Telegram Web Link
#EURO2024

ስፔናዊው የፊት መስመር ተጨዋች ላሚን ያማል በአውሮፓ ዋንጫ ውድድር ግማሽ ፍፃሜ ጨዋታ የሚሳተፍ በእድሜ ትንሹ ተጨዋች በመሆን አዲስ ታሪክ ይፅፋል።

የ 16ዓመቱ የፊት መስመር ተጨዋች ላሚን ያማል በታላላቅ ኢንተርናሽናል ውድድሮች የተሳተፈ በእድሜ ትንሹ ተጨዋች በመሆንም የፔሌን ሪከርድ ይሰብራል።

ፔሌ እ.ኤ.አ 1958 በ17 አመቱ በአለም ዋንጫ ውድድር ግማሽ ፍፃሜ በመሳተፍ ባለታሪክ ተጨዋች ነበር።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
ሻኪራ የኮፓ አሜሪካ ፍፃሜን ታደምቃለች !

በታላላቅ ኢንተርናሽናል ውድድሮች ባቀረበቻቸው ታሪካዊ ዜማዎች የምትታወቀው ኮሎምቢያዊቷ አርቲስት ሻኪራ የኮፓ አሜሪካ ውድድር ፍፃሜን ታደምቃለች።

የ 47ዓመቷ አርቲስት ሻኪራ በእድሜ አንጋፋ ከሆኑ የስፖርት ውድድሮች አንዱ በሆነው የኮፓ አሜሪካ ውድድር የምታቀነቅን የመጀመሪያዋ አርቲስት እንደምትሆን ተገልጿል።

የኮፓ አሜሪካ ውድድር ፍፃሜ ጨዋታ የፊታችን እሁድ ሌሊት 9:00 ሰዓት 54,000 ደጋፊዎች በሚይዘው ሀርድ ሮክ ስታዲየም ይደረጋል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
TIKVAH-SPORT
ማርሴይ ሜሰን ግሪንውድን ማስፈረም ይፈልጋል ! ጣልያናዊውን አሰልጣኝ ሮቤርቶ ዲ ዘርቢን በአሰልጣኝነት የሾመው የፈረንሳዩ ክለብ ማርሴይ ሜሰን ግሪንውድን ከማንችስተር ዩናይትድ ለማስፈረም ንግግር መጀመሩ ተገልጿል። ማርሴይ በተጨዋቹ ዝውውር ዙሪያ ማንችስተር ዩናይትድን ማነጋገር መጀመራቸው የተገለፀ ሲሆን እስካሁን በዝውውር ሒሳብ ዙሪያ መደራደር እንዳልጀመሩ ተጠቁሟል። የ 22ዓመቱ የፊት መስመር…
ማርሴይ ግሪንውድን ለማስፈረም ተስማማ !

ማርሴይ እንግሊዛዊውን የፊት መስመር ተጨዋች ሜሰን ግሪንውድ ለማስፈረም ከማንችስተር ዩናይትድ ጋር ከስምምነት መድረሳቸው ተገልጿል።

ማንችስተር ዩናይትድ ለተጨዋቹ ዝውውር የቀረበለትን አጠቃላይ 31 ሚልዮን ዩሮ የሚደርስ የዝውውር ሒሳብ መቀበሉ ተነግሯል።

በተጨማሪም ማንችስተር ዩናይትድ ከወደፊቱ የተጨዋቹ ሽያጭ ከግማሽ በላይ የሚሆነውን ገንዘብ ለመውሰድ ከስምምነት እንደደረሱ ተዘግቧል።

በሁለቱ ክለቦች መካከል የተደረሰው ስምምነት እስካሁን የሜሰን ግሪንውድን ይሁንታ አለማግኘቱ ተጠቁሟል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
ተጀመረ

ስፔን 0 - 0 ፈረንሳይ

- አፍንጫው ላይ ባጋጠመው ጉዳት ምክንያት ግጭት መከላከያ ማክስ ሲያደርግ የነበረው ኪሊያን ምባፔ ዛሬ ያለ ማስክ በመጫወት ላይ ይገኛል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
8 ' ስፔን 0 - 1 ፈረንሳይ

ሙኣኒ

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
20 ' ስፔን 1 - 1 ፈረንሳይ

ያማል              ሙኣኒ


@tikvahethsport     @kidusyoftahe
25 ' ስፔን 2 - 1 ፈረንሳይ

ያማል              ሙኣኒ
ኦልሞ


@tikvahethsport     @kidusyoftahe
32 ' ስፔን 2 - 1 ፈረንሳይ

ያማል              ሙኣኒ
ኦልሞ

- የ 16ዓመቱ ያሚን ያማል በአውሮፓ ዋንጫ ውድድር ታሪክ በእድሜ ትንሹ ግብ አስቆጣሪ በመሆን አዲስ ታሪክ ፅፏል።

- ፈረንሳይ በአውሮፓ ዋንጫ ውድድሩ የመጀመሪያ ግባቸውን በጨዋታ ማስቆጠር ችለዋል።

- በውድድሩ ፈረንሳይ ባለፉት ጨዋታዎች ያስቆጠረቻቸው ሶስት ግቦች ሁለቱ በራስ ላይ የተቆጠሩ አንዱ ደግሞ በፍፁም ቅጣት ምት የተቆጠረ ነው።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
የእረፍት ሰዓት !

በአውሮፓ ዋንጫ ግማሽ ፍፃሜ ስፔን ከ ፈረንሳይ ጋር እያደረጉ የሚገኙትን ጨዋታ 2ለ1 በሆነ ውጤት እየመሩ ወደ መልበሻ ቤት አምርተዋል።

የስፔንን ግቦች ላሚን ያማል እና ኦልሞ ሲያስቆጥሩ ኮሎ ሙኣኒ የፈረንሳይን ግብ ከመረብ አሳርፏል።

🟨 የቢጫ ካርድ የተመለከቱ ተጫዋቾች እነማን ናቸው ?

- በመጀመሪያው አጋማሽ በስፔን በኩል ጄሱስ ናቫስ የማስጠንቀቂያ ካርድ ተመልክቷል።

የጨዋታው የኳስ ቁጥጥር ምን ይመስላል ?

- በመጀመሪያው አጋማሽ ስፔን 55% - 45% የኳስ ቁጥጥር ብልጫ ነበራቸው።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
ስፔን ለአውሮፓ ዋንጫ ፍፃሜ ደረሰች !

የስፔን ብሔራዊ ቡድን ከፈረንሳይ ብሔራዊ ቡድን ጋር ያደረጉትን የአውሮፓ ዋንጫ ግማሽ ፍፃሜ ጨዋታ 2ለ1 በሆነ ውጤት በማሸነፍ ለፍፃሜ መድረሳቸውን አረጋግጠዋል።

የስፔንን ግቦች ላሚን ያማል እና ዳኒ ኦልሞ ሲያስቆጥሩ ኮሎ ሙኣኒ የፈረንሳይን ግብ ከመረብ አሳርፏል።

የስፔን ብሔራዊ ቡድን ተጨዋች ዳኒ ኦልሞ በውድድሩ ሶስተኛ ግቡን በማስቆጠር ከፍተኛ ግብ አስቆጣሪ መሆን ችሏል።

ስፔን የአውሮፓ ዋንጫ ፍፃሜ ጨዋታዋን የፊታችን እሁድ ከኔዘርላንድ እና እንግሊዝ አሸናፊ ጋር የምታደርግ ይሆናል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
Forwarded from HEY Online Market
Play More and Spend less!

•PS4 Slim, 34,999 Birr
•PS4 PRO, 41,999 Birr
•Original Controller 6,499 Birr

Contact Us
0953964175 @heymobile

@heyonlinemarket
መልካም ዕድል!
ከፍ የተደረጉ ኦዶችን አይተዋል ? እንግዲያውስ ተወራረዱባቸው!
Netherlands - England
ለተሻለ ውርርድ ቤቲካን ይጠቀሙ! አሁኑኑ Betika.et ላይ /በቴሌግራም ቦታችን - @BetikaETBot ይወራረዱ!
" ዋንጫውን በድጋሜ ለማሸነፍ እንጥራለን " ሜሲ

የአርጀንቲና ብሔራዊ ቡድን ትላንት ሌሊት ከካናዳ ብሔራዊ ቡድን ጋር ያደረገውን የኮፓ አሜሪካ ግማሽ ፍፃሜ ጨዋታ 2ለ0 በማሸነፍ ለፍፃሜ አልፈዋል።

በጨዋታው ለአርጀንቲና አንድ ግብ ያስቆጠረው ሊዮኔል ሜሲ ኮፓ አሜሪካ ከባድ ውድድር መሆኑን ከጨዋታው በኋላ በሰጠው አስተያየት ተናግሯል።

" ኮፓ አሜሪካ በጣም ከባድ ውድድር ነው ከአስቸጋሪ ሙቀት ጋር ከባድ ነበር ፣ በድጋሜ ለፍፃሜ መድረሳችን የሚያስደስት ነው ቡድኑ እየሰራ ያለው ነገር አስደናቂ ነገርነው ነው።" ሲል ሜሲ ተናግሯል።

ለኮፓ አሜሪካ ፍፃሜ መብቃት ቀላል አለመሆኑ አያይዞ የገለፀው ሊዮኔል ሜሲ " ቡድኑ አራተኛ ፍፃሜው ነው በቀጣይ በድጋሜ ሻምፒዮን ለመሆን ከፍተኛ ጥረት ማድረግ አለብን " ብሏል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
" አውሮፓ ዋንጫ ለእኔ ጥሩ አልነበረም " ምባፔ

ፈረንሳዊው የፊት መስመር ተጨዋች ኪሊያን ምባፔ የአውሮፓ ዋንጫ ውድድር ለእሱ ጥሩ እንዳልነበረ ከቡድኑ ስንብት በኋላ በሰጠው አስተያየት ተናግሯል።

" የአውሮፓ ዋንጫውን ማሸነፍ ፈልጌ ነበር " የሚለው ኪሊያን ምባፔ በእግርኳስ አንድ ጊዜ ጥሩ ትሆናለህ ሌላ ጊዜ ደግሞ ተቃራኒ ይህ አውሮፓ ዋንጫ ለእኔ ጥሩ አልነበረም ሲል ተደምጧል።

በቀጣይ ብዙ ነገሮች እንደሚጠብቁት ያስታወሰው ኪሊያን ምባፔ " አሁን ራሴን የተወሰነ ማዝናናት እና ለአዲሱ ህይወቴ መዘጋጀት አለብኝ " ብሏል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
" የፍፃሜ ተፋላሚያችን ማንም ቢሆን ለውጥ የለውም " ሮድሪ

የስፔን ብሔራዊ ቡድን የመሐል ሜዳ ተጨዋች ሮድሪ በአውሮፓ ዋንጫ ፍፃሜ ጨዋታ ጠንካራ ተጋጣሚ እንደሚጠብቃቸው ከምሽቱ ጨዋታ በኋላ በሰጠው አስተያየት ተናግሯል።

" የፍፃሜ ተፋላሚያችን ቡድን ማንም ይሁን ማን ለውጥ የለውም " ያለው ሮድሪ ነገርግን በፍፃሜው የሚጠብቀን ተጋጣሚ ጠንካራ እንደሚሆን እናውቃለን ብሏል።

በላሚን ያማል እንቅስቃሴ መኩራቱን የገለፀው ሮድሪ በቀጣይ እሱ የሚጠብቀው የወደፊት እግርኳስ ህይወት አስደናቂ ነው በማለት ተናግሯል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
ባርሴሎና ብዙ የካሳ ክፍያ ያገኛል !

የካታላኑ ክለብ ባርሴሎና በዘንድሮው የአውሮፓ ዋንጫ ውድድር ከዩኤፋ ለለቀቃቸው ተጨዋቾች የሚያገኘው የካሳ ክፍያ ከዚህ በፊት ካገኘው የበለጠ እንደሚሆን ተገልጿል።

የባርሴሎናን አራት ተጨዋቾች የያዘችው ስፔን ለአውሮፓ ዋንጫ ፍፃሜ መድረሷን ተከትሎ ክለቡ ከአውሮፓ እግርኳስ ማህበር ከ3.1 ሚልዮን ዩሮ በላይ እንደሚያገኝ ተነግሯል።

የአውሮፓ እግርኳስ ማህበር ተጨዋቾቹ በአውሮፓ ዋንጫ ውድድር በቆዩበት ቀን ልክ በአንድ ቀን 10,000 ዩሮ ለክለባቸው ካሳ የሚከፍል ይሆናል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
TIKVAH-SPORT
Photo
" ጥያቄ ጠይቀህ መልስ የማታገኝለት ሀገር የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን " አትሌት ጽጌ ገ/ሰላማ

ኢትዮጵያዊቷ አትሌት ጽጌ ገ/ሰላማ በቀጣዩ የፓሪስ ኦሎምፒክ ውድድር አትሌት ምርጫ ላይ ላቀረበችው ቅሬታ ምላሽ አለማግኘቷን በማህበራዊ ትስስር ገጿ ገልፃለች።

አትሌቷ በ 5000 ሜትር 14፡18 የሆነ የአመቱ ፈጣን ሰዓት ማስመዝገቧን ገልፃ ወቅታዊ ብቃቴ ታይቶ ሁለተኛ ፊልዴ ተደርጎ እንድመረጥ ስትል የኢትዮጵያ ኦሎምፒክ ኮሚቴን በደብዳቤ ጠይቃ እንደነበር አሳውቃለች።

አትሌቷ ያቀረበችው ቅሬታ ተቀባይነት አለማግኘቱን በማህበራዊ ትስስር ገጿ ያሳወቀች ሲሆን " ተገቢ ጥያቄ ጠይቀህ መልስ የማታገኝለት ሀገር የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ፍትህ እፈልጋለሁ " ስትል መልዕክቷን አስፍራለች።

የኢትዮጵያ ኦሎምፒክ ኮሚቴ ፕሬዝዳንት ዶ/ር አሸብር ወ/ጊዮርጊስ ትላንት በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ " ኢትዮጵያን የሚወክሉ አትሌቶች የመጨረሻ ዝርዝር ሰኞ ዕለት ለአለም አቀፉ ኦሎምፒክ ኮሚቴ ተልኳል።"ሲሉ አረጋግጠዋል።

ፕሬዝዳንቱ አያይዘውም " ለቀሩ አትሌቶች ልባቸው እንዳይሰበር እንመኛለን ይቅርታም እንጠይቃለን።"ሲሉ ተናግረዋል።

አትሌት ጽጌ ገ/ሰላማ የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ባሳወቀው የኦሎምፒክ ተሳታፊ አትሌቶች ዝርዝር ውስጥ በ10000 ሜትር መመረጧ ይታወሳል።

የ 2024 የፈረንሳይ ፓሪስ ኦሎምፒክ ውድድር ሊጀምር አስራ ስድስት ቀናቶች ቀርተውታል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
TIKVAH-SPORT
አርሰናል ግብ ጠባቂ ለማስፈረም አነጋግሯል ! የሰሜን ለንደኑ ክለብ አርሰናል እንግሊዛዊውን ግብ ጠባቂ ዳንኤል ቤንትሌይ ለማስፈረም ክለቡ ዎልቭስን ማነጋገራቸው ተገልጿል። በአሰልጣኝ ሚኬል አርቴታ የሚመሩት መድፈኞቹ ተጨዋቹ ለአርሰናል ጥሩ አማራጭ ግብ ጠባቂ ይሆናል የሚል እምነት እንዳላቸው ተነግሯል። ዎልቭስ የ 31ዓመቱን ግብ ጠባቂ ዳንኤል ቤንትሌይ ስለመሸጥ የሚያስበው ጥሩ የሚባል የዝውውር…
አርሰናል ለዎልቭስ ስንት አቅርቦ ነበር ?

የሰሜን ለንደኑ ክለብ አርሰናል እንግሊዛዊውን ግብ ጠባቂ ዳንኤል ቤንትሌይ ከዎልቭስ ለማስፈረም የመጀመሪያ የዝውውር ሒሳብ አቅርበው ውድቅ ተደርጎባቸዋል።

መድፈኞቹ ዳንኤል ቤንትሌይን ለማስፈረም አቅርበው ውድቅ የሆነባቸው ሒሳብ 50,000 ፓውንድ እንደነበር ለዎልቭስ ቅርብ የሆኑ ምንጮች ዘግበዋል።

በአሰልጣኝ ሚኬል አርቴታ የሚመሩት አርሰናሎች የ 30ዓመቱን ግብ ጠባቂ ዳንኤል ቤንትሌይ ለክለቡ ሶስተኛ አማራጭ ግብ ጠባቂ አድርገው ለማስፈረም እየሰሩ ይገኛሉ።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
ሙለር ራሱን ከብሔራዊ ቡድኑ ሊያገል ነው !

የጀርመን ብሔራዊ ቡድን የመሐል ሜዳ ተጨዋች ቶማስ ሙለር ራሱን ከብሔራዊ ቡድኑ ለማግለል ከውሳኔ መድረሱ ተገልጿል።

የ 34ዓመቱ ተጨዋች ቶማስ ሙለር ለጀርመን ብሔራዊ ቡድን አንድ መቶ ሰላሳ አንድ ጨዋታዎችን ማድረግ ችሏል።

ቶማስ ሙለር ከጀርመን ብሔራዊ ቡድን ጋር አንድ የአለም ዋንጫን ማሸነፍ ችሏል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
2024/09/30 22:29:25
Back to Top
HTML Embed Code: