Telegram Web Link
" አርሰናል እያለሁ ጫማ ልሰቅል አስቤ ነበር " ፔፔ

የቱርኩን ክለብ ትራብዞንስፖር የተቀላቀለው የቀድሞ የአርሰናል አይቮሪ ኮስታዊ የፊት መስመር ተጨዋች ኒኮላስ ፔፔ በመድፈኞቹ ቤት ስለነበረው ቆይታ ዙሪያ አስተያየቱን ሰጥቷል።

ኒኮላስ ፔፔ ስለ አርሰናል ቆይታው ምን አለ ?

- " አርሰናልን ብዙም ሳልቆይ መልቀቅ እችል ነበር ነገርግን ለእኔ ካወጡት የበለጠ ገንዘብ ጠይቀው ስለነበር አልተሳካም።

- አርሰናል እያለሁ ከጋዜጦች ፣ ማህበራዊ ሚዲያ እና ከክለቡ አንዳንድ ሰዎች በደረሰብኝ ትችት ጫማ ልሰቅል አስቤ ነበር ሁልጊዜ ከጎኔ የሚቆሙት የአርሰናል ደጋፊዎች ብቻ ነበሩ።

- አርሰናል የእኔን ኮንትራት ለማቋረጥ ከስምምነት የደረሱት ወደ ሳውዲ አረቢያ ሊግ አልሄድም በሚል ቅድመ ሁኔታ ነበር።

- አሁን በትራብዞንስፖር እቀጥላለሁ ወደ ሳውዲ ወይም ሌላ ቦታ ማምራት አልፈልግም አልልም ፣ ነገርግን አውሮፓ ውስጥ ያልጨረስኩት ነገር አለ አሁንም ማድረግ የምችለው ነገር መኖሩን ማሳየት እፈልጋለሁ።

- አርሰናል ውስጥ የእግርኳስ ፍቅሬን ትንሽ አጥቻለሁ ፣ በዚህ ልክ ለምን እንደተተቸሁ አስባለሁ እኔን በፕርሚየር ሊጉ ታሪክ ያልተሳካለት ሰው ለማድረግ ፈልገው ነበር።"ሲል ተደምጧል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
ቼልሲ አሁንም የፖተርን ደሞዝ እየከፈሉ ነው !

የምዕራብ ለንደኑ ክለብ ቼልሲ የቀድሞ አሰልጣኛቸው ግራም ፖተርን ደሞዝ አሁንም በመክፈል ላይ መሆናቸው ተገልጿል።

ሰማያዊዎቹ ለአሰልጣኙ በሳምንት 200,000 ፓውንድ በመክፈል ላይ መሆናቸው ሲገለፅ ክፍያው እስከ ቀጣዩ ጥቅምት ወር እንደሚቀጥል ተነግሯል።

እንግሊዛዊው አሰልጣኝ ግራም ፖተር ከቼልሲ አሰልጣኝነታቸው ከተሰናበቱ ከአንድ አመት በላይ እንደሆናቸው አይዘነጋም።

ከእንግሊዝ ብሔራዊ ቡድን ጋር ስማቸው እየተያያዘ የሚገኙት አሰልጣኝ ግራም ፖተር ቡድኑን የሚረከቡ ከሆነ ቼልሲ አንድ ሚልዮን ፓውንድ እንደሚያተርፉ ተገልጿል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
የወደፊቱ የሲቲ ተጨዋች አዲስ ታሪክ ፅፏል !

ማንችስተር ሲቲዎች ከወዲሁ ያስፈረሙት የወደፊት ተስፈኛ ታዳጊ ካቫን ሱሊቫን ትላንት በአሜሪካ ሜጀር ሊግ ሶከር ውድድር ለፊላደልፊያ ዩኒየን ተሰልፎ ተጫውቷል።

ታዳጊው በ 14ዓመቱ በአሜሪካ ሜጀር ሊግ ውድድር ላይ ተሰልፎ መጫወት የቻለ በታሪክ በእድሜ ትንሹ ተጨዋች በመሆን አዲስ ታሪክ መፃፍ ችሏል።

ማንችስተር ሲቲዎቹ ባለ ትልቅ ተሰጥኦ ባለቤቱን ታዳጊ ካቫን ሱሊቫን በቅርቡ አንድ ሚልዮን ዶላር አውጥተው ለቡድናቸው አስፈርመውታል።

አሜሪካዊው ታዳጊ ካቫን ሱሊቫን በሚቀጥለው አመት በ2025 ማንችስተር ሲቲን እንደሚቀላቀል ይጠበቃል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
TIKVAH-SPORT
ኦባምያንግ ከማርሴይ ጋር መለያየቱን አሳወቀ ! ጋቦናዊው የፊት መስመር ተጨዋች ኦባምያንግ ከፈረንሳዩ ክለብ ኦሎምፒክ ማርሴይ ጋር መለያየቱን በማህበራዊ ትስስር ገፁ ይፋ አድርጓል። ተጨዋቹ ባሰፈረው መልዕክትም ጠንካራ እንድሆን አድርጋችሁኛል የቡድን አጋሮቼን እና መላውን ክለቡን አመሰግናለሁ በማለት ተናግሯል። ኦባምያንግ በቀጣይ የሳውዲ አረቢያውን ክለብ አል ቃዲሲያ በሁለት አመት ኮንትራት እንደሚቀላቀል…
ኦባምያንግ በይፋ አል ቃዲሲያን ተቀላቀለ !

ጋቦናዊው የፊት መስመር ተጨዋች ፔር ኤምሪክ ኦባምያንግ የሳውዲ አረቢያውን ክለብ አል ቃዲሲያ መቀላቀሉ ይፋ ተደርጓል።

ኦባምያንግ ከቀናት በፊት ከፈረንሳዩ ክለብ ኦሎምፒክ ማርሴይ ጋር መለያየቱን በማህበራዊ ትስስር ገፁ ይፋ ማድረጉ ይታወሳል።

ኦባምያንግ የሳውዲ አረቢያውን ክለብ አል ቃዲሲያ በሁለት አመት ኮንትራት መቀላቀሉ ተገልጿል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
ጁቬንቱስ ከተጨዋቹ ጋር ተለያይቷል !

የጣልያን ሴርያው ክለብ ጁቬንቱስ ከፈረንሳዊው የመሐል ሜዳ ተጨዋቻቸው አድሪያን ራቢዮ ጋር መለያየታቸውን ይፋ አድርገዋል።

የ 29ዓመቱ የመሐል ሜዳ ተጨዋች አድሪያን ራቢዮ በጁቬንቱስ ቤት የቀረበለትን በአመት 7 ሚልዮን ዩሮ ክፍያ አለመቀበሉ ተገልጿል።

ተጫዋቹ አሁን ላይ በነፃ ዝውውር አዲስ ክለብ ለመቀላቀል በንግግር ላይ መሆኑ ተነግሯል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
ፓትሪክ ቬይራ ከስትራስቦርግ ጋር ተለያይቷል !

የፈረንሳዩ ክለብ ስትራስቦርግ የ 48ዓመቱ ዋና አሰልጣኝ ፓትሪክ ቬይራ ከአንድ የውድድር አመት ቆይታ በኃላ በጋራ ስምምነት ከሀላፊነት መልቀቁን ይፋ አድርጓል።

ስትራስቦርግ በሊጉ አመርቂ ያልሆነ የውድድር አመት ያሳለፈ ሲሆን በ2023/24 የውድድር ዘመን አስራ ሶስተኛ ደረጃን ይዞ ነበር ያጠናቀቀው።

ፈረንሳዊው አሰልጣኝ ፓትሪክ ቬይራ የእንግሊዙን ክለብ ክሪስታል ፓላስ ከ2021 እስከ 2023 ለሁለት የውድድር አመታት ማሰልጠኑ አይዘነጋም።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
TIKVAH-SPORT
ፈረንሳይ የአርጀንቲና ተጨዋቾችን ከሰሰች ! የፈረንሳይ እግርኳስ ፌዴሬሽን የአርጀንቲና ብሔራዊ ቡድን ተጨዋቾች ላይ ለአለም የእግርኳስ የበላይ ፊፋ ቅሬታ ማቅረቡን በይፋ አስታውቋል። ፌዴሬሽኑ ቅሬታውን ለፊፋ ያቀርበው የኮፓ አሜሪካ አሸናፊው አርጀንቲና ብሔራዊ ተጨዋቾች ከድል በኋላ ባሰሙት ዝማሬ ምክንያት መሆኑ ተነግሯል። የአርጀንቲና ብሔራዊ ቡድን ተጨዋቾች ኮፓ አሜሪካ ካሸነፉ በኋላ በጉዞ ላይ…
አርጀንቲና ምክትል የስፖርት ሀላፊዋን አሰናበተች !

የአርጀንቲናው ፕሬዝዳንት ሀቤር ሚሌይ የሀገሪቱን ምክትል የስፖርት ሚንስቴር ጁሊዮ ጋሬሮን ከሀላፊነት ማሰናበታቸው ተገልጿል።

ፕሬዝዳንቱ ሀላፊውን ያሰናበቱት የአርጀንቲና ብሔራዊ ቡድን ተጫዋቾች ያሰሙትን ዝማሬ ተከትሎ ለቀረበው ተቃውሞ የቡድኑ አምበል ሊዮኔል ሜሲ ወጥቶ በይፋ ይቅርታ ይጠይቅ በማለታቸው መሆኑ ተገልጿል።

የሀገሪቱ ፕሬዝዳንት በማህበራዊ ትስስር ገፃቸው ባሰፈሩት ፅሁፍም " የትኛውም የመንግስት አካል የአለም ዋንጫ እና ሁለት የኮፓ አሜሪካ አሸናፊውን ብሔራዊ ቡድን ማዘዝ አይችልም " ሲሉ ገልጸዋል።

የአርጀንቲና ምክትል ፕሬዝዳንት የሆኑት ቪክቶሪያ ቫላሩኤል በበኩላቸው በሰጡት አስተያየት " የትኛውም ቅኝ ገዢ ሀይል ለእግርኳስ በተዘመረ ዝማሬ አያስፈራራንም።"ብለዋል።

ምክትል ፕሬዝዳንቷ አክለውም " ሊቀበሉት የማይፈልጉት እውነት ነው የተነገረው ፣ የተናደዳችሁ ማስመሰሉን አቁሙ እኔ ከቡድኑ ጎን እቆማለሁ።" በማለት ድጋፋቸውን አሳይተዋል።

የአርጀንቲና ብሔራዊ ቡድን ተጨዋቾች በቅርቡ የፈረንሳይ ብሔራዊ ቡድን ተጨዋቾችን የተመለከተ ዝማሬ በጋራ ማሰማታቸውን ተከትሎ ቅሬታ እየቀረበባቸው ይገኛል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
ዶርትመንድ ሴርሁ ጉራሲን በይፋ አስፈረመ !

የቡንደስሊጋው ክለብ ቦርስያ ዶርትመንድ የስቱትጋርቱን የፊት መስመር አጥቂ ሴርሁ ጉራሲ ማስፈረማቸውን ይፋ አድርገዋል።

ከምዕራብ አፍሪካዊቷ ሀገር ጊኒ የተገኘው የፊት መስመር አጥቂ ሴርሁ ጉራሲ በተጠናቀቀው የውድድር ዘመን ጥሩ የሚባል ጊዜን በስቱትጋርት ማሳለፉ አይዘነጋም።

ዶርትመንድ ተጫዋቹን የውል ማፍረሻውን 17.5 ሚልዮን ዩሮ በመክፈል በአራት አመት ኮንትራት ማስፈረማቸው ተገልጿል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
ኮል ፓልመር የደሞዝ ጭማሬ ሊያገኝ ነው !

ቼልሲዎች ለቡድኑ ጥሩ ግልጋሎት በመስጠት ላይ ለሚገኘው እንግሊዛዊ ተጨዋች ኮል ፓልመር የደሞዝ ጭማሬ ሊያደርጉለት መሆኑ ተገልጿል።

ሰማያዊዎቹ ባለፈው አመት ከማንችስተር ሲቲ ባስፈረሙት ኮል ፓልመር ደስተኛ መሆናቸው እና በቀጣይ አስር አመታት በክለቡ ሊያቆዩት እንደሚፈልጉ ተነግሯል።

ኮል ፓልመር አሁን ላይ በቼልሲ በሳምንት 80,000 ፓውንድ እንደሚያገኝ ሲገለፅ ጭማሬውን በውስጥ ለመጨረስ ማሰባቸው ተጠቁሟል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
TIKVAH-SPORT
ሌኒ ዮሮ ወደ እንግሊዝ እያመራ መሆኑ ተገለፀ ! ፈረንሳዊው የተከላካይ ስፍራ ተጨዋች ሌኒ ዮሮ ወደ ማንችስተር ዩናይትድ የሚያደርገውን ዝውውር ለማጠናቀቅ ወደ እንግሊዝ በማምራት ላይ መሆኑ ተገልጿል። ተጨዋቹ በቀጣይ ማንችስተር ዩናይትድን ለመቀላቀል የህክምና ምርመራውን እንደሚያደርግ እና የግል ስምምነቶችን እንደሚያጠናቅቅ ተነግሯል። ማንችስተር ዩናይትድ ተጫዋቹን በ50 ሚልዮን ዩሮ እና ተጨማሪ…
ሌኒ ዮሮ ለዩናይትድ መፈረሙ ተገለጸ !

ፈረንሳዊው የተከላካይ ስፍራ ተጨዋች ሌኒ ዮሮ የማንችስተር ዩናይትድ ተጨዋች የሚያደርገውን ፊርማ መፈረሙ ተገልጿል።

ተጨዋቹ በዛሬው ዕለት ቀርቶት የነበረውን ሁለተኛ የህክምና ምርመራ በማጠናቀቅ የአምስት አመት ኮንትራት መፈረሙ ተነግሯል።

በማንችስተር ዩናይትድ እና ሊል መካከል የወረቀት ስራዎች መጠናቀቃቸውም እንዲሁ ሲገለፅ በቀጣይ ዝውውሩ ይፋ መደረግ እንደሚቀረው ተጠቁሟል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
TIKVAH-SPORT
“ ለተፈጠረው ነገር ከልብ ይቅርታ እጠይቃለሁ “ ኢንዞ ፈርናንዴዝ አርጀንቲናዊው የቼልሲ የመሐል ሜዳ ተጨዋች ኢንዞ ፈርናንዴዝ በማህበራዊ ትስስር ገፁ ስለ ተሰራጨው ቪድዮ ከልብ ይቅርታ መጠየቅ እንደሚፈልግ ተናግሯል። " በኢንስታግራም ገፄ ለተሰራጨው የደስታ አገላለፅ ዝማሬ ቪዲዮ ከልብ ይቅርታ እጠይቃለሁ " ሲል የገለፀው ኢንዞ ፈርናንዴዝ ዝማሬው አፀያፊ ቃላትን ይዟል ለነዚህ ቃላት ምንም ሰበብ የለም…
የቼልሲ ተጨዋቾች ብስጭት ውስጥ መሆናቸው ተገለጸ !

የምዕራብ ለንደኑ ክለብ ቼልሲ በርካታ ተጨዋቾች በአርጀንቲናዊው ተጨዋች ኢንዞ ፈርናንዴዝ ባህሪ ከፍተኛ ብስጭት ውስጥ ገብተው እንደሚገኙ ተገልጿል።

ተጨዋቾቹ ኢንዞ ፈርናንዴዝ ለምን ይህን ያደርጋል የሚል ጥያቄ በመጠየቅ ላይ መሆናቸውን ለክለቡ መልበሻ ቤት ቅርበት ያላቸው የመረጃ ምንጮች ገልጸዋል።

የክለቡ መልበሻ ቤት በዚሁ ምክንያት መከፋፈሉ የተነገረ ሲሆን ነገሩ በቡድኑ ውስጥ የከፋ ሊሆን እንደሚችል ተዘግቧል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
ሊቨርፑል የቲኬት ሽያጩን ማቆሙን ገለጸ !

የመርሲሳይዱ ክለብ ሊቨርፑል ትላንት ለአባላቱ ጀምሮት የነበረውን የቀጣይ የሊጉ የሜዳ ጨዋታዎች የመግቢያ ትኬት ሽያጭ ላልተወሰነ ጊዜ ማቋረጡን አስታውቋል።

የስታዲየም መግቢያ ትኬት ሽያጩ የተቋረጠው የሳይበር ጥቃት ተፈፅሞ የቴክኒክ ችግር ስላጋጠማቸው መሆኑን ሊቨርፑሎች አስረድተዋል።

ክለቡ ጥቃቱ የተፈፀመው ትኬቶችን አጭበርብሮ ለመግዛት ይሁን ወይም ለሌላ አላማ የሚለውን ለማወቅ ምርመራ መጀመሩን አስውቋል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
TIKVAH-SPORT
ማንችስተር ሲቲ ተጨዋች ለማስፈረም ተስማማ ! ማንችስተር ሲቲ ብራዚላዊውን የጂሮና ወጣት የፊት መስመር ተጨዋች ሳቭዮ በሚቀጥለው ክረምት ወደ ስብሰባቸው ለመቀላቀል ከስምምነት መድረሳቸው ተገልጿል። የ 19ዓመቱ ብራዚላዊ የፊት መስመር አጥቂ ሳቭዮ በሚቀጥሉት ቀናት ለማንችስተር ሲቲ እንደሚፈርም እና በውድድር አመቱ መጨረሻ ቡድኑን እንደሚቀላል ተነግሯል። ተጨዋቹ በዘንድሮው የውድድር ዘመን ለጂሮና ባደረጋቸው…
ማንችስተር ሲቲ ተጨዋች አስፈረመ !

ማንችስተር ሲቲ ብራዚላዊውን ወጣት የፊት መስመር ተጨዋች ሳቭዮ ማስፈረማቸውን ይፋ አድርገዋል።

በአሰልጣኝ ፔፕ ጋርዲዮላ የሚመራው ማንችስተር ሲቲዎች የ 19ዓመቱን የፊት መስመር አጥቂ ሳቭዮ በ21 ሚልዮን ዩሮ የዝውውር ሒሳብ ማስፈረማቸው ተገልጿል።

ባለፈው የውድድር አመት በጂሮና ጥሩ የሚባል ጊዜን ማሳለፍ የቻለው ሳቪዮ ለማንችስተር ሲቲ የአምስት አመት ኮንትራት መፈረሙ ተነግሯል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
" ልጄ የዘረኝነት ባህሪ የለበትም " የኢንዞ ፈርናንዴዝ ወላጅ አባት

የአርጀንቲናዊው የመሐል ሜዳ ተጨዋች ኢንዞ ፈርናንዴዝ ወላጅ አባት " ልጄ የዘረኝነት ባህሪ የለበትም " ሲሉ ልጃቸው እየቀረበበት ስለሚገኘው ተቃውሞ አስተያየታቸውን ሰጥተዋል።

" እኔ ልጄን በደንብ አውቀዋለሁ በፍፁም የዘረኝነት ባህሪ የለበትም " ሲሉ ያስረዱት የተጫዋቹ ወላጅ አባት የእኛን የእግርኳስ ባህል እና የደስታ አገላለፅ ለአውሮፓውያን ለመረዳት አስቸጋሪ ነው ብለዋል።

" 2014 ጀርመን በአለም ዋንጫው አሸንፋን ከባህላችን ጋር በተያያዘ ሲሰድቡን ነበር ፣ በ2022 ፈረንሳዮች ሜሲን በቁመቱ ምክንያት ሲቀልዱበት ነበር እኛ ግን በፍጹም ዘረኝነት ብለን አልወጣንም።" ሲሉ የኢንዞ ፈርናንዴዝ ወላጅ አባት ተናግረዋል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
TIKVAH-SPORT
ግሪንውድ ማርሴይን ለመቀላቀል ተስማማ ! እንግሊዛዊው የፊት መስመር ተጨዋች ሜሰን ግሪንውድ የፈረንሳዩን ክለብ ማርሴይ ለመቀላቀል በቃል ደረጃ ከስምምነት መድረሱ ይፋ ተደርጓል። ማርሴይ ከሳምንት በፊት ተጫዋቹን በ31 ሚልዮን ዩሮ ለማስፈረም ከማንችስተር ዩናይትድ ጋር ከስምምነት መድረሳቸው ይታወሳል። የ 22ዓመቱ የፊት መስመር ተጨዋች ሜሰን ግሪንውድ በቀጣይ የህክምና ምርመራውን ለማድረግ እንደሚጓዝ…
ሜሰን ግሪንውድ በይፋ ማርሴይን ተቀላቀለ !

የፈረንሳዩ ክለብ ማርሴይ እንግሊዛዊውን የፊት መስመር ተጨዋች ሜሰን ግሪንውድ ከማንችስተር ዩናይትድ ማስፈረማቸውን ይፋ አድርገዋል።

ማርሴይ የ 22ዓመቱን የፊት መስመር ተጨዋች ሜሰን ግሪንውድ በ30 ሚልዮን ዩሮ መስፈረማቸው ተገልጿል።

ማንችስተር ዩናይትድ ከወደፊት የሜሰን ግሪንውድ ሽያጭ ሀምሳ በመቶውን የሚያስገኝላቸው መብት በውሉ ውስጥ መካተቱ ተገልጿል።

ግሪንውድ በማርሴይ የአምስት አመት ኮንትራት መፈረሙ ሲገለፅ በክለቡ የአስር ቁጥር ማልያ እንደሚለብስ ታውቋል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
ማንችስተር ዩናይትድ በይፋ ተጨዋች አስፈረመ !

በዝውውር መስኮቱ ንቁ ተሳትፎ በማድረግ ላይ የሚገኙት ማንችስተር ዩናይትዶች ፈረንሳዊውን ተከላካይ ሌኒ ዮሮ ከሊል ማስፈረማቸውን በይፋ አስታውቀዋል።

ቀያዮቹ ሴጣኖች ለዝውውሩ 50 ሚልዮን ዩሮ ቀጥታ ክፍያ እና ታይቶ የሚጨምር 12 ሚልዮን ዩሮ የዝውውር ሒሳብ ወጪ እንደሚያደርጉ ተገልጿል።

ማንችስተር ዩናይትዶች " የተከላካዩ ኪሊያን ምባፔ " የሚል ቅፅል ስም ያገኘውን የ 18ዓመት ተከላካይ ሊኒ ዮሮ በአምስት አመት ኮንትራት አስፈርመውታል።

ተጨዋቹ ፊርማውን ካኖረ በኋላ " አቅሜን አውጥቼ ለማሳየት እና ህልሜን ለማሳካት ትክክለኛው ቦታ እንደሚሆን ይሰማኛል " ሲል ተደምጧል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
ዩናይትድ ተጨማሪ ተከላካይ ያስፈርማል ?

የሌኒ ዮሮን ዝውውር ያጠናቀቀው ማንችስተር ዩናይትድ አሁንም ማትያስ ዴሊት እና ብራንዝዌትን የማስፈረም ፍላጎት እንዳለው ተገልጿል።

ማንችስተር ዩናይትድ በቀጣይ ተጨማሪ የመሐል ተከላካይ የማስፈረም እቅዱ በተጫዋች ሽያጭ ላይ የተመረኮዘ ሊሆን እንደሚችል ተነግሯል።

የቱርኩ ክለብ ፌነርባቼ የማንችስተር ዩናይትዱን ተከላካይ ቪክቶር ሊንድሎፍ የማስፈረም ፍላጎት እንዳለው ተጠቁሟል።

በሌላ በኩል ቀያዮቹ ሴጣኖች ሌኒ ዮሮን ሲያስፈርሙ የቀድሞ ተጨዋቻቸው ሪዮ ፈርዲናንድ ተጫዋቹ ክለቡን እንዲቀላቀል ማሳመኑ ተነግሯል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
TIKVAH-SPORT
ማኑኤል ኡጋርት ወደ ማንችስተር ዩናይትድ ? ማንችስተር ዩናይትድ ዩራጓዊውን የመሐል ሜዳ ተጨዋች ማኑኤል ኡጋርት ለማስፈረም ከፈረንሳዩ ክለብ ፒኤስጂ ጋር ንግግር ማድረጋቸው ተገልጿል። የ 23ዓመቱ የመሐል ሜዳ ተጨዋች ማኑኤል ኡጋርት ማንችስተር ዩናይትድ በአውሮፓ ሻምፒየንስ ሊግ ባይሳተፍም እንኳን የመቀላቀል ፍላጎት እንዳለው ተነግሯል። ባለፈው አመት ፒኤስጂን ከስፖርቲንግ ሊስበን በአምስት አመት…
ዩናይትድ ተጨዋች ለማስፈረም ተስማማ !

ማንችስተር ዩናይትድ ዩራጓዊውን የመሐል ሜዳ ተጨዋች ማኑኤል ኡጋርትን ለማስፈረም በግል ከተጨዋቹ ጋር ከስምምነት መድረሳቸው ተገልጿል።

የ 23ዓመቱ የመሐል ሜዳ ተጨዋች ማኑኤል ኡጋርት ማንችስተር ዩናይትድ በአውሮፓ ሻምፒየንስ ሊግ ባይሳተፍም እንኳን ክለቡን ለመቀላቀል መፈለጉ ተነግሯል።

ማንችስተር ዩናይትዶች በተጨዋቹ ዝውውር ሒሳብ ዙሪያ ከፒኤስጂ ጋር የሚያደርጉትን ንግግር አሁንም መቀጠላቸው ተገልጿል።

ቀያዮቹ ሴጣኖች ማኑኤል ኡጋርትን ለማስፈረም አንድ የመሐል ሜዳ ተጨዋቻቸውን መሸጥ ሊጠበቅባቸው እንደሚችል ተጠቁሟል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
Forwarded from WANAW SPORT
Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
🏆🇪🇹 #2016_የኢትዮጵያ_ሴቶች_ፕሪሚየር_ሊግ የመዝጊያ ስነስርዓት! 🇪🇹🏆

ዋናው ስፖርት የዚህ ደማቅ ውድድር አጋር ስለነበር በድጋሚ ኩራት ይሰማዋል።

Instagram | Facebook | TikTok

🏅 ዋናው ወደፊት...

@wanawsportwear
Forwarded from HEY Online Market
•PlayStation 5, 73,000 Birr
•Playstaion 5 Slim, 78,000 Birr

•PlayStation 4 Slim, 35,000 Birr
•PlayStation 4 Pro, 43,000 Birr

•Playstaion portal, 35,000 Birr
•Meta Quest 2, 55,000 Birr
•Meta Quest 3, 83,000 Birr

Contact
0953964175 @heymobile

@heyonlinemarket
2024/10/03 23:17:56
Back to Top
HTML Embed Code: