Telegram Web Link
ኢትዮጵያን በኦሎምፒክ የሚወክሉ አትሌቶች ተለዩ !

የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን በቀጣዩ የ2024 ፓሪስ ኦሎምፒክ ውድድር ሀገራችን ኢትዮጵያን በሁሉም ርቀቶች የሚወክሉ አትሌቶች እና ተጠባባቂዎችን ይፋ አድርጓል።

የ10,000 ሜትር የአለም ሻምፒዮኗ አትሌት ጉዳፍ ፀጋይ በውድድሩ በሶስት ርቀቶች ( 1,500 ፣ 5,000 ፣ 10,000ሜ ) ሀገራችን ኢትዮጵያን የምትወክል ይሆናል።

አትሌት ዮሚፍ ቀጄልቻ በበኩሉ ኢትዮጵያን በ5,000ሜ እና 10,000ሜ በሁለት ርቀቶች እንደሚወክል ታውቋል።

ለመጨረሻ ጊዜ በተደረገው የቶኪዮ ኦሎምፒክ ብቸኛውን የወርቅ ሜዳልያ ለኢትዮጵያ ያስመዘገበው አትሌት ሰለሞን ባረጋ በበኩሉ በ10,000ሜ ሀገራችንን ሲወክል በ5000ሜ ተጠባባቂ ሆኖ ይጀመራል።

የሶስት ጊዜ የኦሎምፒክ ወርቅ ሜዳልያ አሸናፊው አትሌት ቀነኒሳ በቀለ ከአስራ ሁለት አመታት በኋላ ኢትዮጵያን በኦሎምፒክ ማራቶን ይወክላል።

ሙሉ የአትሌቶች ዝርዝር ከላይ በምስሉ ተያይዟል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
TIKVAH-SPORT
ሪካርዶ ካላፊዮሪ አርሰናልን መቀላቀል ይፈልጋል ! የሰሜን ለንደኑ ክለብ አርሰናል ጣልያናዊውን የቦሎኛ የተከላካይ ስፍራ ተጨዋች ሪካርዶ ካላፊዮሪ ለማስፈረም ጥረት በማድረግ ላይ መሆናቸው ተገልጿል። መድፈኞቹ ለተጨዋቹ የዝውውር ጥያቄያቸውን ማቅረባቸው የተገለፀ ሲሆን በቀጣይ ከቦሎኛ ጋር የሚስማሙ ከሆነ ተጨዋቹ አርሰናልን ለመቀላቀል እንደሚፈልግ ተነግሯል። ከአርሰናል በተጨማሪም የምዕራብ ለንደኑ…
አርሰናል ተጨዋች ለማስፈረም ተስማማ !

የሰሜን ለንደኑ ክለብ አርሰናል ጣልያናዊውን የቦሎኛ የተከላካይ ስፍራ ተጨዋች ሪካርዶ ካላፊዮሪ ለማስፈረም ከተጨዋቹ ጋር ከስምምነት መድረሱ ተገልጿል።

መድፈኞቹ ለተጨዋቹ ባቀረቡት እስከ 2029 የሚቆይ የአምስት አመት ኮንትራት ከስምምነት መድረሳቸው ተነግሯል።

አርሰናል በተጨዋቹ ዝውውር ሒሳብ ዙሪያ ከቦሎኛ ጋር ንግግር በማድረግ ላይ መሆናቸው ሲገለፅ ክለቡ 50 ሚልዮን ዩሮ የሚደርስ ክፍያ መጨየቁ ተዘግቧል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
ወልቂጤ ከተማ አመቱን በድል አጠናቀዋል !

በኢትዮጵያ ፕርሚየር ሊግ የመጨረሻ ሳምንት መርሐ ግብር ወልቂጤ ከተማ ከአዳማ ከተማ ጋር ያደረጉትን ጨዋታ 1ለ0 በሆነ ውጤት አሸንፈዋል።

የወልቂጤ ከተማን ብቸኛ የማሸነፊያ ግብ አዳነ በላይነህ ከመረብ ማሳረፍ ችሏል።

የሊጉ ደረጃቸው ምን ይመስላል ? 

7️⃣ አዳማ ከተማ :- 44 ነጥብ

1️⃣4️⃣ ወልቂጤ ከተማ:- 23 ነጥብ

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
TIKVAH-SPORT
የሲቲ እና ጂሮና የሻምፒየንስ ሊግ ተሳትፎ ሁኔታ ! በሲቲ ፉትቦል ግሩፕ ባለቤትነት የተያዙት ማንችስተር ሲቲ እና የስፔኑ ክለብ ጂሮና በሚቀጥለው የውድድር አመት በአውሮፓ ሻምፒየንስ ሊግ ውድድር የሚያሳትፋቸውን ቦታ አግኝተዋል። ክለቦቹ በተመሳሳይ ተቋም ባለቤትነት የተያያዙ መሆኑን ተከትሎ በዩኤፋ የውድድር ህግ መሰረት በሻምፒየንስ ሊግ ለመሳተፍ ማድረግ የሚጠበቅባቸው ቅድመ ሁኔታ መኖሩ ተገልጿል።…
ዩኤፋ ተመሳሳይ ባለቤት ላላቸው ክለቦች ፍቃድ ሰጠ !

የፕርሚየር ሊጉ አሸናፊ ማንችስተር ሲቲ በሚቀጥለው የውድድር አመት ከጂሮና ጋር በተመሳሳይ በአውሮፓ ሻምፒየንስ ሊግ መወዳደር እንዲችሉ እንደተፈቀደላቸው ተገልጿል።

በተጨማሪም ማንችስተር ዩናይትድ እና የፈረንሳዩ ክለብ ኒስ በቀጣይ የውድድር አመት በዩሮፓ ሊግ መወዳደር እንደሚችሉ የአውሮፓ እግርኳስ ማህበር አሳውቋል።

ክለቦቹ በአንድ ተቋም ባለቤትነት የተያዙ መሆኑን ተከትሎ በዩኤፋ ህግ መሰረት በአውሮፓ መድረክ አንድ ላይ ለመወዳደር ላይፈቀድላቸው ይችላል ሲባል እንደነበር አይዘነጋም።

አሁን ላይ የአውሮፓ እግርኳስ ማህበር ያስቀመጣቸው አማራጭ ሀሳቦች በክለብ ባለቤቶች ተቀባይነት ማግኘቱን ተከትሎ ፍቃዱን እንደሰጠ ተዘግቧል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
TIKVAH-SPORT
ዩኤፋ ተመሳሳይ ባለቤት ላላቸው ክለቦች ፍቃድ ሰጠ ! የፕርሚየር ሊጉ አሸናፊ ማንችስተር ሲቲ በሚቀጥለው የውድድር አመት ከጂሮና ጋር በተመሳሳይ በአውሮፓ ሻምፒየንስ ሊግ መወዳደር እንዲችሉ እንደተፈቀደላቸው ተገልጿል። በተጨማሪም ማንችስተር ዩናይትድ እና የፈረንሳዩ ክለብ ኒስ በቀጣይ የውድድር አመት በዩሮፓ ሊግ መወዳደር እንደሚችሉ የአውሮፓ እግርኳስ ማህበር አሳውቋል። ክለቦቹ በአንድ ተቋም ባለቤትነት…
#Update

የአውሮፓ እግርኳስ ማህበር ማንችስተር ሲቲ እና ጂሮና በሻምፒየንስ ሊግ እንዲሁም ማንችስተር ዩናይትድ እና ኒስ በዩሮፓ ሊግ እንዲወዳደሩ ፍቃድ ሰጥቷል።

ይሁን እንጂ የአውሮፓ እግርኳስ ማህበር በክለቦቹ መካከል ክልከላዎችን ያስቀመጠ ሲሆን

- ማንችስተር ዩናይትድ እና ኒስ ከሐምሌ ወር እስከ ቀጣይ 2025 መስከረም ወር በቋሚነትም ሆነ በውሰት ዝውውሮችን ማድረግ አይችሉም።

- በተመሳሳይ ማንችስተር ሲቲ እና ጂሮና በቋሚነትም ሆነ በውሰት ዝውውሮችን ማድረግ እንደማይችሉ ተገልጿል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
የጨዋታ አሰላለፍ !

1:00 ጀርመን ከ ስፔን

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
Forwarded from WANAW SPORT
💪🏾⚽️ #ዋናው ሰዓት ደርሷል! 💪🏾⚽️

🇪🇹 ዋናው ስፖርት 🤝 መቻል ስፖርት ክለብ 🇪🇹

መልካም ዕድል ለዋናዎቹ!

🏅 ዋናው ወደፊት...

@wanawsportwear
ቼልሲ ተጨዋች ለማስፈረም ተስማማ !

የምዕራብ ለንደኑ ክለብ ቼልሲ ፖርቹጋላዊውን ወጣት የግራ መስመር ተጨዋች ራናቶ ቬጋ ከባዝል ለማስፈረም ከስምምነት መድረሳቸው ተገልጿል።

ሰማያዊዎቹ ተጫዋቹን እስከ 2032 በሚቆይ የስምንት አመት ኮንትራት በ14 ሚልዮን ዩሮ የዝውውር ሒሳብ ለማስፈረም ከስምምነት መድረሳቸው ተዘግቧል።

የ 21ዓመቱ ተጨዋች ራናቶ ቬጋ በግራ የመሐል ተከላካይ እንዲሁም በመሐል ሜዳ ተጨዋችነት ቡድኑን የማገልገል ክህሎት እንዳለው ተዘግቧል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
11 '

ስፔን 0 - 0 ጀርመን

- የስፔን ብሔራዊ ቡድን አማካይ ፔድሪ ከባድ ጉዳት አስተናግዶ በዳኒ ኦልሞ ተቀይሮ ለመውጣት ተገዷል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
እረፍት

ስፔን 0 - 0 ጀርመን

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
ሻሸመኔ ከተማ አመቱን በድል አጠናቀዋል !

በኢትዮጵያ ፕርሚየር ሊግ የመጨረሻ ሳምንት መርሐ ግብር ሻሸመኔ ከተማ ከሀምበሪቾ ዱራሜ ጋር ያደረጉትን ጨዋታ 3ለ1 በሆነ ውጤት አሸንፈዋል።

የሻሸመኔ ከተማን የማሸነፊያ ግብ ስንታየሁ መንግስቱ 2x እና ሱራፌል ሙሉወርቅ ከመረብ ማሳረፍ ሲችሉ ለሀምበሪቾ ዱራሜ ብርሀኑ አሻሞ አስቆጥሯል።

ሀምበሪቾ ዱራሜ በውድድር አመቱ ካደረጋቸው ሰላሳ የሊግ ጨዋታዎች ሀያ ሶስቱን የተሸነፈ ሲሆን ማሸነፍ የቻለው በአንዱ ነው።

1️⃣5️⃣ ሻሸመኔ ከተማ :- 17 ነጥብ

1️⃣6️⃣ ሀምበሪቾ ዱራሜ :- 9 ነጥብ

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
52 '

ስፔን 1 - 0 ጀርመን

ኦልሞ

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
63 '

ስፔን 1 - 0 ጀርመን

ኦልሞ

- የ 16ዓመቱ ስፔናዊ የፊት መስመር ተጨዋች ላሚን ያማል በውድድሩ ከየትኛውም ተጨዋች በላይ ሶስት ለግብ የሆኑ ኳሶችን አመቻችቶ ማቀበል ችሏል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
89 '

ስፔን 1 - 1 ጀርመን

ኦልሞ ፍሎሪያን ቨርትዝ

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
ተጠናቀቀ

ስፔን 1 - 1 ጀርመን

ኦልሞ       ፍሎሪያን ቨርትዝ

- ሁለቱ ብሔራዊ ቡድኖች ጨዋታቸውን በአቻ ውጤት ማጠናቀቃቸውን ተከትሎ ወደ ተጨማሪ ሰዓት አምርተዋል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
የጨዋታ አሰላለፍ !

4:00 ፈረንሳይ ከ ፖርቹጋል

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
118 '

ስፔን 1 - 1 ጀርመን

ኦልሞ       ፍሎሪያን ቨርትዝ

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
2024/12/25 06:23:04
Back to Top
HTML Embed Code: