Telegram Web Link
ኮል ፓልመር የደሞዝ ጭማሬ ሊያገኝ ነው !

ቼልሲዎች ለቡድኑ ጥሩ ግልጋሎት በመስጠት ላይ ለሚገኘው እንግሊዛዊ ተጨዋች ኮል ፓልመር የደሞዝ ጭማሬ ሊያደርጉለት መሆኑ ተገልጿል።

ሰማያዊዎቹ ባለፈው አመት ከማንችስተር ሲቲ ባስፈረሙት ኮል ፓልመር ደስተኛ መሆናቸው እና በቀጣይ አስር አመታት በክለቡ ሊያቆዩት እንደሚፈልጉ ተነግሯል።

ኮል ፓልመር አሁን ላይ በቼልሲ በሳምንት 80,000 ፓውንድ እንደሚያገኝ ሲገለፅ ጭማሬውን በውስጥ ለመጨረስ ማሰባቸው ተጠቁሟል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
TIKVAH-SPORT
ሌኒ ዮሮ ወደ እንግሊዝ እያመራ መሆኑ ተገለፀ ! ፈረንሳዊው የተከላካይ ስፍራ ተጨዋች ሌኒ ዮሮ ወደ ማንችስተር ዩናይትድ የሚያደርገውን ዝውውር ለማጠናቀቅ ወደ እንግሊዝ በማምራት ላይ መሆኑ ተገልጿል። ተጨዋቹ በቀጣይ ማንችስተር ዩናይትድን ለመቀላቀል የህክምና ምርመራውን እንደሚያደርግ እና የግል ስምምነቶችን እንደሚያጠናቅቅ ተነግሯል። ማንችስተር ዩናይትድ ተጫዋቹን በ50 ሚልዮን ዩሮ እና ተጨማሪ…
ሌኒ ዮሮ ለዩናይትድ መፈረሙ ተገለጸ !

ፈረንሳዊው የተከላካይ ስፍራ ተጨዋች ሌኒ ዮሮ የማንችስተር ዩናይትድ ተጨዋች የሚያደርገውን ፊርማ መፈረሙ ተገልጿል።

ተጨዋቹ በዛሬው ዕለት ቀርቶት የነበረውን ሁለተኛ የህክምና ምርመራ በማጠናቀቅ የአምስት አመት ኮንትራት መፈረሙ ተነግሯል።

በማንችስተር ዩናይትድ እና ሊል መካከል የወረቀት ስራዎች መጠናቀቃቸውም እንዲሁ ሲገለፅ በቀጣይ ዝውውሩ ይፋ መደረግ እንደሚቀረው ተጠቁሟል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
TIKVAH-SPORT
“ ለተፈጠረው ነገር ከልብ ይቅርታ እጠይቃለሁ “ ኢንዞ ፈርናንዴዝ አርጀንቲናዊው የቼልሲ የመሐል ሜዳ ተጨዋች ኢንዞ ፈርናንዴዝ በማህበራዊ ትስስር ገፁ ስለ ተሰራጨው ቪድዮ ከልብ ይቅርታ መጠየቅ እንደሚፈልግ ተናግሯል። " በኢንስታግራም ገፄ ለተሰራጨው የደስታ አገላለፅ ዝማሬ ቪዲዮ ከልብ ይቅርታ እጠይቃለሁ " ሲል የገለፀው ኢንዞ ፈርናንዴዝ ዝማሬው አፀያፊ ቃላትን ይዟል ለነዚህ ቃላት ምንም ሰበብ የለም…
የቼልሲ ተጨዋቾች ብስጭት ውስጥ መሆናቸው ተገለጸ !

የምዕራብ ለንደኑ ክለብ ቼልሲ በርካታ ተጨዋቾች በአርጀንቲናዊው ተጨዋች ኢንዞ ፈርናንዴዝ ባህሪ ከፍተኛ ብስጭት ውስጥ ገብተው እንደሚገኙ ተገልጿል።

ተጨዋቾቹ ኢንዞ ፈርናንዴዝ ለምን ይህን ያደርጋል የሚል ጥያቄ በመጠየቅ ላይ መሆናቸውን ለክለቡ መልበሻ ቤት ቅርበት ያላቸው የመረጃ ምንጮች ገልጸዋል።

የክለቡ መልበሻ ቤት በዚሁ ምክንያት መከፋፈሉ የተነገረ ሲሆን ነገሩ በቡድኑ ውስጥ የከፋ ሊሆን እንደሚችል ተዘግቧል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
ሊቨርፑል የቲኬት ሽያጩን ማቆሙን ገለጸ !

የመርሲሳይዱ ክለብ ሊቨርፑል ትላንት ለአባላቱ ጀምሮት የነበረውን የቀጣይ የሊጉ የሜዳ ጨዋታዎች የመግቢያ ትኬት ሽያጭ ላልተወሰነ ጊዜ ማቋረጡን አስታውቋል።

የስታዲየም መግቢያ ትኬት ሽያጩ የተቋረጠው የሳይበር ጥቃት ተፈፅሞ የቴክኒክ ችግር ስላጋጠማቸው መሆኑን ሊቨርፑሎች አስረድተዋል።

ክለቡ ጥቃቱ የተፈፀመው ትኬቶችን አጭበርብሮ ለመግዛት ይሁን ወይም ለሌላ አላማ የሚለውን ለማወቅ ምርመራ መጀመሩን አስውቋል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
TIKVAH-SPORT
ማንችስተር ሲቲ ተጨዋች ለማስፈረም ተስማማ ! ማንችስተር ሲቲ ብራዚላዊውን የጂሮና ወጣት የፊት መስመር ተጨዋች ሳቭዮ በሚቀጥለው ክረምት ወደ ስብሰባቸው ለመቀላቀል ከስምምነት መድረሳቸው ተገልጿል። የ 19ዓመቱ ብራዚላዊ የፊት መስመር አጥቂ ሳቭዮ በሚቀጥሉት ቀናት ለማንችስተር ሲቲ እንደሚፈርም እና በውድድር አመቱ መጨረሻ ቡድኑን እንደሚቀላል ተነግሯል። ተጨዋቹ በዘንድሮው የውድድር ዘመን ለጂሮና ባደረጋቸው…
ማንችስተር ሲቲ ተጨዋች አስፈረመ !

ማንችስተር ሲቲ ብራዚላዊውን ወጣት የፊት መስመር ተጨዋች ሳቭዮ ማስፈረማቸውን ይፋ አድርገዋል።

በአሰልጣኝ ፔፕ ጋርዲዮላ የሚመራው ማንችስተር ሲቲዎች የ 19ዓመቱን የፊት መስመር አጥቂ ሳቭዮ በ21 ሚልዮን ዩሮ የዝውውር ሒሳብ ማስፈረማቸው ተገልጿል።

ባለፈው የውድድር አመት በጂሮና ጥሩ የሚባል ጊዜን ማሳለፍ የቻለው ሳቪዮ ለማንችስተር ሲቲ የአምስት አመት ኮንትራት መፈረሙ ተነግሯል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
" ልጄ የዘረኝነት ባህሪ የለበትም " የኢንዞ ፈርናንዴዝ ወላጅ አባት

የአርጀንቲናዊው የመሐል ሜዳ ተጨዋች ኢንዞ ፈርናንዴዝ ወላጅ አባት " ልጄ የዘረኝነት ባህሪ የለበትም " ሲሉ ልጃቸው እየቀረበበት ስለሚገኘው ተቃውሞ አስተያየታቸውን ሰጥተዋል።

" እኔ ልጄን በደንብ አውቀዋለሁ በፍፁም የዘረኝነት ባህሪ የለበትም " ሲሉ ያስረዱት የተጫዋቹ ወላጅ አባት የእኛን የእግርኳስ ባህል እና የደስታ አገላለፅ ለአውሮፓውያን ለመረዳት አስቸጋሪ ነው ብለዋል።

" 2014 ጀርመን በአለም ዋንጫው አሸንፋን ከባህላችን ጋር በተያያዘ ሲሰድቡን ነበር ፣ በ2022 ፈረንሳዮች ሜሲን በቁመቱ ምክንያት ሲቀልዱበት ነበር እኛ ግን በፍጹም ዘረኝነት ብለን አልወጣንም።" ሲሉ የኢንዞ ፈርናንዴዝ ወላጅ አባት ተናግረዋል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
TIKVAH-SPORT
ግሪንውድ ማርሴይን ለመቀላቀል ተስማማ ! እንግሊዛዊው የፊት መስመር ተጨዋች ሜሰን ግሪንውድ የፈረንሳዩን ክለብ ማርሴይ ለመቀላቀል በቃል ደረጃ ከስምምነት መድረሱ ይፋ ተደርጓል። ማርሴይ ከሳምንት በፊት ተጫዋቹን በ31 ሚልዮን ዩሮ ለማስፈረም ከማንችስተር ዩናይትድ ጋር ከስምምነት መድረሳቸው ይታወሳል። የ 22ዓመቱ የፊት መስመር ተጨዋች ሜሰን ግሪንውድ በቀጣይ የህክምና ምርመራውን ለማድረግ እንደሚጓዝ…
ሜሰን ግሪንውድ በይፋ ማርሴይን ተቀላቀለ !

የፈረንሳዩ ክለብ ማርሴይ እንግሊዛዊውን የፊት መስመር ተጨዋች ሜሰን ግሪንውድ ከማንችስተር ዩናይትድ ማስፈረማቸውን ይፋ አድርገዋል።

ማርሴይ የ 22ዓመቱን የፊት መስመር ተጨዋች ሜሰን ግሪንውድ በ30 ሚልዮን ዩሮ መስፈረማቸው ተገልጿል።

ማንችስተር ዩናይትድ ከወደፊት የሜሰን ግሪንውድ ሽያጭ ሀምሳ በመቶውን የሚያስገኝላቸው መብት በውሉ ውስጥ መካተቱ ተገልጿል።

ግሪንውድ በማርሴይ የአምስት አመት ኮንትራት መፈረሙ ሲገለፅ በክለቡ የአስር ቁጥር ማልያ እንደሚለብስ ታውቋል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
ማንችስተር ዩናይትድ በይፋ ተጨዋች አስፈረመ !

በዝውውር መስኮቱ ንቁ ተሳትፎ በማድረግ ላይ የሚገኙት ማንችስተር ዩናይትዶች ፈረንሳዊውን ተከላካይ ሌኒ ዮሮ ከሊል ማስፈረማቸውን በይፋ አስታውቀዋል።

ቀያዮቹ ሴጣኖች ለዝውውሩ 50 ሚልዮን ዩሮ ቀጥታ ክፍያ እና ታይቶ የሚጨምር 12 ሚልዮን ዩሮ የዝውውር ሒሳብ ወጪ እንደሚያደርጉ ተገልጿል።

ማንችስተር ዩናይትዶች " የተከላካዩ ኪሊያን ምባፔ " የሚል ቅፅል ስም ያገኘውን የ 18ዓመት ተከላካይ ሊኒ ዮሮ በአምስት አመት ኮንትራት አስፈርመውታል።

ተጨዋቹ ፊርማውን ካኖረ በኋላ " አቅሜን አውጥቼ ለማሳየት እና ህልሜን ለማሳካት ትክክለኛው ቦታ እንደሚሆን ይሰማኛል " ሲል ተደምጧል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
ዩናይትድ ተጨማሪ ተከላካይ ያስፈርማል ?

የሌኒ ዮሮን ዝውውር ያጠናቀቀው ማንችስተር ዩናይትድ አሁንም ማትያስ ዴሊት እና ብራንዝዌትን የማስፈረም ፍላጎት እንዳለው ተገልጿል።

ማንችስተር ዩናይትድ በቀጣይ ተጨማሪ የመሐል ተከላካይ የማስፈረም እቅዱ በተጫዋች ሽያጭ ላይ የተመረኮዘ ሊሆን እንደሚችል ተነግሯል።

የቱርኩ ክለብ ፌነርባቼ የማንችስተር ዩናይትዱን ተከላካይ ቪክቶር ሊንድሎፍ የማስፈረም ፍላጎት እንዳለው ተጠቁሟል።

በሌላ በኩል ቀያዮቹ ሴጣኖች ሌኒ ዮሮን ሲያስፈርሙ የቀድሞ ተጨዋቻቸው ሪዮ ፈርዲናንድ ተጫዋቹ ክለቡን እንዲቀላቀል ማሳመኑ ተነግሯል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
TIKVAH-SPORT
ማኑኤል ኡጋርት ወደ ማንችስተር ዩናይትድ ? ማንችስተር ዩናይትድ ዩራጓዊውን የመሐል ሜዳ ተጨዋች ማኑኤል ኡጋርት ለማስፈረም ከፈረንሳዩ ክለብ ፒኤስጂ ጋር ንግግር ማድረጋቸው ተገልጿል። የ 23ዓመቱ የመሐል ሜዳ ተጨዋች ማኑኤል ኡጋርት ማንችስተር ዩናይትድ በአውሮፓ ሻምፒየንስ ሊግ ባይሳተፍም እንኳን የመቀላቀል ፍላጎት እንዳለው ተነግሯል። ባለፈው አመት ፒኤስጂን ከስፖርቲንግ ሊስበን በአምስት አመት…
ዩናይትድ ተጨዋች ለማስፈረም ተስማማ !

ማንችስተር ዩናይትድ ዩራጓዊውን የመሐል ሜዳ ተጨዋች ማኑኤል ኡጋርትን ለማስፈረም በግል ከተጨዋቹ ጋር ከስምምነት መድረሳቸው ተገልጿል።

የ 23ዓመቱ የመሐል ሜዳ ተጨዋች ማኑኤል ኡጋርት ማንችስተር ዩናይትድ በአውሮፓ ሻምፒየንስ ሊግ ባይሳተፍም እንኳን ክለቡን ለመቀላቀል መፈለጉ ተነግሯል።

ማንችስተር ዩናይትዶች በተጨዋቹ ዝውውር ሒሳብ ዙሪያ ከፒኤስጂ ጋር የሚያደርጉትን ንግግር አሁንም መቀጠላቸው ተገልጿል።

ቀያዮቹ ሴጣኖች ማኑኤል ኡጋርትን ለማስፈረም አንድ የመሐል ሜዳ ተጨዋቻቸውን መሸጥ ሊጠበቅባቸው እንደሚችል ተጠቁሟል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
Forwarded from WANAW SPORT
Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
🏆🇪🇹 #2016_የኢትዮጵያ_ሴቶች_ፕሪሚየር_ሊግ የመዝጊያ ስነስርዓት! 🇪🇹🏆

ዋናው ስፖርት የዚህ ደማቅ ውድድር አጋር ስለነበር በድጋሚ ኩራት ይሰማዋል።

Instagram | Facebook | TikTok

🏅 ዋናው ወደፊት...

@wanawsportwear
Forwarded from HEY Online Market
•PlayStation 5, 73,000 Birr
•Playstaion 5 Slim, 78,000 Birr

•PlayStation 4 Slim, 35,000 Birr
•PlayStation 4 Pro, 43,000 Birr

•Playstaion portal, 35,000 Birr
•Meta Quest 2, 55,000 Birr
•Meta Quest 3, 83,000 Birr

Contact
0953964175 @heymobile

@heyonlinemarket
ዌስትሀም ካንቴን ለማስፈረም ንግግር ላይ ነው !

የእንግሊዙ ክለብ ዌስትሀም ዩናይትድ የአል ኢትሀዱን የመሀል ሜዳ ተጫዋች ንጎሎ ካንቴን ለማስፈረም በንግግር ላይ መሆናቸው ተገልጿል።

ዌስትሀም ዩናይትድ ለ 33ዓመቱ የመሀል ሜዳ ተጫዋች ንጎሎ ካንቴ 20 ሚሊየን ፓወንድ የዝውውር ሒሳብ እንዳቀረቡም ታውቋል።

ፈረንሳዊው አማካኝ በ2023 ከቼልሲ በመልቀቅ ወደ ሳውዲ አረቢያ ከተቀላቀለ በኃላ ወደ እንግሊዝ ፕርሚየር ሊግ የመመለሱ ነገር የተቃረበ መሆኑ እየተዘገበ ነው።

የለንደኑ ክለብ ዌስትሀም ዩናይትድ ፈረንሳዊውን የመሀል ሜዳ ተጫዋች ንጎሎ ካንቴ የካልቪን ፊሊፕስ ተተኪ ለማድረግ እንዳሰቡ ተዘግቧል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
አንቾሎቲ ምባፔን በቡድናቸው እንዴት ይጠቀማሉ ?

ፈረንሳዊውን የፊት መስመር ተጨዋች ኪሊያን ምባፔ በነፃ ዝውውር ያስፈረሙት ሎስ ብላንኮዎቹ በቀጣይ በቡድናቸው ካሉ ኮከቦች ጋር ይጣመራል።

ኪሊያን ምባፔ በቡድኑ ከቤሊንግሀም ፣ ቪንሰስ እና ሮድሪጎ ጋር እንዴት ይጣመራል የሚለው የብዙዎች ጥያቄ ቢሆንም አሰልጣኝ ካርሎ አንቾሎቲ የራሳቸው እቅድ እንዳላቸው ተገልጿል።

ጣልያናዊው አሰልጣኝ ካርሎ አንቾሎቲ በሚቀጥለው አመት አጥቅተው ለመጫወት በሚመርጡበት ወቅት ምባፔን በዘጠኝ ቁጥር ቦታ በማሰለፍ 4-3-3 የጨዋታ አሰላለፍ እንደሚጠቀሙ ተነግሯል።

በተጨማሪም ተከላክለው ለመጫወት ሲመርጡ ሮድሪጎን ወደ ኋላ በመመለስ የ4-4-2 የጨዋታ አሰላለፍ ለመጠቀም ማሰባቸው ተገልጿል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
TIKVAH-SPORT
Photo
" ጥያቄዬ ካልተመለሰ ለውይይት አልቀመጥም ጥሪውን አልተቀበልኩም " ኃይሌ

" ቢመጣ ጥሩ ነው ይመጣል ብዬ ተስፋ አደርጋለሁ " ዶ/ር አሸብር

ሻለቃ አትሌት ኃይሌ ገብረ ሥላሴ የኢትዮጵያ ኦሎምፒክ ኮሚቴ በዛሬው ዕለት ለውይይት ያቀረበለትን ጥሪ እንደማይቀበል በሰጠው አስተያየት አረጋግጧል።

ሻለቃ አትሌት ኃይሌ ገብረ ሥላሴ ከሸገር ኤፍ ኤም ጋር ባደረገው ቆይታ ኮሚቴው በዝግ ያደረገው ምርጫ ካልተሰረዘና ወደ ነበረበት ካልተመለሰ ለውይይት አልቀመጥም በማለት ተናግሯል።

" የጠየቅኩት ሁሉም በነበረበት እንዲመለስ ነው " ያለው ኃይሌ " ጥያቄዬን አሁን ቢያስተካክሉትና ሁሉም በነበረበት ቢመለስ ደስ ይለኛል ይህ ካልሆነና ምን ያመጣሉ በሚል ከቀጠሉ ነገሩ በማንፈልገው አቅጣጫ ሊሄድ ይችላል " ብሏል።

ሻለቃ ኃይሌ አያይዞም " ኦሎምፒክ ኮሚቴው ሁሉንም በነበረበት የሚመልስ ከሆነ ስለወደፊቱ ምርጫ አደራረግ እና ቀጣይ ስራዎች ለመወያየት ዝግጁ ነኝ በደስታ እቀበላለሁ " በማለት ገልጿል።

" የኢትዮጵያ ባህል እና ስፖርት ሚኒስቴር በዚህ ጉዳይ ለምን አቅም እንዳጣ አይገባኝም ?" ሲል የጠየቀው ኃይሌ " በጣም አዝናለሁ አቅም ማጣት አልነበረበትም ወይስ ኦሎምፒክ ኮሚቴ ከስፖርት ሚንስቴሩ በላይ ሆኖ ነው " ሲል ገልጿል።

የኢትዮጵያ ኦሎምፒክ ኮሚቴ ፕሬዝዳንት ዶ/ር አሸብር ወ/ጊዮርጊስ በበኩላቸው ከስፖርት ዞን ጋር በነበራቸው ቆይታ " ኃይሌ አልገኝም ብሎ ምላሽ ሰጥቶናል " ብለው በጉዳዩ ላይ ማረጋገጫ ሲሰጡ በግላቸው ውሳኔው እንዳላስደሰታቸውም ተናግረዋል።

ፕሬዝዳንቱ ቀጥለውም " ቢመጣ ጥሩ ነው ይመጣል ብዬ ተስፋ አደርጋለሁ ተስፋ አልቆረጥኩም ከውይይት የዘለለ ነገር የለም በመወያየት ብቻ ነው መፍታት የሚቻለው " ሲሉ አስተያየታቸውን ሰጥተዋል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
TIKVAH-SPORT
ድንቅ ጊዜ እያሳለፈ የሚገኘው የአርሰናል ታዳጊ ! የሰሜን ለንደኑ ክለብ አርሰናል ከ 18ዓመት በታች ቡድን የፊት መስመር ተጨዋች የሆነው ኦቢ ማርቲን በርካታ ግቦች እያስቆጠረ ድንቅ ጊዜ ማሳለፉን ቀጥሏል። የ 16ዓመቱ ኦቢ ማርቲን ቡድኑ ዛሬ የኖርዊች ሲቲ አቻውን 9ለ0 በሆነ ውጤት ሲያሸንፍ #ሰባት ግቦችን ማስቆጠር ችሏል። ማርቲን ቡድኑ ባለፉት ሰባት የ 18ዓመት በታች ፕርሚየር ሊግ ጨዋታዎች…
ተስፈኛው የአርሰናል ታዳጊ ወደ ዩናይትድ ?

የሰሜን ለንደኑ ክለብ አርሰናል ታዳጊ የፊት መስመር አጥቂ ቺዶ ኦቢ ማርቲን ወደ ማንችስተር ዩናይትድ ለማምራት ካሪንግተን ተገኝቶ መነጋገሩ ተገልጿል።

በሚያስቆጥራቸው በርካታ ግቦች መነጋገሪያ የነበረው ኦቢ ማርቲን ከአርሰናል የቀረበለትን ውል እስካሁን አለመቀበሉ ተነግሯል።

ታዳጊው በመድፈኞቹ እንዲቆይ በቅርቡ አሰልጣኝ ሚኬል አርቴታ አግኝተው አነጋግረውት እንደነበር ተዘግቧል።

የ 16ዓመቱ ታዳጊ ኦቢ ማርቲን በአርሰናል ታዳጊ ቡድን ውስጥ በአንድ ጨዋታ ሰባት ግብ እንዲሁም በሰባት ጨዋታዎች ሀያ አራት ግቦች በማስቆጠር አድናቆት ሲቸረው ነበር።

ተጨዋቹ የናይጄሪያ ፣ እንግሊዝ እና ዴንማርክ ዜግነት እንዳለው ተገልጿል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
ማድሪድ ለተጨዋቹ አቀባበል ያደርጋል !

ሪያል ማድሪዶች ለአዲሱ ብራዚላዊ የፊት መስመር አጥቂያቸው ኢንድሪክ ይፋዊ አቀባበል እንደሚያደርጉ ይፋ አድርገዋል።

ሎስ ብላንኮዎቹ በሚቀጥለው ሳምንት ቅዳሜ በሳንትያጎ በርናቦ ስታዲየም ይፋዊ አቀባበል እንደሚያደርጉ አሳውቀዋል።

በዕለቱ የክለቡ ፕሬዝዳንት ፍሎሬንቲኖ ፔሬዝ ለሌሎች ተጨዋቾች እንደሚያደርጉት በክለቡ ማዕከል ተገኝተው ኢንድሪክን የስድስት አመት ውል እንደሚያስፈርሙ ተገልጿል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
የፓሪስ ኦሎምፒክ 7 ቀን ብቻ ቀረው!

ብርቅዬ አትሌቶቻችንን በፓሪሱ ኦሎምፒክስ ለመቀላቀል ጊዜው አሁን ነው! ዛሬውኑ ደንበኝነትዎን ያራዝሙ የአትሌቶቻችንን ብቃት እና ወኔ በጎጆ ፓኬጅ በ350 ብር ይከታተሉ! 

እናሸንፈለን ድሉን እናያለን!

የፓሪስ ኦሎምፒክስን በ350 ብር በጎጆ ፓኬጅ ይከታተሉ! ከታች ያለውን ሊንክ በመጫን ዛሬውኑ ደንበኝነትዎን ያራዝሙ!
👇
https://mydstv.onelink.me/vGln/dg1

#ParisOlympics #2024Olympics #ሁሉምያለውእኛጋርነው #DStvEthiopia
መልካም ዕድል!
ከፍ የተደረጉ ኦዶችን አይተዋል ? እንግዲያውስ ተወራረዱባቸው!
Aarhus - Midtjylland
Sirius - Malmo
ለተሻለ ውርርድ ቤቲካን ይጠቀሙ! አሁኑኑ Betika.et ላይ /በቴሌግራም ቦታችን - @BetikaETBot ይወራረዱ!
TIKVAH-SPORT
አልቫሮ ሞራታ ኤሲ ሚላንን ለመቀላቀል ተስማማ ! የስፔን ብሔራዊ ቡድን አምበል አልቫሮ ሞራታ አትሌቲኮ ማድሪድን በመልቀቅ የሴርያውን ክለብ ኤሲ ሚላን ለመቀላቀል ከስምምነት መድረሱ ተገልጿል። ተጨዋቹ በኤሲ ሚላን ቤት የአራት አመታት ኮንትራት ለመፈረም በቃል ደረጃ ከስምምነት መድረሱ ተነግሯል። ኤሲ ሚላን አልቫሮ ሞራታን የውል ማፍረሻውን 13 ሚልዮን ዩሮ ከፍለው እንደሚያስፈርሙት ተዘግቧል። …
አልቫሮ ሞራታ ወደ አዲስ ክለብ አምርቷል !

የጣሊያኑ ክለብ ኤሲ ሚላን የአትሌቲኮ ማድሪዱን የፊት መስመር ተጨዋች አልቫሮ ሞራታን ማስፈረሙን ይፋ አድርጓል።

ኤሲ ሚላን የተጨዋቹን የውል ማፍረሻ 13 ሚሊየን ዩሮ በመክፈል በአራት አመታት ኮንትራት አስፈርመውታል።

ስፔናዊው አጥቂ አልቫሮ ሞራታ ወደ ኤሲ ሚላን ያደረገው ዝውውር በእግርኳስ ህይወቱ ስምንተኛው ዝውውር መሆኑ ተዘግቧል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
2024/10/01 22:29:07
Back to Top
HTML Embed Code: