Telegram Web Link
ጃን ቨርቶንገን ራሱን ከብሔራዊ ቡድኑ አገለለ !

የቤልጅየም ብሔራዊ ቡድን የተከላካይ ስፍራ ተጨዋች ጃን ቨርቶንገን በ 37ዓመቱ ከብሔራዊ ቡድኑ ራሱን ማግለሉን ይፋ አድርጓል።

የቀድሞ የቶተንሀም ተከላካይ ጃን ቨርቶንገን ለቤልጂየም ብሔራዊ ቡድን አንድ መቶ ሀምሳ ሰባት ጨዋታዎችን ተሰልፎ መጫወት ችሏል።

ጃን ቨርቶንገን ከአውሮፓ ዋንጫው በፈረንሳይ ተሸንፎ ከጥሎ ማለፍ የተሰናበተውን የቤልጂየም ብሔራዊ ቡድን ወክሎ እንደነበር ይታወሳል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
🔥እንደ ዋንጫ ጨዋታ የሚታየው ፍልሚያ!
⭐️በውድድሩ ሁሉንም ጨዋታ አሸንፋ ለሩብ ፍጻሜ የደረሰችው ስፔን ከአስተናጋጇ ሃገር ጀርመን ጋር ትፋለማለች::

በጨዋታው ማን ቀድሞ ጎል ያገባል?
በጨዋታው ለመወራረድ - https://betika.et/et/competition/16724425/match/12905742

ቤቲካ! የአሸናፊዎች ቤት!
💥 ከአስገራሚ ትንቅንቅ በኋላ የአውሮፓ ዋንጫ ሩብ ፍፃሜ ዛሬ ምሽት ይጀምራል!

⚽️  Spain vs Germany ከምሽቱ 1፡00 ሰዓት | 7፡00 PM
⚽️  Portugal vs France ከምሽቱ 4፡00 ሰዓት | 10፡00 PM

👉SS Football ቻናል 225 በጎጆ ፓኬጅ
👉SS Euro2024 ቻናል 222 በሜዳ  ፓኬጅ

ግማሽ ፍፃሜ የሚድርሱትን 2ቱን ሃገራት አሁኑኑ ይገምቱ!

ዛሬውኑ ደንበኝነትዎን ያራዝሙ የአውሮፓ ዋንጭ ሩብ ፍፃሜ ጨዋታዎችን በጎጆ ፓኬጅ በ350ብር በሱፐርስፖርት ይከታተሉ!

የዲኤስቲቪ አገልግሎቶችን ለማግኘት ከታች ያለውን የMyDStv Telegram bot ሊንክ ይጫኑ!
👇
https://bit.ly/3RFtEvh

#Euro2024onDStv #ሁሉምያለውእኛጋርነው #DStvEthiopia
ፈረንሳይ ወሳኝ ተጨዋቾቿ ለቅጣት ተቃርበዋል !

ዛሬ ምሽት ከፖርቹጋል ጋር ወሳኝ የአውሮፓ ዋንጫ ሩብ ፍፃሜ ጨዋታ ያለባት ፈረንሳይ ወሳኝ የብሔራዊ ቡድኑ ተጨዋቾቿ ለቅጣት ተቃርበዋል።

የቡድኑ አምበል ኪሊያን ምባፔ እንዲሁም ኦርሊየን ቹዋሜኒ በምሽቱ ጨዋታ የቢጫ ካርድ የሚመለከቱ ከሆነ ፈረንሳይ ግማሽ ፍፃሜ ከደረሰች በቅጣት ጨዋታው የሚያልፋቸው ይሆናል።

ፈረንሳይ ከፖርቹጋል ጋር የሚያደርጉት ተጠባቂ የሩብ ፍፃሜ ጨዋታ ዛሬ ምሽት 4:00 ሰዓት ይደረጋል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
" ቡድኔ አጥቅቶ እንዲጫወት ነው የምፈልገው " አርኔ ስሎት

የመርሲሳይዱ ክለብ ሊቨርፑል ዋና አሰልጣኝ አርኔ ስሎት በቀጣይ የሚሰሩት ቡድን ሀይል ያለው አጥቅቶ የሚጫወት ቡድን መሆኑን ገልጸዋል።

አሰልጣኝ አርኔ ስሎት በሊቨርፑል ቤት ከጋዜጠኞች ጋር የመጀመሪያ ቆይታቸውን ያደረጉ ሲሆን ካነሷቸው ሀሳቦች መካከልም :-

- " የማሰለጥነው ቡድን በትልቅ ጉልበት እና በማጥቃት ላይ የተመሰረተ እግርኳስን እንዲጫወት እፈልጋለሁ።

- በዚህ ሊግ ስታሰለጥን ሁልጊዜም መሻሻል አለብን ምክንያቱም ሁሉም የተሻለ እየሆነ ነው የሚመጣው ይህ በትልቅ ሊግ የተለመደ ነው።

- አሰልጣኝ የርገን ክሎፕን ብዙ ጊዜ አነጋግሬዋለሁ ነገርግን እሱ አሁንም አብሮን ይሆናል ስለእኔ የዘመረው ልዩ ነበር።

- ትልቅ ተጨዋቾች ዋንጫ ማሸነፍ ይፈልጋል መሐመድ ሳላህ እና ቫን ዳይክም እንዲሁ ከእኛ ጋር ዋንጫ ማሸነፍ ይፈልጋሉ።"ሲሉ ተደምጠዋል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
TIKVAH-SPORT
ጁድ ቤሊንግሀም ቅጣት አይጣልበትም ! የእንግሊዝ ብሔራዊ ቡድን ተጨዋች ጁድ ቤሊንግሀም ቡድኑ ስሎቫኪያን ባሸነፈበት ምሽት የተጋጣሚ የቡድን አባላት ላይ ያነጣጠረ ያልተገባ ድርጊት አሳይቷል በሚል ምርመራ ተደርጎበት ነበር። አሁን ላይ የአውሮፓ እግርኳስ ማህበር ጁድ ቤሊንግሀም ላይ የቅጣት ውሳኔ እንደማይጥል እና ለስዊዘርላንዱ የሩብ ፍፃሜ ጨዋታ ዝግጁ እንደሚሆን ተገልጿል። ጁድ ቤሊንግሀም በሰዓቱ…
ዩኤፋ ቤሊንግሀም ላይ ምን ውሳኔ አሳለፈ ?

የአውሮፓ እግርኳስ ማህበር እንግሊዛዊው ተጨዋች ጁድ ቤሊንግሀም በስሎቫኪያ ጨዋታ ያልተገባ እንቅስቃሴ አሳይቷል በሚል ምርመራ ላይ እንደነበር ይታወሳል።

ዩኤፋ አሁን ላይ ጁድ ቤሊንግሀም 30,000 ዩሮ እንዲቀጣ እንዲሁም በቀጣይ አንድ አመት ውስጥ አንድ ጨዋታ እንዲቀጣ መወሰኑን ይፋ አድርጓል።

ጁድ ቤሊንግሀም የሚቀጣውን ጨዋታ በቀጣይ አንድ አመት መርጦ መቀጣት እንዲችል ፍቃድ ማግኘቱን ተከትሎ በነገው የስዊዘርላንድ ጨዋታ መጫወት እንደሚችል ተገልጿል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
በርንማውዝ ፍራን ጋርሽያን ማስፈረም ይፈልጋል !

የፕርሚየር ሊጉ ክለብ በርንማውዝ ስፔናዊውን ግራ መስመር ተጨዋች ፍራን ጋርሽያን ከሪያል ማድሪድ ለማስፈረም እንደሚፈልጉ ተገልጿል።

የበርንማውዙ ዋና አሰልጣኝ አንዶኒ ኢራኦላ የተጨዋቹ አድናቂ መሆናቸው ሲገለፅ ክለቡ በበኩሉ ተጫዋቹን ለማስፈረም ጥረት ለመጀመር ማሰቡ ተነግሯል።

ሪያል ማድሪድ በፍራን ጋርሽያ የጨዋታ ቦታ ላይ ሌሎች አማራጮች ያላቸው መሆኑን ተከትሎ ሊለቁት እንደሚችሉ ተዘግቧል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
ኢትዮጵያን በኦሎምፒክ የሚወክሉ አትሌቶች ተለዩ !

የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን በቀጣዩ የ2024 ፓሪስ ኦሎምፒክ ውድድር ሀገራችን ኢትዮጵያን በሁሉም ርቀቶች የሚወክሉ አትሌቶች እና ተጠባባቂዎችን ይፋ አድርጓል።

የ10,000 ሜትር የአለም ሻምፒዮኗ አትሌት ጉዳፍ ፀጋይ በውድድሩ በሶስት ርቀቶች ( 1,500 ፣ 5,000 ፣ 10,000ሜ ) ሀገራችን ኢትዮጵያን የምትወክል ይሆናል።

አትሌት ዮሚፍ ቀጄልቻ በበኩሉ ኢትዮጵያን በ5,000ሜ እና 10,000ሜ በሁለት ርቀቶች እንደሚወክል ታውቋል።

ለመጨረሻ ጊዜ በተደረገው የቶኪዮ ኦሎምፒክ ብቸኛውን የወርቅ ሜዳልያ ለኢትዮጵያ ያስመዘገበው አትሌት ሰለሞን ባረጋ በበኩሉ በ10,000ሜ ሀገራችንን ሲወክል በ5000ሜ ተጠባባቂ ሆኖ ይጀመራል።

የሶስት ጊዜ የኦሎምፒክ ወርቅ ሜዳልያ አሸናፊው አትሌት ቀነኒሳ በቀለ ከአስራ ሁለት አመታት በኋላ ኢትዮጵያን በኦሎምፒክ ማራቶን ይወክላል።

ሙሉ የአትሌቶች ዝርዝር ከላይ በምስሉ ተያይዟል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
TIKVAH-SPORT
ሪካርዶ ካላፊዮሪ አርሰናልን መቀላቀል ይፈልጋል ! የሰሜን ለንደኑ ክለብ አርሰናል ጣልያናዊውን የቦሎኛ የተከላካይ ስፍራ ተጨዋች ሪካርዶ ካላፊዮሪ ለማስፈረም ጥረት በማድረግ ላይ መሆናቸው ተገልጿል። መድፈኞቹ ለተጨዋቹ የዝውውር ጥያቄያቸውን ማቅረባቸው የተገለፀ ሲሆን በቀጣይ ከቦሎኛ ጋር የሚስማሙ ከሆነ ተጨዋቹ አርሰናልን ለመቀላቀል እንደሚፈልግ ተነግሯል። ከአርሰናል በተጨማሪም የምዕራብ ለንደኑ…
አርሰናል ተጨዋች ለማስፈረም ተስማማ !

የሰሜን ለንደኑ ክለብ አርሰናል ጣልያናዊውን የቦሎኛ የተከላካይ ስፍራ ተጨዋች ሪካርዶ ካላፊዮሪ ለማስፈረም ከተጨዋቹ ጋር ከስምምነት መድረሱ ተገልጿል።

መድፈኞቹ ለተጨዋቹ ባቀረቡት እስከ 2029 የሚቆይ የአምስት አመት ኮንትራት ከስምምነት መድረሳቸው ተነግሯል።

አርሰናል በተጨዋቹ ዝውውር ሒሳብ ዙሪያ ከቦሎኛ ጋር ንግግር በማድረግ ላይ መሆናቸው ሲገለፅ ክለቡ 50 ሚልዮን ዩሮ የሚደርስ ክፍያ መጨየቁ ተዘግቧል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
ወልቂጤ ከተማ አመቱን በድል አጠናቀዋል !

በኢትዮጵያ ፕርሚየር ሊግ የመጨረሻ ሳምንት መርሐ ግብር ወልቂጤ ከተማ ከአዳማ ከተማ ጋር ያደረጉትን ጨዋታ 1ለ0 በሆነ ውጤት አሸንፈዋል።

የወልቂጤ ከተማን ብቸኛ የማሸነፊያ ግብ አዳነ በላይነህ ከመረብ ማሳረፍ ችሏል።

የሊጉ ደረጃቸው ምን ይመስላል ? 

7️⃣ አዳማ ከተማ :- 44 ነጥብ

1️⃣4️⃣ ወልቂጤ ከተማ:- 23 ነጥብ

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
TIKVAH-SPORT
የሲቲ እና ጂሮና የሻምፒየንስ ሊግ ተሳትፎ ሁኔታ ! በሲቲ ፉትቦል ግሩፕ ባለቤትነት የተያዙት ማንችስተር ሲቲ እና የስፔኑ ክለብ ጂሮና በሚቀጥለው የውድድር አመት በአውሮፓ ሻምፒየንስ ሊግ ውድድር የሚያሳትፋቸውን ቦታ አግኝተዋል። ክለቦቹ በተመሳሳይ ተቋም ባለቤትነት የተያያዙ መሆኑን ተከትሎ በዩኤፋ የውድድር ህግ መሰረት በሻምፒየንስ ሊግ ለመሳተፍ ማድረግ የሚጠበቅባቸው ቅድመ ሁኔታ መኖሩ ተገልጿል።…
ዩኤፋ ተመሳሳይ ባለቤት ላላቸው ክለቦች ፍቃድ ሰጠ !

የፕርሚየር ሊጉ አሸናፊ ማንችስተር ሲቲ በሚቀጥለው የውድድር አመት ከጂሮና ጋር በተመሳሳይ በአውሮፓ ሻምፒየንስ ሊግ መወዳደር እንዲችሉ እንደተፈቀደላቸው ተገልጿል።

በተጨማሪም ማንችስተር ዩናይትድ እና የፈረንሳዩ ክለብ ኒስ በቀጣይ የውድድር አመት በዩሮፓ ሊግ መወዳደር እንደሚችሉ የአውሮፓ እግርኳስ ማህበር አሳውቋል።

ክለቦቹ በአንድ ተቋም ባለቤትነት የተያዙ መሆኑን ተከትሎ በዩኤፋ ህግ መሰረት በአውሮፓ መድረክ አንድ ላይ ለመወዳደር ላይፈቀድላቸው ይችላል ሲባል እንደነበር አይዘነጋም።

አሁን ላይ የአውሮፓ እግርኳስ ማህበር ያስቀመጣቸው አማራጭ ሀሳቦች በክለብ ባለቤቶች ተቀባይነት ማግኘቱን ተከትሎ ፍቃዱን እንደሰጠ ተዘግቧል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
TIKVAH-SPORT
ዩኤፋ ተመሳሳይ ባለቤት ላላቸው ክለቦች ፍቃድ ሰጠ ! የፕርሚየር ሊጉ አሸናፊ ማንችስተር ሲቲ በሚቀጥለው የውድድር አመት ከጂሮና ጋር በተመሳሳይ በአውሮፓ ሻምፒየንስ ሊግ መወዳደር እንዲችሉ እንደተፈቀደላቸው ተገልጿል። በተጨማሪም ማንችስተር ዩናይትድ እና የፈረንሳዩ ክለብ ኒስ በቀጣይ የውድድር አመት በዩሮፓ ሊግ መወዳደር እንደሚችሉ የአውሮፓ እግርኳስ ማህበር አሳውቋል። ክለቦቹ በአንድ ተቋም ባለቤትነት…
#Update

የአውሮፓ እግርኳስ ማህበር ማንችስተር ሲቲ እና ጂሮና በሻምፒየንስ ሊግ እንዲሁም ማንችስተር ዩናይትድ እና ኒስ በዩሮፓ ሊግ እንዲወዳደሩ ፍቃድ ሰጥቷል።

ይሁን እንጂ የአውሮፓ እግርኳስ ማህበር በክለቦቹ መካከል ክልከላዎችን ያስቀመጠ ሲሆን

- ማንችስተር ዩናይትድ እና ኒስ ከሐምሌ ወር እስከ ቀጣይ 2025 መስከረም ወር በቋሚነትም ሆነ በውሰት ዝውውሮችን ማድረግ አይችሉም።

- በተመሳሳይ ማንችስተር ሲቲ እና ጂሮና በቋሚነትም ሆነ በውሰት ዝውውሮችን ማድረግ እንደማይችሉ ተገልጿል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
የጨዋታ አሰላለፍ !

1:00 ጀርመን ከ ስፔን

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
Forwarded from WANAW SPORT
💪🏾⚽️ #ዋናው ሰዓት ደርሷል! 💪🏾⚽️

🇪🇹 ዋናው ስፖርት 🤝 መቻል ስፖርት ክለብ 🇪🇹

መልካም ዕድል ለዋናዎቹ!

🏅 ዋናው ወደፊት...

@wanawsportwear
ቼልሲ ተጨዋች ለማስፈረም ተስማማ !

የምዕራብ ለንደኑ ክለብ ቼልሲ ፖርቹጋላዊውን ወጣት የግራ መስመር ተጨዋች ራናቶ ቬጋ ከባዝል ለማስፈረም ከስምምነት መድረሳቸው ተገልጿል።

ሰማያዊዎቹ ተጫዋቹን እስከ 2032 በሚቆይ የስምንት አመት ኮንትራት በ14 ሚልዮን ዩሮ የዝውውር ሒሳብ ለማስፈረም ከስምምነት መድረሳቸው ተዘግቧል።

የ 21ዓመቱ ተጨዋች ራናቶ ቬጋ በግራ የመሐል ተከላካይ እንዲሁም በመሐል ሜዳ ተጨዋችነት ቡድኑን የማገልገል ክህሎት እንዳለው ተዘግቧል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
11 '

ስፔን 0 - 0 ጀርመን

- የስፔን ብሔራዊ ቡድን አማካይ ፔድሪ ከባድ ጉዳት አስተናግዶ በዳኒ ኦልሞ ተቀይሮ ለመውጣት ተገዷል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
እረፍት

ስፔን 0 - 0 ጀርመን

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
2024/10/02 20:33:58
Back to Top
HTML Embed Code: