Telegram Web Link
" ሮናልዶን ባደንቅውም ነገ እንዲደሰት አልፈልግም " ምባፔ

የፈረንሳይ ብሔራዊ ቡድን አምበል ኪሊያን ምባፔ ወደ ሪያል ማድሪድ የሚያመራው የሮናልዶን ቀጣይ ታሪክ ለማስቀጠል ሳይሆን የራሱን ታሪክ ለመፃፍ መሆኑን ተናግሯል።

ኪሊያን ምባፔ ከነገው የፖርቹጋል የአውሮፓ ዋንጫ ሩብ ፍፃሜ ጨዋታ በፊት ከጋዜጠኞች ጋር ቆይታ አድርጎ ነበር።

ኪሊያን ምባፔ በቆይታው ምን አለ ?

- " በሪያል ማድሪድ የመጫወት ህልሜን የማሳካበት እድል አግኝቻለሁ በማድሪድ ቤት የራሴን ታሪክ መፃፍ እፈልጋለሁ።

- ሮናልዶ በሪያል ማድሪድ ደማቅ ታሪክ አለው እኔም የራሴን መፃፍ እፈልጋለሁ ለእሱ አድናቆት አለኝ ከእሱ ጋር ግንኙነት አለን አሁንም ቢሆን በየጨዋታው ኮከብ ነው።

- ለክርስቲያኖ ሮናልዶ ትልቅ ክብር አለኝ ነገርግን በነገው ጨዋታ ደስተኛ እንዲሆን አልፈልግም ምክንያቱም እኛ ግማሽ ፍፃሜ መድረስ እንፈልጋለን።

- ፔፔን መጋፈጥ ቀላል አለመሆኑን እናውቃለን በማድሪድ እና ፖርቹጋል ላለው አስደናቂ ታሪክ ክብር አለኝ ከእነደሱ አይነት ተጨዋች ጋር መጫወት ክብር ነው።"ሲል ተደምጧል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
ሲዳማ ቡና አመቱን በድል አጠናቀዋል !

በኢትዮጵያ ፕርሚየር ሊግ የመጨረሻ ሳምንት መርሐ ግብር ሲዳማ ቡና ከባሕር ዳር ከተማ ጋር ያደረጉትን ጨዋታ 2ለ1 በሆነ ውጤት አሸንፈዋል።

የሲዳማ ቡናንን የማሸነፊያ ግቦች ይገዙ ቦጋለ ከመረብ ማሳረፍ ሲችል ለባሕር ዳር ከተማ ፍፁም ጥላሁን አስቆጥሯል።

ባሕር ዳር ከተማ መሸነፉን ተከትሎ ኢትዮጵያ ቡና የዘንድሮውን የኢትዮጵያ ፕርሚየር ሊግ ሶስተኛ ደረጃን ይዘው ማጠናቀቃቸው ተረጋግጧል።

የሊጉ ደረጃቸው ምን ይመስላል ? 

4️⃣ ባሕር ዳር ከተማ :- 50 ነጥብ

1️⃣1️⃣ ሲዳማ ቡና :- 40 ነጥብ

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
TIKVAH-SPORT
" ቶኒ ክሩስን አርብ ወደ ጡረታው እንሸኘዋለን " ሆሴሉ የስፔን ብሔራዊ ቡድን የፊት መስመር ተጨዋች ሆሴሉ ቶኒ ክሩስ አርብ የመጨረሻ ጨዋታውን እንደሚያደርግ በሰጠው አስተያየት ተናግሯል። " ከክሩስ ጋር መጫወት ለእኔ ክብር ነው የመልበሻ ቤት ጓደኛዬ ነበር ብዙ ነገሮችን አግዞኛል ብዙ ምክረም ሰጥቶኛል እሱን ማመስገን እፈልጋለሁ።"ሲል ሆሴሉ ተናግሯል። " እሱ የማድሪድም ሆነ የጀርመን ቁልፍ ተጨዋች…
" ነገ የክሩስ መጨረሻ ጨዋታ እንዳይሆን የቻልነውን እናደርጋለን " ጉንዶጋን

የጀርመን ብሔራዊ ቡድን አምበል ኢልካይ ጉንዶጋን በነገው የሩብ ፍፃሜ ጨዋታ ቡድናቸው ስፔንን ለማሸነፍ የቻለውን ሁሉ እንደሚያደርግ ተናግሯል

" የነገው የስፔን ጨዋታ የቶኒ ክሩስ የመጨረሻ ጨዋታ አይሆንም " የሚለው ኢልካይ ጉንዶጋን ይህ እንዳይሆን በጨዋታው የቻልነውን ሁሉ እናደርጋለን በማለት ተናግሯል።

" ለነገው ጨዋታ ጓጉተናል ከከባድ ጨዋታዎች አንዱ ነው ፣ ሁሉም ጨዋታ እንደ ፍፃሜ ነው ባለፉት ጨዋታዎች ቁጥሮች ካየን ስፔን ከእኛ ይሻላሉ ነገ መቀየር አለብን።" ጉንዶጋን

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
TIKVAH-SPORT
ቶተንሀም ከተጫዋቹ ጋር በይፋ ተለያየ ! ቶተንሀም ከፈረንሳዊው የመሐል ሜዳ ተጨዋች ታንጎይ ንዶምቤሌ ጋር ያላቸውን ኮንትራት በስምምነት ማቋረጣቸውን ይፋ አድርገዋል። ያለፈውን የውድድር አመት በውሰት በቱርኩ ክለብ ጋላታሳራይ ቤት ያሳለፈው ታንጎይ ንዶምቤሌ በቶተንሀም ቤት የአንድ አመት ውል ይቀረው ነበሩ። የ 27ዓመቱ ተጨዋች ታንጎይ ንዶምቤሌ ከአምስት አመታት በፊት ከፈረንሳዩ ክለብ ሊዮን በ55…
ታንጎይ ንዶምቤሌ አዲስ ክለብ ተቀላቅሏል !

በቅርቡ ከቶተንሀም ጋር የተለያየው ፈረንሳዊው የመሐል ሜዳ ተጨዋች ታንጎይ ንዶምቤሌ ኒስን በነፃ ዝውውር መቀላቀሉ ይፋ ተደርጓል።

የ 27ዓመቱ የመሐል ሜዳ ተጨዋች ታንጎይ ንዶምቤሌ በፈረንሳዩ ክለብ ኒስ ቤት እስከ 2026 የሚያቆየውን የሁለት አመት ኮንትራት መፈረሙ ተገልጿል።

ያለፈውን የውድድር አመት በውሰት በቱርኩ ክለብ ጋላታሳራይ ቤት ያሳለፈው ታንጎይ ንዶምቤሌ ከአምስት አመታት በፊት ከፈረንሳዩ ክለብ ሊዮን በ55 ሚልዮን ፓውንድ ቶተንሀምን መቀላቀሉ አይዘነጋም።

@tikvahethsport      @kidusyoftahe
ዩናይትድ የግብ ጠባቂ አሰልጣኝ ሊቀጥር ነው !

ማንችስተር ዩናይትድ ያለፈውን የውድድር አመት በበርንሌይ ቤት ያሳለፉትን የግብ ጠባቂዎች አሰልጣኝ ጄሌ ቴን ሮዌላርን በሀላፊነት ሊሾሙ መሆኑ ተገልጿል።

የግብ ጠባቂዎች አሰልጣኙ በቅርቡ ከበርንሌይ ጋር ከተለያዩ በኋላ አያክስን የተቀላቀሉ ቢሆንም ማንችስተር ዩናይትድ ካሳ ከፍሎ ለመውሰድ እየሰራ መሆኑ ተገልጿል።

ያለፉትን አምስት አመታት በማንችስተር ዩናይትድ የግብ ጠባቂዎች አሰልጣኝ ሆነው ያገለገሉት ሪቻርድ ሀርቲስ ክለቡን እንደሚለቁ ተዘግቧል።

አሰልጣኝ ኤሪክ ቴንሀግ በበኩላቸው አሰልጣኙ በግብ ጠባቂዎች በኩል ከሚፈልጉት የጨዋታ እቅድ ጋር የሚስማሙ ናቸው የሚል እምነት እንዳላቸው ተነግሯል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
Forwarded from HEY Online Market
Stock Clearance Discount 2

📞 0925927457 @eBRO4
📞 0953964175 @heymobile

•iP 7+, Black, 128GB, 99% 12K
•iP X, Black, 256 GB, 100%,12K ⚠️
•iP XS, White, 64 GB, 100% 19K
•iP XS Max, Gold, 64GB, 83%, 25K
•iP XS Max, Gold, 256GB, 88% 29K
•iP 11, Red, 64GB, 100% 28K ⚠️
•iP 11, Black, 128GB, 85%, 33K
•iP 11, Purple, 128GB, 88% 33K
•11 Pro, Black, 64GB, 100% 39K ⚠️
•11 Pro, White, 64GB, 87% 36K
•11 Pro Max, Black, 64GB, 86%, 46K

•11 Pro Max, Black, 256GB, -% 40⚠️
•iP 12, Red, 128GB, 88%, 42K
•iP 12, White, 128GB, 88% 42K
•iP 12, Green, 128GB, 86% 42K
•12 Pro, Blue, 128GB, 89% 49K
•12 Pro Max, Blue, 512GB, 84% 64K
•iP 13 Min, Pink, 256GB, 92% 34K
•iP 13, Blueback, 128GB, 90% 56K
•iP 13, Black, 128GB, 92% 49K ⚠️

•iP 13, Red, 128GB, 86%, 56K
•iP 13, Black, 128GB, 89%, 58K
•13 Pro, Golden, 256GB, 87% 69K
•13 Pro, Blue, 512GB/88% 69K ⚠️
•13 ProMax, Black, 128 GB, 87% 74K
•13 ProMax, 256GB, 86%, 64K⚠️
•13 ProMax, 256GB, 85%, 74K⚠️
•13 ProMax, Gold, 256GB, 86%, 79K
•13 Pro Max, Gold, 256 GB,88% 79K
•13 Pro Max, Blue, 256GB, 94% 79K
•13 Pro Max, 1TB, 88%, 69K ⚠️
•13 Pro Max, Blu, 256GB/ -% 70K ⚠️

Exchange Available!
Free Delivery 🚚

@heyonlinemarket
https://heymobile.store/catalogue
ሽመልስ በቀለ 1⃣8⃣ ገስት ሀውስ

በውቢቷ ሀዋሳ ቆይታዎ የት ለማረፍ አስበዋል ? ንፁህ እና በደንበኞቻችን ተወዳጅ በሆነው የእንግዳ ማረፊያችን መጥተው የእረፍት ጊዜውን ያሳልፉ።

እንግዶቻችንን ተቀበልን ለእይታ ሳቢ በሆነው የእንግዳ ማረፊያችን ማስተናገድ ከጀመርን አመታትን አስቆጥረናል።

አድራሻችን :- ሀዋሳ አርቴፍሻል ስታዲየም መንገድ ላይ ያገኙናል።

ለተጨማሪ መረጃ እና ለትዕዛዝዎ ይደውሉልን :- 0928684848

#ShemelesBekele18
#CopaAmerica2024

በኮፓ አሜሪካ ሩብ ፍፃሜ ጨዋታ አርጀንቲና ከኢኳዶር ጋር ያደረገችውን ጨዋታ በመለያ ምት 4ለ2 በማሸነፍ ግማሽ ፍፃሜውን ተቀላቅላለች።

ሁለቱ ብሔራዊ ቡድኖች መደበኛውን የጨዋታ ክፍለጊዜ 1ለ1 በሆነ አቻ ውጤት ሲያጠናቅቁ ግቦቹን ለአርጀንቲና ሊሳንድሮ ማርቲኔዝ ለኢኳዶር ሮድሪጉዌዝ አስቆጥረዋል።

የአርጀንቲና ግብ ጠባቂ ኤሚሊያኖ ማርቲኔዝ ሁለት የመለያ ምቶችን ማዳን ሲችል ሊዮኔል ሜሲ የመጀመሪያውን የአርጀንቲና መለያ ምት ማስቆጠር ሳይችል ቀርቷል።

አርጀንቲና በግማሽ ፍፃሜው ዛሬ ሌሊት 10:00 ሰዓት ከሚጫወቱት ካናዳ እና ቬንዙዌላ አሸናፊ ጋር የምትጫወት ይሆናል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
" ሮናልዶ ለጨዋታው ዝግጁ ነው " ሮቤርቶ ማርቲኔዝ

የፖርቹጋል ብሔራዊ ቡድን አሰልጣኝ ሮቤርቶ ማርቲኔዝ ከዛሬ ምሽቱ የፈረንሳይ የአውሮፓ ዋንጫ ሩብ ፍፃሜ ጨዋታ በፊት አስተያየታቸውን ሰጥተዋል።

ሮቤርቶ ማርቲኔዝ ካነሷቸው ሀሳቦች መካከልም :-

- " በስሎቬንያ ጨዋታ የተፈጠረው ተፈጥሯል ሮናልዶ የመጀመሪያውን መለያ ምት ሀላፊነት በመውሰድ አስቆጥሯል ያለውን ብስለትም አሳይቷል።

- የቡድኑ አምበል ክርስቲያኖ ሮናልዶ ለዛሬው የፈረንሳይ ጨዋታ ዝግጁ በደንብ ዝግጅት አድርጓል ለጨዋታው ዝግጁ ነው።

- በጨዋታው ወሳኙ ነገር በመልሶ ማጥቃት ሲጫወቱ መጠንቀቅ ነው ፈረንሳይ ምባፔ ብቻ አይደለም ያላት ሌሎች ከባድ አጥቂዎች አሏቸው እነሱን ማስቆም አለብን።

- ለፈረንሳይ ክብር አለን በጥሩ መልኩ ይከላከላሉ ጥሩ ያጠቃሉ እኛ እንደ ቡድን ጥሩ አቋም ማሳየት አለብን በሜዳ ክፍላችን ላይ ጠንክረን መከላከል አለብን ለአንድ ተጨዋች እቅድ የለንም።"ሲሉ ተደምጠዋል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
" ተጋጣሚ ሲያጠቃ መከላከል ሳይሆን የበለጠ ማጥቃት አለብን " ሉዊስ ዴ ላ ፉንቴ

የስፔን ብሔራዊ ቡድን ዋና አሰልጣኝ ሉዊስ ዴ ላ ፉንቴ በምሽቱ የጀርመን ብሔራዊ ቡድን ጨዋታ ቡድናቸው የትኛውንም ስህተት ከመስራት እንዲጠነቀቅ አሳስበዋል።

" ተጋጣሚ አጥቅቶ ሲጫወት ምላሽ ለመስጠት ትክክለኛው መንገድ የበለጠ አጥቅቶ መጫወት ነው " የሚሉት ሉዊስ ዴ ላ ፉንቴ በዚህ ጨዋታ ምንም አይነት ስህተት መስራት የለብንም በማለት ተናግረዋል።

" ጀርመን ጠንካራ የሚባል ቡድን ይዛ ትገባለች እኛም ይህንኑ ለማድረግ እንሞክራለን ፣ የራሳችንን አቅም እናውቃለን የእነሱንም አቅም እናውቃለን እርስበርስ እንከባበራለን።" ሉዊስ ዴ ላ ፉንቴ

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
ኢኳዶር ከአሰልጣኟ ጋር ተለያይታለች !

ከኮፓ አሜሪካ የተሰናበተው የኢኳዶር ብሔራዊ ቡድን ከስፔናዊው አሰልጣኝ ፌሊክስ ሳንቼዝ ጋር መለያየቱ ተገልጿል።

አሰልጣኝ ፌሊክስ ሳንቼዝ ከሀላፊነታቸው የተነሱት ኢኳዶር በአርጀንቲና በመለያ ምት ተሸንፋ ከኮፓ አሜሪካ ውድድር ውጪ መሆኗን ተከትሎ እንደሆነ ተገልጿል።

በቡድኑ የሁለት አመት ኮንትራት የነበራቸው አሰልጣኝ ፌሊክስ ሳንቼዝ ቡድኑን ለኮፓ አሜሪካ ሩብ ፍፃሜ ሲያደርሱ በአለም ዋንጫ ማጣሪያ መሳተፍ በሚያስችላቸው ደረጃ ላይ ይገኛሉ።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
TIKVAH-SPORT
ሳሙኤል ኤቶ ክስ ላይ እንደሚገኝ ተገለፀ ! የካሜሮን እግር ኳስ ፌዴሬሽን ፕሬዝዳንት እና የቀድሞ ታሪካዊ ተጨዋች ሳሙኤል ኤቶ ክስ ቀርቦበት በአፍሪካ እግርኳስ ኮንፌዴሬሽን ( ካፍ ) እና ፊፋ ምርመራ እየተካሄደበት እንደሚገኝ ተገልጿል። ሳሙኤል ኤቶ በጨዋታ ማጭበርበር ፣ አካላዊ ጥቃት በማድረስ ፣ ሁከት በማነሳሳት እና የተሳሳተ መረጃ በማሰራጨት ተከሶ ምርመራ ላይ መሆኑ ተዘግቧል። ክሶቹን የሚያስረዱ…
ሳሙኤል ኤቶ በሀላፊነቱ ይቀጥላል !

የካሜሮን እግር ኳስ ፌዴሬሽን ፕሬዝዳንት እና የቀድሞ ታሪካዊ ተጨዋች ሳሙኤል ኤቶ ቀርቦበት በነበረው ክስ በአንዱ ጥፋተኛ ሆኖ መገኘቱ ተገልጿል።

የካፍ ዲሲፕሊን ኮሚቴ ሳሙኤል ኤቶ የቀረበበትን የጨዋታ ማጭበርበር እና በስፖርት ስነምግባር ጥሰት ክስ ምርመራ ሲያደርግ እንደነበር ይታወሳል።

አሁን ላይ ካፍ ይፋ ባደረገው መረጃ ሳሙኤል ኤቶ የተከሰሰበትን የጨዋታ ማጭበርበር ጥፋት የሚያረጋግጥ ማስረጃ ማግኘት እንዳልቻለ አሳውቋል።

ይሁን እንጂ ሳሙኤል ኤቶ የሀገሪቱ እግርኳስ ፌዴሬሽን ሀላፊ ሆኖ ሳለ ከስፖርት ውርርድ ተቋም ጋር በገባው የአምባሳደርነት ስምምነት ምክንያት 200,000 ዶላር ቅጣት ተጥሎበታል።

ሳሙኤል ኤቶ በቀረቡበት ክሶች ጥፋተኛ የሚሆን ከሆነ ከእግርኳስ ሊታገድ እንደሚችል ሲገለፅ የነበረ ቢሆንም አሁን ላይ በሀላፊነት እንደሚቀጥል ካፍ አሳውቋል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
ጃን ቨርቶንገን ራሱን ከብሔራዊ ቡድኑ አገለለ !

የቤልጅየም ብሔራዊ ቡድን የተከላካይ ስፍራ ተጨዋች ጃን ቨርቶንገን በ 37ዓመቱ ከብሔራዊ ቡድኑ ራሱን ማግለሉን ይፋ አድርጓል።

የቀድሞ የቶተንሀም ተከላካይ ጃን ቨርቶንገን ለቤልጂየም ብሔራዊ ቡድን አንድ መቶ ሀምሳ ሰባት ጨዋታዎችን ተሰልፎ መጫወት ችሏል።

ጃን ቨርቶንገን ከአውሮፓ ዋንጫው በፈረንሳይ ተሸንፎ ከጥሎ ማለፍ የተሰናበተውን የቤልጂየም ብሔራዊ ቡድን ወክሎ እንደነበር ይታወሳል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
🔥እንደ ዋንጫ ጨዋታ የሚታየው ፍልሚያ!
⭐️በውድድሩ ሁሉንም ጨዋታ አሸንፋ ለሩብ ፍጻሜ የደረሰችው ስፔን ከአስተናጋጇ ሃገር ጀርመን ጋር ትፋለማለች::

በጨዋታው ማን ቀድሞ ጎል ያገባል?
በጨዋታው ለመወራረድ - https://betika.et/et/competition/16724425/match/12905742

ቤቲካ! የአሸናፊዎች ቤት!
💥 ከአስገራሚ ትንቅንቅ በኋላ የአውሮፓ ዋንጫ ሩብ ፍፃሜ ዛሬ ምሽት ይጀምራል!

⚽️  Spain vs Germany ከምሽቱ 1፡00 ሰዓት | 7፡00 PM
⚽️  Portugal vs France ከምሽቱ 4፡00 ሰዓት | 10፡00 PM

👉SS Football ቻናል 225 በጎጆ ፓኬጅ
👉SS Euro2024 ቻናል 222 በሜዳ  ፓኬጅ

ግማሽ ፍፃሜ የሚድርሱትን 2ቱን ሃገራት አሁኑኑ ይገምቱ!

ዛሬውኑ ደንበኝነትዎን ያራዝሙ የአውሮፓ ዋንጭ ሩብ ፍፃሜ ጨዋታዎችን በጎጆ ፓኬጅ በ350ብር በሱፐርስፖርት ይከታተሉ!

የዲኤስቲቪ አገልግሎቶችን ለማግኘት ከታች ያለውን የMyDStv Telegram bot ሊንክ ይጫኑ!
👇
https://bit.ly/3RFtEvh

#Euro2024onDStv #ሁሉምያለውእኛጋርነው #DStvEthiopia
ፈረንሳይ ወሳኝ ተጨዋቾቿ ለቅጣት ተቃርበዋል !

ዛሬ ምሽት ከፖርቹጋል ጋር ወሳኝ የአውሮፓ ዋንጫ ሩብ ፍፃሜ ጨዋታ ያለባት ፈረንሳይ ወሳኝ የብሔራዊ ቡድኑ ተጨዋቾቿ ለቅጣት ተቃርበዋል።

የቡድኑ አምበል ኪሊያን ምባፔ እንዲሁም ኦርሊየን ቹዋሜኒ በምሽቱ ጨዋታ የቢጫ ካርድ የሚመለከቱ ከሆነ ፈረንሳይ ግማሽ ፍፃሜ ከደረሰች በቅጣት ጨዋታው የሚያልፋቸው ይሆናል።

ፈረንሳይ ከፖርቹጋል ጋር የሚያደርጉት ተጠባቂ የሩብ ፍፃሜ ጨዋታ ዛሬ ምሽት 4:00 ሰዓት ይደረጋል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
" ቡድኔ አጥቅቶ እንዲጫወት ነው የምፈልገው " አርኔ ስሎት

የመርሲሳይዱ ክለብ ሊቨርፑል ዋና አሰልጣኝ አርኔ ስሎት በቀጣይ የሚሰሩት ቡድን ሀይል ያለው አጥቅቶ የሚጫወት ቡድን መሆኑን ገልጸዋል።

አሰልጣኝ አርኔ ስሎት በሊቨርፑል ቤት ከጋዜጠኞች ጋር የመጀመሪያ ቆይታቸውን ያደረጉ ሲሆን ካነሷቸው ሀሳቦች መካከልም :-

- " የማሰለጥነው ቡድን በትልቅ ጉልበት እና በማጥቃት ላይ የተመሰረተ እግርኳስን እንዲጫወት እፈልጋለሁ።

- በዚህ ሊግ ስታሰለጥን ሁልጊዜም መሻሻል አለብን ምክንያቱም ሁሉም የተሻለ እየሆነ ነው የሚመጣው ይህ በትልቅ ሊግ የተለመደ ነው።

- አሰልጣኝ የርገን ክሎፕን ብዙ ጊዜ አነጋግሬዋለሁ ነገርግን እሱ አሁንም አብሮን ይሆናል ስለእኔ የዘመረው ልዩ ነበር።

- ትልቅ ተጨዋቾች ዋንጫ ማሸነፍ ይፈልጋል መሐመድ ሳላህ እና ቫን ዳይክም እንዲሁ ከእኛ ጋር ዋንጫ ማሸነፍ ይፈልጋሉ።"ሲሉ ተደምጠዋል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
TIKVAH-SPORT
ጁድ ቤሊንግሀም ቅጣት አይጣልበትም ! የእንግሊዝ ብሔራዊ ቡድን ተጨዋች ጁድ ቤሊንግሀም ቡድኑ ስሎቫኪያን ባሸነፈበት ምሽት የተጋጣሚ የቡድን አባላት ላይ ያነጣጠረ ያልተገባ ድርጊት አሳይቷል በሚል ምርመራ ተደርጎበት ነበር። አሁን ላይ የአውሮፓ እግርኳስ ማህበር ጁድ ቤሊንግሀም ላይ የቅጣት ውሳኔ እንደማይጥል እና ለስዊዘርላንዱ የሩብ ፍፃሜ ጨዋታ ዝግጁ እንደሚሆን ተገልጿል። ጁድ ቤሊንግሀም በሰዓቱ…
ዩኤፋ ቤሊንግሀም ላይ ምን ውሳኔ አሳለፈ ?

የአውሮፓ እግርኳስ ማህበር እንግሊዛዊው ተጨዋች ጁድ ቤሊንግሀም በስሎቫኪያ ጨዋታ ያልተገባ እንቅስቃሴ አሳይቷል በሚል ምርመራ ላይ እንደነበር ይታወሳል።

ዩኤፋ አሁን ላይ ጁድ ቤሊንግሀም 30,000 ዩሮ እንዲቀጣ እንዲሁም በቀጣይ አንድ አመት ውስጥ አንድ ጨዋታ እንዲቀጣ መወሰኑን ይፋ አድርጓል።

ጁድ ቤሊንግሀም የሚቀጣውን ጨዋታ በቀጣይ አንድ አመት መርጦ መቀጣት እንዲችል ፍቃድ ማግኘቱን ተከትሎ በነገው የስዊዘርላንድ ጨዋታ መጫወት እንደሚችል ተገልጿል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
በርንማውዝ ፍራን ጋርሽያን ማስፈረም ይፈልጋል !

የፕርሚየር ሊጉ ክለብ በርንማውዝ ስፔናዊውን ግራ መስመር ተጨዋች ፍራን ጋርሽያን ከሪያል ማድሪድ ለማስፈረም እንደሚፈልጉ ተገልጿል።

የበርንማውዙ ዋና አሰልጣኝ አንዶኒ ኢራኦላ የተጨዋቹ አድናቂ መሆናቸው ሲገለፅ ክለቡ በበኩሉ ተጫዋቹን ለማስፈረም ጥረት ለመጀመር ማሰቡ ተነግሯል።

ሪያል ማድሪድ በፍራን ጋርሽያ የጨዋታ ቦታ ላይ ሌሎች አማራጮች ያላቸው መሆኑን ተከትሎ ሊለቁት እንደሚችሉ ተዘግቧል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
2024/12/25 18:36:08
Back to Top
HTML Embed Code: