Telegram Web Link
TIKVAH-SPORT
ኢትዮጵያ የምድብ ተጋጣሚዎቿን አውቃለች ! የ2025 የሞሮኮ አፍሪካ ዋንጫ ውድድር ማጣሪያ ምድብ ድልድል ከደቂቃዎች በፊት በደቡብ አፍሪካ ጁሀንስበርግ በተደረገ የእጣ ማውጣት ስነ-ስርዓት ይፋ ተደርጓል። በዚህም መሰረት የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን በምድብ ስምንት - #ታንዛኒያ - #ጊኒ እና - #ኮንጎ ጋር ተደልድሏል። በደርሶ መልስ በሚደረግ ጨዋታ የምድቡን አንደኛ እና ሁለተኛ ደረጃ ይዘው…
ዋልያዎቹ የመጀመሪያ ጨዋታቸውን ከሜዳ ውጪ ያደርጋሉ !

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን የሞሮኮ አፍሪካ ዋንጫ ማጣሪያ የመጀመሪያ ጨዋታውን ከሜዳው ውጪ ከታንዛኒያ አቻው ጋር እንደሚያደርግ ይፋ ሆኗል።

በምድብ ስምንት ከታንዛኒያ ፣ ጊኒ እና ኮንጎ ጋር የተደለደለው ብሔራዊ ቡድኑ የምድብ ሁለተኛ ጨዋታውን በሜዳው የሚያደርግ ይሆናል።

የኢትዮጵያ መርሐ ግብሮች ምን ይመስላሉ ?

- የምድብ የመጀመሪያ ጨዋታ :- ታንዛኒያ ከ ኢትዮጵያ

- የምድብ ሁለተኛ ጨዋታ :- ኢትዮጵያ ከ ከ ኮንጎ

- የምድብ ሶስተኛ ጨዋታ :- ጊኒ ከ ኢትዮጵያ

- የምድብ አራተኛ ጨዋታ :- ኢትዮጵያ ከ ጊኒ

- የምድብ አምስተኛ ጨዋታ :- ኢትዮጵያ ከ ታንዛኒያ

- የምድብ ስድስተኛ ጨዋታ :- ኮንጎ ከ ኢትዮጵያ

* የምድብ የመጀመሪያ እና ሁለተኛ ጨዋታዎች ከወራት በኋላ ከነሐሴ 27 እስከ ጳጉሜ 5 / 2016 ዓ.ም ባሉት ቀናት የሚደረጉ ይሆናል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
ኑኖ ታቫሬዝ በውሰት ወደ ላዝዮ ሊያቀና ነው !

ያለፈውን የውድድር አመት በውሰት በኖቲንግሀም ፎረስት ቤት ያሳለፈው የአርሰናል የግራ መስመር ተከላካይ ኑኖ ታቫሬዝ በውሰት ውል ላዝዮን ሊቀላቀል መሆኑ ተገልጿል።

ላዝዮ ፖርቹጋላዊውን ተጫዋች ኑኖ ታቫሬዝ በውሰት ከአርሰናል ለማስፈረም ያቀረቡት ጥያቄ ከመድፈኞቹ ተቀባይነት ማግኘቱ ተነግሯል።

በውሰት ውሉ ውስጥ 8 ሚልዮን ዩሮ በሚደርስ የዝውውር ሒሳብ በቋሚነት የማስፈረም አማራጭ እንደሚካተት ተዘግቧል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
Forwarded from WANAW SPORT
📢 ለቸኮለ ቀላል ዘዴ ከ #ዋናው!

🏃🏾‍♂ #ይምጡ#ትጥቅዎን ይውሰዱ!

📌 ለበለጠ መረጃና ትዕዛዝ 📲 09011382830910851535 እና 0913586742 ላይ ይደውሉ።

👉🏾 እንዲሁም በቴሌግራም @Wanawsales ላይ የሽያጭ ሰራተኞቻችንን በቀጥታ በማናገር ወይም በቴሌግራም ቦት @WanawSportBot ይዘዙን።

🏅 ዋናው ወደፊት...

@wanawsportwear
ኬር ስታርመር የእንግሊዝን ጨዋታ በወረቀት ይከታተላሉ !

አዲሱ የዩናይትድ ኪንግደም ጠቅላይ ሚኒስቴር ኬር ስታርመር የምሽቱን የእንግሊዝ እና ኔዘርላንድ የአውሮፓ ዋንጫ ጨዋታ በወረቀት ፅሁፍ እየቀረበላቸው እንደሚከታተሉ ተገልጿል።

ጠቅላይ ሚንስቴር ኬር ስታርመር በአሁን ሰዓት በ2024 የኔቶ አመታዊ ስብሰባ በመካፈል ላይ ሲሆኑ በስብሰባው ስልክ እና መሰል ኤሌክትሮኒክሶች መታገዳቸው ተነግሯል።

ይህንንም ተከትሎ ጠቅላይ ሚንስቴሩ የጨዋታውን ውጤቶች ሰራተኞቻቸው በወረቀት ፅሁፍ እያመጡ እንዲያስመለክቷቸው ትዕዛዝ መስጠታቸው ተገልጿል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
TIKVAH-SPORT
ኪሊያን ምባፔ መቼ አቀባበል ይደረግለታል ? በቅርቡ በይፋ ሪያል ማድሪድን የተቀላቀለው ፈረንሳዊው የፊት መስመር ተጨዋች ኪሊያን ምባፔ በክለቡ ደማቅ አቀባበል እንደሚደረግለት ተገልጿል። ሎስ ብላንኮዎቹ ለኪሊያን ምባፔ ሐምሌ 9/2016 ዓ.ም ይፋዊ አቀባበል በሳንቲያጎ በርናቦ ስታዲየም ማዘጋጀታቸው ተነግሯል። ከአውሮፓ ዋንጫው ፍፃሜ ሁለት ቀናት በኋላ በሚደረገው ይፋዊ አቀባበል ክርስቲያኖ ሮናልዶ…
ማድሪድ ለኪሊያን ምባፔ አቀባበል ያደርጋል !

ሪያል ማድሪድ በቅርቡ ወደ ቡድናቸው የቀላቀሉትን ፈረንሳዊው የፊት መስመር ተጨዋች ኪሊያን ምባፔ ቀጣይ ሳምንት ደማቅ አቀባበል እንደሚያደርጉለት ይፋ አድርገዋል።

ሎስ ብላንኮዎቹ ለኪሊያን ምባፔ ቀጣይ ሳምንት ማክሰኞ ሐምሌ 9/2016 ዓ.ም ይፋዊ አቀባበል በሳንቲያጎ በርናቦ ስታዲየም ማዘጋጀታቸውን አስታውቀዋል።

ኪሊያን ምባፔ ከይፋዊ ትውውቁ በኋላ በሳንቲያጎ በርናቦ የጋዜጣዊ መግለጫ ክፍል ከጋዜጠኞች ጋር ቆይታ እንደሚያደርግ ተገልጿል።

በኪሊያን ምባፔ የአቀባበል ስነስርዓት እስከ 80,000 የክለቡ ደጋፊዎች ሳንቲያጎ በርናቦ ስታዲየም ሊገኙ እንደሚችሉ ተዘግቧል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
TIKVAH-SPORT
ማድሪድ ለኪሊያን ምባፔ አቀባበል ያደርጋል ! ሪያል ማድሪድ በቅርቡ ወደ ቡድናቸው የቀላቀሉትን ፈረንሳዊው የፊት መስመር ተጨዋች ኪሊያን ምባፔ ቀጣይ ሳምንት ደማቅ አቀባበል እንደሚያደርጉለት ይፋ አድርገዋል። ሎስ ብላንኮዎቹ ለኪሊያን ምባፔ ቀጣይ ሳምንት ማክሰኞ ሐምሌ 9/2016 ዓ.ም ይፋዊ አቀባበል በሳንቲያጎ በርናቦ ስታዲየም ማዘጋጀታቸውን አስታውቀዋል። ኪሊያን ምባፔ ከይፋዊ ትውውቁ በኋላ በሳንቲያጎ…
ምባፔ የዘጠኝ ቁጥር ማልያ ይለብሳል !

ሪያል ማድሪዶች ለሚቀጥለው የውድድር ዘመን ለስድስት ተጨዋቾች አዲስ ቁጥር ማልያ አስተዋውቀዋል።

ፈረንሳዊው የፊት መስመር ተጨዋች ኪሊያን ምባፔ የዘጠኝ ቁጥር ማልያ እንደሚለብስ ሲገለፅ ከነገ ጀምሮ በማድሪድ የሽያጭ ሱቅ በገበያ ላይ ይቀርባልም ተብሏል።

በተጨማሪም በሚቀጥለው አመት :-

ካማቪንጋ 6 ቁጥር ፣ ቫልቬርዴ 8 ቁጥር ፣ ቹዋሜኒ 14 ቁጥር ፣ አርዳ ጉለር 15 ቁጥር እና ጄሱስ ቫሌሆ 18 ቁጥር ለብሰው እንደሚጫወቱ ይፋ ሆኗል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
TIKVAH-SPORT
አስቶን ቪላ የኩቲንሆን ኮንትራት ሊያቋርጥ ነው ! አስቶን ቪላ የብራዚላዊውን የመሐል ሜዳ ተጨዋች ፊሊፔ ኩቲንሆ ኮንትራት ለማቋረጥ በንግግር ላይ መሆናቸው ተገልጿል። ያለፈውን የውድድር አመት በውሰት በኳታሩ ክለብ አል ዱሀይሊ ያሳለፈው ፊሊፔ ኩቲንሆ በአስቶን ቪላ ቤት እስከ 2026 የሚያቆይ ኮንትራት አለው። የ 32ዓመቱ ተጨዋች ፊሊፔ ኩቲንሆ በቀጣይ ወደ ቀድሞ ክለቡ የብራዚሉ ክለብ ቫስኮ ዳጋማ…
ፊሊፔ ኩቲንሆ የቀድሞ ክለቡን ተቀላቀለ !

ብራዚላዊው የመሐል ሜዳ ተጨዋች ፊሊፔ ኩቲንሆ ከፕርሚየር ሊጉ ክለብ አስቶን ቪላ በመልቀቅ የቀድሞ ክለቡ የብራዚሉ ቫስኮ ዳጋማን ተቀላቅሏል።

ያለፈውን የውድድር አመት በውሰት በኳታሩ ክለብ አል ዱሀይሊ ያሳለፈው ፊሊፔ ኩቲንሆ የቀድሞ ክለቡን በረጅም ጊዜ የውሰት ውል መቀላቀሉ ተገልጿል።

ተጨዋቹ ከአስቶን ቪላ ጋር ያለውን ውል በማቋረጥ የቀድሞ ክለቡን ለመቀላቀል ንግግር ላይ የነበረ ቢሆንም ከደሞዝ ክፍያ ጋር በተያያዘ ባለመሳካቱ በውሰት መቀላቀሉ ተገልጿል።

የ 32ዓመቱ የመሐል ሜዳ ተጨዋች ፊሊፔ ኩቲንሆ በአስቶን ቪላ ቤት እስከ 2026 የሚያቆይ ኮንትራት አለው።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
ጁቬንቱስ ተጨዋች አስፈርመዋል !

የጣልያን ሴርያው ክለብ ጁቬንቱስ ፈረንሳዊውን የመሐል ሜዳ ተጨዋች ሄፍረን ቱራም ከኒስ ማስፈረማቸውን ይፋ አድርገዋል።

የ 23ዓመቱ የመሐል ሜዳ ተጨዋች ሄፍረን ቱራም በጁቬንቱስ እስከ 2029 የሚያቆየውን የአምስት አመት ኮንትራት መፈረሙ ተገልጿል።

ጁቬንቱስ ለተጨዋቹ ዝውውር 20 ሚልዮን ዩሮ ወጪ እንደሚያደርግ ተዘግቧል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
የእንግሊዝ ደጋፊዎች እንዲጠነቀቁ ጥሪ ቀረበላቸው !

ከሰዓታት በኋላ ተጠባቂ የአውሮፓ ዋንጫ ግማሽ ፍፃሜ ጨዋታቸውን የሚያደርጉት እንግሊዝ እና ኔዘርላንድ ብሔራዊ ቡድን ደጋፊዎች ፀብ ውስጥ መግባታቸው ተገልጿል።

ጨዋታው በሚደረግበት ዶርትመንድ ከተማ ከ100,000 በላይ የኔዘርላንድ ብሔራዊ ቡድን ደጋፊዎች እንደሚገኙ ተነግሯል።

የኔዘርላንድ ደጋፊዎች ከጨዋታው አስቀድሞ ከእንግሊዝ ብሔራዊ ቡድን ደጋፊዎች ፀብ ውስጥ መግባታቸውን እና ትንኮሳ ማድረጋቸው በማህበራዊ ሚዲያዎች ተዘዋውሯል።

በስፍራው የፀጥታ ስራውን በማገዝ ላይ የሚገኙ የዩናይትድ ኪንግደም ፖሊሶች የኔዘርላንድ ደጋፊዎች የእንግሊዝ ደጋፊዎች ላይ ጥቃት ለማድረስ እየሞከሩ እንደሚገኙ ገልጸዋል።

አምስት የእንግሊዝ ደጋፊዎች መጠነኛ ጉዳት እንዳጋጠማቸው ሲገለፅ ሌሎች ደጋፊዎች ያሉበትን ቦታ እንዲያውቁ እና በአካባቢያቸው የጀርመን ፖሊሶች መኖራቸውን እንዲያረጋግጡ ጥሪ ቀርቦላቸዋል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
ንግድ ባንክ እና ቡናማዎቹ ተጋጣሚያቸውን መቼ ያውቃሉ ?

ሀገራችን ኢትዮጵያን በመወከል በአፍሪካ ሻምፒየንስ ሊግ እና ኮንፌዴሬሽን ዋንጫ ውድድሮች የሚሳተፉት ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ እና ኢትዮጵያ ቡና የቅድመ ማጣሪያ ተጋጣሚያቸውን የሚያውቁበት ቀን ታውቋል።

ይህንንም ተከትሎ የውድድሮቹ የቅድመ ማጣሪያ ተጋጣሚዎች በነገው ዕለት ግብፅ ካይሮ በሚደረግ የዕጣ ማውጣት ስነ ስርዓት ይፋ እንደሚደረግ ተገልጿል።

በምድብ ድልድሉ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በቋት አንድ እንዲሁም ኢትዮጵያ ቡና በቋት ሁለት ይገኛሉ።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
የጨዋታ አሰላለፍ !

4:00 ኔዘርላንድ ከ እንግሊዝ

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
" አጥቅተን መጫወት ነው ፍላጎታችን " ኮማን

የኔዘርላንድ ብሔራዊ ቡድን ዋና አሰልጣኝ ሮናልድ ኮማን በምሽቱ ጨዋታ ቡድናቸው አጥቅቶ እንደሚጫወት በሰጡት አስተያየት ገልጸዋል።

" እንግሊዝ ጥሩ ተጨዋቾች አሏት ነገርግን እኛ ዛሬ አጥቅተን መጫወት ነው የምንፈልገው ፣ ጨዋታው አሰልቺ ከሆነ በእኛ ምክንያት አይሆንም።"ሲሉ ሮናልድ ኮማን ተናግረዋል።

የእንግሊዝ ብሔራዊ ቡድን አሰልጣኝ ጋሪዝ ሳውዝጌት በበኩላቸው " ለጨዋታው ጓጉተናል በሩብ ፍፃሜ ጥሩ ተጫውተናል ዛሬ የምንገጥመው ከስዊዘርላንድ የተሻለ ቡድን ነው።"ሲሉ ተደምጠዋል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
7 ' ኔዘርላንድ 1 - 0 እንግሊዝ

ሲሞንስ

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
17 ' ኔዘርላንድ 1 - 1 እንግሊዝ

ሲሞንስ ኬን

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
33 ' ኔዘርላንድ 1 - 1 እንግሊዝ

ሲሞንስ                ኬን

- ሀሪ ኬን በአውሮፓ ዋንጫ ውድድር ታሪክ በጥሎ ማለፍ ጨዋታዎች ስድስት ግቦችን ያስቆጠረ ቀዳሚው መሆን ችሏሌ።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
የእረፍት ሰዓት !

በአውሮፓ ዋንጫ ግማሽ ፍፃሜ እንግሊዝ ከ ኔዘርላንድ ጋር እያደረጉ የሚገኙትን ጨዋታ 1ለ1 በሆነ አቻ ውጤት ወደ መልበሻ ቤት አምርተዋል።

የኔዘርላንድን ግብ ዣቪ ሲሞንስ ሲያስቆጥር ሀሪ ኬን እንግሊዝን አቻ ማድረግ ችሏል።

🟨 የቢጫ ካርድ የተመለከቱ ተጫዋቾች እነማን ናቸው ?

- በመጀመሪያው አጋማሽ በኔዘርላንድ በኩል ዴንዜል ዱምፍሪስ የማስጠንቀቂያ ካርድ ተመልክቷል።

የጨዋታው የኳስ ቁጥጥር ምን ይመስላል ?

- በመጀመሪያው አጋማሽ እንግሊዝ 63% - 37% የኳስ ቁጥጥር ብልጫ ነበራቸው።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
90 ' ኔዘርላንድ 1 - 2 እንግሊዝ

ሲሞንስ                ኬን
ዋትኪንስ
                                  

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
እንግሊዝ ለአውሮፓ ዋንጫ ፍፃሜ ደረሰች !

የእንግሊዝ ብሔራዊ ቡድን ከኔዘርላንድ ብሔራዊ ቡድን ጋር ያደረጉትን የአውሮፓ ዋንጫ ግማሽ ፍፃሜ ጨዋታ 2ለ1 በሆነ ውጤት በማሸነፍ ለፍፃሜ መድረሳቸውን አረጋግጠዋል።

የእንግሊዝን የማሸነፊያ ግቦች ሀሪ ኬን እና ኦሊ ዋትኪንስ ሲያስቆጥሩ ዣቪ ሲሞንስ የኔዘርላንድን ግብ ከመረብ አሳርፏል።

ኦሊ ዋትኪንስ ለእንግሊዝ ብሔራዊ ቡድን በትልቅ ውድድሮች የመጀመሪያ ግቡን ከመረብ ማሳረፍ ችሏል።

እንግሊዝ የአውሮፓ ዋንጫ ፍፃሜ ጨዋታዋን የፊታችን እሁድ ከስፔን ብሔራዊ ቡድን ጋር የምታደርግ ይሆናል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
2024/10/01 00:16:36
Back to Top
HTML Embed Code: