Telegram Web Link
ፒኤስጂ ኦሲሜንን ለማስፈረም ንግግር ላይ ነው !

የፈረንሳዩ ክለብ ፒኤስጂ የናፖሊውን የፊት መስመር ተጨዋች ቪክቶር ኦሲሜን ለማስፈረም ከተጨዋቹ ወኪሎች ጋር በንግግር ላይ መሆናቸው ተገልጿል።

ናይጄሪያዊው የፊት መስመር ተጨዋች ቪክቶር ኦሲሜን በቀጣይ ፒኤስጂ ከናፖሊ ጋር ከስምምነት ከደረሰ ለመቀላቀል ፍላጎት እንዳለው ተዘግቧል።

ከክለቡ ወሳኝ ተጨዋች ኪሊያን ምባፔ ጋር የተለያየው ፒኤስጂ በቀጣይ ታላላቅ ዝውውሮችን ሊፈፅም እንደሚችል እየተገለጸ ይገኛል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
TIKVAH-SPORT
ፈረንሳይ የአርጀንቲና ተጨዋቾችን ከሰሰች ! የፈረንሳይ እግርኳስ ፌዴሬሽን የአርጀንቲና ብሔራዊ ቡድን ተጨዋቾች ላይ ለአለም የእግርኳስ የበላይ ፊፋ ቅሬታ ማቅረቡን በይፋ አስታውቋል። ፌዴሬሽኑ ቅሬታውን ለፊፋ ያቀርበው የኮፓ አሜሪካ አሸናፊው አርጀንቲና ብሔራዊ ተጨዋቾች ከድል በኋላ ባሰሙት ዝማሬ ምክንያት መሆኑ ተነግሯል። የአርጀንቲና ብሔራዊ ቡድን ተጨዋቾች ኮፓ አሜሪካ ካሸነፉ በኋላ በጉዞ ላይ…
ፊፋ ምርመራ መጀመሩን ይፋ አደረገ !

የአለም እግርኳስ የበላይ ጠባቂ ፊፋ የአርጀንቲና ብሔራዊ ቡድን ተጨዋቾች ያሰሙትን ዝማሬ ቪዲዮ ቅጂ በመመርመር ላይ እንደሚገኝ ይፋ አድርጓል።

" ፊፋ በማህበራዊ ሚዲያ የተሰራጨውን ቪዲዮ ተመልክቷል ጉዳዩ እየተመረመረ ይገኛል ፊፋ በተጨዋቾች ፣ ደጋፊዎች እና ሀላፊዎች የሚቀርብን የተኛውንም መድሎ አጥብቆ ይቃወማል " ሲል ፊፋ በመግለጫው ገልጿል።

ቼልሲ በበኩሉ ባወጣው መግለጫ " የቀረበው ነገር ፍፁም ተቀባይነት የሌለው ነው ፣ ቼልሲ ሁሉንም ማህበረሰቦች እና ማንነቶች በመያዙ እና አካታች ክለብ በመሆኑ ይኮራል።

ተጨዋቾች ለህዝብ የሚያቀርቡትን ይቅርታ እናደንቃለን ለማስተማርም እንጠቀምበታለን ክለቡ በኢንዞ ፈርናንዴዝ ላይ የውስጥ የዲሲፕሊን እርምጃ ወስዷል። " ሲል ገልጿል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
TIKVAH-SPORT
ሊል የዩናይትድን ጥያቄ መቀበላቸው ተገለጸ ! የፈረንሳዩ ክለብ ሊል ማንችስተር ዩናይትድ ለተከላካይ ስፍራ ተጨዋቻቸው ሌኒ ዮሮ በይፋ ያቀረበውን 50 ሚልዮን ዩሮ የዝውውር ሒሳብ መቀበላቸው ተገልጿል። ሊል ተጨዋቹ ማንችስተር ዩናይትድ ያቀረበለትን ጥያቄ እንዲቀበል መጠየቃቸው የተገለፀ ሲሆን ተጨዋቹ አሁንም ቅድሚያ የሚሰጠው ለሪያል ማድሪድ መሆኑ ተዘግቧል። ሎስ ብላንኮዎ አዲስ ሒሳብ እስካሁን አለማቅረባቸው…
ሌኒ ዮሮ ወደ እንግሊዝ እያመራ መሆኑ ተገለፀ !

ፈረንሳዊው የተከላካይ ስፍራ ተጨዋች ሌኒ ዮሮ ወደ ማንችስተር ዩናይትድ የሚያደርገውን ዝውውር ለማጠናቀቅ ወደ እንግሊዝ በማምራት ላይ መሆኑ ተገልጿል።

ተጨዋቹ በቀጣይ ማንችስተር ዩናይትድን ለመቀላቀል የህክምና ምርመራውን እንደሚያደርግ እና የግል ስምምነቶችን እንደሚያጠናቅቅ ተነግሯል።

ማንችስተር ዩናይትድ ተጫዋቹን በ50 ሚልዮን ዩሮ እና ተጨማሪ ታይቶ የሚከፈል 12 ሚልዮን ዩሮ የዝውውር ሒሳብ ለማስፈረም ከሊል ጋር ከስምምነት መድረሳቸው አይዘነጋም።

ተጨዋቹ የመጀመሪያ ምርጫው ሪያል ማድሪድን መቀላቀል ቢሆንም ሎስ ብላንኮዎቹ ማንችስተር ዩናይትድ ያቀረበውን ሒሳብ ለማቅረብ ፍላጎት አለማሳየታቸው ተገልጿል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
ሌኒ ዮሮ ዩናይትድን ለመቀላቀል መወሰኑ ለማድሪድ ተነግሮታል !

ሪያል ማድሪድ ፈረንሳዊው የተከላካይ ስፍራ ተጨዋች ሌኒ ዮሮ ማንችስተር ዩናይትድን ለመቀላቀል ከውሳኔ መድረሱን እንደተነገረው ተገልጿል።

ሎስ ብላንኮዎቹ የተጫዋቹን ውሳኔ እንደሚያከብሩ ሲገለፅ በቀጣይ አማራጭ ተከላካይ ለመመልከት ስሞችን መያዛቸው ተነግሯል።

ማንችስተር ዩናይትድ በበኩሉ የተጨዋቹ ዝውውር በሌሎች ክለቦች እንዳይጠለፍ ዝውውሩን በፍጥነት ለማጠናቀቅ እየሰሩ መሆኑ ተገልጿል።

ሪያል ማድሪዶች ራፋ ማሪንን የሸጡት ሌኒ ዮሮ ቡድኑን ይቀላቀላሉ የሚል ትልቅ እምነት ስለነበራቸው እንደነበር ተዘግቧል።

ይህንንም ተከትሎ በቀጣይ አዲስ የመሐል ተከላካይ ለማስፈረም ወደ ዝውውር ገበያው ለመውጣት እንደሚገደዱ ተገልጿል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
Forwarded from WANAW SPORT
🔔 ጥራትን የተላበሱ ማልያዎች በተመጣጣኝ ዋጋ!

👉🏾 ዛሬውኑ #ያናግሩን፣ ይዘዙን!

📌 ለበለጠ መረጃና ትዕዛዝ 📲 09011382830910851535 እና 0913586742 ላይ ይደውሉ።

👉🏾 እንዲሁም በቴሌግራም @Wanawsales ላይ የሽያጭ ሰራተኞቻችንን በቀጥታ በማናገር ወይም በቴሌግራም ቦት @WanawSportBot ይዘዙን።

🏅 ዋናው ወደፊት...

@wanawsportwear
TIKVAH-SPORT
ኦባምያንግ ወደ ሳውዲ አረቢያ ሊያመራ ይችላል ! ጋቦናዊው የኦሎምፒክ ማርሴይ የፊት መስመር ተጨዋች ኦባምያንግ በቀጣይ ወደ ሳውዲ አረቢያ ሊግ ሊያመራ እንደሚችል እየተዘገበ ይገኛል። ተጫዋቹን ለማስፈረም በቅርቡ ናቾን ከሪያል ማድሪድ በይፋ ያስፈረመው የሳውዲ ሊጉ ክለብ አል ቃዲሲያ ከፍተኛ ጥረት እያደረጉ እንደሚገኙ ተገልጿል። ማርሴይ ኦባምያንግን ማቆየት እንደሚፈልጉ ቢገለፅም የወደፊት ቆይታው…
ኦባምያንግ ከማርሴይ ጋር መለያየቱን አሳወቀ !

ጋቦናዊው የፊት መስመር ተጨዋች ኦባምያንግ ከፈረንሳዩ ክለብ ኦሎምፒክ ማርሴይ ጋር መለያየቱን በማህበራዊ ትስስር ገፁ ይፋ አድርጓል።

ተጨዋቹ ባሰፈረው መልዕክትም ጠንካራ እንድሆን አድርጋችሁኛል የቡድን አጋሮቼን እና መላውን ክለቡን አመሰግናለሁ በማለት ተናግሯል።

ኦባምያንግ በቀጣይ የሳውዲ አረቢያውን ክለብ አል ቃዲሲያ በሁለት አመት ኮንትራት እንደሚቀላቀል ተገልጿል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
TIKVAH-SPORT
ማድሪድ የተጫዋቹን ውል ለማራዘም ተቃርቧል ! የአውሮፓ ሻምፒየንስ ሊግ አሸናፊው ሪያል ማድሪድ የክሮሽያዊውን የመሐል ሜዳ ተጨዋች ሉካ ሞድሪች ኮንትራት ለማራዘም መስማማታቸው ተገልጿል። የ 38ዓመቱ የመሐል ሜዳ ተጨዋች ሉካ ሞድሪች በሎስ ብላንኮዎቹ ቤት ለአንድ የውድድር አመት ለመቆየት መስማማቱ ተገልጿል። ሉካ ሞድሪች ከምሽቱ የሻምፒየንስ ሊግ ድል በኋላ አስተያየቱን ሲሰጥ በሪያል ማድሪድ ቤት…
ማድሪድ የተጫዋቹን ውል አራዘመ !

ሪያል ማድሪድ የክሮሽያዊውን የመሐል ሜዳ ተጨዋች ሉካ ሞድሪች ኮንትራት ለተጨማሪ የውድድር አመት ማራዘማቸውን ይፋ አድርገዋል።

የ 38ዓመቱ የመሐል ሜዳ ተጨዋች ሉካ ሞድሪች በሎስ ብላንኮዎቹ ቤት ለአንድ የውድድር አመት ለመቆየት ፊርማውን ማኖሩ ይፋ ሆኗል።

የክለቡ አምበል ናቾ ፈርናንዴዝ ሎስ ብላንኮዎቹን መልቀቁን ተከትሎ ሉካ ሞድሪች አዲሱ የሪያል ማድሪድ አምበል መሆኑ ተገልጿል።

ሞድሪች በሪያል ማድሪድ ቤት ባሳለፋቸው አስራ ሁለት የውድድር አመታት ስድስት የሻምፒየንስ ሊግ እና አራት የላሊጋ ዋንጫዎችን ጨምሮ ሀያ ስድስት ዋንጫዎችን አሳክቷል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
ጆኒ ሄቲንጋ የሊቨርፑልን አሰልጣኞች ቡድን ተቀላቀለ !

የቀድሞ ኔዘርላንዳዊ የተከላካይ ስፍራ ተጨዋች ጆኒ ሄቲንጋ የመርሲሳይዱ ክለብ ሊቨርፑልን አሰልጣኞች ቡድን መቀላቀሉ ይፋ ሆኗል።

በኤቨርተን ቤት በተጨዋችነት ያሳለፈው ጆኒ ሄቲንጋ የአዲሱ የሊቨርፑል አሰልጣኝ አርኔ ስሎት ምክትል አሰልጣኝነት ሚናን ማግኘቱ ተገልጿል።

የቀድሞ ተጨዋቹ ጆኒ ሄቲንጋ በኤቨርተን ቤት አንድ መቶ አርባ ጨዋታዎች ላይ ተሰልፎ መጫወት ችሏል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
TIKVAH-SPORT
“ በይፋ ራሴን ከኦሎምፒክ ኮሚቴ አግልያለሁ “ ሻለቃ ኃይሌ ገብረ ሥላሴ “ የተከበሩ ዶክተር አሸብር የትም ሂዱ ብለውናል የትም እንሄዳለን “ የኢትዮጵያ ኦሎምፒክ ኮሚቴ አባል የነበረው ሻለቃ ኃይሌ ገብረ ሥላሴ በወረቀት ላይ ብቻ ከተካተትኩበት የኦሎምፒክ የኮሚቴ አባልነት በይፋ መልቀቄን ህዝብ ይወቅልኝ ሲል ተናግሯል። አሁን ያለው የኢትዮጵያ ኦሎምፒክ ኮሚቴ አባል የስራ ዘመኑ ሊጠናቀቅ ስምንት ወይም…
ኦሎምፒክ ኮሚቴ ለኃይሌ ጥሪ አቀረበ !

የኢትዮጵያ ኦሎምፒክ ኮሚቴ በዛሬው ዕለት በፅ/ቤት ኃላፊው በአቶ ዳዊት አስፋው ተፈርሞ በወጣ ደብዳቤ ሻለቃ አትሌት ኃይሌ ገብረ ሥላሴን ለውይይት መጥራቱ  ተገልጿል።

የኢትዮጵያ ኦሎምፒክ ኮሚቴ በደብዳቤው ሻለቃ አትሌት ኃይሌ ገብረ ሥላሴን ከሰሞኑ በተፈጠሩ አለመግባባቶች ዙሪያ " እንወያይ " ሲል መጠየቁን ለመመልከት ተችሏል።

ሻለቃ ኃይሌ ገብረ ሥላሴ ትላንት ለሸገር ኤፍ ኤም በሰጠው አስተያየት በቅርቡ በዝግ በተደረገው የኦሎምፒክ ኮሚቴ ምርጫ ዙሪያ የጀመረውን ሂደት አጠናክሮ እንደሚቀጥል መግለፁ አይዘነጋም።

የኢትዮጵያ ኦሎምፒክ ኮሚቴ ዛሬ ለኃይሌ በላከው ደብዳቤ " ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ከኦሎምፒክ ኮሚቴ ጋር መግባባት #እንደሌልዎትና በአሰራሩም ቅሬታ እንዳልዎት ለእኛ በቀጥታ በፅሁፍ ፣ ወይንም በተለመደ አሰራር ያቀረቡት ነገር ባይኖርም ከሚዲያ እየሰማን እንገኛለን።

ይህንን ተከትሎ ጀግናውን አትሌታችንን ማዳመጥ #አለብን ብለን ስላመንን ዓርብ ሐምሌ 12/11/16 ዓ.ም ከቀኑ 9:00 በኦሎምፒክ ፅ/ቤት ተገኝተው እንድንወያይ በአክብሮት ጥሪያችንን እናስተላልፋለን " ብሏል።

ሻለቃ ኃይሌ ገብረ ሥላሴ ትላንት ከሸገር ኤፍ ኤም ጋር በነበረው ቆይታ " የተከበሩ ዶክተር አሸብር የትም ሂዱ ብለውናል የትም እንሄዳለን ፣ በኋላ ግን ለምን ሄዳችሁ እንዳይሉ እፈራለሁ" ማለቱ ይታወሳል።

ፎቶ :- ሀትሪክ ስፖርት

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
መልካም ዕድል!
ከፍ የተደረጉ ኦዶችን አይተዋል ? እንግዲያውስ ተወራረዱባቸው!
Maribor - Botev Plovdiv
ለተሻለ ውርርድ ቤቲካን ይጠቀሙ! አሁኑኑ Betika.et ላይ /በቴሌግራም ቦታችን - @BetikaETBot ይወራረዱ!
Forwarded from HEY Online Market
•PlayStation 5, 73,000 Birr
•Playstaion 5 Slim, 78,000 Birr

•PlayStation 4 Slim, 35,000 Birr
•PlayStation 4 Pro, 43,000 Birr

•Playstaion portal, 35,000 Birr
•Meta Quest 2, 55,000 Birr
•Meta Quest 3, 83,000 Birr

Contact
0953964175 @heymobile

@heyonlinemarket
ግሪንውድ በማርሴይ ደማቅ አቀባበል ተደርጎለታል !

የ 22ዓመቱ የፊት መስመር ተጫዋች ሜሰን ግሪንውድ ወደ ፈረንሳዩ ክለብ ማርሴይ የሚያደርገው ዝውውር ለማጠናቀቅ ምሽቱን ከቤተሰቡ ጋር ማርሴይ ከተማ ደርሷል።

ብዙ የፈረንሳዩ ክለብ ማርሴይ ደጋፊዎች በአየር ማረፊያ በመገኘት ለሜሰን ግሪንውድ ደማቅ አቀባበል አድርገዋል ደጋፊዎቹ በተደጋጋሚ ስሙን ስጠሩም ተስተውሏል።

ሜሰን ግሪንውድ ወደ ማርሴይ በሚያደርገው ዝውውር ዙሪያ ውዝግቦች መኖራቸው ሲገለፅ ከቀናት በፊት የማርሴይ ከንቲባ ቤኖይት ፓያን በዝውውር አለመደሰታቸውን ገልፀው ነበር።

ሜሰን ግሪንውድ የ2023/24 የውድድር ዘመን በስፔኑ ክለብ ሄታፌ ያሳለፈ ሲሆን በቆይታውም ስምንት የላሊጋ ጎሎችን ማስቆጠር ችሏል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
ቪንሰስ ጁኒየር ገቢ ማሰባሰቢያ አዘጋጅቷል !

የሪያል ማድሪዱ የፊት መስመር ተጫዋች ቪንሰስ ጁኒየር በብራዚል ለተቸገሩ ህፃናት የሚሆን የእርዳታ ገቢ ማሰባሰቢያ የጨረታ ዝግጅት ማካሄዱ ተገልጿል።

በብራዚል በተካሄደው ዝግጅት ላይ የቡድን አጋሮቹ ፌርላንድ ሜንዲ ፣ ኤደር ሚሊታኦ እና ኤድዋርዶ ካማቪንጋ መገኘታቸው ታውቋል።

በዝግጅቱ ላይ ኪሊያን ምባፔ የተፈረመበት ማልያውን እንዲሁም ጁድ ቤሊንግሀም በአውሮፓ ሻምፒየንስ ሊግ ግማሽ ፍፃሜ የተጫወተባቸውን ጫማዎች ለጨረታ መለገሳቸው ተገልጿል።

በተጨማሪም ሉካ ሞድሪች የተፈረመበት ማልያ መስጠቱ ሲገለፅ ሌላኛው የቡድን አጋሩ ኤደር ሚሊታኦ በበኩሉ ለገቢ ማሰባሰቢያው 35,000 ዩሮ መለገሱ ተገልጿል።

ቪንሰስ ጁኒየር በሀገሩ የሚገኙ ህፃናት ትምህርታቸውን እንዳያቋርጡ እገዛ የሚያደርግ ሲሆን ባለፈው አመት የበጎ አድራጎት ስራን የሚያበረታታውን የባሎን ዶር የሶክራተስ አዋርድ ማሸነፉ ይታወሳል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
አርጀንቲና ደረጃዋን አስጠብቃለች !

የፊፋ የአለም ብሔራዊ ቡድኖች ወርሀዊ ደረጃ ይፋ ሲደረግ የኮፓ አሜሪካ አሸናፊው የአርጀንቲና ብሔራዊ ቡድን የአንደኝነትን ደረጃውን አስጠብቋል።

የአውሮፓ ዋንጫን ያሸነፈው የስፔን ብሔራዊ ቡድን አምስት ደረጃዎችን በማሻሻል ሶስተኛ ደረጃ ላይ መቀመጥ ችሏል።

በአውሮፓ ዋንጫው ጥሩ ጉዞ ማድረግ የቻለው የቱርክ ብሔራዊ ቡድን አስራ ስድስት ደረጃዎች በማሻሻል ሀያ ስድስተኛ ደረጃ ላይ ተቀምጠዋል።

በኮፓ አሜሪካ ካደረጋቸው አራት ጨዋታዎች ሶስቱን አሸንፎ ከሩብ ፍፃሜ በመለያ ምት የተሰናበተው የቬንዙዌላ ብሔራዊ ቡድን በበኩሉ አስራ ሰባት ደረጃዎች በማሻሻል ሰላሳ ሰባተኛ ደረጃን ይዟል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
የኢብራሂሞቪች ልጅ ለኤሲ ሚላን ፈርሟል !

የስዊድናዊው የቀድሞ ተጨዋች ዝላታን ኢብራሂሞቪች ልጅ ማክሲሚሊያን ኢብራሂሞቪች በኤሲ ሚላን ቤት የመጀመሪያ ፕሮፌሽናል ኮንትራቱን መፈረሙ ተገልጿል።

የ 18ዓመቱ ተጨዋች ማክሲሚሊያን ኢብራሂሞቪች በጣልያን ሴርያ ሲ ለሚወዳደረው የኤሲ ሚላን ሁለተኛ ቡድን በመጫወት እንደሚጀመር ተነግሯል።

ባለፈው አመት በይፋ ጫማውን የሰቀለው ዝላታን ኢብራሂሞቪች በአሁኑ ሰዓት በኤሲ ሚላን ቤት በአዲስ ሚና እያገለገለ ይገኛል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
TIKVAH-SPORT
ማድሪድ የተጫዋቹን ውል ሊያራዝም ነው ! በአሰልጣኝ ካርሎ አንቾሎቲ የሚሰለጥኑት ሪያል ማድሪዶች የስፔናዊውን የመስመር ተጨዋች ሉካስ ቫስኩዌስ ኮንትራት ሊያራዝሙ መሆኑ ተገልጿል። የ 32ዓመቱ ተጨዋች ሉካስ ቫስኩዌስ በሎስ ብላንኮዎቹ ቤት ለአንድ የውድድር አመት ለመቆየት መስማማቱ ተገልጿል። ሉካስ ቫስኩዌስ በዚህ አመት ለሪያል ማድሪድ በሰላሳ ስምንት ጨዋታዎች ተሰልፎ መጫወት የቻለ ሲሆን የላሊጋ…
ማድሪድ የተጫዋቹን ውል አራዘመ !

በአሰልጣኝ ካርሎ አንቾሎቲ የሚሰለጥኑት ሪያል ማድሪዶች የስፔናዊውን የመስመር ተጨዋች ሉካስ ቫስኩዌስ ኮንትራት ማራዘማቸውን ይፋ አድርገዋል።

የ 32ዓመቱ የመስመር ተጨዋች ሉካስ ቫስኩዌስ በሎስ ብላንኮዎቹ ቤት ለአንድ የውድድር አመት ለመቆየት ፊርማውን ማኖሩ ተገልጿል።

ሉካስ ቫስኩዌስ በሪያል ማድሪድ ቤት አስራ ሰባት አመታትን ሲያሳልፍ አራት የላሊጋ እና አምስት የሻምፒየንስ ሊግ ዋንጫዎችን ጨምሮ ሀያ አንድ ዋንጫዎች አሳክቷል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
ዱሳን ታዲች ከብሔራዊ ቡድኑ ራሱን አገለለ !

በቱርኩ ክለብ ፌነርባቼ የሚጫወተው የፊት መስመር ተጨዋቹ ዱሳን ታዲች ራሱን ከሰርቢያ ብሔራዊ ቡድን ማግልለሉን ይፋ አድርጓል።

የ 35ዓመቱ ዱሳን ታዲች በሰርቢያ ብሔራዊ ቡድን ውስጥ ብዙ ጨዋታዎች ማድረግ የቻለ ባለታሪክ ተጨዋች ነው።

በሰርቢያ እግርኳስ በቀዳሚነት የሚጠቀሰው ዱሳን ታዲች ለብሔራዊ ቡድኑ ሀያ ሶስት ግቦችን ማስቆጠር ችሏል።

ዱሳን ታዲች ብሔራዊ ቡድኑን ለአስራ አምስት አመታት ማገልገል ችሏል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
Forwarded from WANAW SPORT
📢 #ከዋናው ትጥቆችን ለድርጅትዎ ሲያዙ...

👉🏾 #ያናግሩን#ይምጡ#ይዘዙን!

📌 ለበለጠ መረጃና ትዕዛዝ 📲 0911955221 እና 0995114226 ላይ ይደውሉ።

👉🏾 እንዲሁም በቴሌግራም @Wanawsales ላይ የሽያጭ ሰራተኞቻችንን በቀጥታ በማናገር ወይም በቴሌግራም ቦት @WanawSportBot ይዘዙን።

🏅 ዋናው ወደፊት...

@wanawsportwear
2024/10/03 21:33:17
Back to Top
HTML Embed Code: