Telegram Web Link
Forwarded from HEY Online Market
iPhone 15 Promax
•256GB = 139,000 Birr
•512GB = 159,000 Birr

Samsung 24 Ultra
•256GB = 111,000 Birr
•512GB = 128,000 Birr

Contact us :
0953964175 @heymobile
0925927457

@Heyonlinemarket
" ከእነሱ የተሻለ ለመሆን እንጥራለን " አርቴታ

የሰሜን ለንደኑ ክለብ አርሰናል ዋና አሰልጣኝ ሚኬል አርቴታ ቡድናቸው በሚቀጥለው የውድድር አመት ማንችስተር ሲቲን መፎካከሩን እንደሚቀጥል ገልጸዋል።

" በመጨረሻው ሰዓት ዋንጫ ማጣታችን ያበሳጫል " ያሉት ሚኬል አርቴታ ለፔፕ ጋርዲዮላ እና ሰራተኞቻቸው እንኳን ደስ አላችሁ ብያቸዋለሁ በመጨረሻ ይገባቸዋል አሸናፊ ናቸው።"ብለዋል።

" ነገርግን እኛ አሁንም እነሱን ለማቆም መሞከራችንን አናቋርጥም " ያሉት አሰልጣኙ  ከእነሱ የተሻልን የመሆን ጥረት ማድረጋችንን አጠናክረን እንቀጥላለን በማለት ተናግረዋል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
ጎንሳሎ ኢናስዮ ወዴት ያመራ ይሆን ?

የፖርቹጋሉ ክለብ ስፖርቲንግ ሊስበኑ የመሐል ተከላካይ ጎንሳሎ ኢናስዮ በእንግሊዝ ታላላቅ ክለቦች እየተፈለገ እንደሚገኝ ተዘግቧል።

ካለፈው አመት ጀምሮ ፖርቹጋላዊውን ጎንሳሎ ኢናስዮ ሲከታተሉ የቆዩት ሊቨርፑሎች አሁን ላይ በክረምቱ የተጨዋቾች የዝውውር መስኮት ለማስፈረም ሊንቀሳቀሱ መሆኑ ተገልጿል።

በዚህ ክረምት ሁለት የመሐል ተከላካይ ለማስፈረም ያቀደው ማንችስተር ዩናይትድ በበኩሉ ተጫዋቹን አንዱ ፈራሚ ለማድረግ እየተከታተሉ እንደሚገኙ እና ማስፈረም እንደሚፈልጉ ተነግሯል።

የ 22ዓመቱ የተከላካይ ስፍራ ተጨዋች ጎንሳሎ ኢናስዮ በፖርቹጋሉ ክለብ ስፖርቲንግ ሊስበን ቤት ያለው ውል ማፍረሻ 60 ሚልዮን ዩሮ እንደሚደርስ ተጠቁሟል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
ኔይማር በአል ሂላል እንደሚቀጥል ገለጸ !

ብራዚላዊው የፊት መስመር ተጨዋች ኔይማር በሚቀጥለው የውድድር ዘመን በሳውዲ አረቢያው ክለብ አል ሂላል ቤት እንደሚቀጥል ተናግሯል።

ከአል ሂላል ጋር ሶስት ዋንጫዎች በማሳካቱ መደሰቱን የገለፀው ኔይማር " ቀጣይ አመት በአል ሂላል እቆያለሁ እዚህ አንድ አመት ውል አለኝ ቀጣይ አመት ከአል ሂላል ጋር ጥሩ አመት ማሳለፍ እፈልጋለሁ።"ብሏል።

ኔይማር አያይዞም አል ሂላል አል ናስርን አሸንፎ የሳውዲ አረቢያ ኪንግስ ካፕ ዋንጫን ካሸነፈ በኋላ ሊዮኔል ሜሲ የእንኳን ደስ አለህ መልዕክት እንደላከለት ተናግሯል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
አርሰናል በቀጣይ ምን ማስፈረም ይፈልጋል ?

የሰሜን ለንደኑ ክለብ አርሰናል በክረምቱ የተጨዋቾች የዝውውር መስኮት የፊት መስመራቸውን ለማጠናከር አጥቂ ለማስፈረም በዝግጅት ላይ መሆናቸው ተገልጿል።

በተጨማሪም መድፈኞቹ የግራ መስመር ተጨዋች ለማስፈረም እየተመለከቱ መሆኑ ሲዘገብ ሶስተኛ ግብ ጠባቂም ለማስፈረም ከሚመለከቱት የሜዳ ክፍል አንዱ መሆኑ ተነግሯል።

አርሰናል በቀጣይ ለማስፈረም የሚመለከተው የፊት መስመር ተጨዋች የሌፕዚጉ ቤንጃሚን ሴስኮ መሆኑ ሲገለፅ ተጨዋቹ በውሉ ውስጥ ውል ማፍረሻ 65 ሚልዮን ዩሮ መኖሩ ተጠቁሟል።

በተጨማሪም የኒውካስል ዩናይትዱ አሌክሳንደር አይሳክ ፣ የዎልቭሱ ፔድሮ ኔቶ እና የአትሌቲክ ቢልባኦው ኒኮ ዊልያምስ በዝርዝራቸው ውስጥ እንደሚገኙ ታውቋል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
ቼልሲ አዲስ አጥቂ ማስፈረም ይፈልጋል !

አዲስ አሰልጣኝ የሾመው የምዕራብ ለንደኑ ክለብ ቼልሲ በቀጣይ አዲስ የፊት መስመር አጥቂ ለማስፈረም ወደ ዝውውር ገበያው እንደሚገቡ ተገልጿል።

ሰማያዊዎቹ ስማቸው በስፋት ሲያያዝ ከቆዩት ቪክቶር ኦሲሜን እና ኢቫን ቶኒ ዝውውር በተለያዩ ምክንያቶች ራሳቸውን ማስወጣታቸው ተነግሯል።

ቼልሲ በቀጣይ ክረምት የክሪስታል ፓላሶቹን ተጨዋቾች ሚሼል ኦሊሴ እና ኢበሪች ኢዜ ለማስፈረም ከፍተኛ ፍላጎት እንዳላቸው ተዘግቧል።

በአሰልጣኝ ኢንዞ ማሬስካ የሚመራው ቼልሲ በተጨማሪም ወደ ሻምፒዮን ሺፑ የወረደው በርንሌይ ግብ ጄምስ ትራፎርድን ለማስፈረም ፍላጎት እንዳላቸው ተገልጿል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
TIKVAH-SPORT
ጎንሳሎ ኢናስዮ ወዴት ያመራ ይሆን ? የፖርቹጋሉ ክለብ ስፖርቲንግ ሊስበኑ የመሐል ተከላካይ ጎንሳሎ ኢናስዮ በእንግሊዝ ታላላቅ ክለቦች እየተፈለገ እንደሚገኝ ተዘግቧል። ካለፈው አመት ጀምሮ ፖርቹጋላዊውን ጎንሳሎ ኢናስዮ ሲከታተሉ የቆዩት ሊቨርፑሎች አሁን ላይ በክረምቱ የተጨዋቾች የዝውውር መስኮት ለማስፈረም ሊንቀሳቀሱ መሆኑ ተገልጿል። በዚህ ክረምት ሁለት የመሐል ተከላካይ ለማስፈረም ያቀደው ማንችስተር…
ዩናይትድ በቀጣይ ምን ሊያስፈርም ይችላል ?

ማንችስተር ዩናይትድ በሚቀጥለው ክረምት የመሐል ተከላካዮች ፣ አማካይ እና የፊት መስመር አጥቂ ለማስፈረም ወደ ዝውውር ገበያው እንደሚገቡ ተገልጿል።

ቀያዮቹ ሴጣኖች በቀጣይ ክረምት ለማስፈረም ከተመለከቷቸው ተከላካዮች የኤቨርተኑ እንግሊዛዊ ተጨዋች ጃሬድ ብራንዝዌት ቀዳሚው መሆኑ ተነግሯል።

ኤቨርተን ለ 21ዓመቱ ተከላካይ ጃሬድ ብራንዝዌት ጥሩ ዋጋ እንደሚፈልጉ ሲገለፅ ሀሪ ማጓየር ፣ ዊስሌይ ፎፋና እና ጆስኮ ቫርዲዮል ባለፉት ጊዜያት የተሸጡበት ሒሳብ ( ከ £75m በላይ ) ይገባዋል የሚል እምነት እንዳላቸው ተዘግቧል።

በተጨማሪም ማንችስተር ዩናይትድ የኒሱን ተከላካይ ጂያን ቶዲቦ እና ቼልሲን በነፃ ለመቀላቀል የተቃረበውን የፉልሀም ተጨዋች ቶሲን አዳራብዮ የማስፈረም ፍላጎት እንዳላቸው ተገልጿል።

በፊት መስመሩ በኩል ማንችስተር ዩናይትድ ለአመታት የተከታተሉትን የሌፕዚግ ተጨዋች ቤንጃሚን ሴስኮ በቅርበት እየተከታተሉ መሆኑ ሲገለፅ ከሌላኛው የሊጉ ክለብ አርሰናል ከፍተኛ ፉክክር ይጠብቃቸዋል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
ኪሊያን ምባፔ በርካታ ተከታዮች አፍርቷል !

በትላንትናው ዕለት በይፋ ሪያል ማድሪድን የተቀላቀለው ፈረንሳዊው የፊት መስመር ተጨዋች ኪሊያን ምባፔ በርካታ የማህበራዊ ትስስር ገፅ ተከታዮችን ማፍራት ችሏል።

ኪሊያን ምባፔ ሪያል ማድሪድን ከተቀላቀለበት ትላንት ምሽት ወዲህ ከ #ሁለት ሚልዮን በላይ የኢንስታግራም ማህበራዊ ትስስር ገፅ ተከታዮችን አፍርቷል።

ሪያል ማድሪድ ተጫዋቹን ከአውሮፓ ዋንጫ በኋላ በልዩ ሁኔታ በስታዲየሙ አቀባበል ሊያደርግ መሰቡ ሲገለፅ ከ80,000 በላይ ደጋፊዎች ይገኛሉ ተብሎ እንደሚጠበቅ ተነግሯል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
ሽመልስ በቀለ 1⃣8⃣ ገስት ሀውስ

በውቢቷ ሀዋሳ ቆይታዎ የት ለማረፍ አስበዋል ? ንፁህ እና በደንበኞቻችን ተወዳጅ በሆነው የእንግዳ ማረፊያችን መጥተው የእረፍት ጊዜውን ያሳልፉ።

እንግዶቻችንን ተቀበልን ለእይታ ሳቢ በሆነው የእንግዳ ማረፊያችን ማስተናገድ ከጀመርን አመታትን አስቆጥረናል።

አድራሻችን :- ሀዋሳ አርቴፍሻል ስታዲየም መንገድ ላይ ያገኙናል።

ለተጨማሪ መረጃ እና ለትዕዛዝዎ ይደውሉልን :- 0928684848

#ShemelesBekele18
Forwarded from WANAW SPORT
📢 ልዩ የሽያጭ ብስራቱ 3 ቀን ብቻ ቀረው!

👉🏾 ለአትሌቲክስ፣ ለቴኳንዶ እና ሌሎች ከእግር ኳስ ውጪ ላሉ ስፖርቶች

🔥 #እንዳያመልጥዎ፣ አሁኑኑ ይዘዙን!

📍አድራሻችን:- ገርጂ መብራት ሃይል የካቲት ወረቀት ፊትለፊት፣ አለም ገብሬ ህንፃ፣ 2ተኛ ፎቅ።

📌 ለበለጠ መረጃና ትዕዛዝ 📲 09011382830910851535 እና 0913586742 ላይ ይደውሉ።

👉🏾 እንዲሁም በቴሌግራም @Wanawsales ላይ የሽያጭ ሰራተኞቻችንን በቀጥታ በማናገር ወይም በቴሌግራም ቦት @WANAWSbot በኩል ይዘዙን።

Instagram | Facebook | TikTok

🏅 ዋናው ወደፊት...

@wanawsportwear
" ቪንሰስ ባሎን ዶር ይገባዋል " ኔይማር

ብራዚላዊው የአል ሂላል የፊት መስመር ተጨዋች ኔይማር የሪያል ማድሪዱ ተጨዋች ቪንሰስ ጁኒየር የባሎን ዶር አሸናፊ መሆን እንደሚገባው ገልጿል።

ኔይማር በንግግሩም " ቪንሰስ ጁኒየር አስደናቂ አመት አሳልፏል ባሎን ዶር ማሸነፍ አለበት ብዬ አስባለሁ ከእሱ ሌላ ሊያሸንፍ የሚችል ተጨዋች የለም።

እሱ ማሸነፍ ይገባዋል ምክንያቱም ሙሉ ህይወቱን በርካታ ፈተናዎች ቢያጋጥሙትም ትችቶቹን ሁሉ አልፎ አሁንም ተፋላሚ ነው ፣ የብራዚልን ባንዲራ በአለም ሁሉ ከፍ በማድረጉ ደስተኛ ነኝ።"ሲል ተደምጧል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
" በዚህ እድሜዬ ስለ ገንዘብ ማሰብ አለብኝ " ዴብሮይን

የማንችስተር ሲቲው የመሐል ሜዳ ተጨዋች ኬቨን ዴብሮይን ከሳውዲ አረቢያ የሚቀርቡለትን ከፍተኛ ገንዘብ የሚያስገኙ ጥያቄዎች ለመመልከት ዝግጁ መሆኑን ገልጿል።

በማንችስተር ሲቲ ቤት የአንድ አመት ውል የቀረው ኬቨን ዴብሮይን " በዚህ እድሜዬ ለሁሉም ጥያቄዎች ክፍት መሆን አለብኝ በዚህ የእግርኳስ የመጨረሻ ጊዜ ላይ ስለ ትልቅ ገንዘብ ማሰብ አለብኝ።"በማለት ተናግሯል።

ቤልጂየማዊው የመሐል ሜዳ ተጨዋች ኬቨን ዴብሮይን በአስተያየቱ አሁን ያለበት የእግርኳስ መጨረሻ እድሜ ብዙ ገንዘብ ስለማግኘት የማሰቢያ መሆኑን ጠቁሟል።

" ሳውዲ አረቢያ ውስጥ ሁለት አመታት ብጫወት የማይታመን ገንዘብ ማግኘት እችላለሁ ምናልባት ለአስራ አምስት አመታት ስጫወት ያገኘሁት ያንን ላያክል ይችላል።" ዴብሮይን

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
⚽️በጉጉት ሲጠበቅ የነበረው የአውሮፓ ዋንጫ ሊጀመር ነው 10 ቀናት በቻ ቀሩት!

👉 ዛሬውኑ ፓኬጅዎን ያሳድጉ የአውሮፓ ታላላቆችን ዋንጫ ፍልሚያ በወር 350 ብር!  ጨዋታዎችን ከትንታኔ ፣ ከተጫዋች ብቃት እስከ ቡድን ወኔ በሱፐርስፖርት ይከታተሉ!!

የዲኤስቲቪ አገልግሎቶችን ለማግኘት ከታች ያለውን የMyDStv Telegram bot ሊንክ ይጫኑ!
👇
https://mydstv.onelink.me/vGln/eth2

#Euro2024 #ሁሉምያለውእኛጋርነው #DStvEthiopia
ካሴሚሮ የክለብ ባለቤት መሆኑ ተገለፀ !

ብራዚላዊው የማንችስተር ዩናይትድ የመሐል ሜዳ ተጨዋች ካሴሚሮ የስፔን ሶስተኛ ሊግ ተወዳዳሪ የሆነውን ማርቤላ እግርኳስ ክለብ ከፍተኛ ድርሻ መግዛቱ ተገልጿል።

ካሴሚሮ ባደረገው ንግግርም " ማርቤላን መቀላቀሌ ለእኔ ትልቅ ክብር ነው ፣ በቀጣይ በጋራ ክለቡን ትልቅ ቦታ ለማድረስ እንደምናልም ጥርጥር የለውም።"ሲል ተደምጧል።

በቀጣይ ከማንችስተር ዩናይትድ ጋር ሊለያይ እንደሚችል እየተነገረ የሚገኘው ካሴሚሮ በአዲሱ ክለቡ የዳይሬክተሮች ቦርድ አባል እንደሚሆን ይፋ ሆኗል።

ክለቡ ከቀናት በፊት ከታችኛው እርከን ወደ ስፔን ሶስተኛ ሊግ ማደጉን አረጋግጧል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
" አምራባት በዩናይትድ መቆየት ይፈልጋል "

ሞሮኳዊው የመሐል ሜዳ ተጨዋች ሶፍያን አምራባት በቀጣይ በማንችስተር ዩናይትድ ቤት መቆየት እንደሚፈልግ የፊዮሬንቲና ዳይሬክተር ፕሬድ ገልጸዋል።

ዳይሬክተሩ በንግግራቸውም " ሶፍያን አምራባት ፕርሚየር ሊግ ውስጥ መቆየት ይፈልጋል ማንችስተር ዩናይትድ ምንም ነገር አልነገሩንም ከፊዮሬንቲና ጋር እንዲቆይ እንፈልጋለን ነገርግን እሱ ሌላ አቅም ያለው ይመስለኛል።"ብለዋል።

ማንችስተር ዩናይትድ ሶፍያን አምራባትን የመግዛት አማራጭ ባካተተ የውሰት ውል እስከ ውድድር አመቱ መጨረሻ ከፊዮሬንቲና ማስፈረማቸው አይዘነጋም።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
በዚህ ክረምት የሲቲ የዝውውር ሁኔታ ምን ይመስላል ?

በአሰልጣኝ ፔፕ ጋርዲዮላ የሚመራው ማንችስተር ሲቲ የኬቨን ዴብሮይን እና በርናርዶ ሲልቫ ቆይታ አጠራጣሪ መሆኑን ተከትሎ በዝውውር መስኮቱ የመሐል ሜዳ ተጨዋች በቅድሚያ እንደሚመለከቱ ተገልጿል።

ማንችስተር ሲቲዎች በተጨማሪም #የቀኝ የፊት መስመር ተጨዋች ለመመልከት በዝውውር መስኮቱ ለመግባት በአጀንዳነት መያዛቸውን ታማኝ የመረጃ ምንጮች ገልጸዋል።

ሲቲ በዝርዝራቸው ውስጥ የያዟቸው አማካዮች የውል ማፍረሻው £100 ሚልዮን የሆነው የኒውካስል ተጨዋች ብሩኖ ጉማሬስ ፣ ጀማል ሙሲያላ ፣ ፓኩዌታ እና ጆሹዋ ኪሚች መሆናቸው ተነግሯል።

በተጨማሪም ማንችስተር ሲቲ የግብ ጠባቂዎችን እንዲሁም ካይል ዎከርን የወደፊት ሁኔታ ተመልክተው በቦታው ተጨዋቾች ለማስፈረም እንደሚንቀሳቀሱ ተዘግቧል።

እንግሊዛዊው ተጨዋች ካይል ዎከር ክለቡን የሚለቅ ከሆነ ማንችስተር ሲቲ የቀድሞ ተጨዋቻቸው ጄርሚ ፍሪምፖንግን ከባየር ሌቨርኩሰን ለማስፈረም እንደሚሰሩ ተገልጿል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
" ከአለም ዋንጫ አውሮፓ ዋንጫ ከባድ ነው " ምባፔ

የፈረንሳይ ብሔራዊ ቡድን አምበል እና አዲሱ የሪያል ማድሪድ ተጨዋች ኪሊያን ምባፔ የአውሮፓ ዋንጫ ውድድር ለማሸነፍ አስቸጋሪ መሆኑን በሰጠው አስተያየት ገልጿል።

አንድ ጊዜ የአለም ዋንጫን ያሳካው ኪሊያን ምባፔ ሲናገርም " ከአለም ዋንጫ ውድድር ይልቅ የአውሮፓ ዋንጫ ውድድር ለማሸነፍ እጅግ አስቸጋሪ ነው።"በማለት ተናግሯል።

ስለ ሪያል ማድሪድ ፊርማው ያነሳው ኪሊያን ምባፔ " በጣም ደስተኛ ነኝ መመልከት ትችላላችሁ ለህልሜ ክለብ ልጫወት ነው ቢያንስ አምስት አመት ማድሪድ ውስጥ እሆናለሁ።"ብሏል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
" ምባፔ ማድሪድ መግባቱ ጥሩ ዜና አይደለም " ላፖርታ

የካታላኑ ክለብ ባርሴሎና ፕሬዝዳንት ሁዋን ላፖርታ ቡድናቸው እያደረገ ባለው ሂደት እና የክለቡ አካዳሚ ተጨዋቾች እምነት እንዳላቸው በሰጡት አስተያየት ገልጸዋል።

በአንድ የመገናኛ ብዙሀን ቃለ ምልልስ ያደረጉት የባርሴሎናው ፕሬዝዳንት ሁዋን ላፖርታ በቆይታቸውም የተለያዩ ጉዳዮችን አንስተዋል።

ፕሬዝዳንት ሁዋን ላፖርታ ምን አሉ ?

- " በሚቀጥለው የውድድር አመት የአውሮፓ ሻምፒየንስ ሊግ ዋንጫን ማሸነፍ እንፈልጋለን ፣ ባሉን ተጨዋቾች ሊጉንም ማሳካት እንችላለን።

- እኛ ከአካዳሚያችን በሚወጡ ተጨዋቾች እናምናለን ባለን ነገር ደስተኛ ነን ፣ ሪያል ማድሪድ ኪሊያን ምባፔን ማስፈረሙ እንደ ባርሴሎና ደጋፊ ጥሩ ዜና አይደለም።

- ዣቪን ማሰናበት ከወሰንኳቸው ውሳኔዎች ሁሉ በጣም ከባዱ ነበር ሜሲ ፣ ቡስኬት እና ጆርዲ አልባ ላይም ተፈጥሯል የክለቡን ጥቅም ግዴታ ማስቀደም አለብኝ።

- ጇ ፊሊክስ እና እና ካንሴሎ ለተጨማሪ የውድድር አመት በባርሴሎና እንዲቀጥሉ እንፈልጋለን።

- በእኛ በኩል ለዳኞች ምንም አይነት ክፍያ አልከፈልንም ሪያል ማድሪድ በዳኞች የሚወደደው ክለብ ነው።" ሲሉ ተደምጠዋል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
ቨርቹዋል ጨዋታዎች የሚጨበጡ ሽልማቶች, ዳጎስ ያሉ የገንዘብ ሽልማቶችን በቤቲካ ቨርቹዋል!
Forwarded from HEY Online Market
iPhone 15 Promax
•256GB = 139,000 Birr
•512GB = 159,000 Birr

Samsung 24 Ultra
•256GB = 111,000 Birr
•512GB = 128,000 Birr

Contact us :
0953964175 @heymobile
0925927457

@Heyonlinemarket
2024/10/04 13:21:38
Back to Top
HTML Embed Code: