Telegram Web Link
" ላሳየነው ደካማ አቋም ማብራሪያ የለኝም " ቫን ዳይክ

የኔዘርላንድ ብሔራዊ ቡድን አምበል ቨርጅል ቫን ዳይክ ቡድናቸው በምሽቱ ጨዋታ ያደረገው እንቅስቃሴ ደካማ መሆኑን ከጨዋታው በኋላ በሰጠው አስተያየት ተናግሯል።

" በጣም መጥፎ ጨዋታ  " ሲል ጨዋታውን የገለፀው ቨርጅል ቫን ዳይክ " አስከፊ ምሽት ነበር ያሳለፍነው ጨዋታውን የጀመርነው ደካማ ሆነን ነበር ስላደረግነው ደካማ እንቅስቃሴ ማብራሪያ የለኝም " ሲል ተደምጧል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
" የመጀመሪያ ግባችንን አሳክተናል " ዴሻምፕ

የፈረንሳይ ብሔራዊ ቡድን ዋና አሰልጣኝ ዲዴ ዴሻምፕ ቡድናቸው የምድቡ የበላይ ሆኖ ባያጠናቅቅም የመጀመሪያ ግቡን ማሳካቱን ገልፀዋል።

" ምንም የምንበሳጭበት ነገር የለም " ሲሉ ከፖላንድ ጨዋታ በኋላ የገለፁት አሰልጣኝ ዲዴ ዴሻምፕ ምንም እንኳን የፈለግንበት ቦታ ላይ ባንሆንም የመጀመሪያ ግባችንን አሳክተናል ብለዋል።

ፈረንሳይ ምድቧን በሁለተኝነት ማጠናቀቋን ተከትሎ በጥሎ ማለፉ በመጀመሪያው ምድብ ስትገኝ ለፍፃሜ ለመድረስ ትልቅ ግምት የተሰጣቸውን ስፔን ፣ ጀርመን እና ፖርቹጋልን ለማሸነፍ ትገደዳለች።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
2 '

ዴንማርክ 0 - 0 ሰርቢያ

እንግሊዝ 0 - 0 ስሎቬኒያ

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
32 '

ዴንማርክ 0 - 0 ሰርቢያ

እንግሊዝ 0 - 0 ስሎቬኒያ

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
#እረፍት

ዴንማርክ 0 - 0 ሰርቢያ

እንግሊዝ 0 - 0 ስሎቬኒያ

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
55 '

ዴንማርክ 0 - 0 ሰርቢያ

እንግሊዝ 0 - 0 ስሎቬኒያ

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
75 '

ዴንማርክ 0 - 0 ሰርቢያ

እንግሊዝ 0 - 0 ስሎቬኒያ

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
90 '

ዴንማርክ 0 - 0 ሰርቢያ

እንግሊዝ 0 - 0 ስሎቬኒያ

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
#EURO2024

በአውሮፓ ዋንጫ የምድብ ሶስት የመጨረሻ ጨዋታዎች ሲደረጉ የእንግሊዝ ብሔራዊ ቡድን ከስሎቬኒያ ብሔራዊ ቡድን ጋር ያደረጉትን ጨዋታ 0ለ0 በሆነ አቻ ውጤት አጠናቀዋል።

በሌላኛው የምድብ ጨዋታ የዴንማርክ ብሔራዊ ቡድን ከሰርቢያ ብሔራዊ ቡድን ጋር ያደረጉትን ጨዋታ 0ለ0 በሆነ አቻ ውጤት ተለያይተዋል።

የምድቡ ደረጃ ምን ይመስላል ?

1️⃣ እንግሊዝ :- 5 ነጥብ

2️⃣ ዴንማርክ :- 3 ነጥብ

3️⃣ ስሎቬኒያ :- 3 ነጥብ

4️⃣ ሰርቢያ :- 2 ነጥብ

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
Forwarded from HEY Online Market
Samsung Galaxy S22 Ultra
256 GB - 67,000 ETB
512 GB - 78,000 ETB

Samsung Galaxy S23 Ultra
256 GB - 92,000 ETB
512 GB - 109,000 ETB

Samsung Galaxy S24 Ultra
256 GB - 109,000 ETB
512 GB - 124,000 ETB

Exchange Available
🏍️ Free Delivery

Contact us :
0925927457 @eBRO4
@Heyonlinemarket
ሽመልስ በቀለ 1⃣8⃣ ገስት ሀውስ

በውቢቷ ሀዋሳ ቆይታዎ የት ለማረፍ አስበዋል ? ንፁህ እና በደንበኞቻችን ተወዳጅ በሆነው የእንግዳ ማረፊያችን መጥተው የእረፍት ጊዜውን ያሳልፉ።

እንግዶቻችንን ተቀበልን ለእይታ ሳቢ በሆነው የእንግዳ ማረፊያችን ማስተናገድ ከጀመርን አመታትን አስቆጥረናል።

አድራሻችን :- ሀዋሳ አርቴፍሻል ስታዲየም መንገድ ላይ ያገኙናል።

ለተጨማሪ መረጃ እና ለትዕዛዝዎ ይደውሉልን :- 0928684848

#ShemelesBekele18
አርጀንቲና ጥሎ ማለፉን ተቀላቅለዋል !

የአርጀንቲና ብሔራዊ ቡድን ትላንት ሌሊት ከቺሊ ብሔራዊ ቡድን ያደረጉትን የኮፓ አሜሪካ የምድብ ሁለተኛ ጨዋታ በላውታሮ ማርቲኔዝ ግብ 1ለ0 ማሸነፍ ችለዋል።

አርጀንቲና የምድብ ሁለት ጨዋታዎችን ማሸነፏን ተከትሎ በስድስት ነጥቦች ወደ ሩብ ፍፃሜ መቀላቀሏን አረጋግጣለች።

አርጀንቲና አሁንም በኮፓ አሜሪካ ውድድር ታሪክ በመደበኛ ጨዋታ በቺሊ ብሔራዊ ቡድን ያላትን ያለመሸነፍ ጉዞ አስቀጥላለች።

ለአስራ ዘጠኝ ወራት ለአርጀንቲና ብሔራዊ ቡድን ግብ ሳያስቆጥር የቆየው ላውታሮ ማርቲኔዝ ባለፉት አምስት ጨዋታዎች አምስት ግቦች አስቆጥሯል።

አርጀንቲና የምድብ የመጨረሻ ጨዋታዋን ከፔሩ ጋር ቅዳሜ ሌሊት የምታደርግ ይሆናል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
ሊዮኔል ሜሲ መጠነኛ ጉዳት አጋጥሞታል !

የአርጀንቲና ብሔራዊ ቡድን አምበል ሊዮኔል ሜሲ በትናንቱ ምሽቱ የቺሊ የኮፓ አሜሪካ የምድብ ሁለተኛ ጨዋታ መጠነኛ ጉዳት እንዳጋጠመው ተገልጿል።

የጨዋታውን ሙሉ ዘጠና ደቂቃ ተጫውቶ ያጠናቀቀው ሊዮኔል ሜሲ ይሁን እንጂ ከመጀመሪያው ደቂቃ ጀምሮ ምቾት እንዳልተሰማው ተናግሯል።

" በቀኝ እግሬ ላይ ከመጀመሪያው ምቾት እየተሰማኝ አልነበረም ነገርግን ጨዋታውን ማጠናቀቅ ችያለሁ በቀጣይ እንዴት እንደሚሆን እናያለን።"ሲል ሊዮኔል ሜሲ ከጨዋታው በኋላ ለጋዜጠኞች ተናግሯል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
" ሮናልዶ በቋሚ አሰላለፍ ይጀምራል " ሮቤርቶ ማርቲኔዝ

አስራ ስድስቱን የተቀላቀለው ፖርቹጋል ብሔራዊ ቡድን ዋና አሰልጣኝ ሮቤርቶ ማርቲኔዝ በዛሬው የጆርጂያ የምድብ የመጨረሻ ጨዋታ ክርስቲያኖ ሮናልዶ በቋሚ አሰላለፍ እንደሚጀመር ገልጸዋል።

ቡድኑ ጥሎ ማለፉን መቀላቀሉን ተከትሎ ሮናልዶን ሊያሳርፉ ይችሉ እንደሆነ የተጠየቁት አሰልጣኝ ሮቤርቶ ማርቲኔዝ " ክርስቲያኖ ሮናልዶ በጨዋታው በቋሚ አስራ አንድ ውስጥ ይካተታል " ብለዋል።

" የአውሮፓ ዋንጫውን ያሸንፋል ተብሎ የሚገመት ቡድን መኖሩን እጠራጠራለሁ " ያሉት አሰልጣኝ ሮቤርቶ ማርቲኔዝ ሁሉም ብሔራዊ ቡድኖች በውድድሩ የተለያዩ ናቸው "ብለዋል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
በኮፓ አሜሪካ ረዳት ዳኛው ራሳቸውን ስተዋል !

ትላንት ሌሊት በኮፓ አሜሪካ ውድድር ፔሩ ከካናዳ ጋር ባደረጉት የምድብ ሁለተኛ ጨዋታ የጨዋታው ረዳት ዳኛ ራሳቸውን ስተው ሜዳ ላይ መውደቃቸው ተገልጿል።

ረዳት ዳኛው ራሳቸውን ስተው የወደቁት በነበረው ከፍተኛ ሙቀት ምክንያት መሆኑ የተገለፀ ሲሆን በህክምና ባለሞያዎች እርዳታ ከተደረገላቸው በኋላ ከሜዳ መውጣታቸው እና በጥሩ ሁኔታ እንደሚገኙ ተጠቁሟል።

ጨዋታውን የካናዳ ብሔራዊ ቡድን በጆናታን ዴቪድ ግብ 1ለ0 በሆነ ውጤት ማሸነፍ ችለዋል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
#ዳሽን_ከፍታ: በጉጉት ሲጠበቅ የነበረው "ዳሽን ከፍታ" የሥራ ፈጠራ ውድድር ሶስተኛ ምዕራፍ ሊጀመር ነው፡፡

በዳሸን ከፍታ የመጀመሪያውና ሁለተኛው ዙር የስራ ፈጠራ ውድድሮች ተሳትፈው አሸናፊ የሆኑ ተወዳዳሪዎች ሸልማትና የፋይናስ ድጋፍ አግኝተው በተለያዩ የስራ ዘርፎች ስኬታማ እየሆኑ ነው፡፡ ለሌሎችም የስራ ዕድል መፍጠር ችለዋል፡፡

በዚህ ውድድር ላይ ለመሳተፍ ዝግጁ ነዎት?

ዳሽን ከፍታ የሥራ ፈጠራ ውድድር በምዕራፍ ሶስት የቅድመ ውድድር ጅማሬ ስልጠና ለመስጠት በተለያዩ የአገራችን ክፍሎች ይንቀሳቀሳል!

የስልጠና ቦታዎች ፡ አዲስ አበባ ፣ ባህርዳር ፣ አዳማ ፣ መቀሌ ፣ ድሬዳዋ ፣ ሀዋሳ ፣ ወላይታ ፣ ጅማ እና ደሴ

ምዝገባ እስከ #ሰኔ_22/2016 ዓ.ም. ድረስ በሁሉም የዳሸን ባንክ ቅርንጫፎች የሚካሄድ ይሆናል፡፡

ለበለጠ መረጃ ወደ 6333 ይደውሉ ወይም የባንኩን የማህበራዊ ትስስር ገጾች ይጎብኙ፡፡

ዳሸን ባንክ ሁልጊዜም አንድ እርምጃ ቀዳሚ!
" የቤልጅየም ወርቃማ ትውልድ አያልቅም " ታዴስኮ

የቤልጅየም ብሔራዊ ቡድን ዋና አሰልጣኝ ዶሜኒኮ ታዴስኮ የቤልጅየም ወርቃማ ትውልድ እንደማያልቅ እና አሁንም መኖሩን በሰጡት አስተያየት ገልፀዋል።

" አንዳንድ ተጨዋቾች ጫማ ቢሰቅሉም የቤልጅየም ወርቃማ ትውልድ መቼም አያልቅም " ያሉት አሰልጣኝ ዶሜኒኮ ታዴስኮ " ከወጣት ተጨዋቾች ጋር አዲስ ነገር እየገነባን ነው " ሲሉ ተደምጠዋል።

ስለ ምሽቱ የዩክሬን ጨዋታ አስተያየት የሰጡት አሰልጣኝ ዶሜኒኮ ታዴስኮ " ሶስት ነጥቡን ማሳካት እንፈልጋለን ዩክሬን ጠንካራ ቡድን ናቸው ነገርግን ፍላጎታችን ማሸነፍ ብቻ ነው።"ብለዋል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
ሜክሲኮ አምበሏ በጉዳት ከኮፓ አሜሪካ ውጪ ሆነ !

የሜክሲኮ ብሔራዊ ቡድን አምበል ኤድስን አልቫሬዝ በጉዳት ምክንያት እየተካሄደ ከሚገኘው የኮፓ አሜሪካ ውድድር ውጪ መሆኑ ተገልጿል።

የዌስትሀም ዩናይትዱ የመሐል ሜዳ ተጨዋች ኤድስን አልቫሬዝ ከቀናት በፊት ጃማይካን ባሸነፉበት ጨዋታ ጉዳት ማስተናገዱ ይታወሳል።

ኤድስን አልቫሬዝ በጉዳት ምክንያት ተሰልፎ መጫወት ባይችልም በብሔራዊ ቡድኑ በመቆየት ቡድኑን እንደሚያበረታታ ተገልጿል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
ምድብ ሶስትን ሁለተኛ ሆኖ ያጠናቀቀው ማን ነው ?

የአውሮፓ ዋንጫ ውድድር ምድብ ሶስትን በሁለተኝነት ያጠናቀቀው የዴንማርክ ብሔራዊ ቡድን መሆኑን የአውሮፓ እግርኳስ ማህበር በይፋ አስታውቋል።

ዴንማርክ እና ስሎቬኒያ የምድብ ውድድሩን በእኩል ነጥብ ፣ የጎል ልዩነት እንዲሁም ተመሳሳይ የተጨዋቾች ቢጫ ካርድ ቁጥር በማስመዝገብ ማጠናቀቃቸው ይታወቃል።

ይሁን እንጂ የስሎቬኒያ ምክትል አሰልጣኝ የማስጠንቀቂያ ካርድ መመልከቱን ተከትሎ ዴንማርክ ሁለተኛ ደረጃን ይዛ ማጠናቀቋን ዩኤፋ አስታውቋል።

ይህንንም ተከትሎ በጥሎ ማለፉ የዴንማርክ ብሔራዊ ቡድን ከጀርመን ብሔራዊ ቡድን የሚገናኝ ይሆናል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
🔥በቤቲካ እለታዊ ጃክፖት ቀኖን ይጀምሩ!🔥


🤩በየእለቱ የ100 ሺ ብር አሸናፊነት ይጠብቅዎታል!

👇🏾👇🏾👇🏾👇🏾👇🏾
የዛሬውን ጃክፖት https://betika.com.et/et/daily-jackpot ላይ ይጫወቱ!

ቤቲካ የአሸናፊዎች ቤት!
2024/10/01 12:24:27
Back to Top
HTML Embed Code: