Telegram Web Link
" በማድሪድ ፍቅር መውደቅህን አውቃለሁ " ፔሬዝ

የሪያል ማድሪዱ ፕሬዝዳንት ፍሎረንቲኖ ፔሬዝ በሳንቲያጎ በርናቦ ስታዲየም እየተደረገ በሚገኘው የኪሊያን ምባፔ አቀባበል ስነስርዓት ላይ ንግግር በማድረግ ላይ ናቸዉ።

ፕሬዝዳንት ፍሎረንቲኖ ፔሬዝ ምን አሉ ?

- " ኪሊያን ምባፔ እዚህ በመሆንህ አመሰግናለሁ አንተ በሪያል ማድሪድ ፍቅር መውደቅህን አውቃለሁ ገና በ18ዓመትህ አለም ዋንጫ አሸንፈሀል።

- ሪያል ማድሪድ ኢንተርናሽናል ክለብ ነው በአለም ላይ ታዋቂ ነው ፣ ሪያል ማድሪድ ውስጥ ሌላ ምርጫ የለም ማሸነፍ ብቻ ነው።

- ኪሊያን ምባፔ እዚህ ያለኸው እኛ ብቻ ሳንሆን አንተም መምጣት ስለፈለግክ ነው።

- አሁን የምትለብሰው አስራ አምስት የሻምፒየንስ ሊግ ዋንጫዎችን የያዘውን ነጩን ማልያ ነው።"ሲሉ ተደምጠዋል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
" ለማድሪድ ህይወቴን እሰጣለሁ " ምባፔ

የሪያል ማድሪድ ተጨዋች በመሆን በመታወወቅ ላይ የሚገኘው ኪሊያን ምባፔ ለክለቡ ህይወቱን እንደሚሰጥ በስነስርዓቱ ላይ በሰጠው አስተያየት ተናግሯል።

ኪሊያን ምባፔ ምን አለ ?

- " የሪያል ማድሪድ ተጨዋች የመሆን ህልም ነበረኝ ማሳካት ችያለሁ አሁን እዚህ ነኝ አሁን በትልቁ ክለብ ትልቅ ደረጃ ላይ መድረስ እፈልጋለሁ።

- እዚህ ቦታ ለመገኘት በርካታ አስቸጋሪ ሁኔታዎችን አልፌያለሁ አሁን በአለም ምርጡ ክለብ ውስጥ እገኛለሁ።

- ለወጣቶች ማለት የምፈልገው የማይሆን ህልም እንደሌለ ነው አሁን እኔ ደስተኛው ሰው ሆኛለሁ።

- ለሪያል ማድሪድ ሙሉ ህይወቴን እሰጣለሁ ሪያል ማድሪድ በእግርኳስ ታሪክ ውስጥ ምርጡ ክለብ ነው።"ሲል ተደምጧል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
" ከቪንሰስ ጋር እስከምጫወት ጓጉቻለሁ " ምባፔ

በዛሬው ዕለት በይፋ የሪያል ማድሪድ በመሆን ደጋፊውን የተዋወቀው ኪሊያን ምባፔ ቪንሰስ ጁኒየር ማድሪድን እንዲቀላቀል እንደጠየቀው በሰጠው አስተያየት ተናግሯል።

ሪያል ማድሪድን እንዲቀላቀል ቪንሰስ ጁኒየር መልዕክት በመላክ በተደጋጋሚ እንደጠየቀው የገለፀው ኪሊያን ምባፔ " ከእሱ ጋር እስክጫወት ጓጉቻለሁ ፣ እንዲሁም ከቤሊንግሀም እና ሌሎች ኮከቦች ጋር " ብሏል።

" ቪንሰስ ጁኒየር ልዩ ተጨዋች ነው " የሚለው ኪሊያን ምባፔ እርስበርስ ለመላመድ ችግር አይኖርብንም ትልቅ ተጨዋቾች እንዴት አብረው እንደሚጫወቱ ያውቃሉ ከእሱ ጋር መጫወት ምንም ችግር የለብኝም " ብሏል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
Forwarded from WANAW SPORT
🎙 ለአካዳሚ ሰልጣኞች የሚሆኑ ትጥቆች ለእናንተ!

👉🏾 #አሁኑኑ ይዘዙን!

📌 ለበለጠ መረጃና ትዕዛዝ 📲 09011382830910851535 እና 0913586742 ላይ ይደውሉ።

👉🏾 እንዲሁም በቴሌግራም @Wanawsales ላይ የሽያጭ ሰራተኞቻችንን በቀጥታ በማናገር ወይም በቴሌግራም ቦት @WanawSportBot ይዘዙን።

🏅 ዋናው ወደፊት...

@wanawsportwear
የፓሪስ ኦሎምፒክ 10 ቀን ብቻ ቀረው!

ከሐምሌ 19 እስከ ነሐሴ 5 በዲኤስቲቪ  ሙሉ የቀጥታ ስርጭት በ9 ቻናሎች ይተላለፋል!

ብርቅዬ አትሌቶቻችንን በፓሪሱ ኦሎምፒክስ ለመቀላቀል ጊዜው አሁን ነው! ዛሬውኑ ደንበኝነትዎን ያራዝሙ የአትሌቶቻችንን ብቃት እና ወኔ በጎጆ ፓኬጅ በ350 ብር ይከታተሉ! 

እናሸንፈለን ድሉን እናያለን!

የፓሪስ ኦሎምፒክስን በ350 ብር በጎጆ ፓኬጅ ይከታተሉ! ከታች ያለውን ሊንክ በመጫን ዛሬውኑ ደንበኝነትዎን ያራዝሙ!
👇
https://mydstv.onelink.me/vGln/dg1

#ParisOlympics #2024Olympics #ሁሉምያለውእኛጋርነው #DStvEthiopia
TIKVAH-SPORT
" አለምአቀፍ የኦሎምፒክ ደንቦች ተጥሰዋል " ኃይሌ ገብረ ሥላሴ ሻለቃ አትሌት ኃይሌ ገብረ ሥላሴ የኢትዮጵያ ኦሎምፒክ ኮሚቴ በቅርቡ በዝግ ባደረገው ምርጫ አለምአቀፍ ህጎችን መጣሱን በመግለፅ " ህግ መከበር አለበት " ሲል አስተያየቱን ሰጥቷል። በኦሎምፒክ ኮሚቴው ምክትል ፕሬዝዳንት ሆኖ የተመረጠው ሻለቃ አትሌት ኃይሌ ገብረ ሥላሴ " የኦሎምፒክ ኮሚቴው መሪዎች ስራ መልቀቅ ከነበረብን ከሶስት አመታት…
“ በይፋ ራሴን ከኦሎምፒክ ኮሚቴ አግልያለሁ “ ሻለቃ ኃይሌ ገብረ ሥላሴ

“ የተከበሩ ዶክተር አሸብር የትም ሂዱ ብለውናል የትም እንሄዳለን “

የኢትዮጵያ ኦሎምፒክ ኮሚቴ አባል የነበረው ሻለቃ ኃይሌ ገብረ ሥላሴ በወረቀት ላይ ብቻ ከተካተትኩበት የኦሎምፒክ የኮሚቴ አባልነት በይፋ መልቀቄን ህዝብ ይወቅልኝ ሲል ተናግሯል።

አሁን ያለው የኢትዮጵያ ኦሎምፒክ ኮሚቴ አባል የስራ ዘመኑ ሊጠናቀቅ ስምንት ወይም ዘጠኝ ወራት እንደሚቀሩት የገለፀው ኃይሌ " እኔ በወረቀት ላይ ብኖርም ጥዬ የወጣሁት ግን ከቶኪዮ ኦሎምፒክ በፊት ነው " ብሏል።

ከሶስት አመታት በፊት ከአባልነት መልቀቁን ለህዝብ ያላሳወቀው የባሰ ብጥብጥ ውስጥ እንዳይገባ በመስጋት መሆኑን ሻለቃ ኃይሌ ገብረ ሥላሴ ከሸገር ኤፌ ኤም ጋር በነበረው ቆይታ ገልጿል።

" በድጋሜ ያለ አግባብ ሌላ ምርጫ ማድረግ እና ሌላ ስህተት ግን ተቀባይነት የለውም ያንጊዜ ማድረግ የነበረብኝ ነው አሁን ከአባልነት መልቀቄን በይፋ አሳውቃለሁ።" ሲል ሻለቃ ኃይሌ ገብረ ሥላሴ ተናግሯል።

ሻለቃ ኃይሌ ገብረ ሥላሴ አያይዞም በቅርቡ በዝግ በተደረገው ምርጫ ጋር በተያያዘ የተነሳውን ውዝግብ ለአዲሷ የባህል እና ስፖርት ሚኒስቴር ወ/ሮ ሸዊት ሻንካ አቅርበው መልስ እየተጠበቀ መሆኑን አስረድቷል።

" የተከበሩ ዶክተር አሸብር የትም ሂዱ ብለውናል የትም እንሄዳለን " ያለው ኃይሌ " በኋላ ግን ለምን ሄዳችሁ ለምን ይህንን አደረጋችሁ እንዳይሉ እፈራለሁ ፣ እንኳን ይሄን 42 ኪ.ሜ በሞት እና በህይወት ውስጥ ሆነን ሮጠናል " በማለት ተናግሯል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
TIKVAH-SPORT
" ደጋፊው ግሪንውድን ከፈለገ ገንዘብ ያዋጣ " የጣልያኑ ክለብ ላዝዮ ፕሬዝዳንት የሆኑት ክላውዲዮ ሎቲቶ የክለቡ ደጋፊ ለተጨዋች ፊርማ ገንዘብ መክፈል እንዳለበት ገልጸዋል። ግሪንውድን ከማንችስተር ዩናይትድ ለማስፈረም እያደረጉ ስለሚገኙት ጥረት የተናገሩት ክላውዲዮ ሎቲቶ " ደጋፊዎች ግሪንውድን ማስፈረም ከፈለጉ ገንዘብ መክፈል አለባቸው " ሲሉ ተናግረዋል። ፕሬዚዳንቱ አያይዘውም ለግሪንውድ ዝውውር…
የላዝዮ ደጋፊዎች ፕሬዝዳንቱን ተቃውመዋል !

የጣልያን ሴርያው ክለብ ላዝዮ ደጋፊዎች የክለቡ ፕሬዝዳንት ክላውዲዮ ሎቲቶ የሰጡት አስተያየት ላይ ተቃውሟቸውን ገልጸዋል።

የላዝዮ ፕሬዝዳንት ክላውዲዮ ሎቲቶ በትላንትናው ዕለት በሰጡት አስተያየት " የክለቡ ደጋፊዎች ግሪንውድን ከማንችስተር ዩናይትድ ማስፈረም ከፈለጉ ገንዘብ መክፈል አለባቸው " ሲሉ ተናግረው ነበር።

የክለቡ ደጋፊዎች ዛሬ ቡድኑ የቅድመ ውድድር ልምምድ በሚያደርግበት ስፍራ " ለተጨዋቾች ግዢ እርዳታ " የሚል ፅሁፍ የያዘ የእርዳታ ማሰባሰቢያ ሳጥን በማስቀመጥ ተቃውመዋል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
TIKVAH-SPORT
ማርሴይ ግሪንውድን ለማስፈረም ተስማማ ! ማርሴይ እንግሊዛዊውን የፊት መስመር ተጨዋች ሜሰን ግሪንውድ ለማስፈረም ከማንችስተር ዩናይትድ ጋር ከስምምነት መድረሳቸው ተገልጿል። ማንችስተር ዩናይትድ ለተጨዋቹ ዝውውር የቀረበለትን አጠቃላይ 31 ሚልዮን ዩሮ የሚደርስ የዝውውር ሒሳብ መቀበሉ ተነግሯል። በተጨማሪም ማንችስተር ዩናይትድ ከወደፊቱ የተጨዋቹ ሽያጭ ከግማሽ በላይ የሚሆነውን ገንዘብ ለመውሰድ ከስምምነት…
ግሪንውድ ማርሴይን ለመቀላቀል ተስማማ !

እንግሊዛዊው የፊት መስመር ተጨዋች ሜሰን ግሪንውድ የፈረንሳዩን ክለብ ማርሴይ ለመቀላቀል በቃል ደረጃ ከስምምነት መድረሱ ይፋ ተደርጓል።

ማርሴይ ከሳምንት በፊት ተጫዋቹን በ31 ሚልዮን ዩሮ ለማስፈረም ከማንችስተር ዩናይትድ ጋር ከስምምነት መድረሳቸው ይታወሳል።

የ 22ዓመቱ የፊት መስመር ተጨዋች ሜሰን ግሪንውድ በቀጣይ የህክምና ምርመራውን ለማድረግ እንደሚጓዝ ተገልጿል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
ፈረንሳይ የአርጀንቲና ተጨዋቾችን ከሰሰች !

የፈረንሳይ እግርኳስ ፌዴሬሽን የአርጀንቲና ብሔራዊ ቡድን ተጨዋቾች ላይ ለአለም የእግርኳስ የበላይ ፊፋ ቅሬታ ማቅረቡን በይፋ አስታውቋል።

ፌዴሬሽኑ ቅሬታውን ለፊፋ ያቀርበው የኮፓ አሜሪካ አሸናፊው አርጀንቲና ብሔራዊ ተጨዋቾች ከድል በኋላ ባሰሙት ዝማሬ ምክንያት መሆኑ ተነግሯል።

የአርጀንቲና ብሔራዊ ቡድን ተጨዋቾች ኮፓ አሜሪካ ካሸነፉ በኋላ በጉዞ ላይ እያሉ " ለፈረንሳይ ይጫወታሉ ግን ሁሉም የመጡት ከአንጎላ ነው " እያሉ ሲዘምሩ ተሰምተው ነበር።

ተጨዋቾቹ ዝማሬውን ሲያሰሙ በኢንዞ ፈርናንዴዝ ማህበራዊ ትስስር ገፅ በቀጥታ እየተላለፈ እንደነበር ተገልጿል።

የፈረንሳይ እግርኳስ ፌዴሬሽን የአርጀንቲና ተጨዋቾች ያሰሙት ዝማሬ የዘረኝነት እና አድሏዊ የሆነ ተቀባይነት የሌለው ነው በማለት አውግዟል።

አርጀንቲና ፈረንሳይን በ2022 አለም ዋንጫ ፍፃሜ ጨዋታ ስትረታት የአርጀንቲና ደጋፊዎች ይህንን ዝማሬ በተመሳሳይ ሲያሰሙ ነበር።

በቅርቡ በተጠናቀቀው አውሮፓ ዋንጫ ውድድር ፈረንሳይ ያሳተፈቻቸው አስራ አራት ተጨዋቾቿ የአፍሪካ የዘር ሀረግ ያላቸው ናቸው።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
TIKVAH-SPORT
ፈረንሳይ የአርጀንቲና ተጨዋቾችን ከሰሰች ! የፈረንሳይ እግርኳስ ፌዴሬሽን የአርጀንቲና ብሔራዊ ቡድን ተጨዋቾች ላይ ለአለም የእግርኳስ የበላይ ፊፋ ቅሬታ ማቅረቡን በይፋ አስታውቋል። ፌዴሬሽኑ ቅሬታውን ለፊፋ ያቀርበው የኮፓ አሜሪካ አሸናፊው አርጀንቲና ብሔራዊ ተጨዋቾች ከድል በኋላ ባሰሙት ዝማሬ ምክንያት መሆኑ ተነግሯል። የአርጀንቲና ብሔራዊ ቡድን ተጨዋቾች ኮፓ አሜሪካ ካሸነፉ በኋላ በጉዞ ላይ…
የቼልሲ ተጨዋቾች ኢንዞ ፈርናንዴዝን ተቃወሙ !

የአርጀንቲና ብሔራዊ ቡድን ተጨዋቾች ያሰሙት ዝማሬ በምዕራብ ለንደኑ ክለብ ቼልሲ የሚጫወቱ ፈረንሳዊ ተጨዋቾችን ማበሳጨቱ ተገልጿል።

ፈረንሳዊ የቼልሲ ተጨዋቾችን ያበሳጨው በተለይም ዝማሬው በቡድን አጋራቸው ኢንዞ ፈርናንዴዝ ማህበራዊ ትስስር ገፅ መሰራጨቱ እንደሆነ ተነግሯል።

ፈረንሳዊው ተጨዋች ዊስሌይ ፎፋና በ " X " ማህበራዊ ትስስር ገፁ " እግርኳስ በ2024 ዘረኝነት ያልተከለከለበት " ሲል ብስጭቱን ገልጿል።

ፈረንሳዊ የሆኑት የቼልሲ ተጨዋቾች አክሴል ዲሳሲ ፣ ማሎ ጉስቶ እና ዊስሌይ ፎፋና አሁን ላይ በኢንስታግራም የማህበራዊ ትስስር ገፅ ኢንዞ ፈርናንዴዝን " Unfollow " አድርገዋል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
TIKVAH-SPORT
" ኒኮ ዊሊያምስን የማስፈረም አቅም አለን " ላፖርታ የካታላኑ ክለብ ባርሴሎና ፕሬዝዳንት ሁዋን ላፖርታ ክለባቸው አሁን ላይ በአውሮፓ ዋንጫው ጥሩ እንቅስቃሴ በማድረግ ላይ የሚገኘውን ኒኮ ዊሊያምስ ማስፈረም እንደሚችል ገልጸዋል። ኒኮ ዊሊያምስን በጣም አደንቀዋለሁ በማለት የገለፁት ፕሬዝዳንት ሁዋን ላፖርታ " ባርሴሎና በአሁን ሰዓት እሱን የማስፈረም አቅም አለው " ብለዋል። የ 21ዓመቱ የፊት መስመር…
ኒኮ ዊሊያምስ ባርሴሎናን መቀላቀል ይፈልጋል !

ስፔናዊው የአትሌቲክ ቢልባኦ የፊት መስመር ተጨዋች ኒኮ ዊሊያምስ በቀጣይ የካታላኑን ክለብ ባርሴሎና መቀላቀል እንደሚፈልግ ተገልጿል።

በርካታ ታላላቅ ክለቦች ለማስፈረም እየተመለከቱት የሚገኘው ተጨዋቹ ቀጣይ ማረፍያውን ለመምረጥ ከተገደደ ለባርሴሎና ቅድሚያ እንደሚሰጥ ተነግሯል።

የእንግሊዝ ፕርሚየር ሊግ ክለቦች አርሰናል እና ቼልሲ አሁንም ኒኮ ዊሊያምስን ማስፈረም እንደሚፈልጉ ተገልጿል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
TIKVAH-SPORT
የቼልሲ ተጨዋቾች ኢንዞ ፈርናንዴዝን ተቃወሙ ! የአርጀንቲና ብሔራዊ ቡድን ተጨዋቾች ያሰሙት ዝማሬ በምዕራብ ለንደኑ ክለብ ቼልሲ የሚጫወቱ ፈረንሳዊ ተጨዋቾችን ማበሳጨቱ ተገልጿል። ፈረንሳዊ የቼልሲ ተጨዋቾችን ያበሳጨው በተለይም ዝማሬው በቡድን አጋራቸው ኢንዞ ፈርናንዴዝ ማህበራዊ ትስስር ገፅ መሰራጨቱ እንደሆነ ተነግሯል። ፈረንሳዊው ተጨዋች ዊስሌይ ፎፋና በ " X " ማህበራዊ ትስስር ገፁ " እግርኳስ…
ቼልሲ ምርመራ መጀመሩ ተገለጸ !

የምዕራብ ለንደኑ ክለብ ቼልሲ ተቃውሞ የቀረበበትን የአርጀንቲናውን የመሐል ሜዳ ተጨዋቻቸው ኢንዞ ፈርናንዴዝ የቪዲዮ ቅጂ በመመርመር ላይ መሆናቸው ተገልጿል።

ሰማያዊዎቹ ጉዳዩን በቁምነገር በመያዝ በምርመራ ላይ መሆናቸው ሲዘገብ ከምርመራው በኋላ ውሳኔ ያሳልፋሉ ተብሎ እንደሚጠበቅ ተነግሯል።

በምዕራብ ለንደኑ ክለብ ቼልሲ ከስድስት በላይ ፈረንሳዊ ተጨዋቾች ይገኛሉ።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
መልካም ዕድል!
ከፍ የተደረጉ ኦዶችን አይተዋል ? እንግዲያውስ ተወራረዱባቸው!
Dinamo Batumi - Ludogorets
ለተሻለ ውርርድ ቤቲካን ይጠቀሙ! አሁኑኑ Betika.et ላይ /በቴሌግራም ቦታችን - @BetikaETBot ይወራረዱ!
Forwarded from HEY Online Market
•PlayStation 5, 73,000 Birr
•Playstaion 5 Slim, 78,000 Birr

•PlayStation 4 Slim, 35,000 Birr
•PlayStation 4 Pro, 43,000 Birr

•Playstaion portal, 35,000 Birr
•Meta Quest 2, 55,000 Birr
•Meta Quest 3, 83,000 Birr

Contact
0953964175 @heymobile

@heyonlinemarket
TIKVAH-SPORT
ቼልሲ ምርመራ መጀመሩ ተገለጸ ! የምዕራብ ለንደኑ ክለብ ቼልሲ ተቃውሞ የቀረበበትን የአርጀንቲናውን የመሐል ሜዳ ተጨዋቻቸው ኢንዞ ፈርናንዴዝ የቪዲዮ ቅጂ በመመርመር ላይ መሆናቸው ተገልጿል። ሰማያዊዎቹ ጉዳዩን በቁምነገር በመያዝ በምርመራ ላይ መሆናቸው ሲዘገብ ከምርመራው በኋላ ውሳኔ ያሳልፋሉ ተብሎ እንደሚጠበቅ ተነግሯል። በምዕራብ ለንደኑ ክለብ ቼልሲ ከስድስት በላይ ፈረንሳዊ ተጨዋቾች ይገኛሉ።…
“ ለተፈጠረው ነገር ከልብ ይቅርታ እጠይቃለሁ “ ኢንዞ ፈርናንዴዝ

አርጀንቲናዊው የቼልሲ የመሐል ሜዳ ተጨዋች ኢንዞ ፈርናንዴዝ በማህበራዊ ትስስር ገፁ ስለ ተሰራጨው ቪድዮ ከልብ ይቅርታ መጠየቅ እንደሚፈልግ ተናግሯል።

" በኢንስታግራም ገፄ ለተሰራጨው የደስታ አገላለፅ ዝማሬ ቪዲዮ ከልብ ይቅርታ እጠይቃለሁ " ሲል የገለፀው ኢንዞ ፈርናንዴዝ ዝማሬው አፀያፊ ቃላትን ይዟል ለነዚህ ቃላት ምንም ሰበብ የለም ብሏል።

" ሁልጊዜም ከእንደዚህ አይነት ጉዳዮች በተቃራኒ ነው የምቆመው ቪዲዮው እና ቃላቶቹ የእኔን ባህሪ እና እምነት እያንፀባርቁም ከልብ አዝኛለሁ " ሲል ኢንዞ ፈርናንዴዝ ጨምሮ ተናግሯል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
ሊዮኔል ሜሲ በጉዳት ከሜዳ ይርቃል !

አርጀንቲናዊው የፊት መስመር ተጨዋች ሊዮኔል ሜሲ ባጋጠመው ጉዳት ምክንያት ላልተወሰነ ጊዜ ከሜዳ እንደሚርቅ ክለቡ ኢንተር ሚያሚ ይፋ አድርጓል።

ሊዮኔል ሜሲ አርጀንቲና ሻምፒዮን በሆነችበት የኮፓ አሜሪካ ፍፃሜ ውድድር ጉዳት በቀኝ እግሩ ላይ ጉዳት አጋጥሞት ተቀይሮ መውጣቱ አይዘነጋም።

ኢንተር ሚያሚ ሊዮኔል ሜሲ ወደ ሜዳ የሚመለስበት ጊዜ በእሱ የማገገም ፍጥነት እንደሚሆን የገለፀ ሲሆን የክለቡ አሰልጣኝ ታታ ማርቲኖ በበኩላቸው ከቀጣይ ሁለት ጨዋታዎች ውጪ መሆኑን አረጋግጠዋል።

ኢንተር ሚያሚ ነገ ሌሊት ከቶሮንቶ እንዲሁም ቅዳሜ ሌሊት ከቺጋጎ የአሜሪካ ሜጀር ሊግ ሶከር ጨዋታውን የሚያደርግ ይሆናል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
ጁድ ቤሊንግሀም ቀዶ ጥገና ያስፈልገዋል !

እንግሊዛዊው የሎስ ብላንኮዎቹ የመሐል ሜዳ ተጨዋች ጁድ ቤሊንግሀም የትከሻ ቀዶ ጥገና ሊያደርግ እንደሚችል ተገልጿል።

ሪያል ማድሪዶች ቀኑ ይዋል ይደር እንጂ እንግሊዛዊው አማካይ ጁድ ቤሊንግሀም የትከሻ ቀዶ ጥገናውን ማድረግ እንደሚያስፈልገው እንደሚያውቁ ተገልጿል።

ጁድ ቤሊንግሀም የትከሻ ቀዶ ጥገናውን የሚያደርግ ከሆነ ከሁለት እስከ ሶስት ወራት ከሜዳ ሊርቅ እንደሚችል ተነግሯል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
ምባፔ ከቡድኑ ጋር ወደ አሜሪካ አይቀናም !

ፈረንሳዊው የፊት መስመር ተጨዋች ኪሊያን ምባፔ ከሪያል ማድሪድ የቡድን ስብስብ ጋር ለቅድመ ውድድር ዝግጅት ወደ አሜሪካ እንደማያመራ ተገልጿል።

ሪያል ማድሪድ ኪሊያን ምባፔ ከአታላንታ ጋር በሚደረጉት የአውሮፓ ሱፐር ካፕ ጨዋታ ዝግጁ እንዲሆን እንደሚፈልጉ ተነግሯል።

ሪያል ማድሪድ በአሜሪካ በሚኖረው የዝግጅት ቆይታ ከባርሴሎና ፣ ቼልሲ እና ኤሲ ሚላን ጋር የወዳጅነት ጨዋታዎች ያደርጋል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
2024/10/03 23:18:01
Back to Top
HTML Embed Code: