Telegram Web Link
#CopaAmerica2024

የኮፓ አሜሪካ ውድድር የምድብ የመጨረሻ ጨዋታዎች ሲደረጉ አርጀንቲና ፔሩን በላውታሮ ማርቲኔዝ ሁለት ግቦች 2ለ0 በሆነ ውጤት በማሸነፍ ምድቧን በበላይነት አጠናቃለች።

ካናዳ በበኩሏ የምድቡን የመጨረሻ ጨዋታ በአቻ ውጤት ማጠናቀቋን ተከትሎ ሁለተኛ ደረጃ በመያዝ ሩብ ፍፃሜውን መቀላቀል ችለዋል።

ፔሩ ከአስራ ዘጠኝ አመታት በኋላ ከምድቧ ማለፍ ሳትችል የቀረች ሲሆን በተጨማሪ በታሪኳ ለመጀመሪያ ጊዜ በምድብ ጨዋታ ግብ ሳታስቆጥር አጠናቃለች።

ላውታሮ ማርቲኔዝ በምድብ ጨዋታዎች አራት ግቦችን በማስቆጠር የውድድሩ ከፍተኛ ግብ አስቆጣሪነት ደረጃውን እየመራ ይገኛል።

አርጀንቲና ምድብ ሁለትን ሁለተኛ ደረጃ ይዞ የሚያጠናቅቀውን ቡድን በሩብ ፍፃሜው ስትገጥም ካናዳ አንደኛ ደረጃ ይዞ የሚያጠናቅቀውን ቡድን ታገኛለች።

እስካሁን ሩብ ፍፃሜውን እነማን ተቀላቀሉ ?

- አርጀንቲና

- ካናዳ

- ዩራጓይ

- ቬንዙዌላ

- ኮሎምቢያ

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
" ቫር እግርኳሳችንን ፍትሀዊ አድርጎታል " ኔግልስማን

የጀርመን ብሔራዊ ቡድን ዋና አሰልጣኝ ጁሊያን ኔግልስማን በምሽቱ የጥሎ ማለፍ ጨዋታ ቫር የነበረው ሚና ፍትሀዊ እንደነበር ከጨዋታው በኋላ ገልጸዋል።

" ቫር ስፖርታችንን ፍትሀዊ አድርጎታል " ሲሉ የገለፁት አሰልጣኝ ጁሊያን ኔግልስማን ዴንማርኮች ለምን እንደተናደዱ ይገባኛል ነገርግን ህጉ ነው አንደርሰን ፈልጎ አልነበረም እኛ ላይ ቢሆንም ቅር እሰኝ ነበር ግን መቀበል አለብኝ ብሏል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
TIKVAH-SPORT
" ቫር እግርኳሳችንን ፍትሀዊ አድርጎታል " ኔግልስማን የጀርመን ብሔራዊ ቡድን ዋና አሰልጣኝ ጁሊያን ኔግልስማን በምሽቱ የጥሎ ማለፍ ጨዋታ ቫር የነበረው ሚና ፍትሀዊ እንደነበር ከጨዋታው በኋላ ገልጸዋል። " ቫር ስፖርታችንን ፍትሀዊ አድርጎታል " ሲሉ የገለፁት አሰልጣኝ ጁሊያን ኔግልስማን ዴንማርኮች ለምን እንደተናደዱ ይገባኛል ነገርግን ህጉ ነው አንደርሰን ፈልጎ አልነበረም እኛ ላይ ቢሆንም ቅር…
" የቫር ውሳኔ ጨዋታውን ቀይሮታል "

የዴንማርክ ብሔራዊ ቡድን ዋና አሰልጣኝ ካስፐር ሁልማንድ በምሽቱ የጀርመን ጨዋታ በቫር የተወሰነባቸው ውሳኔ እንዳበሳጫቸው ከጨዋታው በኋላ ገልፀዋል።

" ሁለት የቫር ውሳኔዎች ጨዋታችንን ቀይረውብናል " ያሉት አሰልጣኙ " ያስቆጠርነው ግብ አንድ ሴንቲሜትር ከጨዋታ ውጪ ነበር ግቡን ለመሻር ጥቂት ነገር ተመልክተዋል ይህ የጨዋታ ውጪ ህግ አሰልችቶኛል ።"ሲሉ ተናግረዋል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
አትሌቲኮ ማድሪድ ከተጨዋቾቹ ጋር ተለያየ !

የስፔን ላሊጋው ክለብ አትሌቲኮ ማድሪድ ኮንትራታቸው ከተጠናቀቀ ሶስት ተጨዋቾቹ ጋር መለያየቱን በይፋ አስታውቋል።

ሜምፊስ ዴፓይ ፣ ማርዮ ሄርሞሶ እና ጋብሬል ፖሊስታ ኮንትራታቸው መጠናቀቁን ተከትሎ ክለቡን በነፃ መልቀቃቸው ይፋ ሆኗል።

ብራዚላዊው የተከላካይ ስፍራ ተጨዋች ጋብሬል ፓውሊስታ በቀጣይ የቱርኩን ክለብ ቤሺክታሽ ለመቀላቀል ከስምምነት ደርሷል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
አዝፕሉኬታ በአትሌቲኮ ማድሪድ ውሉን አራዝሟል !

ባለፈው ክረምት የዝውውር መስኮት ከቼልሲ በአንድ አመት ውል አትሌቲኮ ማድሪድን የተቀላቀለው ስፔናዊው የተከላካይ ስፍራ ተጨዋች ሴሳር አዝፕሉኬታ በክለቡ ዉሉን አራዝሟል።

የ 34ዓመቱ የተከላካይ ስፍራ ተጨዋች ሴሳር አዝፕሉኬታ በአትሌቲኮ ማድሪድ ቤት ለተጨማሪ አንድ የውድድር አመት ለመቆየት ውሉን ማራዘሙ ይፋ ተደርጓል።

ሴሳር አዝፕሉኬታ ባለፈው አመት ለአትሌቲኮ ማድሪድ ሰላሳ አራት ጨዋታዎች ላይ ተሰልፎ መጫወት ችሏል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
ቶተንሀም ተጨዋች ለማስፈረም አነጋግረዋል !

የሰሜን ለንደኑ ክለብ ቶተንሀም እንግሊዛዊውን ወጣት የተከላካይ ስፍራ ተጨዋች አርቼ ግሬይ ከሊድስ ዩናይትድ ለማስፈረም ንግግር ላይ መሆናቸው ተገልጿል።

የ 18ዓመቱ ተጨዋች አርቼ ግሬይ ቶተንሀምን መቀላቀል እንደሚፈልግ የተገለፀ ሲሆን በቀጣይ ክለቦቹ ከስምምነት ይደርሳሉ ተብሎ ይጠበቃል።

ሊድስ ዩናይትድ ተጨዋቹን ለማስፈረም ከብሬንትፎርድ የቀረበላቸውን ጥያቄ ውድቅ ማድረጋቸው ተዘግቧል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
እጥፍ ድርብ አሸናፊነት!

በቤቲካ ያሸነፉትን ገንዘብ በACCA እስከ 300% ከፍ ያድርጉ!

አሁኑኑ Betika.et ላይ አሸናፊነትን ይጀምሩ!

ቤቲካ የአሸናፊዎች ቤት!
ሉቺያኖ ስፓሌቲ በሀላፊነታቸው ይቀጥላሉ !

የጣልያን ብሔራዊ ቡድን ዋና አሰልጣኝ ሉቺያኖ ስፓሌቲ በቀጣይ በሀላፊነታቸው እንደሚቀጥሉ የሀገሪቱ እግርኳስ ፌዴሬሽን ከውሳኔ መድረሱ ተገልጿል።

ብሔራዊ ቡድኑ ከአውሮፓ ዋንጫ ውድድር ቢሳነብትም አሰልጣኝ ሉቺያኖ ስፓሌቲ በአሰልጣኝነታቸው እንደሚቀጥሉ የጣልያን እግርኳስ ፌዴሬሽን ሀላፊ ጋብሬል ግራቪና ገልጸዋል።

አሰልጣኝ ሉቺያኖ ስፓሌቲ ቢያንስ እስከ 2026 አለም ዋንጫ ውድድር ድረስ የጣልያን ብሔራዊ ቡድንን እንደሚመሩ ተጠቁሟል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
ጇ ፊሊክስ በባርሴሎና አይቀጥልም !

የካታላኑ ክለብ ባርሴሎና ያለፈውን አመት በውሰት በክለቡ ካሳለፈው ፖርቹጋላዊው የፊት መስመር ተጨዋች ጇ ፊሊክስ ጋር እንደማይቀጥሉ በይፋ አስታውቀዋል።

ፖርቹጋላዊው የፊት መስመር ተጨዋች ጇ ፊሊክስ ባለፈው አመት ከአትሌቲኮ ማድሪድ በውሰት ባርሴሎናን መቀላቀሉ ይታወሳል።

በተጨማሪም ባርሴሎና ከስፔናዊው የተከላካይ ስፍራ ተጨዋች ማርኮስ አሎንሶ ጋር በነፃ ዝውውር መለያየታቸውን ይፋ አድርገዋል።

በውሰት ከማንችስተር ሲቲ አስፈርመውት የነበረው ጇ ካንሴሎ በበኩሉ በተመሳሳይ በባርሴሎና እንደማይቀጥል እና ወደ ክለቡ እንደሚመለስ ይፋ ሆኗል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
ጁቬንቱስ ተጨዋች አስፈርመዋል !

የጣልያን ሴርያው ክለብ ጁቬንቱስ ብራዚላዊውን የመሐል ሜዳ ተጨዋች ዳግላስ ሉዊዝ ከአስቶን ቪላ ማስፈረማቸውን ይፋ አድርገዋል።

የ 26ዓመቱ የመሐል ሜዳ ተጨዋች ዳግላስ ሉዊዝ በጁቬንቱስ እስከ 2029 የሚያቆየውን የአምስት አመት ኮንትራት መፈረሙ ተገልጿል።

ጁቬንቱስ ለተጨዋቹ ዝውውር በአራት አመት ተከፋፍሎ የሚከፈል 50 ሚልዮን ዩሮ ወጪ እንደሚያደርግ ተዘግቧል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
TIKVAH-SPORT
ቼልሲ ለሌስተር ይፋዊ ጥያቄ አቅርበዋል ! የምዕራብ ለንደኑ ክለብ ቼልሲ እንግሊዛዊውን የመሐል ሜዳ ተጨዋች ኬርናን ዴውስቡሪ ሀልን ለማስፈረም ለሌስተር ሲቲ ይፋዊ ጥያቄ ማቅረባቸው ተገልጿል። ቼልሲ እና ሌስተር ሲቲ በተጨዋቹ ዝውውር ዙሪያ ዴቪድ ፎፋና እና ሴሳር ካሳዴን የዝውውሩ አካል ለማድረግ በመነጋገር ላይ መሆናቸው ተዘግቧል። የ 25ዓመቱ የመሐል ሜዳ ተጨዋች ኬርናን ዴውስቡሪ ሀል በቀጣይ…
ቼልሲ ተጨዋች ለማስፈረም ተስማማ !

የምዕራብ ለንደኑ ክለብ ቼልሲ እንግሊዛዊውን የመሐል ሜዳ ተጨዋች ኬርናን ዴውስቡሪ ሀልን ከሌስተር ሲቲ ለማስፈረም ከስምምነት መድረሳቸው ተገልጿል።

ሰማያዊዎቹ ተጨዋቹን በ30 ሚልዮን ፓውንድ በስድስት አመት ኮንትራት ለማስፈረም ከስምምነት መድረሳቸው ይፋ ተደርጓል።

ተጨዋቹ በዛሬው ዕለት የህክምና ምርመራውን በማጠናቀቀ በይፋ በቀድሞ አሰልጣኙ ኢንዞ ማሬስካ የሚመራውን ቼልሲ የመቀላቀል ይሆናል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
ሻሸመኔ ከተማ ወደ ከፍተኛ ሊግ ወረደ !

በኢትዮጵያ ፕርሚየር ሊግ የሀያ ዘጠነኛ ሳምንት መርሐ ግብር የሊጉ መሪ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ከሻሸመኔ ከተማ ጋር ያደረጉትን ጨዋታ 2ለ0 በሆነ ውጤት አሸንፈዋል።

የንግድ ባንክን የማሸነፊያ ግቦች አዲስ ግደይ እና ሱሌይማን ሀሚድ ከመረብ ማሳረፍ ችለዋል።

ሻሸመኔ ከተማ መሸነፉን ተከትሎ ከኢትዮጵያ ፕርሚየር ሊግ ወደ ከፍተኛ ሊግ መውረዳቸው ተረጋግጧል።

በሌላ ጨዋታ ወልቂጤ ከተማ ከሀምበሪቾ ዱራሜ ጋር ያደረጉትን ጨዋታ በመድን ተክሉ እና ጋዲሳ መብራቴ ግቦች 2ለ0 ማሸነፍ ችለዋል።

የመውረድ ስጋት ውስጥ የነበረው ወልቂጤ ከተማ በሚቀጥለው አመት በኢትዮጵያ ፕርሚየር ሊግ መቆየቱን አረጋግጠዋል።

የሊጉ ደረጃ ሰንጠረዥ ምን ይመስላል ? 

1️⃣ ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ:- 61 ነጥብ

1️⃣4️⃣ ወልቂጤ ከተማ :- 20 ነጥብ

1️⃣5️⃣ ሻሸመኔ ከተማ :- 14 ነጥብ

1️⃣6️⃣ ሀምበሪቾ ዱራሜ :- 9

* የሊጉ መሪ ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የሊጉን የመጨረሻ ሳምንት መርሐ ግብር ቀጣይ ሳምንት ቅዳሜ ከኢትዮጵያ መድን ጋር የሚያደርግ ይሆናል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
የጨዋታ አሰላለፍ !

1:00 እንግሊዝ ከ ስሎቫኪያ

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
TIKVAH-SPORT
የጨዋታ አሰላለፍ ! 1:00 እንግሊዝ ከ ስሎቫኪያ @tikvahethsport     @kidusyoftahe
#EURO2024

የእንግሊዝ ብሔራዊ ቡድን አሰልጣኝ ጋሪዝ ሳውዝጌት በምድቡ የመጨረሻ ጨዋታ የተጠቀሙትን ኮነር ጋላገር ተጠባባቂ በማድረግ ኮቢ ማይኖን በቋሚ አሰላለፍ አካተዋል።

የማንችስተር ዩናይትዱ አማካይ ኮቢ ማይኖ በትልቅ ውድድር የመጀመሪያ ጨዋታውን ለእንግሊዝ በቋሚ አሰላለፍ ገብቶ የሚያደርግ ይሆናል።

በምድብ ጨዋታዎች ትችት ሲሰነዘርባቸው የነበሩት ሶስቱ አናብስት በምሽቱ ጨዋታ የመሐል ክፍላቸው  በዴክላን ራይስ ፣ ኮቢ ማይኖ እና ቤሊንግሀም የወጣቶች ጥምረት ይመራል።

የስሎቫኪያ ብሔራዊ ቡድን አንድ አቻ በተለያዩበት የሮማንያ የምድብ የመጨረሻ ጨዋታ የተጠቀሙትን ቋሚ አስራ አንድ ይዘው እንግሊዝን የሚገጥሙ ይሆናል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
#EURO2024

የእንግሊዝ ብሔራዊ ቡድን ቁጥር አንድ ግብ ጠባቂ ጆርዳን ፒክፎርድ ለምሽቱ የስሎቫኪያ ጨዋታ በሟሟቅ ላይ እያለ ጣቶቹን መጉዳቱ ተገልጿል።

ፒክፎርድ በአሁን ሰዓት የግራ እጁን ህመም እተሰማው እንደሚገኝ የተገለፀ ሲሆን በጨዋታው መሰለፍ ካልቻለ አሮን ራምስዴል የሚተካው ይሆናል።

ጆርዳን ፒክፎርድ ከቀናት በፊትም በተመሳሳይ ከጨዋታ በፊት ሲያሟሙቅ ጣቶቹ ላይ ጉዳት አድርሶ ለህመም ተጋልጦ እንደነበር ተነግሯል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
2 ' እንግሊዝ 0 - 0 ስሎቫኪያ

- የእንግሊዝ ግብ ጠባቂ ጆርዳን ፒክፎርድ በእጁ ላይ ጉዳት ቢያጋጥመው በቋሚ አሰላለፍ ጨዋታውን ለማድረግ ገብቷል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
20 ' እንግሊዝ 0 - 0 ስሎቫኪያ

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
24 ' እንግሊዝ 0 - 1 ስሎቫኪያ

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
2024/12/28 03:57:43
Back to Top
HTML Embed Code: