Telegram Web Link
ሻሸመኔ ከተማ አመቱን በድል አጠናቀዋል !

በኢትዮጵያ ፕርሚየር ሊግ የመጨረሻ ሳምንት መርሐ ግብር ሻሸመኔ ከተማ ከሀምበሪቾ ዱራሜ ጋር ያደረጉትን ጨዋታ 3ለ1 በሆነ ውጤት አሸንፈዋል።

የሻሸመኔ ከተማን የማሸነፊያ ግብ ስንታየሁ መንግስቱ 2x እና ሱራፌል ሙሉወርቅ ከመረብ ማሳረፍ ሲችሉ ለሀምበሪቾ ዱራሜ ብርሀኑ አሻሞ አስቆጥሯል።

ሀምበሪቾ ዱራሜ በውድድር አመቱ ካደረጋቸው ሰላሳ የሊግ ጨዋታዎች ሀያ ሶስቱን የተሸነፈ ሲሆን ማሸነፍ የቻለው በአንዱ ነው።

1️⃣5️⃣ ሻሸመኔ ከተማ :- 17 ነጥብ

1️⃣6️⃣ ሀምበሪቾ ዱራሜ :- 9 ነጥብ

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
52 '

ስፔን 1 - 0 ጀርመን

ኦልሞ

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
63 '

ስፔን 1 - 0 ጀርመን

ኦልሞ

- የ 16ዓመቱ ስፔናዊ የፊት መስመር ተጨዋች ላሚን ያማል በውድድሩ ከየትኛውም ተጨዋች በላይ ሶስት ለግብ የሆኑ ኳሶችን አመቻችቶ ማቀበል ችሏል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
89 '

ስፔን 1 - 1 ጀርመን

ኦልሞ ፍሎሪያን ቨርትዝ

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
ተጠናቀቀ

ስፔን 1 - 1 ጀርመን

ኦልሞ       ፍሎሪያን ቨርትዝ

- ሁለቱ ብሔራዊ ቡድኖች ጨዋታቸውን በአቻ ውጤት ማጠናቀቃቸውን ተከትሎ ወደ ተጨማሪ ሰዓት አምርተዋል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
የጨዋታ አሰላለፍ !

4:00 ፈረንሳይ ከ ፖርቹጋል

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
118 '

ስፔን 1 - 1 ጀርመን

ኦልሞ       ፍሎሪያን ቨርትዝ

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
119 '

ስፔን 2 - 1 ጀርመን

ኦልሞ       ፍሎሪያን ቨርትዝ
ሜሪኖ

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
ስፔን ግማሽ ፍፃሜውን ተቀላቀሉ !

የስፔን ብሔራዊ ቡድን ከጀርመን ብሔራዊ ቡድን ጋር ያደረገውን የአውሮፓ ዋንጫ ሩብ ፍፃሜ ጨዋታ 2ለ1 በሆነ ውጤት በማሸነፍ ግማሽ ፍፃሜውን ተቀላቅለዋል።

የስፔን ብሔራዊ ቡድን የማሸነፊያ ግቦችን ዳኒ ኦልሞ እና ሚኬል ሜሪኖ ከመረብ ማሳረፍ ሲችሉ ለጀርመን ፍሎሪያን ቨርትዝ አስቆጥሯል።

የአውሮፓ ዋንጫው አዘጋጅ ሀገር ጀርመን ከውድድሩ ውጪ ሆነዋል።

ጨዋታው ለጀርመን ብሔራዊ ቡድን አማካይ ቶኒ ክሩስ የእግርኳስ ህይወቱ የመጨረሻ ጨዋታው ሆኗል።

በጨዋታው እንግሊዛዊው የመሐል ዳኛ አንቶኒ ቴለር አስራ ስድስት የማስጠንቀቂያ ካርዶችን እና አንድ ቀይ ካርድ መዘዋል።

ስፔን በግማሽ ፍፃሜው የፖርቹጋል እና ፈረንሳይን አሸናፊ የሚገጥሙ ይሆናል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
እረፍት

ፈረንሳይ 0 - 0 ፖርቹጋል

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
#ተጠናቀቀ

ፈረንሳይ 0 - 0 ፖርቹጋል

- ሁለቱ ብሔራዊ ቡድኖች ጨዋታቸውን በአቻ ውጤት ማጠናቀቃቸውን ተከትሎ ወደ ተጨማሪ ሰዓት አምርተዋል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
#ተጠናቀቀ

ፈረንሳይ 0 - 0 ፖርቹጋል

- ጨዋታው በአቻ ውጤት መጠናቀቁን ተከትሎ ሁለቱ ብሔራዊ ቡድኖች ወደ መለያ ምት አምርተዋል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
የመለያ ምት ተጀምሯል !

🇵🇹 ፖርቹጋል

🇫🇷 ፈረንሳይ

ውጤት በዚሁ ፖስት ላይ " Update " ይደረጋል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
ፈረንሳይ ግማሽ ፍፃሜውን ተቀላቀሉ !

የፈረንሳይ ብሔራዊ ቡድን ከፖርቹጋል አቻው ጋር ያደረገውን የአውሮፓ ዋንጫ ሩብ ፍፃሜ ጨዋታ በመለያ ምት 5ለ3 በማሸነፍ ግማሽ ፍፃሜ መድረሳቸውን አረጋግጠዋል።

በፖርቹጋል ብሔራዊ ቡድን በኩል ጇ ፊሊክስ የመለያ ምት ሳይጠቀም ቀርቷል።

ሁለቱ ብሔራዊ ቡድኖች መደበኛውን የጨዋታ ክፍለ ጊዜ ጨዋታቸውን 0ለ0 በሆነ አቻ ውጤት አጠናቀዋል።

የፈረንሳይ ብሔራዊ ቡድን የግማሽ ፍፃሜ ጨዋታውን ከስፔን ብሔራዊ ቡድን ጋር የሚያደርግ ይሆናል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
መልካም ዕድል!
ከፍ የተደረጉ ኦዶችን አይተዋል ? እንግዲያውስ ተወራረዱባቸው!
England - Switzerland
Netherlands - Turkey
ለተሻለ ውርርድ ቤቲካን ይጠቀሙ! አሁኑኑ Betika.et ላይ /በቴሌግራም ቦታችን - @BetikaETBot ይወራረዱ!
Forwarded from HEY Online Market
Play More and Spend less!

•PS4 Slim, 34,999 Birr
•PS4 PRO, 41,999 Birr
•Original Controller 6,499 Birr

Contact Us
0953964175 @heymobile

@heyonlinemarket
" ከውድድሩ መውጣታችን ያማል " ኔግልስማን

የጀርመን ብሔራዊ ቡድን ዋና አሰልጣኝ ጁሊያን ኔግልስማን ቡድኑ በስፔን ተሸንፎ ከአውሮፓ ዋንጫ ውድድር መውጣቱ " የሚያም ነበር " ሲሉ ገልጸዋል።

" በድጋሜ በምናዘጋጀው ውድድር የመሳተፍ እድል የምናገኝ አይመስለኝም " ያሉት አሰልጣኙ ከውድድሩ መውጣታችን ያማል አጨዋወታችን መጥፎ ቢሆን እንቀበለው ነበር ነገርግን ጥሩ ነው የተጫወትነው ሲሉ ተናግረዋል።

የቡድኑ የመጨረሻ ጨዋታውን ያደረገው ቶኒ ክሩስ በበኩሉ " ሁላችንም ያለምነው ህልም ቀርቷል ፣ ያለንን ሁሉ ሰጥተናል በዚህም ኩራት ይሰማናል።

ለጀርመን እግርኳስ በድጋሜ ተስፋ ሰጥተነዋል ነገርግን ከውድድሩ መውጣታችን ቅር አሰኝቶናል።"ሲል ተናግሯል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
የኢትዮጵያን ፕርሚየር ሊግ ማን ያሳካል ?

የሊጉን አሸናፊ እስከ መጨረሻው ጨዋታ ያላሳወቀው የዘንድሮው የ2016 የኢትዮጵያ ፕርሚየር ሊግ ውድድር በዛሬው ዕለት ከሚደረጉ ተጠባቂ ጨዋታዎች በኋላ አሸናፊውን ይለያል።

ፕርሚየር ሊጉን የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በስልሳ አንድ ነጥቦች እና በሀያ ስምንት ንፁህ ግቦች በበላይነት እየመራው ይገኛል።

መቻል በበኩሉ ከሊጉ መሪ በአንድ ነጥብ ዝቅ ብሎ በስልሳ ነጥቦች እና በአስራ ዘጠኝ ንፁህ ግቦች ሁለተኛ ደረጃ ላይ ተቀምጠዋል።

በሊጉ የመጨረሻ ሳምንት መርሐግብር ዛሬ ቀን 10:00 ሰዓት የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ከ ኢትዮጵያ መድን እንዲሁም መቻል ከ ድሬዳዋ ከተማ በተመሳሳይ ሰዓት የሚጫወቱ ይሆናል።

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ጨዋታውን ማሸነፍ በቀጥታ የሊጉ ሻምፒዮን ሲያደርገው ነጥብ የሚጥል ወይም የሚሸነፍ ከሆነ እና መቻሎች የሚያሸንፉ ከሆነ ሊጉን ማሳካት ይችላሉ።

የኢትዮጵያ ፕርሚየር ሊግ ውድድር አሸናፊውን በመጨረሻ ሳምንት ጨዋታ ሲለይ በውድድሩ ታሪክ ይህ ለስምንተኛ ጊዜ መሆኑ ተገልጿል።

Video Credit - Haileegziabher Adhanom

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
2024/10/02 22:34:41
Back to Top
HTML Embed Code: