Telegram Web Link
" ዋንጫውን ለሮናልዶ ስጦታ መስጠት እንፈልጋለን " ሜንዴዝ

የፖርቹጋል ብሔራዊ ቡድን ተከላካይ ኑኖ ሜንዴዝ ቡድናቸው የአውሮፓ ዋንጫውን አሸንፎ ለክርስቲያኖ ሮናልዶ ስጦታ ማበርከት እንደሚፈልግ ተናግሯል።

የአውሮፓ ዋንጫው ለክርስትያኖ ሮናልዶ የመጨረሻው መሆኑን የገለፀው ኑኖ ሜንዴዝ " ዋንጫውን አሸንፈን ለሮናልዶ በስጦታነት ለማበርከት ሁሉንም ነገር እናደርጋለን " በማለት ተናግሯል።

" ኪሊያን ምባፔን ማስቆም በጣም ከባድ ነው ነገርግን እኔ የተወሰነ አውቀዋለሁ እሱን ለማስቆም የቻልኩትን ሁሉ አደርጋለሁ።" ኑኖ ሜንዴዝ

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
" ከባድ ጨዋታ ይሆናል " ጀማል ሙሲያላ

የጀርመን ብሔራዊ ቡድን የመሐል ሜዳ ተጨዋች ጀማል ሙሲያላ ቡድናቸው አርብ ምሽት ከስፔን ጋር የሚያደርገው የሩብ ፍፃሜ ጨዋታ ከባድ እንደሚሆን ተናግሯል።

" ጨዋታው ከባድ ይሆናል ሁለቱም ብሔራዊ ቡድኖች ፍፃሜ የመድረስ ችሎታ አላቸው እኛ ጨዋታውን ማሸነፍ እንደምንችል በራሳችን ማመን አለብን።" ሲል ሙሲያላ ተናግሯል።

" ስፔን እንደ ላሚን ያማል ፣ ፔድሪ እና ኒኮ ዊሊያምስ ያሉ አደገኛ ተጨዋቾች አሏቸው ጨዋታውን መወሰን ይችላሉ ፣ ነገርግን እኛም እንደነሱው ልዩ ተጨዋቾች አሉን በራሳችን እናምናለን።" ጀማል ሙሲያላ

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
Forwarded from HEY Online Market
Stock Clearance Discount 2

📞 0925927457 @eBRO4
📞 0953964175 @heymobile

•iP 7+, Black, 128GB, 99% 12K
•iP X, Black, 256 GB, 100%,12K ⚠️
•iP XS, White, 64 GB, 100% 19K
•iP XS Max, Gold, 64GB, 83%, 25K
•iP XS Max, Gold, 256GB, 88% 29K
•iP 11, Red, 64GB, 100% 28K ⚠️
•iP 11, Black, 128GB, 85%, 33K
•iP 11, Purple, 128GB, 88% 33K
•11 Pro, Black, 64GB, 100% 39K ⚠️
•11 Pro, White, 64GB, 87% 36K
•11 Pro Max, Black, 64GB, 86%, 46K

•11 Pro Max, Black, 256GB, -% 40⚠️
•iP 12, Red, 128GB, 88%, 42K
•iP 12, White, 128GB, 88% 42K
•iP 12, Green, 128GB, 86% 42K
•12 Pro, Blue, 128GB, 89% 49K
•12 Pro Max, Blue, 512GB, 84% 64K
•iP 13 Min, Pink, 256GB, 92% 34K
•iP 13, Blueback, 128GB, 90% 56K
•iP 13, Black, 128GB, 92% 49K ⚠️

•iP 13, Red, 128GB, 86%, 56K
•iP 13, Black, 128GB, 89%, 58K
•13 Pro, Golden, 256GB, 87% 69K
•13 Pro, Blue, 512GB/88% 69K ⚠️
•13 ProMax, Black, 128 GB, 87% 74K
•13 ProMax, 256GB, 86%, 64K⚠️
•13 ProMax, 256GB, 85%, 74K⚠️
•13 ProMax, Gold, 256GB, 86%, 79K
•13 Pro Max, Gold, 256 GB,88% 79K
•13 Pro Max, Blue, 256GB, 94% 79K
•13 Pro Max, 1TB, 88%, 69K ⚠️
•13 Pro Max, Blu, 256GB/ -% 70K ⚠️

Exchange Available!
Free Delivery 🚚

@heyonlinemarket
https://heymobile.store/catalogue
ሽመልስ በቀለ 1⃣8⃣ ገስት ሀውስ

በውቢቷ ሀዋሳ ቆይታዎ የት ለማረፍ አስበዋል ? ንፁህ እና በደንበኞቻችን ተወዳጅ በሆነው የእንግዳ ማረፊያችን መጥተው የእረፍት ጊዜውን ያሳልፉ።

እንግዶቻችንን ተቀበልን ለእይታ ሳቢ በሆነው የእንግዳ ማረፊያችን ማስተናገድ ከጀመርን አመታትን አስቆጥረናል።

አድራሻችን :- ሀዋሳ አርቴፍሻል ስታዲየም መንገድ ላይ ያገኙናል።

ለተጨማሪ መረጃ እና ለትዕዛዝዎ ይደውሉልን :- 0928684848

#ShemelesBekele18
TIKVAH-SPORT
ዋልያዎቹ የምድብ ተጋጣሚያቸውን መቼ ያውቃሉ ? በሞሮኮ አዘጋጅነት ለሚካሄደው የ 2025 አፍሪካ ዋንጫ ውድድር የማጣርያ ጨዋታ ምድብ ድልድል የሚካሄድበት ቀን ታውቋል። ብሔራዊ ቡድኖች የምድብ ተጋጣሚያቸውን ሐሙስ ሰኔ 27/2016 ዓ.ም በደቡብ አፍሪካ ጆሀንስበርግ በሚደረገው የእጣ ማውጣት ስነ ስርዓት እንደሚያውቁ ይፋ ተደርጓል። በምድብ ድልድሉ የቅድመ ማጣሪያውን ያለፉ አራት ሀገራትን ጨምሮ አርባ…
ዋልያዎቹ ተጋጣሚያቸውን ዛሬ ያውቃሉ !

በሞሮኮ አዘጋጅነት ለሚካሄደው የ 2025 አፍሪካ ዋንጫ ውድድር የማጣርያ ጨዋታ ምድብ ድልድል በዛሬው ዕለት በደቡብ አፍሪካ ጆሀንስበርግ ቀን 9:30 ሰዓት በሚደረግ የእጣ ማውጣት ስነ ስርዓት ይፋ ይደረጋል።

በምድብ ድልድሉ የቅድመ ማጣሪያውን ያለፉ አራት ሀገራትን ጨምሮ አርባ ስምንት ብሔራዊ ቡድኖች እንደሚካተቱ ተገልጿል።

በአስራ ሁለት ምድብ ተክፈለው የማጣሪያ ጨዋታቸውን የሚያደርጉት ብሔራዊ ቡድኖቹ የምድብ አንደኛ እና ሁለተኛ የመጀመሪያ ሀያ አራት ቡድኖች ለአፍሪካ ዋንጫው የሚያልፉ ይሆናል።

የማጣሪያ ጨዋታዎቹ ከሚቀጥለው አመት መስከረም ወር ጀምሮ መካሄዳቸውን ይጀምራሉ ተብሎ ይጠበቃል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
" ሊጉን ለማሸነፍ የበለጠ ጠንክረን እንመጣለን " ኦዴጋርድ

የሰሜን ለንደኑ ክለብ አርሰናል አምበል ማርቲን ኦዴጋርድ ቡድናቸው በሚቀጥለው የውድድር ዘመን ሊጉን ለማሸነፍ የበለጠ ጠንክሮ እንደሚመጣ በሰጠው አስተያየት ተናግሯል።

" ያለፈው አመት ጥሩ ነበርን ነገርግን ሊጉን ለማሸነፍ በቂ አልነበረም " ያለው ማርቲን ኦዴጋርድ በቀጣይ የበለጠ ጠንክረን እንመለሳለን ሊጉን ለማሸነፍ በጋራ እንሰራለን ጥሩ አመት እናሳልፋለን ብዬ አስባለሁ።"ሲል ተናግሯል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
TIKVAH-SPORT
" አቡበከር ናስር የማሜሎዲ ሰንዳውንስ ተጨዋች አይደለም " ሩላኒ ሞክዌና በደቡብ አፍሪካ ሊግ ለማሜሎዲ ሰንዳውንስ የሚጫወተው ኢትዮጵያዊው የፊት መስመር ተጨዋች አቡበከር ናስር አሁን ላይ የክለቡ ተጨዋች አለመሆኑን አሰልጣኝ ሩላኒ ሞክዌና ተናግረዋል። የማሜሎዲ ሰንዳውንስ ዋና አሰልጣኝ ሩላኒ ሞክዌና ትላንት ምሽት ከሀገሪቱ መገናኛ ብዙሀን ጋር ባደረጉት ቆይታ ስለ አቡበከር ናስር የክለቡ ሁኔታ ተጠይቀው…
የአቡበከር ናስር የማሜሎዲ ሰንዳውንስ ሁኔታ ?

በጉዳት ለረጅም ጊዜ ከሜዳ ርቆ የቆየው ኢትዮጵያዊው የፊት መስመር አጥቂ አቡበከር ናስር አሁን ላይ ክለቡ በግሉ መጠነኛ ልምምድ ማድረግ እንዲጀምር ማድረጉ ተገልጿል።

በትላንትናው ዕለት ከክለቡ ጋር በይፋ የተለያዩት የማሜሎዲ ሰንዳውንስ ዋና አሰልጣኝ ሩላኒ ሞክዌና በቅርቡ " አቡበከር ናስር የእኛ ተጨዋች አይደለም "  የሚል አስተያየት ሰጥተው ነበር።

አሰልጣኝ ሩላኒ ሞክዌና ስለ አቡበከር ናስር የሰጡት አስተያየት የክለቡን ጥቅም ያላስጠበቀ እና አላስፈላጊ ነው በሚል የክለቡን ቦርድ አለማስደሰቱ ተዘግቧል።

አቡበከር ናስር ባለፉት ወራት ያጋጠሙት ተደጋጋሚ ከባድ ጉዳቶች እንዲሁም ተጨማሪ ጉዳት ያጋጥመዋል የሚሉ ስጋቶች በፍጥነት ወደ ሜዳ እንዳይመለስ እና የማገገሚያ ጊዜው እንዲረዝም እንዳደረገው ተነግሯል።

ማሜሎዲ ሰንዳውንስ ከቀናት በፊት ከክለቡ ጋር የሚለያዩ ተጨዋቾችን በማህበራዊ ትስስር ገፁ ይፋ ሲያደርግ አቡበከር ናስር እንዳልተካተተ አይዘነጋም።

ምንጭ - መኳንንት በርሄ ፖድካስት

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
የሮማንያ ተጨዋቾች መልበሻ ቤቱን አፅድተዋል !

በኔዘርላንድ ተሸንፈው ከአውሮፓ ዋንጫው የተሰናበቱት የሮማንያ ብሔራዊ ቡድን ተጨዋቾች ከጨዋታው በኋላ መልበሻ ቤቱን አፅድተው ወደነበርንበት መልሰው መሄዳቸው ተገልጿል።

የብሔራዊ ቡድኑ ተጨዋቾች መልበሻ ቤቱን ካፀዱ በኋላም በጀርመን በነበራቸው ቆይታ ለተደረገላቸው አቀባበል የምስጋና የፅሁፍ መልዕክት ማስቀመጣቸው ተዘግቧል።

ሮማንያ የአውሮፓ ዋንጫ የጥሎ ማለፍ ጨዋታዋን በኔዘርላንድ 3ለ0 ተሸንፋ ከውድድሩ መሰናበቷ አይዘነጋም።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
ፈርጉሰን ሮናልዶ በቀጣይ ሊከብደው እንደሚችል ገለጹ !

የቀድሞ የማንችስተር ዩናይትድ ታሪክ አይሽሬ አሰልጣኝ ሰር አሌክስ ፈርጉሰን ክርስቲያኖ ሮናልዶ በቀጣዩ አለም ዋንጫ ውድድር መሳተፍ ሊከብደው እንደሚችል ገልፀዋል።

ፖርቹጋላዊው ተጨዋች ክርስቲያኖ ሮናልዶ በቀጣዩ የ2026 የአለም ዋንጫ ውድድር ስለመሳተፍ ሊያስብ እንደሚችል እየተዘገበ ይገኛል።

በጉዳዩ ላይ አስተያየታቸውን የሰጡት ሰር አሌክስ ፈርጉሰን " በቀጣይ እግርኳስ ፈጣን ይሆናል " ያሉ ሲሆን በተለይ በእድሜ ለሚገፉ ተጨዋቾች በትልቅ ደረጃ መጫወት ሊከብዳቸው ይችላል " ብለዋል።

" ሮናልዶ ከምንግዜም ምርጥ ተጨዋቾች አንዱ ነው ፣ ከዚህ በኋላ ማረጋገጥ የሚያስፈልገው ነገር የለም፣ አንድ ወይም ሁለት ዋንጫ የሚጨምርለት ነገር የለም አሁንም ልዩ የእግርኳስ ህይወት ነው ያለው ውሳኔው የእሱ ነው።" ፈርጉሰን

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
TIKVAH-SPORT
ኤሪክ ቴንሀግ ውላቸውን ለማራዘም ተቃርበዋል ! ኔዘርላንዳዊው አሰልጣኝ ኤሪክ ቴንሀግ በማንችስተር ዩናይትድ ቤት ያላቸውን ኮንትራት ለተጨማሪ አመታት ለማራዘም ለስምምነት መቃረባቸው ተገልጿል። ማንችስተር ዩናይትድ በቅርቡ ባሳለፈው ውሳኔ አሰልጣኝ ኤሪክ ቴንሀግን ለማቆየት መወሰኑ እና ውላቸውን ለማራዘም ንግግር መጀመሩ እንደተገለፀ ይታወሳል። አሰልጣኝ ኤሪክ ቴንሀግ በቀጣይ የአሰልጣኞች ቡድን ለውጥ…
አሰልጣኝ ኤሪክ ቴንሀግ ውላቸውን አራዘሙ !

ኔዘርላንዳዊው አሰልጣኝ ኤሪክ ቴንሀግ በማንችስተር ዩናይትድ ቤት ያላቸውን ኮንትራት ለተጨማሪ አመታት ማራዘማቸው ይፋ ተደርጓል።

በቅርቡ በክለቡ ለመቆየት ከስምምነት የደረሱት አሰልጣኝ ኤሪክ ቴንሀግ በቀጣይ እስከ 2026 ለመቆየት ውላቸውን ማራዘማቸው ተገልጿል።

" በክለቡ ለመቆየት ውሌን በማራዘሜ ተደስቻለሁ ባለፉት አመታት በነበሩን እድገቶች መኩራት እንችላለን ፣ ቢሆንም ብዙ መስራት ያሉብን ነገሮች እንዳሉ እናውቃለን።"ሲሉ ኤሪክ ቴንሀግ ተናግረዋል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
የጣሊያን ሴርያ መርሐግብር ይፋ ሆነ !

የጣሊያን ሴርያ የ2024/25 የውድድር ዘመን የጨዋታ መርሐ ግብሮች ይፋ ተደርገዋል።

በመጀመሪያ ሳምንት መርሐግብር የወቅቱ የሴርያው ሻምፒዮን ኢንተር ሚላን ከጂኖኣ ፣ ጁቬንቱስ ከኮሞ ፣ ኤሲ ሚላን ከቶሪኖ እንዲሁም ናፖሊ ከሄላስ ቬሮና ጋር ይገናኛሉ።

ተጠባቂው የኤሲ ሚላን እና ኢንተር ሚላን የመጀመሪያው የሚላን ደርቢ ጨዋታ በሊጉ የአምስተኛ ሳምንት መርሐግብር እንደሚደረግ ተገልጿል።

የ2024/25 የውድድር ዘመን የጣልያን ሴርያ እሁድ ነሐሴ 12/2016 ዓ.ም የሚጀምር ይሆናል።

*የመጀመሪያ ሳምንት ሙሉ መርሐ ግብር ከላይ በምስሉ ላይ ተያይዘዋል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
TIKVAH-SPORT
ዋልያዎቹ ተጋጣሚያቸውን ዛሬ ያውቃሉ ! በሞሮኮ አዘጋጅነት ለሚካሄደው የ 2025 አፍሪካ ዋንጫ ውድድር የማጣርያ ጨዋታ ምድብ ድልድል በዛሬው ዕለት በደቡብ አፍሪካ ጆሀንስበርግ ቀን 9:30 ሰዓት በሚደረግ የእጣ ማውጣት ስነ ስርዓት ይፋ ይደረጋል። በምድብ ድልድሉ የቅድመ ማጣሪያውን ያለፉ አራት ሀገራትን ጨምሮ አርባ ስምንት ብሔራዊ ቡድኖች እንደሚካተቱ ተገልጿል። በአስራ ሁለት ምድብ ተክፈለው የማጣሪያ…
#AFCON2025 🇲🇦

የ2025 የሞሮኮ አፍሪካ ዋንጫ ውድድር ማጣሪያ ምድብ ድልድል ከሰዓታት በኋላ በሚደረግ የእጣ ማውጣት ስነ ስርዓት ይካሄዳል።

በማጣሪያው የሚሳተፉ ብሔራዊ ቡድኖች በፊፋ ወርሀዊ ደረጃ መሰረት በአራት ቋት ሲከፈሉ ኢትዮጵያ በመጨረሻው ቋት ትገኛለች።

በምድብ ድልድሉ ኢትዮጵያ ከቀሪ ሶስት ቋቶች ውስጥ ከሚወጣጡ ሶስት ብሔራዊ ቡድኖች ጋር የምትደለደል ይሆናል።

የምድቡን አንደኛ እና ሁለተኛ ደረጃ ይዘው የሚያጠናቅቁ ብሔራዊ ቡድኖች ወደ ሞሮኮ የሚያመሩ ይሆናል።

አዘጋጇ ሀገር ሞሮኮ በምን መልኩ ወደ ውድድሩ ታልፋለች ?

የውድድሩ አዘጋጅ ሞሮኮ ምድቧን አንደኛ ወይም ሁለተኛ ሆና #የማታጠናቅቅ ከሆነ የምድቡን ሁለተኛ ደረጃ የሚይዘው ብሔራዊ ቡድን በውድድሩ የማይሳተፍ ይሆናል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
👋🏾 ሰላም! ለታማኝነትዎ እንሸልምዎ!

🤩 የቤቲካ ታማኝ ደንበኞች በየቀኑ እስከ 5000 ነጥቦችን ይሰበስባሉ።

👉🏾 እርሶም Betika.et ላይ ተቀላቀሏቸው።

ቤቲካ የአሸናፊዎች ቤት!
Forwarded from WANAW SPORT
📢 ልዩ ቅናሹ 5 ቀናት ቀሩት!

📌 እሰከ ሐምሌ 1 ብቻ በዋናው አዲስ የቴሌግራም ቦት የስፖርት ትጥቆችን በማዘዝ ልዩ የ5% ቅናሽን ያግኙ።

👉🏾 @WanawSportBot 👈🏾

📌 #እንዳያመልጥዎ፣ ይዘዙን!

🏅ዋናው ወደፊት...

@wanawsportwear
" ቡድኑን ለማጠናከር እየሰራን ነው  " አርቴታ

የሰሜን ለንደኑ ክለብ አርሰናል በቀጣይ በሁሉም የሜዳ ክፍሎች ቡድኑን ለማጠናከር እየተንቀሳቀሰ እንደሚገኝ አሰልጣኝ ሚኬል አርቴታ ገልጸዋል።

" ልናጠናክራቸው የሚገቡ ነገሮች አሉን " ያሉት አሰልጣኝ ሚኬል አርቴታ እየተመለከትን እንገኛለን በሁሉም ቦታዎች ላይ ህጉን አክብረን ቡድኑን ለማጠናከር ጥረት እናደርጋለን ብለዋል።

" በኮንትራት ማራዘም ዙሪያ የምናገረው አዲስ ነገር የለም ያልተቀየረ ነገር ቢኖር እዚህ በመሆኔ ደስተኛ መሆኔ እና አርሰናልን ማሰልጠኔን ምን ያህል እንደምወደው ነው።" አርቴታ

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
ጁድ ቤሊንግሀም ቅጣት አይጣልበትም !

የእንግሊዝ ብሔራዊ ቡድን ተጨዋች ጁድ ቤሊንግሀም ቡድኑ ስሎቫኪያን ባሸነፈበት ምሽት የተጋጣሚ የቡድን አባላት ላይ ያነጣጠረ ያልተገባ ድርጊት አሳይቷል በሚል ምርመራ ተደርጎበት ነበር።

አሁን ላይ የአውሮፓ እግርኳስ ማህበር ጁድ ቤሊንግሀም ላይ የቅጣት ውሳኔ እንደማይጥል እና ለስዊዘርላንዱ የሩብ ፍፃሜ ጨዋታ ዝግጁ እንደሚሆን ተገልጿል።

ጁድ ቤሊንግሀም በሰዓቱ ያደረገው ነገር የተጋጣሚ አባላትን ክብር ለመንካት እና እነሱ ላይ ያነጣጠረ እንዳልሆነ እና ትልቅ ክብርም እንዳለው በማህበራዊ ትስስር ገፁ ገልፆ ነበር።

እንግሊዝ ቅዳሜ ምሽት 1:00 ከስዊዘርላንድ አቻዋ ጋር የሩብ ፍፃሜ ጨዋታዋን የምታደርግ ይሆናል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
ኢትዮጵያ የምድብ ተጋጣሚዎቿን አውቃለች !

የ2025 የሞሮኮ አፍሪካ ዋንጫ ውድድር ማጣሪያ ምድብ ድልድል ከደቂቃዎች በፊት በደቡብ አፍሪካ ጁሀንስበርግ በተደረገ የእጣ ማውጣት ስነ-ስርዓት ይፋ ተደርጓል።

በዚህም መሰረት የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን በምድብ ስምንት

- #ታንዛኒያ

- #ጊኒ እና

- #ኮንጎ ጋር ተደልድሏል።

በደርሶ መልስ በሚደረግ ጨዋታ የምድቡን አንደኛ እና ሁለተኛ ደረጃ ይዘው የሚያጠናቅቁ ብሔራዊ ቡድኖች ለአፍሪካ ዋንጫው ያልፋሉ።

የማጣሪያ ጨዋታዎቹ ከሚቀጥለው አመት መስከረም ወር ጀምሮ መካሄዳቸውን ይጀምራሉ ተብሎ ይጠበቃል።

*ሙሉ የምድብ ድልድሉ ከላይ በምስሉ ላይ ተያይዟል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
" አንቶኒዮ ሩዲገር አያስፈራንም "  ፔድሪ

የስፔን ብሔራዊ ቡድን የመሐል ሜዳ ተጨዋች ፔድሪ የነገ ተጋጣሚያቸው ጀርመን ተከላካይ አንቶኒዮ ሩዲገር እንደማያስፈራቸው ገልጿል።

ፔድሪ በንግግሩም " አንቶኒዮ ሩዲገር ጠንካራ እና ምርጥ ተከላካይ ነው " ሲል የተደመጠ ሲሆን " ነገርግን እሱ እኛን አያስፈራንም " በማለት ገልጿል።

ስፔን ከጀመርን ጋር ነገ ምሽት 1:00 ሰዓት የሩብ ፍፃሜ ጨዋታቸውን የሚያደርጉ ይሆናል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
ፈረሰኞቹ አመቱን በድል አጠናቀዋል !

በኢትዮጵያ ፕርሚየር ሊግ የመጨረሻ ሳምንት መርሐ ግብር ቅዱስ ጊዮርጊስ ከፋሲል ከነማ ጋር ያደረጉትን ጨዋታ 4ለ0 በሆነ ውጤት አሸንፈዋል።

የፈረሰኞቹን የማሸነፊያ ግቦች አማኑኤል ኤርቦ 2x ፣ ተገኑ ተሾመ እና ዳዊት ተፈራ ከመረብ ማሳረፍ ችለዋል።

ቅዱስ ጊዮርጊስ በውድድር ዘመኑ አስራ ሶስት ጨዋታ አሸንፎ ዘጠኝ አቻ ወጥቶ ስምንት ተሸንፎ አጠናቋል።

ፋሲል ከነማ በበኩሉ አስራ አንድ አሸንፎ አስራ አንድ አቻ ተለያይቶ በስምንቱ ተሸንፎ አጠናቀዋል።

የቅዱስ ጊዮርጊሱ የፊት መስመር አጥቂ አማኑኤል ኤርቦ በክለቡ የመጀመሪያ አመት ቆይታው አስራ ሶስት የሊግ ግቦችን በማስቆጠር አጠናቋል።

የሊጉ ደረጃቸው ምን ይመስላል ? 

5️⃣ ቅዱስ ጊዮርጊስ :- 48 ነጥብ

6️⃣ ፋሲል ከነማ :- 44 ነጥብ

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
TIKVAH-SPORT
አርሰናል ዴቪድ ራያን በቋሚነት አስፈርሟል ! የሰሜን ለንደኑ ክለብ አርሰናል በውሰት ከብሬንትፎርድ ያስፈረሙትን ስፔናዊ ግብ ጠባቂ ዴቪድ ራያ ኮንትራት የመግዛት አማራጫቸውን ተጠቅመው ቋሚ ማድረጋቸው ተገልጿል። መድፈኞቹ ለግብ ጠባቂው የዝውውር ሒሳብ በውሉ ውስጥ ተካቶ የነበረውን የመግዛት አማራጭ ሒሳብ 27 ሚልዮን ፓውንድ መክፈላቸው ተነግሯል። የእንግሊዝ ፕርሚየር ሊግ የወርቅ ጓንት አሸናፊው…
ዴቪድ ራያ በይፋ የአርሰናል ተጨዋች ሆኗል !

የሰሜን ለንደኑ ክለብ አርሰናል ስፔናዊውን ግብ ጠባቂ ዴቪድ ራያ ከብሬንትፎርድ በቋሚነት ማስፈረማቸውን ይፋ አድርገዋል።

ዴቪድ ራያ በአርሰናል ቤት የረጅም ጊዜ ኮንትራት መፈረሙ ሲገለፅ " እዚህ መሆኔ ህልሜን እውን አድርጎልኛል ለተደረገልኝ ድጋፍ ሁሉ አመሰግናለሁ።"ሲል ከፊርማው በኋላ ተናግሯል።

ሚኬል አርቴታ በበኩላቸው " ዴቪድ ራያ ባለፈው አመት የእኛ አስፈላጊ ተጨዋች መሆኑን አሳይቷል ለቡድኑ ትልቅ ዜና ነው ከእሱ ጋር በመስራታችን ደስተኞች ነን።"ብለዋል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
2024/09/30 06:17:29
Back to Top
HTML Embed Code: