Telegram Web Link
TIKVAH-SPORT
ካሜሮን አዲስ አሰልጣኟን ማሰናበቷ ተገለጸ ! በቀድሞ ተጨዋች ሳሙኤል ኤቶ የሚመራው የካሜሮን እግርኳስ ፌዴሬሽን ከወር በፊት የሾሙትን አዲስ የብሔራዊ ቡድኑ አሰልጣኝ ማርክ ብራይስ ምንም ጨዋታ ሳያደርጉ ማሰናበታቸው ተገልጿል። አሰልጣኝ ሪጎበርት ሶንግን ከአፍሪካ ዋንጫው ውድድር በኋላ ያሰናበተው የካሜሩን ብሔራዊ ቡድን አሰልጣኝ ማርክ ብራይስን የሾመው በሀገሪቱ ስፖርት ሚንስቴር በኩል ነበር። በአዲሱ…
ሳሙኤል ኤቶ አሰልጣኙን ይቅርታ ጠየቀ !

የካሜሮን እግርኳስ ፌዴሬሽንን እየመራ የሚገኘው የቀድሞ ተጨዋች ሳሙኤል ኤቶ ቤልጂየማዊውን አሰልጣኝ ማርክ ብራይስ ይቅርታ መጠየቁ ተገልጿል።

ሳሙኤል ኤቶ ከቀናት በፊት ከእሱ ፍቃድ ውጪ በሀገሪቱ ስፖርት ሚንስቴር ከተሾሙት የብሔራዊ ቡድኑ አዲስ አሰልጣኝ ማርክ ብራይስ ጋር ፀብ ውስጥ መግባቱ እና ከሀላፊነት ማሰናበቱ ይታወሳል።

አሁን ላይ ፕሬዝዳንት ሳሙኤል ኤቶ ይቅርታ መጠየቁ እና አሰልጣኝ ማርክ ብራይስ በሀላፊነታቸው እንዲቀጥሉ ከስምምነት መድረሱ ተገልጿል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
TIKVAH-SPORT
ኬረን ማኬን ኮንትራታቸውን ሊያራዝሙ ነው ! በሊጉ ታላላቅ ክለቦች እየተፈለጉ የሚገኙት አሰልጣኝ ኬረን ማኬን አዲስ የረጅም ጊዜ ኮንትራት ሊፈራረሙ መሆኑ ተዘግቧል። ኢፕስዊች ታውንን በማሰልጠን ላይ የሚገኙት ኬረን ማኬን ክለቡን ወደ ሊጉ ካሳደጉ በኋላ ኮንትራታቸውን ለማራዘም ከጫፍ መድረሳቸው ታውቋል። ቼልሲ ፣ ማንችስተር ዩናይትድ እና ብራይተን የ 38ዓመቱን አሰልጣኝ ኬረን ማኬንን ለማስፈረም…
አሰልጣኝ ኬረን ማኬና ኮንትራታቸውን አራዘሙ !

ከሊጉ ታላላቅ ክለቦች ጋር ስማቸው በስፋት ሲያያዝ የቆዩት አሰልጣኝ ኬረን ማኬና አዲስ የረጅም ጊዜ ኮንትራት መፈራረማቸው ይፋ ሆኗል።

ኢፕስዊች ታውንን በማሰልጠን ላይ የሚገኙት አሰልጣኝ ኬረን ማኬና ክለቡን ወደ ሊጉ ካሳደጉ በኋላ ኮንትራታቸውን እስከ 2028 ማራዘማቸው ታውቋል።

" ባለፉት አመታት በጋራ ባመጣናቸው አስደናቂ ስኬቶች ተደስተናል ኢትስዊችን ከሀያ ሁለት አመታት በኋላ በሊጉ የሚያደርገውን ጉዞ እንድመራ በተሰጠኝ ሀላፊነት እና እድል ተደስቻለሁ።" ሲሉ ኬረን ማኬና ከፊርማው በኋላ ተናግረዋል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
የጀርመን ብሔራዊ ቡድን ተጨዋቾች ከፖሊስ ጋር ልምምድ ሰርተዋል !

ሀገራቸው ለምታዘጋጀው የ2024 አውሮፓ ዋንጫ ውድድር በዝግጅት ላይ የሚገኙት የጀርመን ብሔራዊ ቡድን ተጨዋቾች ዛሬ ከፖሊስ ጋር የተለየ የልምምድ ጊዜ ማሳለፋቸው ተገልጿል።

ተጨዋቾቹ ከፖሊስ ጋር በነበራቸው ስልጠና ወቅት የተለያዩ መስናክሎችን ሲወጡ እና አጫጭር የውጊያ ስልጠናዎችን ሲወስዱ እንዲሁም ልዩ ተግባራትን ሲፈከውኑ መስተዋላቸው ተገልጿል።

በተጨማሪም ተጨዋቾቹ የፖሊስ ደህንነት መከላከያ በማድረግ እርስበርስ መደባደባቸው ሲገለፅ ሀያ ሜትር ከፍታ ያለው ግምብ ላይ በመውጣት የጀርመንን ባንዲራ እንዲሰቅሉ መታዘዛቸው ተነግሯል።

ልዩ ስልጠናውን ያዘጋጁት የብሔራዊ ቡድኑ ዋና አሰልጣኝ ጁሊያን ኔግልስማን መሆናቸው የተገለፀ ሲሆን አላማውም አብሮነትን ፣ መግባባትን እና ለቡድኑ ዋጋ የመክፈል አስተሳሰብን ለማሳደግ መሆኑ ተዘግቧል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
ኤዲሰን ካቫኒ ራሱን ከብሔራዊ ቡድኑ አገለለ !

ዩራጓዊው የፊት መስመር ተጨዋች ኤዲሰን ካቫን በሰላሳ ሰባት አመቱ ራሱን ከዩራጓይ ብሔራዊ ቡድን ማግለሉን ይፋ አድርጓል።

ለአርጀንቲናው ክለብ ቦካ ጁኒየር በመጫወት ላይ የሚገኘው ኤዲሰን ካቫኒ ለብሔራዊ ቡድኑ ባደረጋቸው አንድ መቶ ሰላሳ ስድስት ጨዋታዎች ሀምሳ ስምንት ግቦችን ከመረብ ማሳረፍ ችሏል።

በተጨማሪም ኤዲሰን ካቫኒ ከዩራጓይ ብሔራዊ ቡድን ጋር እ.ኤ.አ 2011 የኮፓ አሜሪካ ዋንጫን ማሳካት ችሏል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
TIKVAH-SPORT
የሮድሪጎ የሪያል ማድሪድ ቆይታ ? ብራዚላዊው የሪያል ማድሪድ የፊት መስመር ተጨዋች ሮድሪጎ በቀጣይ ሎስ ብላንኮዎቹን ስለመልቀቅ ሊያስብ የሚችልበት አጋጣሚ ሊፈጠር እንደሚችል ተገልጿል። ተጨዋቹ አሁን ላይ በሪያል ማድሪድ ቤት ደስተኛ እንደሆነ እና ለመልቀቅ እያሰበ እንደማይገኝ ተነግሯል። ይሁን እንጂ ሮድሪጎ በክለቡ ያለውን የመጫወቻ ጊዜ በሌላ ተጨዋች የሚቀማ ከሆነ ሌሎች ተጨዋቾች እንደሚያደርጉት…
" ሲቲ የአለም ምርጡ ክለብ ነው " ሮድሪጎ

ብራዚላዊው የሪያል ማድሪድ የፊት መስመር ተጨዋች ሮድሪጎ ማንችስተር ሲቲ አሁን ላይ የአለማችን ምርጡ ክለብ መሆኑን በሰጠው አስተያየት ገልጿል።

" እውነት ለመናገር በሩብ ፍፃሜው ማንችስተር ሲቲ ከእኛ የበላይ እንደነበር ሁላችንም እናውቃለን " ያለው ሮድሪጎ እነሱ የአለም ምርጥ ክለብ ናቸው የሚጫወቱት ምርጥ እግርኳስ ነው ነገርግን እኛ ልገልጸው የማልችለው የተለየ ነገር አለን።"ብሏል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
በርንሌይ ፍራንክ ላምፓርድን መሾም ይፈልጋል !

ከአሰልጣኝ ቪንሴንት ኮምፓኒ ጋር የተለያየው በርንሌይ አሰልጣኝ ፍራንክ ላምፓርድን በሀላፊነት ለመሾም ፍላጎት እንዳላቸው ተገልጿል።

ወደ እንግሊዝ ሻምፒዮን ሺፕ የወረደው በርንሌይ አሰልጣኝ ቪንሴንት ኮምፓኒን በባየር ሙኒክ ከተቀማ ወዲህ አዲስ አሰልጣኝ እያፈላለገ ሲሆን ፍራንክ ላምፓርድ የመጀመሪያ ተመራጭ መሆኑ ተነግሯል።

የ 45ዓመቱ አሰልጣኝ ፍራንክ ላምፓርድ ባለፈው የውድድር አመት መጨረሻ ቼልሲን በጊዜያዊ አሰልጣኝነት ከመራ ወዲህ ያለ ሀላፊነት ይገኛል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
🥁ተጀመረ ተጀመረ ተተተጀመረ!🔥
በነጻ ውርርዶች ደንበኞችን ሊያንበሸብሽ የአቪዬተር ሻሞ ተጀመረ!
በየቀኑ እስከ 4000 ብር ዋጋ ያላቸው ሻሞዎች እርሶን ይጠብቃሉ!
በውርርዶች እያሸነፉ ከሻሞው የድርሻዎን ይቅለቡ!
አሁን ነው መብረር!

ቤቲካ - የአሸናፊዎች ቤት!"
Forwarded from HEY Online Market
Apple Vision Pro

🔹VisionPro provides a comprehensive set of vision tools for applications like inspection, gauging, and guidance.
🔸It's commonly used in industries such as automotive, electronics, pharmaceuticals, and more to improve manufacturing processes, ensure product quality, and increase productivity.

Contact Us
0953964175 @heymobile

@heyonlinemarket
ጆቤ ቤሊንግሀም ወዴት ሊያመራ ይችላል ?

ለሰንደርላንድ የሚጫወተው እንግሊዛዊው የጁድ ቤሊንግሀም ወንድም ወጣቱ ጆቤ ቤሊንግሀም በፕርሚየር ሊግ ክለቦች እየተፈለገ ይገኛል።

የ 18ዓመቱ ተጨዋች ጆቤ ቤሊንግሀምን ለማስፈረም በአሰልጣኝ ቶማስ ፍራንክ የሚመራው ብሬንትፎርድ ከፍተኛ ፍላጎት እንዳላቸው ተገልጿል።

በተጨማሪም ክሪስታል ፓላስ ተጨዋቹን ለማስፈረም ወደ ዝውውሩ መግባታቸው እና ንግግር መጀመራቸው ተዘግቧል።

ተጨዋቹ በመሐል ሜዳ እና በፊት መስመር ተጨዋችነት ግልጋሎት የመስጠት ክህሎት እንዳለው ሲገለፅ ባለፈው አመት ለሰንደርላንድ ባደረጋቸው አርባ አምስት ጨዋታዎች ሰባት ግቦች አስቆጥሯል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
ቼልሲ አዲስ አጥቂ ማስፈረም ይፈልጋል !

የምዕራብ ለንደኑ ክለብ ቼልሲ በክረምቱ የተጨዋቾች የዝውውር መስኮት አዲስ የፊት መስመር አጥቂ ማስፈረም እንደሚፈልጉ ተገልጿል።

በሚቀጥለው አመት ተፎካካሪ ሆነው መቅረብ የሚፈልጉት ሰማያዊዎቹ አሁን ላይ ለማስፈረም ከሚፈልጓቸው አጥቂዎች መካከል ናይጄሪያዊው ተጨዋች ቪክቶር ኦሲሜን #አለመኖሩ ተነግሯል።

ሰማያዊዎቹ በቀጣይ ቤልጂየማዊውን የፊት መስመር ተጨዋች ሮሜሎ ሉካኩ እና አርማንዶ ብሮሀን በቋሚነት ለመሸጥ እየተንቀሳቀሱ ይገኛሉ።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
ጄራርድ ፒኬ ምርመራ እንደተከፈተበት ተገለጸ !

የቀድሞ የስፔን ብሔራዊ ቡድን እና ባርሴሎና የተከላካይ ስፍራ ተጨዋች ጄራርድ ፒኬ በሙስና ወንጀል ተጠርጥሮ ምርመራ እየተደረገበት እንደሆነ ተገልጿል።

ጄራርድ ፒኬ ምርመራው የተከፈተበት ሉዊስ ሩብያሌስ የስፔን እግርኳስ ፌዴሬሽን ፕሬዝዳንት በነበሩበት ወቅት የስፔን ሱፐር ካፕ ውድድር ወደ ሳውዲ አረቢያ ማምራት ጋር በተያያዘ መሆኑ ተነግሯል።

የስፔን ሱፐር ካፕ ውድድር ሳውዲ አረቢያ ላይ እንዲደረግ የአምስት አመት ውል ሲፈፀም የጄራርድ ፒኬ ተቋም የኮሚሽን ክፍያ ማግኘቱ ተገልጿል።

እስከ 2025 በሚዘልቀው ስምምነቱ የጄራርድ ፒኬ ተቋም እንደ ኮሚሽን በአመት #አራት ሚልዮን ዩሮ እንደሚቀበል ሲገለፅ የስፔን እግርኳስ ፌዴሬሽን #አርባ ሚልዮን ዩሮ እንደሚያገኝ ተዘግቧል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
ጆዜ ሞሪንሆ ወደ ቱርክ ሊያመሩ ነው !

ፖርቹጋላዊው አሰልጣኝ ጆዜ ሞሪንሆ የቱርክ ሱፐር ሊጉን ክለብ ፌነርባቼ በሀላፊነት ለመረከብ በንግግር ላይ መሆናቸው ተገልጿል።

ስማቸው ከሳውዲ አረቢያ ክለቦች ጋር ሲያያዝ የቆዩት አሰልጣኝ ጆዜ ሞሪንሆ ፌነርባቼን ለሁለት የውድድር አመታት ለማሰልጠን በቃል ደረጃ መስማማታቸው ተገልጿል።

አሰልጣኝ ጆዜ ሞሪንሆ ከወራት በፊት ከሴርያው ክለብ ሮማ ከተሰናበቱ ወዲህ ያለ ሀላፊነት እንደሚገኙ ይታወቃል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
ሞናኮ ተጨዋቹ የጨዋታ እገዳ ተጣለበት !

ማሊያዊው የሞናኮው የመሐል ሜዳ ተጨዋች መሐመድ ካማራ ከፈረንሳይ እግርኳስ ሊግ የአራት ጨዋታዎች እገዳ ቅጣት እንደተጣለበት ተገልጿል።

ተጨዋቹ እገዳው የተጣለበት በሊጉ የመጨረሻ ሳምንት መርሐ ግብር በማልያው ላይ የነበረውን ግብረ ሰዶማዊያንን የሚደግፍ አርማ እንዳይታይ መሸፈኑን ተከትሎ መሆኑ ተነግሯል።

ተጨዋቹ በተጨማሪም ጨዋታው ከመጀመሩ አስቀድሞ ተጨዋቾቹ ከግብረ ሰዶማዊያን አርማ ጋር በነበራቸው የፎቶ ጊዜ ላይ ለመገኘት ፍቃደኛ ሳይሆን ቀርቶ እንደነበር ተገልጿል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
Forwarded from WANAW SPORT
🏀 ለቅርጫት ኳስ አፍቃሪዎች! 🏀

ዋናው ስፖርት በፈለጉት ዲዛይንና የቀለም ምርጫ የሚዘጋጁ ውበትን ከጥራት ጋር ያጣመሩ የቅርጫት ኳስ ትጥቆችን አቅርቦሎታል።

🔥 #ይምጡ፣ ይዘዙን!

📍አድራሻችን:- ገርጂ መብራት ሃይል የካቲት ወረቀት ፊትለፊት፣ አለም ገብሬ ህንፃ፣ 2ተኛ ፎቅ።

📌 ለበለጠ መረጃና ትዕዛዝ 📲 09011382830910851535 እና 0913586742 ላይ ይደውሉ።

👉🏾 እንዲሁም በቴሌግራም @Wanawsales ላይ የሽያጭ ሰራተኞቻችንን በቀጥታ በማናገር ወይም በቴሌግራም ቦት @WANAWSbot በኩል ይዘዙን።

Instagram | Facebook | TikTok

🏅 ዋናው ወደፊት...

@wanawsportwear
ሽመልስ በቀለ 1⃣8⃣ ገስት ሀውስ

በውቢቷ ሀዋሳ ቆይታዎ የት ለማረፍ አስበዋል ? ንፁህ እና በደንበኞቻችን ተወዳጅ በሆነው የእንግዳ ማረፊያችን መጥተው የእረፍት ጊዜውን ያሳልፉ።

እንግዶቻችንን ተቀበልን ለእይታ ሳቢ በሆነው የእንግዳ ማረፊያችን ማስተናገድ ከጀመርን አመታትን አስቆጥረናል።

አድራሻችን :- ሀዋሳ አርቴፍሻል ስታዲየም መንገድ ላይ ያገኙናል።

ለተጨማሪ መረጃ እና ለትዕዛዝዎ ይደውሉልን :- 0928684848

#ShemelesBekele18
ላውታሮ ማርቲኔዝ ውሉን ሊያራዝም ነው !

አርጀንቲናዊው የኢንተር ሚላን የፊት መስመር ተጨዋች ላውታሮ ማርቲኔዝ በክለቡ ያለውን ኮንትራት ለረጅም ጊዜ ለማራዘም ከስምምነት መድረሱ ተገልጿል።

ተጨዋቹ በደሞዝ ክፍያ ዙሪያ ከኢንተር ሚላን ጋር መስማማቱ ሲገለፅ የአምስት አመት ኮንትራት እንደሚፈርም ተነግሯል።

ላውታሮ ማርቲኔዝ በአዲሱ ኮንትራት ስምምነት በአመት ዘጠኝ ሚልዮን ዩሮ እና ተጨማሪ የጉርሻ ክፍያ እንደሚያገኝ ተገልጿል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
አንድሬ ሉኒን ነገ ቡድኑን ይቀላቀላል !

የሪያል ማድሪዱ ግብ ጠባቂ አንድሬ ሉኒን ለሻምፒየንስ ሊግ ፍፃሜ ጨዋታ ለንደን የሚገኘውን የሎስ ብላንኮዎቹ ስብስብ ለመቀላቀል በነገው ዕለት ወደ ስፍራው እንደሚያቀና ተገልጿል።

አንድሬ ሉኒን ባጋጠመው የጉንፋን ህመም ምክንያት ለጥንቃቄ በትላንትናው ዕለት ወደ እንግሊዝ ካመራው የሪያል ማድሪድ ስብስብ ጋር አልተካተተም ነበር።

ዩክሬናዊው ግብ ጠባቂ አንድሬ ሉኒን በነገው የሻምፒየንስ ሊግ ፍፃሜ ጨዋታ ተጠባባቂ ሆኖ እንደሚጀመር ይጠበቃል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
ዩናይትድ የአርሰናልን ሀኪም ሊቀጥር ነው !

የሰሜን ለንደኑን ክለብ አርሰናል የፊዚዮቴራፒ ባለሞያ ጆርዳን ሬስ ክለቡን በመልቀቅ ማንችስተር ዩናይትድን ለመቀላቀል መስማማታቸው ተገልጿል።

ጆርዳን ሬስ ባለፈው አመት ከአርሰናል ማንችስተር ዩናይትድን ከተቀላቀለው የህክምና ክፍል ሀላፊ ዶክተር ጋሪ ኦድሪስኮል ጋር በድጋሜ የሚሰሩ ይሆናል።

ጆርዳን ሬስ በማንችስተር ዩናይትድ ቤት ባለፈው ጥር ወር ክለቡን በለቀቀው ሮቢን ሳድለር ምትክ የፊዚዮቴራፒ ሀላፊ እንደሚሆኑ ተገልጿል።

ማንችስተር ዩናይትድ በተጠናቀቀው የውድድር አመት በርካታ ተጨዋቾቹን በጉዳት ሲያጣ እንደነበር ይታወቃል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
ለኦሎምፒክ ጨዋታ የታቀደ ጥቃት መክሸፉ ተገለጸ !

የፈረንሳይ ሀገር ውስጥ ሚኒስቴር በቀጣይ ክረምት በሚደረገው የፓሪስ ኦሎምፒክ እግርኳስ ጨዋታ ላይ የሽብር ጥቃት ለማድረስ የታሰበ እቅድ ማክሸፉን አስታውቋል።

ጥቃቱን ለማድረስ ሲያዘጋጅ የነበረውን የ 18ዓመት ወጣት በመኖሪያ ቤቱ በቁጥጥር ስር መዋሉ ተገልጿል።

ጥቃቱ ሊደርስ የነበረው የኦሎምፒክ ጨዋታ በሚደረግበት አንዱ በሆነው ጂኦፍሮይ ጉይቻርድ ስታዲየም በተመልካቾች እና የፀጥታ አካላት ላይ እንደነበር ተነግሯል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
ነገ ምሽት የሚደረገውን የሻምፒየንስ ሊግ ፍፃሜ ጨዋታ ግዮን ሆቴል ከልዩ ምግብ እና መጦጦች እንዲሁም በዓለምአቀፍ ዲጄ ከታጀበ ሙዚቃ ጋር በ360 ዲግሪ ስክሪኖች ጨዋታውን ሊያስመለክታችሁ እናንተን  እየጠበቀ ይገኛል!።

ይህንን ድንቅ ጨዋታ ከሄኒከን ጋር እየተዝናን አብረን እንመልከት!
2024/09/28 11:27:14
Back to Top
HTML Embed Code: