Telegram Web Link
ኔዘርላንድ ሩብ ፍፃሜውን ተቀላቅለዋል !

በአውሮፓ ዋንጫ ውድድር ጥሎ ማለፍ የኔዘርላንድ ብሔራዊ ቡድን ከሮማንያ ብሔራዊ ቡድን ጋር ያደረጉትን ጨዋታ 3ለ0 በሆነ ውጤት በማሸነፍ ሩብ ፍፃሜውን ተቀላቅለዋል።

የኔዘርላንድን የማሸነፊያ ግቦች ዶንዬል ማለን 2x እና ኮዲ ጋክፖ ከመረብ ማሳረፍ ችለዋል።

የኔዘርላንድ ብሔራዊ ቡድን የፊት መስመር ተጨዋች ኮዲ ጋክፖ በአውሮፓ ዋንጫው ሶስተኛ ግቡን በማስቆጠር የውድድሩ ከፍተኛ ግብ አስቆጣሪዎች አንዱ ሆኗል።

የኔዘርላንድ ብሔራዊ ቡድን በሩብ ፍፃሜው የቱርክ እና ኦስትሪያን አሸናፊ የሚገጥሙ ይሆናል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
የጨዋታ አሰላለፍ !

4:00 ቱርክ ከ ኦስትሪያ

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
" ለመጨረሻ ጨዋታ ሽንፈት ምላሽ ሰጥተናል " ጋክፖ

ኔዘርላንድ ሮማንያን ባሸነፈችበት የምሽቱ ጨዋታ ኮከብ ተብሎ የተመረጠው ኮዲ ጋክፖ ቡድናቸው ከቀናት በፊት በኦስትሪያ ላጋጠመው ሽንፈት ምላሽ መስጠቱን ገልጿል።

ጥሩ ጨዋታ እና ጥሩ ግቦችን አስቆጥረናል በማለት የተናገረው ኮዲ ጋክፖ " ለኦስትሪያ ሽንፈት ይህ ጥሩ ምላሽ ነው ፣ ሮማንያ ግብ ታስቆጥራለች የሚል እምነት አልነበረንም " ሲል ተደምጧል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
" ኦስትሪያ ካለፈች በድጋሜ ጉድ እንድትሰራን አንፈቅድም " ቫን ዳይክ

የኔዘርላንድ ብሔራዊ ቡድን አምበል ቨርጅል ቫን ዳይክ ቡድናቸው ዛሬ ባደረገው ጥሩ እንቅስቃሴ መኩራት እንዳለበት ተናግሯል።

" በመከላከል ረገድ ጠንካራ ነበርን " ያለው ቨርጅል ቫን ዳይክ ተጨማሪ ግቦችን ማስቆጠር ነበረብን ዛሬ ባደረግነው ነገር በራሳችን መኩራት አለብን ብሏል።

የምድቡን የመጨረሻ ጨዋታ ያሸነፈቻቸው ኦስትሪያ በሩብ ፍፃሜው ሊገናኙ የሚችሉበት እድል ስለመኖሩ አስተያየት የሰጠው ቫን ዳይክ " ኦስትሪያ ካለፈች በድጋሜ ጉድ እንድትሰራን አንፈቅድም።

ማን ሩብ ፍፃሜውን እንደሚቀላቀል እናያለን ቱርክም ጠንካራ ተጋጣሚ ናቸው።"ሲል ተናግሯል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
1 ' ቱርክ 1 - 0 ኦስትሪያ

ዴሚራል

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
13 ' ቱርክ 1 - 0 ኦስትሪያ

ዴሚራል

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
እረፍት | ቱርክ 1 - 0 ኦስትሪያ

ዴሚራል

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
59 ' ቱርክ 2 - 0 ኦስትሪያ

ዴሚራል

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
66 ' ቱርክ 2 - 1 ኦስትሪያ

ዴሚራል ግሪጎሪች

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
ቱርክ ሩብ ፍፃሜውን ተቀላቅለዋል !

በአውሮፓ ዋንጫ ውድድር ጥሎ ማለፍ የቱርክ ብሔራዊ ቡድን ከኦስትሪያ ብሔራዊ ቡድን ጋር ያደረጉትን ጨዋታ 2ለ1 በሆነ ውጤት በማሸነፍ ሩብ ፍፃሜውን ተቀላቅለዋል።

የቱርክን የማሸነፊያ ግቦች መሪህ ዴሚራል 2x ከመረብ ማሳረፍ ሲችሉ ለኦስትሪያ ሚሼል ግሪጎሪች ከመረብ ማሳረፍ ችሏል።

የሳውዲው ክለብ አል አህሊ ተጨዋች መሪህ ዴሚራል ከአውሮፓ ሊጎች ውጪ እየተጫወተ በአውሮፓ ዋንጫ ጨዋታ ሁለት ግቦች ያስቆጠረ የመጀመሪያው ተጨዋች መሆን ችሏል።

ቱርክ በአውሮፓ ዋንጫ ሩብ ፍፃሜ ስታልፍ ከአስራ ስድስት አመታት በኋላ ለመጀመሪያ ጊዜ መሆኑ ተገልጿል።

የቱርክ ብሔራዊ ቡድን በሩብ ፍፃሜው የኔዘርላንድ ብሔራዊ ቡድንን የሚገጥሙ ይሆናል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
#EURO2024

የአውሮፓ ዋንጫው ውድድር ጥሎ ማለፍ ጨዋታዎች ሲጠናቀቁ ሩብ ፍፃሜውን የተቀላቀሉ ስምንት ብሔራዊ ቡድኖች ተለይተው ታውቀዋል።

የሩብ ፍፃሜ ጨዋታዎች ምን ይመስላሉ ?

አርብ 1:00 - ስፔን ከ ጀርመን

አርብ 4:00 - ፖርቹጋል ከ ፈረንሳይ

ቅዳሜ 1:00 - ስዊዘርላንድ ከ እንግሊዝ

ቅዳሜ 4:00 - ቱርክ ከ ኔዘርላንድ

እነማን ግማሽ ፍፃሜ ይደርሳሉ

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
Forwarded from HEY Online Market
Stock Clearance Discount 2

📞 0925927457 @eBRO4
📞 0953964175 @heymobile

•iP 7+, Black, 128GB, 99% 12K
•iP X, Black, 256 GB, 100%,12K ⚠️
•iP XS, White, 64 GB, 100% 19K
•iP XS Max, Gold, 64GB, 83%, 25K
•iP XS Max, Gold, 256GB, 88% 29K
•iP 11, Red, 64GB, 100% 28K ⚠️
•iP 11, Black, 128GB, 85%, 33K
•iP 11, Purple, 128GB, 88% 33K
•11 Pro, Black, 64GB, 100% 39K ⚠️
•11 Pro, White, 64GB, 87% 36K
•11 Pro Max, Black, 64GB, 86%, 46K

•11 Pro Max, Black, 256GB, -% 40⚠️
•iP 12, Red, 128GB, 88%, 42K
•iP 12, White, 128GB, 88% 42K
•iP 12, Green, 128GB, 86% 42K
•12 Pro, Blue, 128GB, 89% 49K
•12 Pro Max, Blue, 512GB, 84% 64K
•iP 13 Min, Pink, 256GB, 92% 34K
•iP 13, Blueback, 128GB, 90% 56K
•iP 13, Black, 128GB, 92% 49K ⚠️

•iP 13, Red, 128GB, 86%, 56K
•iP 13, Black, 128GB, 89%, 58K
•13 Pro, Golden, 256GB, 87% 69K
•13 Pro, Blue, 512GB/88% 69K ⚠️
•13 ProMax, Black, 128 GB, 87% 74K
•13 ProMax, 256GB, 86%, 64K⚠️
•13 ProMax, 256GB, 85%, 74K⚠️
•13 ProMax, Gold, 256GB, 86%, 79K
•13 Pro Max, Gold, 256 GB,88% 79K
•13 Pro Max, Blue, 256GB, 94% 79K
•13 Pro Max, 1TB, 88%, 69K ⚠️
•13 Pro Max, Blu, 256GB/ -% 70K ⚠️

Exchange Available!
Free Delivery 🚚

@heyonlinemarket
https://heymobile.store/catalogue
ሽመልስ በቀለ 1⃣8⃣ ገስት ሀውስ

በውቢቷ ሀዋሳ ቆይታዎ የት ለማረፍ አስበዋል ? ንፁህ እና በደንበኞቻችን ተወዳጅ በሆነው የእንግዳ ማረፊያችን መጥተው የእረፍት ጊዜውን ያሳልፉ።

እንግዶቻችንን ተቀበልን ለእይታ ሳቢ በሆነው የእንግዳ ማረፊያችን ማስተናገድ ከጀመርን አመታትን አስቆጥረናል።

አድራሻችን :- ሀዋሳ አርቴፍሻል ስታዲየም መንገድ ላይ ያገኙናል።

ለተጨማሪ መረጃ እና ለትዕዛዝዎ ይደውሉልን :- 0928684848

#ShemelesBekele18
#CopaAmerica2024

የኮፓ አሜሪካ የምድብ የመጨረሻ ጨዋታዎች ሲደረጉ ብራዚል ከኮሎምቢያ ያደረገችውን ጨዋታ 1ለ1 በሆነ አቻ ውጤት አጠናቃ ኮሎምቢያን በመከተል ሁለተኛ ደረጃን በመያዝ ሩብ ፍፃሜውን ተቀላቅለዋል።

የብራዚል ብሔራዊ ቡድን በምድብ ጨዋታዎች ካደረጋቸው ሶስት ጨዋታዎች አንዱን ሲያሸንፍ በሁለቱ አቻ ተለያይተዋል።

የብራዚል ብሔራዊ ቡድን የፊት መስመር ተጨዋች ቪንሰስ ጁኒየር በምድብ ጨዋታ ሁለት የማስጠንቀቂያ ካርድ መመልከቱን ተከትሎ በቅጣት የሩብ ፍፃሜ ጨዋታ ያመልጠዋል።

በውድድሩ ምድቡን በበላይነት ማጠናቀቅ የቻሉት ሁሉም አራቱ ብሔራዊ ቡድኖች በአርጀንቲናዊያን አሰልጣኞች የሚመሩ ናቸው።

በኮፓ አሜሪካ ውድድር ታሪክ የምድቡ አሸናፊ ሁሉም ብሔራዊ ቡድኖች በአንድ ዜግነት ባላቸው አሰልጣኞች ሲመሩ ለመጀመሪያ ጊዜ መሆኑ ተገልጿል።

የሩብ ፍፃሜ ጨዋታዎች ምን ይመስላሉ ?

ሐሙስ ሌሊት 10:00 - አርጀንቲና ከ ኢኳዶር

አርብ ሌሊት 10:00 - ቬንዙዌላ ከ ካናዳ

ቅዳሜ ሌሊት 7:00 - ኮሎምቢያ ከ ፓናማ

ቅዳሜ ሌሊት 10:00 - ዩራጓይ ከ ብራዚል

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
" መሰናበታችንን ማመን አልቻልኩም "  ራኚክ

የኦስትሪያ ብሔራዊ ቡድን ዋና አሰልጣኝ ራልፍ ራኚክ ቡድናቸው ከአውሮፓ ዋንጫው ውድድር መሰናበቱን ማመን እንደከበዳቸው ገልጸዋል።

" መሰናበታችንን ማመን አልቻልኩም " ያሉት አሰልጣኝ ራልፍ ራኚክ በውድድሩ ውስጥ መቆየት ነበረብን ጨዋታው ወደ ተጨማሪ ሰዓት ቢያመራ አሸንፈን እንወጣ ነበር።"ብለዋል።

" የአቻነት ግብ ለማስቆጠር ጊዜ ነበረን በጣም ተቃርበን ነበር ነገርግን ግብ ጠባቂው ጥሩ ነበር ለማስቆጠር አስቸጋሪ ሆኖብናል ፣ የዛሬውን ጨምሮ ሁሉም ጨዋታዎቻችን አዝናኝ ነበሩ።" ራልፍ ራኚክ

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
አሰልጣኝ ስቴፋኖ ፒዮሊ ወደ ሳውዲ ሊያመሩ ነው !

በቅርቡ ከጣልያን ሴርያው ክለብ ኤሲ ሚላን ጋር የተለያዩት አሰልጣኝ ስቴፋኖ ፒዮሊ ወደ ሳውዲ አረቢያ ሊግ ለማምራት ከስምምነት መድረሳቸው ተገልጿል።

አሰልጣኝ ስቴፋኖ ፒዮሊ የሳውዲ አረቢያውን ክለብ አል ኢትሀድ ለሶስት የውድድር አመታት ለማሰልጠን ከስምምነት እንደደረሱ ተዘግቧል።

አሰልጣኝ ስቴፋኖ ፒዮሊ ከ 2019 ጀምሮ ኤሲ ሚላንን በሀላፊነት የመሩ ሲሆን ክለቡን የሴርያ ዋንጫ አሸናፊ በማድረግ ወደ ሻምፒየንስ ሊግ ውድድርም መመለስ ችለዋል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
ሚኬል አርቴታ ውላቸውን ሊያራዝሙ ነው !

ስፔናዊው አሰልጣኝ ሚኬል አርቴታ በአርሰናል ቤት ያላቸውን ኮንትራት ለተጨማሪ አመታት ለማራዘም ከክለቡ ጋር በንግግር ላይ መሆናቸው ተገልጿል።

አሰልጣኝ ሚኬል አርቴታ በአርሰናል ቤት መቆየት እና በክለቡ ለአመታት መቀጠል እንደሚፈልጉ ተዘግቧል።

መድፈኞቹ በበኩላቸው አሰልጣኝ ሚኬል አርቴታ በክለቡ በጀመሩት ስራ ደስተኞች መሆናቸው ተነግሯል።

አሰልጣኝ ሚኬል አርቴታ በቅርቡ በአርሰናል ለተጨማሪ አመታት የሚያቆያቸውን ኮንትራት በይፋ ይፈርማሉ ተብሎ እንደሚጠበቅ ተገልጿል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
TIKVAH-SPORT
ማንችስተር ዩናይትድ ስፖርቲንግ ዳይሬክተር ሾመ ! ማንችስተር ዩናይትድ የኒውካስል ዩናይትዱን ስፖርቲንግ ዳይሬክተር ዳን አሽዎርዝ በሀላፊነት ለመሾም ከኒውካስል ጋር ከስምምነት መድረሳቸውን ይፋ አድርገዋል። የ 52ዓመቱ ሀላፊ ዳን አሽዎርዝ በቀጣይ የማንችስተር ዩናይትድን የስፖርቲንግ ዳይሬክተርነት ሚና በሀላፊነት እንደሚረከቡ ይፋ ሆኗል። ኒውካስል ዩናይትድ ማንችስተር ዩናይትድ ለሀላፊው ውል ማፍረሻ…
ዳን አሽዎርዝ ምን ሀላፊነት ይሰጣቸዋል ?

የማንችስተር ዩናይትድን የስፖርቲንግ ዳይሬክተርነት ሚና የተረከቡት ዳን አሽዎርዝ በቀጣዩ የክለቡ አዲስ መዋቅር ሁሉንም የስፖርታዊ ጉዳዮች እንዲቆጣጠሩ ሀላፊነት እንደሚሰጣቸው ተገልጿል።

ሀላፊው የክለቡን አካዳሚ እና ሴቶች ቡድን ጨምሮ የህክምና ቡድኑን እና የቡድኑን የአቋም ግምገማ ክፍል ጭምር እንደሚቆጣጠሩ ተዘግቧል።

አዲሱ የቀያዮቹ ሴጣኖች ስፖርቲንግ ዳይሬክተር ዳን አሽዎርዝ ክለቡ ከማንችስተር ሲቲ ላመጣው ዋና ስራ አስፈፃሚው ኦማር ቤራዳ ሪፖርት እንደሚያደርጉ ተነግሯል።

አሰልጣኝ ኤሪክ ቴንሀግ በበኩላቸው ክለቡ በሚያስፈርማቸው ተጨዋቾች ላይ ሀላፊነት እንደሚኖራቸው እና ያለፍቃዳቸው የትኛውም ተጨዋች ለቡድኑ እንደማይፈርም ተገልጿል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
መሐመድ ሳላህ በኦሎምፒክ አይሳተፍም !

ግብፃዊው የሊቨርፑል የፊት መስመር ተጨዋች መሐመድ ሳላህ በቀጣዩ የፓሪስ ኦሎምፒክ ውድድር እንደማይሳተፍ ተገልጿል።

በተጨማሪም የመርሲሳይዱ ክለብ ሊቨርፑል ጃፓናዊውን ተጨዋች ዋታሩ ኢንዶ ለኦሎምፒክ ውድድር ለመላክ ፍቃደኛ ሳይሆኑ መቅረታቸው ተነግሯል።

የግብፅ እና ጃፓን እግርኳስ ፌዴሬሽኖች ተጨዋቾቹን በኦሎምፒክ ቡድናቸው ለማካተት ከሊቨርፑል ጋር ንግግር ሲያደርጉ ነበር።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
2024/10/02 06:35:02
Back to Top
HTML Embed Code: