Telegram Web Link
Forwarded from HEY Online Market
Stock Clearance Discount 2

📞 0925927457 @eBRO4
📞 0953964175 @heymobile

•iP 7+, Black, 128GB, 99% 12K
•iP X, Black, 256 GB, 100%,12K ⚠️
•iP XS, White, 64 GB, 100% 19K
•iP XS Max, Gold, 64GB, 83%, 25K
•iP XS Max, Gold, 256GB, 88% 29K
•iP 11, Red, 64GB, 100% 28K ⚠️
•iP 11, Black, 128GB, 85%, 33K
•iP 11, Purple, 128GB, 88% 33K
•11 Pro, Black, 64GB, 100% 39K ⚠️
•11 Pro, White, 64GB, 87% 36K
•11 Pro Max, Black, 64GB, 86%, 46K

•11 Pro Max, Black, 256GB, -% 40⚠️
•iP 12, Red, 128GB, 88%, 42K
•iP 12, White, 128GB, 88% 42K
•iP 12, Green, 128GB, 86% 42K
•12 Pro, Blue, 128GB, 89% 49K
•12 Pro Max, Blue, 512GB, 84% 64K
•iP 13 Min, Pink, 256GB, 92% 34K
•iP 13, Blueback, 128GB, 90% 56K
•iP 13, Black, 128GB, 92% 49K ⚠️

•iP 13, Red, 128GB, 86%, 56K
•iP 13, Black, 128GB, 89%, 58K
•13 Pro, Golden, 256GB, 87% 69K
•13 Pro, Blue, 512GB/88% 69K ⚠️
•13 ProMax, Black, 128 GB, 87% 74K
•13 ProMax, 256GB, 86%, 64K⚠️
•13 ProMax, 256GB, 85%, 74K⚠️
•13 ProMax, Gold, 256GB, 86%, 79K
•13 Pro Max, Gold, 256 GB,88% 79K
•13 Pro Max, Blue, 256GB, 94% 79K
•13 Pro Max, 1TB, 88%, 69K ⚠️
•13 Pro Max, Blu, 256GB/ -% 70K ⚠️

Exchange Available!
Free Delivery 🚚

@heyonlinemarket
https://heymobile.store/catalogue
ሽመልስ በቀለ 1⃣8⃣ ገስት ሀውስ

በውቢቷ ሀዋሳ ቆይታዎ የት ለማረፍ አስበዋል ? ንፁህ እና በደንበኞቻችን ተወዳጅ በሆነው የእንግዳ ማረፊያችን መጥተው የእረፍት ጊዜውን ያሳልፉ።

እንግዶቻችንን ተቀበልን ለእይታ ሳቢ በሆነው የእንግዳ ማረፊያችን ማስተናገድ ከጀመርን አመታትን አስቆጥረናል።

አድራሻችን :- ሀዋሳ አርቴፍሻል ስታዲየም መንገድ ላይ ያገኙናል።

ለተጨማሪ መረጃ እና ለትዕዛዝዎ ይደውሉልን :- 0928684848

#ShemelesBekele18
#CopaAmerica2024

የኮፓ አሜሪካ የምድብ የመጨረሻ ጨዋታዎች ሲደረጉ ብራዚል ከኮሎምቢያ ያደረገችውን ጨዋታ 1ለ1 በሆነ አቻ ውጤት አጠናቃ ኮሎምቢያን በመከተል ሁለተኛ ደረጃን በመያዝ ሩብ ፍፃሜውን ተቀላቅለዋል።

የብራዚል ብሔራዊ ቡድን በምድብ ጨዋታዎች ካደረጋቸው ሶስት ጨዋታዎች አንዱን ሲያሸንፍ በሁለቱ አቻ ተለያይተዋል።

የብራዚል ብሔራዊ ቡድን የፊት መስመር ተጨዋች ቪንሰስ ጁኒየር በምድብ ጨዋታ ሁለት የማስጠንቀቂያ ካርድ መመልከቱን ተከትሎ በቅጣት የሩብ ፍፃሜ ጨዋታ ያመልጠዋል።

በውድድሩ ምድቡን በበላይነት ማጠናቀቅ የቻሉት ሁሉም አራቱ ብሔራዊ ቡድኖች በአርጀንቲናዊያን አሰልጣኞች የሚመሩ ናቸው።

በኮፓ አሜሪካ ውድድር ታሪክ የምድቡ አሸናፊ ሁሉም ብሔራዊ ቡድኖች በአንድ ዜግነት ባላቸው አሰልጣኞች ሲመሩ ለመጀመሪያ ጊዜ መሆኑ ተገልጿል።

የሩብ ፍፃሜ ጨዋታዎች ምን ይመስላሉ ?

ሐሙስ ሌሊት 10:00 - አርጀንቲና ከ ኢኳዶር

አርብ ሌሊት 10:00 - ቬንዙዌላ ከ ካናዳ

ቅዳሜ ሌሊት 7:00 - ኮሎምቢያ ከ ፓናማ

ቅዳሜ ሌሊት 10:00 - ዩራጓይ ከ ብራዚል

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
" መሰናበታችንን ማመን አልቻልኩም "  ራኚክ

የኦስትሪያ ብሔራዊ ቡድን ዋና አሰልጣኝ ራልፍ ራኚክ ቡድናቸው ከአውሮፓ ዋንጫው ውድድር መሰናበቱን ማመን እንደከበዳቸው ገልጸዋል።

" መሰናበታችንን ማመን አልቻልኩም " ያሉት አሰልጣኝ ራልፍ ራኚክ በውድድሩ ውስጥ መቆየት ነበረብን ጨዋታው ወደ ተጨማሪ ሰዓት ቢያመራ አሸንፈን እንወጣ ነበር።"ብለዋል።

" የአቻነት ግብ ለማስቆጠር ጊዜ ነበረን በጣም ተቃርበን ነበር ነገርግን ግብ ጠባቂው ጥሩ ነበር ለማስቆጠር አስቸጋሪ ሆኖብናል ፣ የዛሬውን ጨምሮ ሁሉም ጨዋታዎቻችን አዝናኝ ነበሩ።" ራልፍ ራኚክ

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
አሰልጣኝ ስቴፋኖ ፒዮሊ ወደ ሳውዲ ሊያመሩ ነው !

በቅርቡ ከጣልያን ሴርያው ክለብ ኤሲ ሚላን ጋር የተለያዩት አሰልጣኝ ስቴፋኖ ፒዮሊ ወደ ሳውዲ አረቢያ ሊግ ለማምራት ከስምምነት መድረሳቸው ተገልጿል።

አሰልጣኝ ስቴፋኖ ፒዮሊ የሳውዲ አረቢያውን ክለብ አል ኢትሀድ ለሶስት የውድድር አመታት ለማሰልጠን ከስምምነት እንደደረሱ ተዘግቧል።

አሰልጣኝ ስቴፋኖ ፒዮሊ ከ 2019 ጀምሮ ኤሲ ሚላንን በሀላፊነት የመሩ ሲሆን ክለቡን የሴርያ ዋንጫ አሸናፊ በማድረግ ወደ ሻምፒየንስ ሊግ ውድድርም መመለስ ችለዋል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
ሚኬል አርቴታ ውላቸውን ሊያራዝሙ ነው !

ስፔናዊው አሰልጣኝ ሚኬል አርቴታ በአርሰናል ቤት ያላቸውን ኮንትራት ለተጨማሪ አመታት ለማራዘም ከክለቡ ጋር በንግግር ላይ መሆናቸው ተገልጿል።

አሰልጣኝ ሚኬል አርቴታ በአርሰናል ቤት መቆየት እና በክለቡ ለአመታት መቀጠል እንደሚፈልጉ ተዘግቧል።

መድፈኞቹ በበኩላቸው አሰልጣኝ ሚኬል አርቴታ በክለቡ በጀመሩት ስራ ደስተኞች መሆናቸው ተነግሯል።

አሰልጣኝ ሚኬል አርቴታ በቅርቡ በአርሰናል ለተጨማሪ አመታት የሚያቆያቸውን ኮንትራት በይፋ ይፈርማሉ ተብሎ እንደሚጠበቅ ተገልጿል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
TIKVAH-SPORT
ማንችስተር ዩናይትድ ስፖርቲንግ ዳይሬክተር ሾመ ! ማንችስተር ዩናይትድ የኒውካስል ዩናይትዱን ስፖርቲንግ ዳይሬክተር ዳን አሽዎርዝ በሀላፊነት ለመሾም ከኒውካስል ጋር ከስምምነት መድረሳቸውን ይፋ አድርገዋል። የ 52ዓመቱ ሀላፊ ዳን አሽዎርዝ በቀጣይ የማንችስተር ዩናይትድን የስፖርቲንግ ዳይሬክተርነት ሚና በሀላፊነት እንደሚረከቡ ይፋ ሆኗል። ኒውካስል ዩናይትድ ማንችስተር ዩናይትድ ለሀላፊው ውል ማፍረሻ…
ዳን አሽዎርዝ ምን ሀላፊነት ይሰጣቸዋል ?

የማንችስተር ዩናይትድን የስፖርቲንግ ዳይሬክተርነት ሚና የተረከቡት ዳን አሽዎርዝ በቀጣዩ የክለቡ አዲስ መዋቅር ሁሉንም የስፖርታዊ ጉዳዮች እንዲቆጣጠሩ ሀላፊነት እንደሚሰጣቸው ተገልጿል።

ሀላፊው የክለቡን አካዳሚ እና ሴቶች ቡድን ጨምሮ የህክምና ቡድኑን እና የቡድኑን የአቋም ግምገማ ክፍል ጭምር እንደሚቆጣጠሩ ተዘግቧል።

አዲሱ የቀያዮቹ ሴጣኖች ስፖርቲንግ ዳይሬክተር ዳን አሽዎርዝ ክለቡ ከማንችስተር ሲቲ ላመጣው ዋና ስራ አስፈፃሚው ኦማር ቤራዳ ሪፖርት እንደሚያደርጉ ተነግሯል።

አሰልጣኝ ኤሪክ ቴንሀግ በበኩላቸው ክለቡ በሚያስፈርማቸው ተጨዋቾች ላይ ሀላፊነት እንደሚኖራቸው እና ያለፍቃዳቸው የትኛውም ተጨዋች ለቡድኑ እንደማይፈርም ተገልጿል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
መሐመድ ሳላህ በኦሎምፒክ አይሳተፍም !

ግብፃዊው የሊቨርፑል የፊት መስመር ተጨዋች መሐመድ ሳላህ በቀጣዩ የፓሪስ ኦሎምፒክ ውድድር እንደማይሳተፍ ተገልጿል።

በተጨማሪም የመርሲሳይዱ ክለብ ሊቨርፑል ጃፓናዊውን ተጨዋች ዋታሩ ኢንዶ ለኦሎምፒክ ውድድር ለመላክ ፍቃደኛ ሳይሆኑ መቅረታቸው ተነግሯል።

የግብፅ እና ጃፓን እግርኳስ ፌዴሬሽኖች ተጨዋቾቹን በኦሎምፒክ ቡድናቸው ለማካተት ከሊቨርፑል ጋር ንግግር ሲያደርጉ ነበር።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
ኤቨርተን ተጨዋች አስፈርመዋል !

የመርሲሳይዱ ክለብ ኤቨርተን ሴኔጋላዊውን የፊት መስመር ተጨዋች ኢሊማን ንድያዬ ከፈረንሳዩ ክለብ ማርሴይ ማስፈረማቸውን ይፋ አድርገዋል።

የ 24ዓመቱ የፊት መስመር ተጨዋች ኢሊማን ንድያዬ በኤቨርተን ቤት የአምስት አመት ኮንትራት መፈረሙ ተገልጿል።

ለተጨዋቹ ዝውውር ኤቨርተን አጠቃላይ 20 ሚልዮን ዩሮ የሚደርስ የዝውውር ሒሳብ ማውጣታቸው ተዘግቧል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
እንግሊዛዊያን ዳኞች ጨዋታዎች ይመራሉ !

የፊታችን አርብ የሚደረጉ ሁለት የአውሮፓ ዋንጫ ሩብ ፍፃሜ ጨዋታዎችን እንግሊዛዊያን ዳኞች በመሐል ዳኝነት እንዲመሩ መመረጣቸው ተገልጿል።

አርብ ምሽት 1:00 የሚደረገውን የስፔን እና ጀርመን ተጠባቂ ጨዋታ አንቶኒ ቴለር እንደሚመሩት ይፋ ሆኗል።

እንዲሁም ምሽት 4:00 የሚደረገውን የፈረንሳይ እና ፖርቹጋል ተጠባቂ ጨዋታ ማይክል ኦሊቨር እንዲመሩ መመረጣቸው ተገልጿል።

ጨዋታዎቹን እነማን ያሸንፋሉ ?

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
TIKVAH-SPORT
ባየር ሙኒክ ተጨዋች ለማስፈረም ተስማማ ! የጀርመን ቡንደስሊጋው ክለብ ባየር ሙኒክ የፉልሀሙን የመሐል ሜዳ ተጨዋች ጇ ፓልሂንሀ ለማስፈረም ከተጨዋቹ ጋር ከስምምነት መድረሳቸው ተገልጿል። ባየር ሙኒክ ፖርቹጋላዊውን የመሐል ሜዳ ተጨዋች ጇ ፓልሂንሀን ለማስፈረም እስከ 45 ሚልዮን ዩሮ የሚደርስ የዝውውር ሒሳብ ሊያወጡ እንደሚችሉ ተነግሯል። የ 28ዓመቱ ተጨዋች በዚህ አመት በሊጉ ለፉልሀም ባደረጋቸው…
የባየር ሙኒክ ጥያቄው ተቀባይነት አገኘ !

የጀርመን ቡንደስሊጋው ክለብ ባየር ሙኒክ የፉልሀሙን የመሐል ሜዳ ተጨዋች ጇ ፓልሂንሀ ለማስፈረም ከክለቡ ጋር ከስምምነት መድረሳቸው ተገልጿል።

ከተጨዋቹ ጋር ቀደም ብለው በግል ከስምምነት የደረሱት ባየር ሙኒኮች አሁን ላይ ለፉልሀም ያቀረቡት 56 ሚልዮን ዩሮ የሚደረሰስ ሒሳብ ተቀባይነት ማግኘቱ ተገልጿል።

ፉልሀም ከተጨዋቹ ዝውውር የሚያገኙት 51 ሚልዮን ዩሮ ክፍያ እና 5 ሚልዮን ዩሮ ታይቶ የሚጨምር ገንዘብ የክለቡ ሪከርድ ሽያጭ ሆኖ መመዝገቡ ተነግሯል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
ሀዋሳ ከተማ አመቱን በድል አጠናቋል !

በኢትዮጵያ ፕርሚየር ሊግ የመጨረሻ ሳምንት መርሐ ግብር ሀዋሳ ከተማ ወላይታ ድቻ ጋር ያደረጉትን ጨዋታ 2ለ0 በሆነ ውጤት አሸንፈዋል።

የሀዋሳ ከተማን የማሸነፊያ ግቦች ዓሊ ሱሌይማን 2x ከመረብ ማሳረፍ ችሏል።

ኤርትራዊው የሀዋሳ ከተማ አጥቂ ዓሊ ሱሌይማን በውድድር አመቱ ያስቆጠራቸውን የሊግ ግቦች ሀያ ማድረስ ችሏል።

የሊጉ ደረጃቸው ምን ይመስላል ? 

8️⃣ ሀዋሳ ከተማ :- 41 ነጥብ

1️⃣3️⃣ ወላይታ ድቻ :- 34 ነጥብ

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
" ዋንጫውን ለማሸነፍ ያለንን ሁሉ እንሰጣለን " ዣካ

የስዊዘርላንድ ብሔራዊ ቡድን አምበል ግራኒት ዣካ ቡድናቸው የአውሮፓ ዋንጫውን ለማሸነፍ ያለውን ሁሉ እንደሚሰጥ በሰጠው አስተያየት ገልጿል።

ግራኒት ዣካ በንግግሩም " የአውሮፓ ዋንጫውን እናሸንፋለን ብዬ ማረጋገጥ ባልችልም ዋንጫውን ለማሳካት የቻልነውን ሁሉ እንደምናደርግ ግን ቃል አገባላችኋለሁ " ሲሉ ለደጋፊዎቹ ተናግሯል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
🔊 ልዩ ቅናሹ 6 ቀናት ብቻ ቀሩት!

👉🏾 እሰከ ሐምሌ 1 በዋናው አዲስ የቴሌግራም ቦት የስፖርት ትጥቆችን በማዘዝ ልዩ የ5% ቅናሽን ይጠቀሙ።

🤖 @WanawSportBot 🤖

👉🏾 #ዛሬም እንዳያመልጥዎ፣ ይዘዙን!

🏅ዋናው ወደፊት...

@wanawsportwear
Betika Eth-Bunna Matchday Magazine [Vol. 25].pdf
36.2 MB
የኢትዮጵያ  ቡና ይፋዊ አጋር የሆነው ቤቲካ - የኢትዮጵያ ቡናን  25ኛ የጨዋታ ቀን የዲጂታል መፅሄት ይዞ ቀርቧል።

በመፅሄቱ ላይ የዕለቱ ጨዋታን የተመለከቱና ሌሎች የተለያዩ መረጃዎች የሚቀርቡ ይሆናል፡፡

የጨዋታ መፅሄት ቁጥር 25
ሀድያ ሆሳዕና ከ ኢትዮጵያ ቡና

ቤቲካ - የኢትዮጵያ ቡና ይፋዊ አጋር
ኢፕስዊች ታውን ተጨዋቾች ለማስፈረም ጠይቀዋል !

በዚህ አመት ወደ እንግሊዝ ፕርሚየር ሊግ ያደገው ኢፕስዊች ታውን ከሀል ሲቲ ጃኮፕ ግሬቭስ እና ጃደን ፊሎጌኔን ለማስፈረም ጥያቄ ማቅረባቸው ተገልጿል።

ኢፕስዊች ታውን ሁለቱን ተጨዋቾች ለማስፈረም ለሀል ሲቲ 35 ሚልዮን ፓውንድ የዝውውር ሒሳብ ማቅረባቸው ተነግሯል።

በተጨዋቾቹ ዝውውር ዙሪያ በሁለቱ ክለቦች መካከል የሚደረገው ንግግር አሁንም መቀጠሉ ተገልጿል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
" ቶኒ ክሩስን አርብ ወደ ጡረታው እንሸኘዋለን " ሆሴሉ

የስፔን ብሔራዊ ቡድን የፊት መስመር ተጨዋች ሆሴሉ ቶኒ ክሩስ አርብ የመጨረሻ ጨዋታውን እንደሚያደርግ በሰጠው አስተያየት ተናግሯል።

" ከክሩስ ጋር መጫወት ለእኔ ክብር ነው የመልበሻ ቤት ጓደኛዬ ነበር ብዙ ነገሮችን አግዞኛል ብዙ ምክረም ሰጥቶኛል እሱን ማመስገን እፈልጋለሁ።"ሲል ሆሴሉ ተናግሯል።

" እሱ የማድሪድም ሆነ የጀርመን ቁልፍ ተጨዋች ነው " የሚለው ሆሴሉ ክሩስን እወደዋለሁ ነገርግን አርብ የመጨረሻ ጨዋታው ይሆናል ወደ ጡረታው እንሸኘዋለን።"ብሏል።

ቶኒ ክሩስ በበኩሉ በሰጠው አስተያየት " የአርቡ ጨዋታ የመጨረሻ ጨዋታዬ እንደማይሆን ተስፋ አደርጋለሁ።"ሲል በሰጠው አስተያየት ተናግሯል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
ዩናይትድ ሰራተኞቹን ሊያሰናብት ነው !

ማንችስተር ዩናይትድ አዲሱ የውድድር ዘመን ከመጀመሩ በፊት የክለቡን ሰራተኞች ለመቀነስ ማሰባቸውን አሳውቀዋል።

ቀያዮቹ ሴጣኖች ካሏቸው 1,100 የክለቡ ሰራተኞች ሩብ የሚሆኑትን ከሁለት መቶ ሀምሳ በላይ ሰራተኞች ለማሰናበት ማሰባቸው ተገልጿል።

ክለቡ ይህንን የሚያደርገው ወጪዎቹን ለመቆጠብ እና ከሰራተኞቹ ጋር ተለያይቶ የሚያተርፈውን ገንዘብ በዋናው ቡድን ላይ በማዋል የፋይናንሻል ፌር ፕሌይ ህግን ለማስተካከል መሆኑ ተነግሯል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
ሪካርዶ ካላፊዮሪ አርሰናልን መቀላቀል ይፈልጋል !

የሰሜን ለንደኑ ክለብ አርሰናል ጣልያናዊውን የቦሎኛ የተከላካይ ስፍራ ተጨዋች ሪካርዶ ካላፊዮሪ ለማስፈረም ጥረት በማድረግ ላይ መሆናቸው ተገልጿል።

መድፈኞቹ ለተጨዋቹ የዝውውር ጥያቄያቸውን ማቅረባቸው የተገለፀ ሲሆን በቀጣይ ከቦሎኛ ጋር የሚስማሙ ከሆነ ተጨዋቹ አርሰናልን ለመቀላቀል እንደሚፈልግ ተነግሯል።

ከአርሰናል በተጨማሪም የምዕራብ ለንደኑ ክለብ ቼልሲ ሪካርዶ ካላፊዮሪን ለማስፈረም ንግግር ላይ እንደሚገኙ ተገልጿል።

ቦሎኛ ለተጨዋቹ ዝውውር እስከ 50 ሚልዮን ዩሮ የዝውውር ሒሳብ ሊጠይቁ እንደሚችሉ ተነግሯል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
ሀድያ ሆሳዕና አመቱን በድል አጠናቋል !

በኢትዮጵያ ፕርሚየር ሊግ የመጨረሻ ሳምንት መርሐ ግብር ሀድያ ሆሳዕና ከኢትዮጵያ ቡና ጋር ያደረጉትን ጨዋታ 2ለ1 በሆነ ውጤት አሸንፈዋል።

የሀድያ ሆሳዕናን የማሸነፊያ ግቦች የኋላሸት ሰለሞን 2x ከመረብ ማሳረፍ ሲችል ለኢትዮጵያ ቡና አንተነህ ተፈራ አስቆጥሯል።

የሊጉ ደረጃቸው ምን ይመስላል ? 

3️⃣ ኢትዮጵያ ቡና :- 51 ነጥብ

8️⃣ ሀድያ ሆሳዕና :- 41 ነጥብ

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
2024/12/24 19:01:41
Back to Top
HTML Embed Code: