የስፔናዊውን የመስመር ተጨዋች ሉካስ ቫስኩዌስ ኮንትራት ሊያራዝሙ መሆኑ ተገልጿል። የ 32ዓመቱ ተጨዋች ሉካስ ቫስኩዌስ በሎስ ብላንኮዎቹ ቤት ለአንድ የውድድር አመት ለመቆየት መስማማቱ ተገልጿል። ሉካስ ቫስኩዌስ በዚህ አመት ለሪያል ማድሪድ በሰላሳ ስምንት ጨዋታዎች ተሰልፎ መጫወት የቻለ ሲሆን የላሊጋ…
ማድሪድ የተጫዋቹን ውል አራዘመ !

በአሰልጣኝ ካርሎ አንቾሎቲ የሚሰለጥኑት ሪያል ማድሪዶች የስፔናዊውን የመስመር ተጨዋች ሉካስ ቫስኩዌስ ኮንትራት ማራዘማቸውን ይፋ አድርገዋል።

የ 32ዓመቱ የመስመር ተጨዋች ሉካስ ቫስኩዌስ በሎስ ብላንኮዎቹ ቤት ለአንድ የውድድር አመት ለመቆየት ፊርማውን ማኖሩ ተገልጿል።

ሉካስ ቫስኩዌስ በሪያል ማድሪድ ቤት አስራ ሰባት አመታትን ሲያሳልፍ አራት የላሊጋ እና አምስት የሻምፒየንስ ሊግ ዋንጫዎችን ጨምሮ ሀያ አንድ ዋንጫዎች አሳክቷል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
ዱሳን ታዲች ከብሔራዊ ቡድኑ ራሱን አገለለ !

በቱርኩ ክለብ ፌነርባቼ የሚጫወተው የፊት መስመር ተጨዋቹ ዱሳን ታዲች ራሱን ከሰርቢያ ብሔራዊ ቡድን ማግልለሉን ይፋ አድርጓል።

የ 35ዓመቱ ዱሳን ታዲች በሰርቢያ ብሔራዊ ቡድን ውስጥ ብዙ ጨዋታዎች ማድረግ የቻለ ባለታሪክ ተጨዋች ነው።

በሰርቢያ እግርኳስ በቀዳሚነት የሚጠቀሰው ዱሳን ታዲች ለብሔራዊ ቡድኑ ሀያ ሶስት ግቦችን ማስቆጠር ችሏል።

ዱሳን ታዲች ብሔራዊ ቡድኑን ለአስራ አምስት አመታት ማገልገል ችሏል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
Forwarded from WANAW SPORT
📢 #ከዋናው ትጥቆችን ለድርጅትዎ ሲያዙ...

👉🏾 #ያናግሩን#ይምጡ#ይዘዙን!

📌 ለበለጠ መረጃና ትዕዛዝ 📲 0911955221 እና 0995114226 ላይ ይደውሉ።

👉🏾 እንዲሁም በቴሌግራም @Wanawsales ላይ የሽያጭ ሰራተኞቻችንን በቀጥታ በማናገር ወይም በቴሌግራም ቦት @WanawSportBot ይዘዙን።

🏅 ዋናው ወደፊት...

@wanawsportwear
" አርሰናል እያለሁ ጫማ ልሰቅል አስቤ ነበር " ፔፔ

የቱርኩን ክለብ ትራብዞንስፖር የተቀላቀለው የቀድሞ የአርሰናል አይቮሪ ኮስታዊ የፊት መስመር ተጨዋች ኒኮላስ ፔፔ በመድፈኞቹ ቤት ስለነበረው ቆይታ ዙሪያ አስተያየቱን ሰጥቷል።

ኒኮላስ ፔፔ ስለ አርሰናል ቆይታው ምን አለ ?

- " አርሰናልን ብዙም ሳልቆይ መልቀቅ እችል ነበር ነገርግን ለእኔ ካወጡት የበለጠ ገንዘብ ጠይቀው ስለነበር አልተሳካም።

- አርሰናል እያለሁ ከጋዜጦች ፣ ማህበራዊ ሚዲያ እና ከክለቡ አንዳንድ ሰዎች በደረሰብኝ ትችት ጫማ ልሰቅል አስቤ ነበር ሁልጊዜ ከጎኔ የሚቆሙት የአርሰናል ደጋፊዎች ብቻ ነበሩ።

- አርሰናል የእኔን ኮንትራት ለማቋረጥ ከስምምነት የደረሱት ወደ ሳውዲ አረቢያ ሊግ አልሄድም በሚል ቅድመ ሁኔታ ነበር።

- አሁን በትራብዞንስፖር እቀጥላለሁ ወደ ሳውዲ ወይም ሌላ ቦታ ማምራት አልፈልግም አልልም ፣ ነገርግን አውሮፓ ውስጥ ያልጨረስኩት ነገር አለ አሁንም ማድረግ የምችለው ነገር መኖሩን ማሳየት እፈልጋለሁ።

- አርሰናል ውስጥ የእግርኳስ ፍቅሬን ትንሽ አጥቻለሁ ፣ በዚህ ልክ ለምን እንደተተቸሁ አስባለሁ እኔን በፕርሚየር ሊጉ ታሪክ ያልተሳካለት ሰው ለማድረግ ፈልገው ነበር።"ሲል ተደምጧል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
ቼልሲ አሁንም የፖተርን ደሞዝ እየከፈሉ ነው !

የምዕራብ ለንደኑ ክለብ ቼልሲ የቀድሞ አሰልጣኛቸው ግራም ፖተርን ደሞዝ አሁንም በመክፈል ላይ መሆናቸው ተገልጿል።

ሰማያዊዎቹ ለአሰልጣኙ በሳምንት 200,000 ፓውንድ በመክፈል ላይ መሆናቸው ሲገለፅ ክፍያው እስከ ቀጣዩ ጥቅምት ወር እንደሚቀጥል ተነግሯል።

እንግሊዛዊው አሰልጣኝ ግራም ፖተር ከቼልሲ አሰልጣኝነታቸው ከተሰናበቱ ከአንድ አመት በላይ እንደሆናቸው አይዘነጋም።

ከእንግሊዝ ብሔራዊ ቡድን ጋር ስማቸው እየተያያዘ የሚገኙት አሰልጣኝ ግራም ፖተር ቡድኑን የሚረከቡ ከሆነ ቼልሲ አንድ ሚልዮን ፓውንድ እንደሚያተርፉ ተገልጿል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
የወደፊቱ የሲቲ ተጨዋች አዲስ ታሪክ ፅፏል !

ማንችስተር ሲቲዎች ከወዲሁ ያስፈረሙት የወደፊት ተስፈኛ ታዳጊ ካቫን ሱሊቫን ትላንት በአሜሪካ ሜጀር ሊግ ሶከር ውድድር ለፊላደልፊያ ዩኒየን ተሰልፎ ተጫውቷል።

ታዳጊው በ 14ዓመቱ በአሜሪካ ሜጀር ሊግ ውድድር ላይ ተሰልፎ መጫወት የቻለ በታሪክ በእድሜ ትንሹ ተጨዋች በመሆን አዲስ ታሪክ መፃፍ ችሏል።

ማንችስተር ሲቲዎቹ ባለ ትልቅ ተሰጥኦ ባለቤቱን ታዳጊ ካቫን ሱሊቫን በቅርቡ አንድ ሚልዮን ዶላር አውጥተው ለቡድናቸው አስፈርመውታል።

አሜሪካዊው ታዳጊ ካቫን ሱሊቫን በሚቀጥለው አመት በ2025 ማንችስተር ሲቲን እንደሚቀላቀል ይጠበቃል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
TIKVAH-SPORT
ኦባምያንግ ከማርሴይ ጋር መለያየቱን አሳወቀ ! ጋቦናዊው የፊት መስመር ተጨዋች ኦባምያንግ ከፈረንሳዩ ክለብ ኦሎምፒክ ማርሴይ ጋር መለያየቱን በማህበራዊ ትስስር ገፁ ይፋ አድርጓል። ተጨዋቹ ባሰፈረው መልዕክትም ጠንካራ እንድሆን አድርጋችሁኛል የቡድን አጋሮቼን እና መላውን ክለቡን አመሰግናለሁ በማለት ተናግሯል። ኦባምያንግ በቀጣይ የሳውዲ አረቢያውን ክለብ አል ቃዲሲያ በሁለት አመት ኮንትራት እንደሚቀላቀል…
ኦባምያንግ በይፋ አል ቃዲሲያን ተቀላቀለ !

ጋቦናዊው የፊት መስመር ተጨዋች ፔር ኤምሪክ ኦባምያንግ የሳውዲ አረቢያውን ክለብ አል ቃዲሲያ መቀላቀሉ ይፋ ተደርጓል።

ኦባምያንግ ከቀናት በፊት ከፈረንሳዩ ክለብ ኦሎምፒክ ማርሴይ ጋር መለያየቱን በማህበራዊ ትስስር ገፁ ይፋ ማድረጉ ይታወሳል።

ኦባምያንግ የሳውዲ አረቢያውን ክለብ አል ቃዲሲያ በሁለት አመት ኮንትራት መቀላቀሉ ተገልጿል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
ጁቬንቱስ ከተጨዋቹ ጋር ተለያይቷል !

የጣልያን ሴርያው ክለብ ጁቬንቱስ ከፈረንሳዊው የመሐል ሜዳ ተጨዋቻቸው አድሪያን ራቢዮ ጋር መለያየታቸውን ይፋ አድርገዋል።

የ 29ዓመቱ የመሐል ሜዳ ተጨዋች አድሪያን ራቢዮ በጁቬንቱስ ቤት የቀረበለትን በአመት 7 ሚልዮን ዩሮ ክፍያ አለመቀበሉ ተገልጿል።

ተጫዋቹ አሁን ላይ በነፃ ዝውውር አዲስ ክለብ ለመቀላቀል በንግግር ላይ መሆኑ ተነግሯል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
ፓትሪክ ቬይራ ከስትራስቦርግ ጋር ተለያይቷል !

የፈረንሳዩ ክለብ ስትራስቦርግ የ 48ዓመቱ ዋና አሰልጣኝ ፓትሪክ ቬይራ ከአንድ የውድድር አመት ቆይታ በኃላ በጋራ ስምምነት ከሀላፊነት መልቀቁን ይፋ አድርጓል።

ስትራስቦርግ በሊጉ አመርቂ ያልሆነ የውድድር አመት ያሳለፈ ሲሆን በ2023/24 የውድድር ዘመን አስራ ሶስተኛ ደረጃን ይዞ ነበር ያጠናቀቀው።

ፈረንሳዊው አሰልጣኝ ፓትሪክ ቬይራ የእንግሊዙን ክለብ ክሪስታል ፓላስ ከ2021 እስከ 2023 ለሁለት የውድድር አመታት ማሰልጠኑ አይዘነጋም።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
TIKVAH-SPORT
ፈረንሳይ የአርጀንቲና ተጨዋቾችን ከሰሰች ! የፈረንሳይ እግርኳስ ፌዴሬሽን የአርጀንቲና ብሔራዊ ቡድን ተጨዋቾች ላይ ለአለም የእግርኳስ የበላይ ፊፋ ቅሬታ ማቅረቡን በይፋ አስታውቋል። ፌዴሬሽኑ ቅሬታውን ለፊፋ ያቀርበው የኮፓ አሜሪካ አሸናፊው አርጀንቲና ብሔራዊ ተጨዋቾች ከድል በኋላ ባሰሙት ዝማሬ ምክንያት መሆኑ ተነግሯል። የአርጀንቲና ብሔራዊ ቡድን ተጨዋቾች ኮፓ አሜሪካ ካሸነፉ በኋላ በጉዞ ላይ…
አርጀንቲና ምክትል የስፖርት ሀላፊዋን አሰናበተች !

የአርጀንቲናው ፕሬዝዳንት ሀቤር ሚሌይ የሀገሪቱን ምክትል የስፖርት ሚንስቴር ጁሊዮ ጋሬሮን ከሀላፊነት ማሰናበታቸው ተገልጿል።

ፕሬዝዳንቱ ሀላፊውን ያሰናበቱት የአርጀንቲና ብሔራዊ ቡድን ተጫዋቾች ያሰሙትን ዝማሬ ተከትሎ ለቀረበው ተቃውሞ የቡድኑ አምበል ሊዮኔል ሜሲ ወጥቶ በይፋ ይቅርታ ይጠይቅ በማለታቸው መሆኑ ተገልጿል።

የሀገሪቱ ፕሬዝዳንት በማህበራዊ ትስስር ገፃቸው ባሰፈሩት ፅሁፍም " የትኛውም የመንግስት አካል የአለም ዋንጫ እና ሁለት የኮፓ አሜሪካ አሸናፊውን ብሔራዊ ቡድን ማዘዝ አይችልም " ሲሉ ገልጸዋል።

የአርጀንቲና ምክትል ፕሬዝዳንት የሆኑት ቪክቶሪያ ቫላሩኤል በበኩላቸው በሰጡት አስተያየት " የትኛውም ቅኝ ገዢ ሀይል ለእግርኳስ በተዘመረ ዝማሬ አያስፈራራንም።"ብለዋል።

ምክትል ፕሬዝዳንቷ አክለውም " ሊቀበሉት የማይፈልጉት እውነት ነው የተነገረው ፣ የተናደዳችሁ ማስመሰሉን አቁሙ እኔ ከቡድኑ ጎን እቆማለሁ።" በማለት ድጋፋቸውን አሳይተዋል።

የአርጀንቲና ብሔራዊ ቡድን ተጨዋቾች በቅርቡ የፈረንሳይ ብሔራዊ ቡድን ተጨዋቾችን የተመለከተ ዝማሬ በጋራ ማሰማታቸውን ተከትሎ ቅሬታ እየቀረበባቸው ይገኛል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
ዶርትመንድ ሴርሁ ጉራሲን በይፋ አስፈረመ !

የቡንደስሊጋው ክለብ ቦርስያ ዶርትመንድ የስቱትጋርቱን የፊት መስመር አጥቂ ሴርሁ ጉራሲ ማስፈረማቸውን ይፋ አድርገዋል።

ከምዕራብ አፍሪካዊቷ ሀገር ጊኒ የተገኘው የፊት መስመር አጥቂ ሴርሁ ጉራሲ በተጠናቀቀው የውድድር ዘመን ጥሩ የሚባል ጊዜን በስቱትጋርት ማሳለፉ አይዘነጋም።

ዶርትመንድ ተጫዋቹን የውል ማፍረሻውን 17.5 ሚልዮን ዩሮ በመክፈል በአራት አመት ኮንትራት ማስፈረማቸው ተገልጿል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
2024/10/01 19:28:48
Back to Top
HTML Embed Code: