Telegram Web Link
ኤቨርተን ተጨዋች አስፈርመዋል !

የመርሲሳይዱ ክለብ ኤቨርተን ሴኔጋላዊውን የፊት መስመር ተጨዋች ኢሊማን ንድያዬ ከፈረንሳዩ ክለብ ማርሴይ ማስፈረማቸውን ይፋ አድርገዋል።

የ 24ዓመቱ የፊት መስመር ተጨዋች ኢሊማን ንድያዬ በኤቨርተን ቤት የአምስት አመት ኮንትራት መፈረሙ ተገልጿል።

ለተጨዋቹ ዝውውር ኤቨርተን አጠቃላይ 20 ሚልዮን ዩሮ የሚደርስ የዝውውር ሒሳብ ማውጣታቸው ተዘግቧል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
እንግሊዛዊያን ዳኞች ጨዋታዎች ይመራሉ !

የፊታችን አርብ የሚደረጉ ሁለት የአውሮፓ ዋንጫ ሩብ ፍፃሜ ጨዋታዎችን እንግሊዛዊያን ዳኞች በመሐል ዳኝነት እንዲመሩ መመረጣቸው ተገልጿል።

አርብ ምሽት 1:00 የሚደረገውን የስፔን እና ጀርመን ተጠባቂ ጨዋታ አንቶኒ ቴለር እንደሚመሩት ይፋ ሆኗል።

እንዲሁም ምሽት 4:00 የሚደረገውን የፈረንሳይ እና ፖርቹጋል ተጠባቂ ጨዋታ ማይክል ኦሊቨር እንዲመሩ መመረጣቸው ተገልጿል።

ጨዋታዎቹን እነማን ያሸንፋሉ ?

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
TIKVAH-SPORT
ባየር ሙኒክ ተጨዋች ለማስፈረም ተስማማ ! የጀርመን ቡንደስሊጋው ክለብ ባየር ሙኒክ የፉልሀሙን የመሐል ሜዳ ተጨዋች ጇ ፓልሂንሀ ለማስፈረም ከተጨዋቹ ጋር ከስምምነት መድረሳቸው ተገልጿል። ባየር ሙኒክ ፖርቹጋላዊውን የመሐል ሜዳ ተጨዋች ጇ ፓልሂንሀን ለማስፈረም እስከ 45 ሚልዮን ዩሮ የሚደርስ የዝውውር ሒሳብ ሊያወጡ እንደሚችሉ ተነግሯል። የ 28ዓመቱ ተጨዋች በዚህ አመት በሊጉ ለፉልሀም ባደረጋቸው…
የባየር ሙኒክ ጥያቄው ተቀባይነት አገኘ !

የጀርመን ቡንደስሊጋው ክለብ ባየር ሙኒክ የፉልሀሙን የመሐል ሜዳ ተጨዋች ጇ ፓልሂንሀ ለማስፈረም ከክለቡ ጋር ከስምምነት መድረሳቸው ተገልጿል።

ከተጨዋቹ ጋር ቀደም ብለው በግል ከስምምነት የደረሱት ባየር ሙኒኮች አሁን ላይ ለፉልሀም ያቀረቡት 56 ሚልዮን ዩሮ የሚደረሰስ ሒሳብ ተቀባይነት ማግኘቱ ተገልጿል።

ፉልሀም ከተጨዋቹ ዝውውር የሚያገኙት 51 ሚልዮን ዩሮ ክፍያ እና 5 ሚልዮን ዩሮ ታይቶ የሚጨምር ገንዘብ የክለቡ ሪከርድ ሽያጭ ሆኖ መመዝገቡ ተነግሯል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
ሀዋሳ ከተማ አመቱን በድል አጠናቋል !

በኢትዮጵያ ፕርሚየር ሊግ የመጨረሻ ሳምንት መርሐ ግብር ሀዋሳ ከተማ ወላይታ ድቻ ጋር ያደረጉትን ጨዋታ 2ለ0 በሆነ ውጤት አሸንፈዋል።

የሀዋሳ ከተማን የማሸነፊያ ግቦች ዓሊ ሱሌይማን 2x ከመረብ ማሳረፍ ችሏል።

ኤርትራዊው የሀዋሳ ከተማ አጥቂ ዓሊ ሱሌይማን በውድድር አመቱ ያስቆጠራቸውን የሊግ ግቦች ሀያ ማድረስ ችሏል።

የሊጉ ደረጃቸው ምን ይመስላል ? 

8️⃣ ሀዋሳ ከተማ :- 41 ነጥብ

1️⃣3️⃣ ወላይታ ድቻ :- 34 ነጥብ

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
" ዋንጫውን ለማሸነፍ ያለንን ሁሉ እንሰጣለን " ዣካ

የስዊዘርላንድ ብሔራዊ ቡድን አምበል ግራኒት ዣካ ቡድናቸው የአውሮፓ ዋንጫውን ለማሸነፍ ያለውን ሁሉ እንደሚሰጥ በሰጠው አስተያየት ገልጿል።

ግራኒት ዣካ በንግግሩም " የአውሮፓ ዋንጫውን እናሸንፋለን ብዬ ማረጋገጥ ባልችልም ዋንጫውን ለማሳካት የቻልነውን ሁሉ እንደምናደርግ ግን ቃል አገባላችኋለሁ " ሲሉ ለደጋፊዎቹ ተናግሯል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
🔊 ልዩ ቅናሹ 6 ቀናት ብቻ ቀሩት!

👉🏾 እሰከ ሐምሌ 1 በዋናው አዲስ የቴሌግራም ቦት የስፖርት ትጥቆችን በማዘዝ ልዩ የ5% ቅናሽን ይጠቀሙ።

🤖 @WanawSportBot 🤖

👉🏾 #ዛሬም እንዳያመልጥዎ፣ ይዘዙን!

🏅ዋናው ወደፊት...

@wanawsportwear
Betika Eth-Bunna Matchday Magazine [Vol. 25].pdf
36.2 MB
የኢትዮጵያ  ቡና ይፋዊ አጋር የሆነው ቤቲካ - የኢትዮጵያ ቡናን  25ኛ የጨዋታ ቀን የዲጂታል መፅሄት ይዞ ቀርቧል።

በመፅሄቱ ላይ የዕለቱ ጨዋታን የተመለከቱና ሌሎች የተለያዩ መረጃዎች የሚቀርቡ ይሆናል፡፡

የጨዋታ መፅሄት ቁጥር 25
ሀድያ ሆሳዕና ከ ኢትዮጵያ ቡና

ቤቲካ - የኢትዮጵያ ቡና ይፋዊ አጋር
ኢፕስዊች ታውን ተጨዋቾች ለማስፈረም ጠይቀዋል !

በዚህ አመት ወደ እንግሊዝ ፕርሚየር ሊግ ያደገው ኢፕስዊች ታውን ከሀል ሲቲ ጃኮፕ ግሬቭስ እና ጃደን ፊሎጌኔን ለማስፈረም ጥያቄ ማቅረባቸው ተገልጿል።

ኢፕስዊች ታውን ሁለቱን ተጨዋቾች ለማስፈረም ለሀል ሲቲ 35 ሚልዮን ፓውንድ የዝውውር ሒሳብ ማቅረባቸው ተነግሯል።

በተጨዋቾቹ ዝውውር ዙሪያ በሁለቱ ክለቦች መካከል የሚደረገው ንግግር አሁንም መቀጠሉ ተገልጿል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
" ቶኒ ክሩስን አርብ ወደ ጡረታው እንሸኘዋለን " ሆሴሉ

የስፔን ብሔራዊ ቡድን የፊት መስመር ተጨዋች ሆሴሉ ቶኒ ክሩስ አርብ የመጨረሻ ጨዋታውን እንደሚያደርግ በሰጠው አስተያየት ተናግሯል።

" ከክሩስ ጋር መጫወት ለእኔ ክብር ነው የመልበሻ ቤት ጓደኛዬ ነበር ብዙ ነገሮችን አግዞኛል ብዙ ምክረም ሰጥቶኛል እሱን ማመስገን እፈልጋለሁ።"ሲል ሆሴሉ ተናግሯል።

" እሱ የማድሪድም ሆነ የጀርመን ቁልፍ ተጨዋች ነው " የሚለው ሆሴሉ ክሩስን እወደዋለሁ ነገርግን አርብ የመጨረሻ ጨዋታው ይሆናል ወደ ጡረታው እንሸኘዋለን።"ብሏል።

ቶኒ ክሩስ በበኩሉ በሰጠው አስተያየት " የአርቡ ጨዋታ የመጨረሻ ጨዋታዬ እንደማይሆን ተስፋ አደርጋለሁ።"ሲል በሰጠው አስተያየት ተናግሯል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
ዩናይትድ ሰራተኞቹን ሊያሰናብት ነው !

ማንችስተር ዩናይትድ አዲሱ የውድድር ዘመን ከመጀመሩ በፊት የክለቡን ሰራተኞች ለመቀነስ ማሰባቸውን አሳውቀዋል።

ቀያዮቹ ሴጣኖች ካሏቸው 1,100 የክለቡ ሰራተኞች ሩብ የሚሆኑትን ከሁለት መቶ ሀምሳ በላይ ሰራተኞች ለማሰናበት ማሰባቸው ተገልጿል።

ክለቡ ይህንን የሚያደርገው ወጪዎቹን ለመቆጠብ እና ከሰራተኞቹ ጋር ተለያይቶ የሚያተርፈውን ገንዘብ በዋናው ቡድን ላይ በማዋል የፋይናንሻል ፌር ፕሌይ ህግን ለማስተካከል መሆኑ ተነግሯል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
ሪካርዶ ካላፊዮሪ አርሰናልን መቀላቀል ይፈልጋል !

የሰሜን ለንደኑ ክለብ አርሰናል ጣልያናዊውን የቦሎኛ የተከላካይ ስፍራ ተጨዋች ሪካርዶ ካላፊዮሪ ለማስፈረም ጥረት በማድረግ ላይ መሆናቸው ተገልጿል።

መድፈኞቹ ለተጨዋቹ የዝውውር ጥያቄያቸውን ማቅረባቸው የተገለፀ ሲሆን በቀጣይ ከቦሎኛ ጋር የሚስማሙ ከሆነ ተጨዋቹ አርሰናልን ለመቀላቀል እንደሚፈልግ ተነግሯል።

ከአርሰናል በተጨማሪም የምዕራብ ለንደኑ ክለብ ቼልሲ ሪካርዶ ካላፊዮሪን ለማስፈረም ንግግር ላይ እንደሚገኙ ተገልጿል።

ቦሎኛ ለተጨዋቹ ዝውውር እስከ 50 ሚልዮን ዩሮ የዝውውር ሒሳብ ሊጠይቁ እንደሚችሉ ተነግሯል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
ሀድያ ሆሳዕና አመቱን በድል አጠናቋል !

በኢትዮጵያ ፕርሚየር ሊግ የመጨረሻ ሳምንት መርሐ ግብር ሀድያ ሆሳዕና ከኢትዮጵያ ቡና ጋር ያደረጉትን ጨዋታ 2ለ1 በሆነ ውጤት አሸንፈዋል።

የሀድያ ሆሳዕናን የማሸነፊያ ግቦች የኋላሸት ሰለሞን 2x ከመረብ ማሳረፍ ሲችል ለኢትዮጵያ ቡና አንተነህ ተፈራ አስቆጥሯል።

የሊጉ ደረጃቸው ምን ይመስላል ? 

3️⃣ ኢትዮጵያ ቡና :- 51 ነጥብ

8️⃣ ሀድያ ሆሳዕና :- 41 ነጥብ

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
" ዋንጫውን ለሮናልዶ ስጦታ መስጠት እንፈልጋለን " ሜንዴዝ

የፖርቹጋል ብሔራዊ ቡድን ተከላካይ ኑኖ ሜንዴዝ ቡድናቸው የአውሮፓ ዋንጫውን አሸንፎ ለክርስቲያኖ ሮናልዶ ስጦታ ማበርከት እንደሚፈልግ ተናግሯል።

የአውሮፓ ዋንጫው ለክርስትያኖ ሮናልዶ የመጨረሻው መሆኑን የገለፀው ኑኖ ሜንዴዝ " ዋንጫውን አሸንፈን ለሮናልዶ በስጦታነት ለማበርከት ሁሉንም ነገር እናደርጋለን " በማለት ተናግሯል።

" ኪሊያን ምባፔን ማስቆም በጣም ከባድ ነው ነገርግን እኔ የተወሰነ አውቀዋለሁ እሱን ለማስቆም የቻልኩትን ሁሉ አደርጋለሁ።" ኑኖ ሜንዴዝ

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
" ከባድ ጨዋታ ይሆናል " ጀማል ሙሲያላ

የጀርመን ብሔራዊ ቡድን የመሐል ሜዳ ተጨዋች ጀማል ሙሲያላ ቡድናቸው አርብ ምሽት ከስፔን ጋር የሚያደርገው የሩብ ፍፃሜ ጨዋታ ከባድ እንደሚሆን ተናግሯል።

" ጨዋታው ከባድ ይሆናል ሁለቱም ብሔራዊ ቡድኖች ፍፃሜ የመድረስ ችሎታ አላቸው እኛ ጨዋታውን ማሸነፍ እንደምንችል በራሳችን ማመን አለብን።" ሲል ሙሲያላ ተናግሯል።

" ስፔን እንደ ላሚን ያማል ፣ ፔድሪ እና ኒኮ ዊሊያምስ ያሉ አደገኛ ተጨዋቾች አሏቸው ጨዋታውን መወሰን ይችላሉ ፣ ነገርግን እኛም እንደነሱው ልዩ ተጨዋቾች አሉን በራሳችን እናምናለን።" ጀማል ሙሲያላ

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
Forwarded from HEY Online Market
Stock Clearance Discount 2

📞 0925927457 @eBRO4
📞 0953964175 @heymobile

•iP 7+, Black, 128GB, 99% 12K
•iP X, Black, 256 GB, 100%,12K ⚠️
•iP XS, White, 64 GB, 100% 19K
•iP XS Max, Gold, 64GB, 83%, 25K
•iP XS Max, Gold, 256GB, 88% 29K
•iP 11, Red, 64GB, 100% 28K ⚠️
•iP 11, Black, 128GB, 85%, 33K
•iP 11, Purple, 128GB, 88% 33K
•11 Pro, Black, 64GB, 100% 39K ⚠️
•11 Pro, White, 64GB, 87% 36K
•11 Pro Max, Black, 64GB, 86%, 46K

•11 Pro Max, Black, 256GB, -% 40⚠️
•iP 12, Red, 128GB, 88%, 42K
•iP 12, White, 128GB, 88% 42K
•iP 12, Green, 128GB, 86% 42K
•12 Pro, Blue, 128GB, 89% 49K
•12 Pro Max, Blue, 512GB, 84% 64K
•iP 13 Min, Pink, 256GB, 92% 34K
•iP 13, Blueback, 128GB, 90% 56K
•iP 13, Black, 128GB, 92% 49K ⚠️

•iP 13, Red, 128GB, 86%, 56K
•iP 13, Black, 128GB, 89%, 58K
•13 Pro, Golden, 256GB, 87% 69K
•13 Pro, Blue, 512GB/88% 69K ⚠️
•13 ProMax, Black, 128 GB, 87% 74K
•13 ProMax, 256GB, 86%, 64K⚠️
•13 ProMax, 256GB, 85%, 74K⚠️
•13 ProMax, Gold, 256GB, 86%, 79K
•13 Pro Max, Gold, 256 GB,88% 79K
•13 Pro Max, Blue, 256GB, 94% 79K
•13 Pro Max, 1TB, 88%, 69K ⚠️
•13 Pro Max, Blu, 256GB/ -% 70K ⚠️

Exchange Available!
Free Delivery 🚚

@heyonlinemarket
https://heymobile.store/catalogue
ሽመልስ በቀለ 1⃣8⃣ ገስት ሀውስ

በውቢቷ ሀዋሳ ቆይታዎ የት ለማረፍ አስበዋል ? ንፁህ እና በደንበኞቻችን ተወዳጅ በሆነው የእንግዳ ማረፊያችን መጥተው የእረፍት ጊዜውን ያሳልፉ።

እንግዶቻችንን ተቀበልን ለእይታ ሳቢ በሆነው የእንግዳ ማረፊያችን ማስተናገድ ከጀመርን አመታትን አስቆጥረናል።

አድራሻችን :- ሀዋሳ አርቴፍሻል ስታዲየም መንገድ ላይ ያገኙናል።

ለተጨማሪ መረጃ እና ለትዕዛዝዎ ይደውሉልን :- 0928684848

#ShemelesBekele18
TIKVAH-SPORT
ዋልያዎቹ የምድብ ተጋጣሚያቸውን መቼ ያውቃሉ ? በሞሮኮ አዘጋጅነት ለሚካሄደው የ 2025 አፍሪካ ዋንጫ ውድድር የማጣርያ ጨዋታ ምድብ ድልድል የሚካሄድበት ቀን ታውቋል። ብሔራዊ ቡድኖች የምድብ ተጋጣሚያቸውን ሐሙስ ሰኔ 27/2016 ዓ.ም በደቡብ አፍሪካ ጆሀንስበርግ በሚደረገው የእጣ ማውጣት ስነ ስርዓት እንደሚያውቁ ይፋ ተደርጓል። በምድብ ድልድሉ የቅድመ ማጣሪያውን ያለፉ አራት ሀገራትን ጨምሮ አርባ…
ዋልያዎቹ ተጋጣሚያቸውን ዛሬ ያውቃሉ !

በሞሮኮ አዘጋጅነት ለሚካሄደው የ 2025 አፍሪካ ዋንጫ ውድድር የማጣርያ ጨዋታ ምድብ ድልድል በዛሬው ዕለት በደቡብ አፍሪካ ጆሀንስበርግ ቀን 9:30 ሰዓት በሚደረግ የእጣ ማውጣት ስነ ስርዓት ይፋ ይደረጋል።

በምድብ ድልድሉ የቅድመ ማጣሪያውን ያለፉ አራት ሀገራትን ጨምሮ አርባ ስምንት ብሔራዊ ቡድኖች እንደሚካተቱ ተገልጿል።

በአስራ ሁለት ምድብ ተክፈለው የማጣሪያ ጨዋታቸውን የሚያደርጉት ብሔራዊ ቡድኖቹ የምድብ አንደኛ እና ሁለተኛ የመጀመሪያ ሀያ አራት ቡድኖች ለአፍሪካ ዋንጫው የሚያልፉ ይሆናል።

የማጣሪያ ጨዋታዎቹ ከሚቀጥለው አመት መስከረም ወር ጀምሮ መካሄዳቸውን ይጀምራሉ ተብሎ ይጠበቃል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
" ሊጉን ለማሸነፍ የበለጠ ጠንክረን እንመጣለን " ኦዴጋርድ

የሰሜን ለንደኑ ክለብ አርሰናል አምበል ማርቲን ኦዴጋርድ ቡድናቸው በሚቀጥለው የውድድር ዘመን ሊጉን ለማሸነፍ የበለጠ ጠንክሮ እንደሚመጣ በሰጠው አስተያየት ተናግሯል።

" ያለፈው አመት ጥሩ ነበርን ነገርግን ሊጉን ለማሸነፍ በቂ አልነበረም " ያለው ማርቲን ኦዴጋርድ በቀጣይ የበለጠ ጠንክረን እንመለሳለን ሊጉን ለማሸነፍ በጋራ እንሰራለን ጥሩ አመት እናሳልፋለን ብዬ አስባለሁ።"ሲል ተናግሯል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
TIKVAH-SPORT
" አቡበከር ናስር የማሜሎዲ ሰንዳውንስ ተጨዋች አይደለም " ሩላኒ ሞክዌና በደቡብ አፍሪካ ሊግ ለማሜሎዲ ሰንዳውንስ የሚጫወተው ኢትዮጵያዊው የፊት መስመር ተጨዋች አቡበከር ናስር አሁን ላይ የክለቡ ተጨዋች አለመሆኑን አሰልጣኝ ሩላኒ ሞክዌና ተናግረዋል። የማሜሎዲ ሰንዳውንስ ዋና አሰልጣኝ ሩላኒ ሞክዌና ትላንት ምሽት ከሀገሪቱ መገናኛ ብዙሀን ጋር ባደረጉት ቆይታ ስለ አቡበከር ናስር የክለቡ ሁኔታ ተጠይቀው…
የአቡበከር ናስር የማሜሎዲ ሰንዳውንስ ሁኔታ ?

በጉዳት ለረጅም ጊዜ ከሜዳ ርቆ የቆየው ኢትዮጵያዊው የፊት መስመር አጥቂ አቡበከር ናስር አሁን ላይ ክለቡ በግሉ መጠነኛ ልምምድ ማድረግ እንዲጀምር ማድረጉ ተገልጿል።

በትላንትናው ዕለት ከክለቡ ጋር በይፋ የተለያዩት የማሜሎዲ ሰንዳውንስ ዋና አሰልጣኝ ሩላኒ ሞክዌና በቅርቡ " አቡበከር ናስር የእኛ ተጨዋች አይደለም "  የሚል አስተያየት ሰጥተው ነበር።

አሰልጣኝ ሩላኒ ሞክዌና ስለ አቡበከር ናስር የሰጡት አስተያየት የክለቡን ጥቅም ያላስጠበቀ እና አላስፈላጊ ነው በሚል የክለቡን ቦርድ አለማስደሰቱ ተዘግቧል።

አቡበከር ናስር ባለፉት ወራት ያጋጠሙት ተደጋጋሚ ከባድ ጉዳቶች እንዲሁም ተጨማሪ ጉዳት ያጋጥመዋል የሚሉ ስጋቶች በፍጥነት ወደ ሜዳ እንዳይመለስ እና የማገገሚያ ጊዜው እንዲረዝም እንዳደረገው ተነግሯል።

ማሜሎዲ ሰንዳውንስ ከቀናት በፊት ከክለቡ ጋር የሚለያዩ ተጨዋቾችን በማህበራዊ ትስስር ገፁ ይፋ ሲያደርግ አቡበከር ናስር እንዳልተካተተ አይዘነጋም።

ምንጭ - መኳንንት በርሄ ፖድካስት

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
የሮማንያ ተጨዋቾች መልበሻ ቤቱን አፅድተዋል !

በኔዘርላንድ ተሸንፈው ከአውሮፓ ዋንጫው የተሰናበቱት የሮማንያ ብሔራዊ ቡድን ተጨዋቾች ከጨዋታው በኋላ መልበሻ ቤቱን አፅድተው ወደነበርንበት መልሰው መሄዳቸው ተገልጿል።

የብሔራዊ ቡድኑ ተጨዋቾች መልበሻ ቤቱን ካፀዱ በኋላም በጀርመን በነበራቸው ቆይታ ለተደረገላቸው አቀባበል የምስጋና የፅሁፍ መልዕክት ማስቀመጣቸው ተዘግቧል።

ሮማንያ የአውሮፓ ዋንጫ የጥሎ ማለፍ ጨዋታዋን በኔዘርላንድ 3ለ0 ተሸንፋ ከውድድሩ መሰናበቷ አይዘነጋም።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
2024/10/02 08:20:16
Back to Top
HTML Embed Code: